Default Image
11, Dec 2023
64 – At-Taghaabun

64 – At-Taghaabun

(1) በሰማያት ውስጥ ያለው በምድርም ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ ያሞግሳል፡፡ ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ለእርሱ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡(1) All that is in the heavens and all that is in the earth glorifies Allah. To Him belongs the dominion, and to Him belongs all praise, and He is Most Capable of all things.
(2) እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው፡፡ ከእናንተም ከሓዲ አልለ፡፡ ከእናንተም አማኝ አልለ፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ተመልካች ነው፡፡(2) It is He Who created you, yet some of you are disbelievers and some of you are believers. And Allah is All-Seeing of what you do.
(3) ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ፡፡ ቀረጻችሁም ቅርጻችሁንም አሳመረ፡፡ መመለሻችሁም ወደእርሱ ነው፡፡(3) He created the heavens and earth for a true purpose, He shaped you and perfected your form. And to Him is the final return.
(4) በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል፡፡ አላህም በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡(4) He knows all that is in the heavens and earth, and He knows whatever you conceal and whatever you reveal. And Allah is All-Knowing of what is in the hearts.
(5) የእነዚያ ከአሁን በፊት የካዱትና የክሕደታቸውን ቅጣት ቅመሱ የተባሉት ሕዝቦች ወሬ አልመጣላችሁምን? ለእነሱም አሳማሚ ቅጣት አልላቸው፡፡(5) Has there not come to you the stories of those who disbelieved before you? They tasted the evil consequence of their deeds, and for them there will be a painful punishment.
(6) ይህ (ቅጣት) እርሱ መልክተኞቻቸው በአስረጂዎች ይመጡባቸው ስለ ነበሩ «ሰዎችም ይመሩናልን?» ስላሉና ስለካዱ (ከእምነት) ስለ ዞሩም ነው፡፡ አላህም (ከእነሱ እምነት) ተብቃቃ፡፡ አላህም ተብቃቂ ምስጉን ነው፡፡(6) That is because their messengers came to them with clear proofs, but they said, “How can a human guide us?” Thus they disbelieved and turned away, but Allah had no need for them, for Allah is Self-Sufficient, Praiseworthy.
(7) እነዚያ የካዱትን በፍጹም የማይቀሰሱ መኾናቸውን አሰቡ፡፡ «አይደለም በጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፡፡ ከዚያም በሠራችሁት ሁሉ ትነገራላችሁ፡፡ ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው፡፡» በላቸው፡፡(7) The disbelievers claim that they will never be resurrected. Say, “Yes, by my Lord, you will surely be resurrected, then you will surely be informed of what you did. And that is easy for Allah.”
(8) በአላህና በመልክተኛውም፡፡ በዚያም ባወረድነው ብርሃን እመኑ፡፡ «አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው» (በላቸው)፡፡(8) So believe in Allah and His Messenger, and in the Light [the Qur’an] that We have sent down. And Allah is All-Aware of what you do.
(9) ለመሰብሰቢያ ቀን የሚሰበስብባችሁን ቀን (አስታውሱ)፤ ይህ የመጎዳዳት (መግለጫ) ቀን ነው፡፡ በአላህም የሚያምን ሰው መልካምንም የሚሠራ ከርሱ ኃጢአቶቹን ይሰርይለታል፤ (ይፍቅለታል)፤ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባዋል፤ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡(9) When He will gather you for the Gathering Day; that is the Day of great loss. But whoever believes in Allah and does righteous deeds, He will absolve them of their bad deeds and will admit them to gardens under which rivers flow, abiding therein forever. That is the supreme triumph.
(10) እነዚያም የካዱና በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ እነዚያ በውስጡ ዘውታሪዎች ሲኾኑ የእሳት ጓዶች ናቸው፤ መመለሻቸውም ከፋ!(10) As for those who disbelieve and reject Our verses, they will be the people of the Fire, abiding therein forever. What a terrible destination!
(11) ከመከራም (ማንንም) አይነካም በአላህ ፈቃድ ቢኾን እንጅ፤ በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን (ለትዕግስት) ይመራዋል፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡(11) No calamity befalls except with Allah’s permission. Whoever believes in Allah, He will guide his heart. And Allah is All-Knowing of everything.
(12) አላህንም ተገዙ፤ መልክተኛውንም ታዘዙ፤ ብትዞሩም (መልክተኛውን አትጎዱም)፤ በመልክተኛውም ላይ ያለበት ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው፡፡(12) Obey Allah and obey the Messenger, but if you turn away, then the duty of Our Messenger is only to convey the message clearly.
(13) አላህ ከርሱ በቀር አምላክ የለም፤ በአላህም ላይ አማኞቹ ይመኩ፡፡(13) Allah, none has the right to be worshiped except Him. So in Allah let the believers put their trust.
(14) እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተጓጎል) ለናንተ ጠላቶች የኾኑ አልሉ፤ ስለዚህ ተጠንቀቋቸው፤ ይቅርታ ብታደርጉ ብታልፏቸውም ብተምሩዋቸውም አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡(14) O you who believe, indeed, among your wives and your children are some who are enemies to you, so beware of them. But if you pardon and overlook, and forgive, then Allah is indeed All-Forgiving, Most Merciful.
(15) ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው፤ አላህም እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አልለ፡፡(15) Your wealth and your children are but a trial, and with Allah is a great reward.
(16) አላህንም የቻላችሁትን የክል ፍሩት፤ ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ ለነፍሶቻችሁ መልካምን (ይሰጣችኋልና)፤ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡(16) So fear Allah as much as you can, listen and obey, and spend in charity; that is better for your souls. Whoever is protected from the stinginess of his soul, it is they who are successful.
(17) ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ (ምንዳውን) ለናንተ ይደራርበዋል፤ ለናንተም ይምራል፤ አላህም አመስጋኝ ታጋሽ ነው፡፡(17) If you lend Allah a goodly loan, He will multiply it for you and forgive you, for Allah is Most Appreciative, Most Forbearing,
(18) ሩቁን ምስጢር ግልጹንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡(18) Knower of the unseen and the seen, the All-Mighty, the All-Wise.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

45 – Al-Jaathiya

                                45 – Al-Jaathiya (1) ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ (1) Hā Mīm. (2) የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ነው፡፡ (2) The…

100 – Al-Aadiyaat

100 – Al-Aadiyaat (1) እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡ (1) By the galloping, panting horses, (2) (በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤ (2) striking sparks…

ሱረቱ አል ሒጅር አማርኛ ቁርአን // Free Amharic Quran Suretu Al-Hijr

ሱረቱ አል ሒጅር አማርኛ ቁርአን // Free Amharic Quran Suretu Al-Hijr الر ۚ تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ وَقُرْآنٍ مُّبِينٍ  [1] (1)…