Default Image
11, Dec 2023
76 – Al-Insaan

76 – Al-Insaan

(1) በሰው ላይ የሚታወስ ነገር ሳይኾን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ በእርግጥ አልፎበታል፡፡(1) Was there not a period of time when man was not a thing [even] mentioned?
(2) እኛ ሰውን (በሕግ ግዳጅ) የምንሞከረው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡(2) Indeed, We created man from a drop of mixed fluids, in order to test him. So We gave him hearing and sight.
(3) እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን መራነው፤ (ገለጽንለት)፡፡(3) Indeed, We showed him the way, whether he is grateful or ungrateful.
(4) እኛ ለከሓዲዎች ሰንሰሎቶችንና እንዛዝላዎችን፣ እሳትንም አዘጋጅተናል፡፡(4) We have surely prepared for the disbelievers chains, shackles, and a Blazing Fire.
(5) በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ ካፉር ከኾነች ጠጅ ይጠጣሉ፡፡(5) Indeed, the righteous will drink from a cup [of wine] flavored with camphor,
(6) ከእርሷ የአላህ ባሮች የሚጠጡላት (ወደፈለጉበት) ማንቧቧትን የሚያንቧቧት ከኾነች ምንጭ (ይጠጣሉ)፡፡(6) a spring from which Allah’s slaves will drink, which will flow as they wish.
(7) (ዛሬ) በስለታቸው ይሞላሉ፡፡ መከራው ተሰራጪ የኾነንም ቀን ይፈራሉ፡፡(7) They fulfill their vows and fear a Day whose evil will spread far and wide,
(8) ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድኻ፣ ለየቲምም፣ ለምርኮኛም ለእስረኛም ያበላሉ፡፡(8) and they give food, despite their love for it, to the needy, the orphans, and the captives,
(9) «የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም፡፡(9) [saying to themselves] “We feed you only for the sake of Allah; we seek from you neither reward nor gratitude.
(10) «እኛ (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና፤» (ይላሉ)፡፡(10) We fear from our Lord a grim and distressful Day.”
(11) አላህም የዚያን ቀን ክፋት ጠበቃቸው፡፡ (ፊታቸው) ማማርንና መደሰትንም ገጠማቸው፡፡(11) So Allah will protect them from the evil of that Day, and will grant them radiance and delight,
(12) በመታገሣቸውም ገነትንና የሐር ልብስን መነዳቸው፡፡(12) and will reward them for their perseverance with Paradise and garments of silk.
(13) በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች በውስጧ ፀሐይንም ጨረቃንም የማያዩ ሲኾኑ፡፡(13) They will recline therein on adorned couches; neither feeling scorching heat nor freezing cold.
(14) ዛፎችዋም በእነርሱ ላይ የቀረበች፣ ፍሬዎችዋም (ለለቃሚዎች) መግገራትን የተገራች ስትኾን (ገነትን መነዳቸው)፡፡(14) with shady branches spread above them, and clusters of fruit will be made within their reach.
(15) በእነርሱም ላይ ከብር በኾኑ ዕቃዎች (ሰሐኖች) የብርጭቆዎች በኾኑ ኩባያዎችም ይዝዞርባቸዋል፡፡(15) They will be served frequently with silver vessels and crystal cups,
(16) መለካትን የለኳቸው በኾኑ የብር ብርጭቆዎች (ይዝዞርባቸዋል)፡፡(16) crystalline goblets of silver, filled precisely as desired.
(17) በእርሷም መበረዣዋ ዘንጀቢል የኾነችን ጠጅ ይጠጣሉ፡፡(17) They will be given a glass [of wine] flavored with ginger
(18) በውስጧ ያለችውን ሰልሰቢል ተብላ የምትጠራውን ምንጭ፡፡(18) from a spring therein called Salsabīl.
(19) በእነርሱም ላይ (ባሉበት ኹነታ) የሚዘወትሩ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡ ባየሃቸው ጊዜ የተበተነ ሉል ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ፡፡(19) They will be served by eternal young boys; if you see them, you would think that they are scattered pearls.
(20) እዚያም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋንና ታላቅ ንግሥናን ታያለህ፡፡(20) If you were to look around, you would see bliss and a vast dominion.
(21) አረንጓዴዎች የኾኑ የቀጭን ሐር ልብሶችና ወፍራም ሐርም በላያቸው ላይ አልለ፡፡ ከብር የኾኑ አንባሮችንም ይሸለማሉ፡፡ ጌታቸውም አጥሪ የኾነን መጠጥ ያጠጣቸዋል፡፡(21) They will be dressed in garments of fine green silk and rich brocade, and will be adorned with bracelets of silver, and their Lord will give them a pure drink.
(22) «ይህ በእርግጥ ለእናንተ ዋጋ ኾነ፡፡ ሥራችሁም ምስጉን ኾነ፤» (ይባላሉ)፡፡(22) [And they will be told,] “Indeed, this is your reward, and your efforts have been appreciated.”
(23) እኛ ቁርኣንን ባንተ ላይ ማውረድን እኛው አወረድነው፡፡(23) Indeed, it is We Who have sent down the Qur’an to you in stages.
(24) ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ ከእነርሱም ኀጢአተኛን ወይም ከሓዲን አትታዘዝ፡፡(24) So be patient with your Lord’s decree, and do not obey any sinner or disbeliever from among them.
(25) የጌታህንም ስም በጧትና ከቀትር በላይ አውሳ፡፡(25) And remember the Name of your Lord morning and evening,
(26) ከሌሊቱም ለእርሱ ስገድ፡፡ በረዢም ሌሊትም አወድሰው፡፡(26) and prostrate to Him at night, and glorify Him at length by night.
(27) እነዚያ ፈጣኒቱን ዓለም ይወዳሉ፡፡ ከባድን ቀንም በስተፊታቸው ኾኖ ይተዋሉ፡፡(27) Indeed, these [pagans] love this fleeting life and pay no heed to a heavy Day ahead of them.
(28) እኛ ፈጠርናቸው፡፡ መለያልያቸውንም አጠነከርን፡፡ በሻንም ጊዜ መሰሎቻቸውን መለወጥን እንለውጣለን፡፡(28) It is We Who created them and strengthened their build. If We will, We can replace them with others like them.
(29) ይህቺ መገሠጫ ናት፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መንገድን ይይዛል፡፡(29) Indeed, this is a reminder; so let anyone who wills may take a way to his Lord.
(30) አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡(30) But you cannot will unless Allah wills. Indeed, Allah is All-Knowing, All-Wise.
(31) የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያገባዋል፡፡ በዳዮቹንም (ዝቶባቸዋል)፡፡ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል፡፡(31) He admits whom He wills into His mercy, but for the wrongdoers He has prepared a painful punishment.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

85 – Al-Burooj

85 – Al-Burooj (1) የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡ (1) By the sky full of constellations, (2) በተቀጠረው ቀንም፤ (2)…

25 – Al -Furqan

25 Al -Furqan (1) ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡ (1) Blessed is the One…

ሱረቱል አል ማዒዳህ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran 

ሱረቱል አል ማዒዳህ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا…