Skip to content

Amharic Quran

ከመሞትህ በፊት ቁርአንን አንብብ! (Read the holy Quran before you die!)

  • Home
    • ቁርአንን እንረዳው
    • Download
  • ሱራዎች / Surah List
    • አል-ፋቲሐ (Al-Fatiha)
    • አል-በቀራህ (Al-Beqerah)
    • አል-ዒምራን (Al-Imran)
    • አል-ኒሳዕ (An-Nisa)
    • አል-ማዒዳህ (Al-Maidah) 
    • አንዓም (Al-anam)
    • አል አዕራፍ (Al-Aeraf)
    • አል አንፋል (Al-Anfal)
    • አል ተውባ (At-Tawba)
    • አል ዩኑስ (Yunus)
    • አል ሁድ (Al-Hud)
    • ዩሱፍ (Yusuf)
    • 13 – Ar-Ra’d
    • 14 – Ibrahim
    • አል ሒጅር (Al-Hijr)
    • 16 – An-Nahl
    • 17 – Al-Israa
    • ከህፍ (Al-Kahf )
    • 19 Maryam
    • ጧሃ (Taa-Ha)
    • 21 – Al-Anbiyaa
    • አል ሐጅ (Al-Hajj)
    • 23 – Al-Muminoon
    • 24 – An-Noor
    • 25 – Al -Furqan
    • 26 – Ash-Shu’araa
    • 27 – An-Naml
    • 28 – Al-Qasas
    • 29 – Al-Ankaboot
    • 30 – Ar-Room
    • 31 – Luqman
    • 32 – As-Sajda
    • 33 – Al-Ahzaab
    • 34 – Saba
    • 35 – Faatir
    • 36 – Yaseen
    • 37 – As-Saaffaat
    • 38 – Saad
    • 39 – Az-Zumar
    • 40 – Al-Ghaafir
    • 41 – Fussilat
    • 42 – Ash-Shura
    • 43 – Az-Zukhruf
    • 44 – Ad-Dukhaan
    • 45 – Al-Jaathiya
    • 46 – Al-Ahqaf
    • 47 – Muhammad
    • 48 – Al-Fath
    • 49 – Al-Hujuraat
    • 50 – Qaaf
    • 51 – Adh-Dhaariyat
    • 52 – At-Tur
    • 53 – An-Najm
    • 54 – Al-Qamar
    • 55 – Ar-Rahmaan
    • 56 – Al-Waaqia
    • 57 – Al-Hadid
    • 58 – Al-Mujaadila
    • 59 – Al-Hashr
    • 60 – Al-Mumtahana
    • 61 – As-Saff
    • 62 – Al-Jumu’a
    • 63 – Al-Munaafiqoon
    • 64 – At-Taghaabun
    • 65 – At-Talaaq
    • 66 – At-Tahrim
    • 67 – Al-Mulk
    • 68 – Al-Qalam
    • 69 – Al-Haaqqa
    • 70 – Al-Ma’aarij
    • 71 – Nooh
    • 72 – Al-Jinn
    • 73 – Al-Muzzammil
    • 74 – Al-Muddaththir
    • 75 – Al-Qiyaama
    • 76 – Al-Insaan
    • 77 – Al-Mursalaat
    • 78 – An-Naba
    • 79 – An-Naazi’aat
    • 80 – Abasa
    • 81 – At-Takwir
    • 82 – Al-Infitaar
    • 83 – Al-Mutaffifin
    • 84 – Al-Inshiqaaq
    • 85 – Al-Burooj
    • 86 – At-Taariq
    • 87 – Al-A’laa
    • 88 – Al-Ghaashiya
    • 89 – Al-Fajr
    • 90 – Al-Balad
    • 91 – Ash-Shams
    • 92 – Al-Lail
    • 93 – Ad-Dhuhaa
    • 94 – Ash-Sharh
    • 95 – At-Tin
    • 96 – Al-Alaq
    • 97 – Al-Qadr
    • 98 – Al-Bayyina
    • 99 – Az-Zalzala
    • 100 – Al-Aadiyaat
    • 101 – Al-Qaari’a
    • 102 – At-Takaathur
    • 103 – Al-Asr
    • 104 – Al-Humaza
    • 105 – Al-Fil
    • 106 – Quraish
    • 107 – Al-Maa’un
    • 108 – Al-Kawthar
    • 109 – Al-Kaafiroon
    • 110 – An-Nasr
    • 111 – Al-Masad
    • 112 – Al-Ikhlaas
    • 113 – Al-Falaq
    • 114 – An-Naas

ክርስቲያኖችም ተሰደው ሲመጡ ተቀበለናቸዋል! በአህመዲን ጀበል

Posted on August 4, 2026August 4, 2026 By Muhammed No Comments on ክርስቲያኖችም ተሰደው ሲመጡ ተቀበለናቸዋል! በአህመዲን ጀበል
ወቅታዊ እስላማዊ ጽሁፎች
ከኡስታዝ አህመድ ዲን ጀበል ጠቃሚ አስተምህሮ የተወሰደ
“ክርስቲያኖች ተሰደው ሲመጡ ተቀበልናቸው”
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
በአሕመዲን ጀበል
✅✅✅✅✅
እኛ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ የተለያዩ እምነት ተከታዮች ነበርን።ከመካከለኛ ምስራቅ በቅድሚያ የአይሁድ እምነት ተከታዮች ተሰደው ወደኛ ሲመጡ በእንግድነት ተቀበልናቸው።እነርሱም እምነቱን መስበክ ጀመሩ። ከኛ ዉስጥ ጥቂቶች እምነቱን ተቀበሉ።
 
ቀጥሎም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ330 ፍሪምናጦስ በተባለ ወጣት መሪነት ጥቂት የሶሪያ ክርስቲያኖች በስደት ወደ አክሱም መጡ። በእንግድነት ተቀበልናቸው። እምነታቸውን እንዲሰብኩ ፈቀድንላቸው።ክርስትናን መስበክ ጀመሩ። የአክሱሙ ንጉሥ ኢዛናን ጨምሮ ከኛ ዉስጥ ጥቂቶች ክርስትናን ተቀበሉ። ወጣት ፍሪምናጦስ ጳጳስ ፍለጋ ወደ ግብጽ አመራ።
 
ንጉሡ ኢዛና ክርስትናን እንዲቀበል እንዳደረገ ገለጸ። ንጉሡን ክርስትና ማስነሳት ከቻልክ አንተኑ ጳጳስ እናድርግህ ብለው “አባ ሰላማ” ብለው ቀቡት። ክርስትናን የተቀበሉት ኢትዮጵያውያን ደግሞ “ከሳቴ ብርሃን” ብለው ሰየሙት።
 
ክርስትና ከ330 እስከ 451 ድረስ የአክሱም ቤተ መንግስት ሃይማኖት እንጂ የአጠቃላዩ ሕዝብ ሃይማኖት መሆን አልቻለም ነበር።
በአምስተኛው ክፍለ ዘመን በሰሜን ኢትዮጵያ ክርስትናን ለሕዝቡ የሰበኩትና ‹‹ዘጠኙ ቅዱሳን›› በሚል የሚታወቁት የሃይማኖት አባቶች ሁሉም መጤና የመካከለኛ ምስራቅ ስደተኞች ናቸው።
 
እነዚህ ስደተኞች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ተሰደው የመጡት እ.ኤ.አ በ451 ከተካሄደው ‹‹ቻልኬዶን ጉባዔ›› በኋላ ነበር። ስደተኞቹ የሃይማኖት አባቶች አባ አፍጼ፣ አባ አሌፍ፣ አባ ገሪማ፣ አባ ጉባ፣ አባ ሊቃኖስ፣ አባ ጴንጤሌዎን፣ አባ ጻሕማ፣ አባ የማታ፣ እና አባ ዘሚካኤል ዓረጋዊ ናቸው።
(The Dictionary of Ethiopian Biography, Vol.1, From Early times to the End of the Zagwe Dynasty C.1270 AD, Institute of Ethiopian studies, Addis Ababa University, 1975, Pp. 209-210)
ቀጥሎም በ615 ከመካ የኢስላም እምነት ተከታይ ሰሀቦች ተሰደው መጡ። ነጻነት በመስጠት የጥገኝነት ጥያቄያቸውን በመቀበል በሀገራችን እንዲኖሩ ፈቀድንላቸው። እምነቱን ሰበኩ።
 
ከኛ ዉስጥም ጥቂቶችም ኢስላምን እንደ እምነት ተቀብለው ሙስሊም ሆኑ። በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ጥቂት ስደተኞች በዚሁ ሞተው በትግራይ ተቀበሩ። የተቀሩት ከ15 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
 
ክርስትና እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ330 ወደ አክሱም ሲገባ ኢስላም ደግሞ ክርስትና ወደ አክሱም ከገባ ከ285(ከሁለት መቶ ሰማንያ አምስት) ዓመታት በኋላ ማለት በ615 ነበር የገባው።
 
ከዚያ በኋላ እኛ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ጊዜ በተቀበልናቸው ሃይማኖቶች ምክንያት እምነታችን የተለያየ ሆነ። ከፊሉ አይሁድ፥ ከፊሉ ክርስቲያን፥ ከፊሉ ሙስሊም ሆነ።
 
ቀጥሎም በ16ኛ ክፈለ ዘመን ካቶሊኮች ወደ ሀገራችን ተሰደው መጡ።ተቀበልናቸው። እምነታቸውን መስበክ ጀመሩ። ከኛ መካከል ከፊሎች የካቶሊክ እምነትን ተቀበሉ።
 
ቀጥሎም በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ መጡ።ተቀበልናቸው።እምነታቸውን እንዲሰብኩ እኛ ኢትዮጵያውያን ፈቀድንላቸው። በዚህ ሁኔታ እኛ ኢትዮጵያውያን እምነታችንን እየቀያየርን ቀጠልን። ከፊላችን ኦርቶዶክስ፣ ሙስሊም፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ወዘተ እየሆንን ቀጠልን።
 
ከላይ በተጠቀሰው መልኩ በመጤ ስደተኞች የተሰበከውን እምነት እየተከተልን ዘለቅን።ነገር ከኛ መካከል በመጤ ስደተኞች የተሰበከው የአንዱ እምነት ከፊል ሰባኪዎች “ሌሎች እንጂ እኛ መጤ አይደለንም።” የሚል እይታ ያዙ።በእርግጥ መጤዎቹ እምነቱን ያመጡልን እንጂ እኛ የተቀበልነው ኢትዮጵያውያን አይደለንም።
 
ከእምነቶቹ መምጣት በፊት ሀገርና ህዝብ ነበር።ዛሬም ሀገራችን የሁላችንም ስለሆነች ሁላችንን በምትመስልና እኩል በምትወክል መልኩ እንገንባት የሚል ጥያቄ ሲነሳ “እኛ ነባር እናንተ መጤ” የሚል የድንቁርና ጫወታ መጫወት ያማራቸውን ታዘብን።
 
እኔም ሀገራችን የሁላችንም ናትና መስተካከል ያለባቸው ነገሮች እንዲስተካከል ሀሳብ ሳነሳ አፍ በማዘጋት ዝም ለማሰኘት ጥቂቶች ተረባረቡ። አክራሪ፣አይ፣ ኤስ፣ወሃቢያ፣ የእጌሌ ተላላኪ፣ ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ አቅደዋል፣ሌላም ሌላም።
ያሻችውን ይበሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተሰደው ሲመጡ በመቀበላችን እንደምንኮራው ክርስቲያን ስደተኞችን በመቀበላችን እንኮራከን።
ቸር እንሰንብት!
Tags: አህመድን ጀበል ወቅታዊ እስላማዊ ጽሁፎች

Post navigation

❮ Previous Post: የእስልምና ታሪክ መበደል

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ሁሉም ሱራዎች / All Chapters

  1. ሱረቱ አል-ፋቲሃ – Al-Fātihah
  2. ሱረቱ አል-በቀራህ – Al-Baqarah
  3. ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን – Āl-‘Imrān
  4. ሱረቱ አን-ኒሳዕ – An-Nisā’
  5. ሱረቱ አል-ማኢዳህ – Al-Mā’idah
  6. ሱረቱ አል-አንዓም – Al-An‘ām
  7. ሱረቱ አል-አዕራፍ – Al-A‘rāf
  8. ሱረቱ አል-አንፋል – Al-Anfāl
  9. ሱረቱ አት-ተውባህ – At-Tawbah
  10. ሱረቱ ዩኑስ – Yūnus
  11. ሱረቱ ሁድ – Hūd
  12. ሱረቱ ዩኑስ – Yūsuf
  13. ሱረቱ አር-ረዕድ – Ar-Ra‘d
  14. ሱረቱ ኢብራሂም – Ibrāhīm
  15. ሱረቱ አል ሒጅር – Al-Hijr
  16. ሱረቱ አን–ነሕል – An-Nahl
  17. ሱረቱ አል ኢስራዕ – Al-Isrā’
  18. ሱረቱ አል ከህፍ – Al-Kahf
  19. ሱረቱ መርየም – Maryam
  20. ሱረቱ ጣሃ – Tā-ha
  21. ሱረቱ አል አንቢያ – Al-Anbiyā’
  22. ሱረቱ አል ሐጅ – Al-Hajj
  23. ሱረቱ አል–ሙዕሚኑን – Al-Mu’minūn
  24. ሱረቱ አልን ኑር – An-Noor
  25. ሱረቱ አል ፉርቃን – Al-Furqān
  26. ሱረቱ አሽ ሹዐራእ – Ash-Shu‘arā’
  27. ሱረቱ አን ነምል – An-Naml
  28. ሱረቱ አል ቀሰስ – Al-Qasas
  29. ሱረቱ አል ዐንከቡት – Al-‘Ankabūt
  30. ሱረቱ አር ሩም – Ar-Rūm
  31. ሱረቱ አል ሉቅማን – Luqmān
  32. ሱረቱ አስ ሰጅደህ – As-Sajdah
  33. ሱረቱ አል አሕዛብ – Al-Ahzāb
  34. ሱረቱ ሰበእ – Saba’
  35. ሱረቱ ፋጢር – Fātir
  36. ሱረቱ ያሲን – Yā-Sīn
  37. ሱረቱ አስ ሷፋት – As-Sāffāt
  38. ሱረቱ ሷድ – Sād
  39. ሱረቱ አዝ ዙመር – Az-Zumar
  40. ሱረቱ ጋፊር – Ghāfir
  41. ሱረቱ ፉሲለት – Fussilat
  42. ሱረቱ አሽ ሹራ – Ash-Shūra
  43. ሱረቱ አዝ ዙኽሩፍ – Az-Zukhruf
  44. ሱረቱ አድ ዱኻን – Ad-Dukhān
  45. ሱረቱ አል ጃሲያህ – Al-Jāthiyah
  46. ሱረቱ አል አህቃፍ – Al-Ahqāf
  47. ሱረቱ ሙሐመድ – Muhammad
  48. ሱረቱ አል ፈትህ – Al-Fat’h
  49. ሱረቱ አል ሑጅራት – Al-Hujurāt
  50. ሱረቱ ቃፍ – Qāf
  51. ሱረቱ አዝ ዛሪያት – Adh-Dhāriyāt
  52. ሱረቱ አጥ ጡር – At-Toor
  53. ሱረቱ አን ነጅም – An-Najm
  54. ሱረቱ አል ቀመር – Al-Qamar
  55. ሱረቱ አር ረሕማን – Ar-Rahmān
  56. ሱረቱ አል ዋቂዓህ – Al-Wāqi‘ah
  57. ሱረቱ አል ሐዲድ – Al-Hadīd
  58. ሱረቱ አል ሙጃደላ – Al-Mujādalah
  59. ሱረቱ አል ሐሽር – Al-Hashr
  60. ሱረቱ አል ሙምተሂና – Al-Mumtahanah
  61. ሱረቱ አስ ሶፍ – As-Saff
  62. ሱረቱ አል ጁሙዓህ – Al-Jumu‘ah
  63. ሱረቱ አል ሙናፊቁን – Al-Munāfiqūn
  64. ሱረቱ አት ተጋቡን – At-Taghābun
  65. ሱረቱ አጥ ጠላቅ – At-Talāq
  66. ሱረቱ አት ተህሪም – At-Tahrīm
  67. ሱረቱ አል ሙልክ – Al-Mulk
  68. ሱረቱ አል ቀለም – Al-Qalam
  69. ሱረቱ አል ሓቃህ – Al-Hāqqah
  70. ሱረቱ አል መዓሪጅ – Al-Ma‘ārij
  71. ሱረቱ ኑህ – Nūh
  72. ሱረቱ አል ጂን – Al-Jinn
  73. ሱረቱ አል ሙዘሚል – Al-Muzzammil
  74. ሱረቱ አል ሙደሲር – Al-Muddaththir
  75. ሱረቱ አል ቂያማህ – Al-Qiyāmah
  76. ሱረቱ አል ኢንሳን – Al-Insān
  77. ሱረቱ አል ሙርሰላት – Al-Mursalāt
  78. ሱረቱ አን ነበእ – An-Naba’
  79. ሱረቱ አን ናዚዓት – An-Nāzi‘āt
  80. ሱረቱ ዐበሰ – ‘Abasa
  81. ሱረቱ አት ተክዊር – At-Takwīr
  82. ሱረቱ አል ኢንፊጣር – Al-Infitār
  83. ሱረቱ አል ሙጠፊፊን – Al-Mutaffifīn
  84. ሱረቱ አል ኢንሺቃቅ – Al-Inshiqāq
  85. ሱረቱ አል ቡሩጅ – Al-Burūj
  86. ሱረቱ አጥ ጣሪቅ – At-Tāriq
  87. ሱረቱ አል አዕላ – Al-A‘lā
  88. ሱረቱ አል ጋሺያህ – Al-Ghāshiyah
  89. ሱረቱ አል ፈጅር – Al-Fajr
  90. ሱረቱ አል በለድ – Al-Balad
  91. ሱረቱ አሽ ሸምስ – Ash-Shams
  92. ሱረቱ አል ለይል – Al-Layl
  93. ሱረቱ አድ ዱሓ – Ad-Duhā
  94. ሱረቱ አሽ ሸርህ – Ash-Sharh
  95. ሱረቱ አት ቲን – At-Teen
  96. ሱረቱ አል ዐለቅ – Al-‘Alaq
  97. ሱረቱ አል ቀድር – Al-Qadr
  98. ሱረቱ አል–በይናህ – Al-Bayyinah
  99. ሱረቱ አል ዘልዘላህ – Az-Zalzalah
  100. ሱረቱ አል ዓዲያት – Al-‘Ādiyāt
  101. ሱረቱ አል ቃሪዓሕ – Al-Qāri‘ah
  102. ሱረቱ አት ተካሱር – At-Takāthur
  103. ሱረቱ አል ዓስር – Al-‘Asr
  104. ሱረቱ አል ሁመዛህ – Al-Humazah
  105. ሱረቱ አል ፊል – Al-Feel
  106. ሱረቱ ቁረይሽ – Quraysh
  107. ሱረቱ አል ማዑን – Al-Mā‘ūn
  108. ሱረቱ አል ከውሰር – Al-Kawthar
  109. ሱረቱ አል ካፊሩን – Al-Kāfirūn
  110. ሱረቱ አን ነስር – An-Nasr
  111. ሱረቱ አል መሰድ – Al-Masad
  112. ሱረቱ አል ኢኽላስ – Al-Ikhlās
  113. ሱረቱ አል ፈለቅ – Al-Falaq
  114. ሱረቱ አን ናስ – An-Nās

Copyright © 2026 Amharic Quran.

Theme: Oceanly by ScriptsTown