Default Image
19, Nov 2023
ሱረቱል አል አዕራፍ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran Al-A’raaf

ሱረቱል አል አዕራፍ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran Al-A’raaf

المص  [1]

(1) አ.ለ.መ.ሰ (አሊፍ፤ ላም ፤ሚም፤ ሷድ)።

(1) Alif Lām Mīm Sād.

كِتَابٌ أُنزِلَ إِلَيْكَ فَلَا يَكُن فِي صَدْرِكَ حَرَجٌ مِّنْهُ لِتُنذِرَ بِهِ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ  [2]

(2) (ይህ) ወደ አንተ የተወረደ መጽሐፍ ነው። በደረትህም ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር። (የተወረደውም) በእርሱ ልታስፈራራበትና ለምእምናን መገሠጫ እንዲኾን ነው።

(2) This is a Book that has been sent down to you [O Prophet], so do not let your heart be troubled by it; so that you may warn thereby and as a reminder to the believers.

اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَا تَتَّبِعُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۗ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ  [3]

(3) ከጌታችሁ ወደእናንተ የተወረደውን ተከተሉ። ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ። ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ።

(3) Follow [O mankind] what has been sent down to you from your Lord, and do not follow any guardians besides Him. Little it is that you take heed!

وَكَم مِّن قَرْيَةٍ أَهْلَكْنَاهَا فَجَاءَهَا بَأْسُنَا بَيَاتًا أَوْ هُمْ قَائِلُونَ  [4]

(4) ከከተማም ልናጠፋት የሻነው ወዲያውም ብርቱ ቅጣታችን ሌሊት ወይም ቀን እነርሱ በቀትር አርፈው ሳሉ የመጣባቸው ብዙ ናቸው።

(4) How many towns We have destroyed, and Our punishment came upon them at night or while they were taking midday rest.

فَمَا كَانَ دَعْوَاهُمْ إِذْ جَاءَهُم بَأْسُنَا إِلَّا أَن قَالُوا إِنَّا كُنَّا ظَالِمِينَ  [5]

(5) ቅጣታችንም በመጣባቸው ጊዜ «ጸሎታቸው እኛ በደለኞች ነበርን» ከማለት በቀር ሌላ አልነበረም።

(5) Their only cry, when Our punishment came upon them, was, “We were indeed wrongdoers.”

فَلَنَسْأَلَنَّ الَّذِينَ أُرْسِلَ إِلَيْهِمْ وَلَنَسْأَلَنَّ الْمُرْسَلِينَ  [6]

(6) እነዚያንም ወደነሱ የተላከባቸውን (ሕዝቦች) በእርግጥ መልክተኞቹንም እንጠይቃለን።

(6) So We will surely question those to whom the messengers were sent, and We will surely question the messengers themselves.

فَلَنَقُصَّنَّ عَلَيْهِم بِعِلْمٍ ۖ وَمَا كُنَّا غَائِبِينَ  [7]

(7) በእነርሱም ላይ (የነበሩበትን ሁሉ) ከዕውቀት ጋር በእርግጥ እንተርክላቸዋለን። የራቅንም አልነበርንም።

(7) Then We will surely give them a full account [of their deeds] on the basis of knowledge, for We were never absent.

وَالْوَزْنُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ ۚ فَمَن ثَقُلَتْ مَوَازِينُهُ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ  [8]

(8) ትክክለኛውም ሚዛን የዚያን ቀን ነው። ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ የፈለጉትን ያገኙ ናቸው።

(8) The weighing [of deeds] on that Day will be true and just. Those whose scales [of good deeds] are heavy, it is they who will be the successful.

وَمَنْ خَفَّتْ مَوَازِينُهُ فَأُولَٰئِكَ الَّذِينَ خَسِرُوا أَنفُسَهُم بِمَا كَانُوا بِآيَاتِنَا يَظْلِمُونَ  [9]

(9) ሚዛኖቻቸው የቀለሉባቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ ተአምራቶቻችንን ይክዱ በነበሩት ምክንያት ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው።

(9) But those whose scales are light, it is they who have lost their own souls, because they wrongfully rejected Our verses.

وَلَقَدْ مَكَّنَّاكُمْ فِي الْأَرْضِ وَجَعَلْنَا لَكُمْ فِيهَا مَعَايِشَ ۗ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ  [10]

(10) በምድርም ላይ በእርግጥ አስመቸናችሁ። በእርሷም ላይ ለናንተ መኖሪያዎችን አደረግንላችሁ፤ ምስጋናችሁ በጣም ጥቂት ነው።

(10) We established you on earth and provided you with means of livelihood therein. Little do you give thanks.

وَلَقَدْ خَلَقْنَاكُمْ ثُمَّ صَوَّرْنَاكُمْ ثُمَّ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ لَمْ يَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ  [11]

(11) በእርግጥም ፈጠርናችሁ። ከዚያም ቀረጽናችሁ። ከዚያም ለመላእክቶች «ለአዳም ስገዱ» አልን። ወዲያውም ሰገዱ። ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም።

(11) We surely created you, then shaped you, then We said to the angels, “Prostrate before Adam,” so they prostrated, except Iblīs [Satan], who was not one of those who prostrated.

قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ ۖ قَالَ أَنَا خَيْرٌ مِّنْهُ خَلَقْتَنِي مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُ مِن طِينٍ  [12]

(12) (አላህ) «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ» አለው። «እኔ ከርሱ የበለጥኩ ነኝ። ከእሳት ፈጠርከኝ። እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው» አለ።

(12) Allah said, “What prevented you from prostrating when I ordered you?” He said, “I am better than him; You created me from fire and created him from clay.”

قَالَ فَاهْبِطْ مِنْهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَاخْرُجْ إِنَّكَ مِنَ الصَّاغِرِينَ  [13]

(13) ከእርሷ ውረድ፤ በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና። ውጣም አንተ ከወራዶቹ ነህና አለው።

(13) Allah said, “Then get down from here! It is not for you to show arrogance here. Get out, for you are one of the disgraced.”

قَالَ أَنظِرْنِي إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ  [14]

(14) «እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ» አለ።

(14) He said, “Grant me respite until the Day they are resurrected.”

قَالَ إِنَّكَ مِنَ الْمُنظَرِينَ  [15]

(15) ፡-አንተ ከሚቆዩት ነህ አለው።

(15) Allah said, “You are of those who are granted respite’’.

قَالَ فَبِمَا أَغْوَيْتَنِي لَأَقْعُدَنَّ لَهُمْ صِرَاطَكَ الْمُسْتَقِيمَ  [16]

(16) «ስለአጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ» አለ።

(16) He said, “Since You have led me astray, I will certainly lie in wait for them on Your straight path.

ثُمَّ لَآتِيَنَّهُم مِّن بَيْنِ أَيْدِيهِمْ وَمِنْ خَلْفِهِمْ وَعَنْ أَيْمَانِهِمْ وَعَن شَمَائِلِهِمْ ۖ وَلَا تَجِدُ أَكْثَرَهُمْ شَاكِرِينَ  [17]

(17) «ከዚያም ከስተፊቶቻቸው ከኋላቸውም ከቀኞቻቸውም ከግራዎቻቸውም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ። አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ኾነው አታገኛቸውም» (አለ)።

(17) Then I will come against them from their front and from their back, from their right and from their left, and You will not find most of them grateful.”

قَالَ اخْرُجْ مِنْهَا مَذْءُومًا مَّدْحُورًا ۖ لَّمَن تَبِعَكَ مِنْهُمْ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكُمْ أَجْمَعِينَ  [18]

(18) «የተጠላህ ብራሪ ስትኾን ከእርሷ ውጣ። ከእነርሱ የተከተለህ ከእናንተ ከመላችሁም ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» አለው።

(18) Allah said, “Get out of here, disgraced and expelled! I will certainly fill Hell with you and those who follow you all together.”

وَيَا آدَمُ اسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ الْجَنَّةَ فَكُلَا مِنْ حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَٰذِهِ الشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ الظَّالِمِينَ  [19]

(19) «አዳም ሆይ! አንተም ሚስትህም በገነት ተቀመጡ። ከሻችሁትም ስፍራ ብሉ። ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ። (ራሳቸውን) ከሚበድሉት ትኾናላችሁና» (አላቸው)።

(19) “O Adam, dwell in Paradise, you and your wife, and eat from wherever you wish, but do not approach this tree, or else you will both be among the wrongdoers.”

فَوَسْوَسَ لَهُمَا الشَّيْطَانُ لِيُبْدِيَ لَهُمَا مَا وُورِيَ عَنْهُمَا مِن سَوْآتِهِمَا وَقَالَ مَا نَهَاكُمَا رَبُّكُمَا عَنْ هَٰذِهِ الشَّجَرَةِ إِلَّا أَن تَكُونَا مَلَكَيْنِ أَوْ تَكُونَا مِنَ الْخَالِدِينَ  [20]

(20) ሰይጣንም ከሐፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ለእነርሱ ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው። «ጌታችሁም መልኣኮች እንዳትኾኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትኾኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም» አላቸው።

(20) Then Satan whispered to them in order to expose what was hidden from them of their private parts. He said, “Your Lord has only forbidden to you this tree to prevent you from becoming angels or immortals.”

وَقَاسَمَهُمَا إِنِّي لَكُمَا لَمِنَ النَّاصِحِينَ  [21]

(21) «እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ» ሲልም አማለላቸው።

(21) And he swore to them, “I am indeed your sincere adviser.”

فَدَلَّاهُمَا بِغُرُورٍ ۚ فَلَمَّا ذَاقَا الشَّجَرَةَ بَدَتْ لَهُمَا سَوْآتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ الْجَنَّةِ ۖ وَنَادَاهُمَا رَبُّهُمَا أَلَمْ أَنْهَكُمَا عَن تِلْكُمَا الشَّجَرَةِ وَأَقُل لَّكُمَا إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمَا عَدُوٌّ مُّبِينٌ  [22]

(22) በማታለልም አዋረዳቸው። ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ኀፍረተ ገላቸው ለሁለቱም ተገለጠችላቸው። ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ ጀመር። ጌታቸውም «ከዚህ ዛፍ አልከለከልኋችሁምን ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁምን» ሲል ጠራቸው።

(22) So he deluded them both with deception. When they tasted the tree, their private parts became visible to them, so they began to put together leaves of the Garden to cover themselves. Their Lord called them, “Did I not forbid you from that tree and tell you that Satan is your sworn enemy?”

قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَا أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ  [23]

(23) «ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን። ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ።

(23) They said, “Our Lord, we have wronged ourselves; if You do not forgive us and have mercy upon us, we will surely be among the losers.”

قَالَ اهْبِطُوا بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ ۖ وَلَكُمْ فِي الْأَرْضِ مُسْتَقَرٌّ وَمَتَاعٌ إِلَىٰ حِينٍ  [24]

(24) (አላህ) « ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ። ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ» አላቸው።

(24) Allah said, “Get down as enemies to one another. You will find a dwelling place on earth and provision for an appointed time.”

قَالَ فِيهَا تَحْيَوْنَ وَفِيهَا تَمُوتُونَ وَمِنْهَا تُخْرَجُونَ  [25]

(25) «በእርሷ ላይ ትኖራላችሁ። በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ። ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ» አላቸው።

(25) He said, “There you will live, and there you will die, and from there you will be raised again.”

يَا بَنِي آدَمَ قَدْ أَنزَلْنَا عَلَيْكُمْ لِبَاسًا يُوَارِي سَوْآتِكُمْ وَرِيشًا ۖ وَلِبَاسُ التَّقْوَىٰ ذَٰلِكَ خَيْرٌ ۚ ذَٰلِكَ مِنْ آيَاتِ اللَّهِ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ  [26]

(26) የአዳም ልጆች ሆይ! ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን። አላህን የመፍራትም ልብስ ይህ የተሻለ ነው። ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው። ይገሠጹ ዘንድ (አወረደላቸው)።

(26) O children of Adam, We have given you garments that cover your private parts and as an adornment. However, the garment of piety – that is best. That is one of the signs of Allah, so that they may take heed.

يَا بَنِي آدَمَ لَا يَفْتِنَنَّكُمُ الشَّيْطَانُ كَمَا أَخْرَجَ أَبَوَيْكُم مِّنَ الْجَنَّةِ يَنزِعُ عَنْهُمَا لِبَاسَهُمَا لِيُرِيَهُمَا سَوْآتِهِمَا ۗ إِنَّهُ يَرَاكُمْ هُوَ وَقَبِيلُهُ مِنْ حَيْثُ لَا تَرَوْنَهُمْ ۗ إِنَّا جَعَلْنَا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ لِلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ  [27]

(27) የአዳም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባትና እናታችሁን ኀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከነሱ የገፈፋቸው ሲኾን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተን አይሞክራችሁ። እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ያዩዋችኋልና። እኛ ሰይጣናትን ለእነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል።

(27) O children of Adam, do not let Satan seduce you as he caused your parents to be expelled from the Garden, stripping them of their garments and making their private parts visible to them. He and his offspring see you from where you cannot see them. We have made the devils allies to those who disbelieve.

وَإِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً قَالُوا وَجَدْنَا عَلَيْهَا آبَاءَنَا وَاللَّهُ أَمَرَنَا بِهَا ۗ قُلْ إِنَّ اللَّهَ لَا يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ ۖ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ  [28]

(28) መጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን አላህም በእርሷ አዞናል ይላሉ። «አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም። በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን» በላቸው።

(28) When they commit a shameful act, they say, “We found our forefathers doing it, and Allah has enjoined it upon us.” Say, “Allah never enjoins shameful acts. Do you say about Allah something of which you have no knowledge?”

قُلْ أَمَرَ رَبِّي بِالْقِسْطِ ۖ وَأَقِيمُوا وُجُوهَكُمْ عِندَ كُلِّ مَسْجِدٍ وَادْعُوهُ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ ۚ كَمَا بَدَأَكُمْ تَعُودُونَ  [29]

(29) ጌታዬ በማስተካከል አዘዘ። በየመስጊዱም ዘንድ ፊቶቻችሁን (እርሱን ለመገዛት) አስተካክሉ። ሃይማኖትንም ለእርሱ ፍጹም አድርጋችሁ ተገዙት። እንደጀመራችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው።

(29) Say [O Prophet], “My Lord has enjoined doing what is right; direct your faces [to Him alone] wherever you pray; call upon Him with sincere devotion to Him. Just as He created you first, so you will be brought back to life.”

فَرِيقًا هَدَىٰ وَفَرِيقًا حَقَّ عَلَيْهِمُ الضَّلَالَةُ ۗ إِنَّهُمُ اتَّخَذُوا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ اللَّهِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُم مُّهْتَدُونَ  [30]

(30) ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ። ከፊሎቹም በእነሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል። እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና። እነርሱም (ቅኑን መንገድ) የተመራን ነን ብለው ያስባሉ።

(30) A group He has guided, and another group deserved to go stray. They have taken devils as their guardians instead of Allah, thinking that they are guided.

يَا بَنِي آدَمَ خُذُوا زِينَتَكُمْ عِندَ كُلِّ مَسْجِدٍ وَكُلُوا وَاشْرَبُوا وَلَا تُسْرِفُوا ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُسْرِفِينَ  [31]

(31) የአዳም ልጆች ሆይ! (ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ። ብሉም፤ ጠጡም፤ አታባክኑም። እርሱ አባካኞችን አይወድምና።

(31) O children of Adam, dress well for every prayer. Eat and drink, but do not waste, for He does not like the wasteful.

قُلْ مَنْ حَرَّمَ زِينَةَ اللَّهِ الَّتِي أَخْرَجَ لِعِبَادِهِ وَالطَّيِّبَاتِ مِنَ الرِّزْقِ ۚ قُلْ هِيَ لِلَّذِينَ آمَنُوا فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا خَالِصَةً يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ  [32]

(32) «የአላህን ጌጥ ያችን ለባሮቹ የፈጠራትን ከሲሳይም ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው» በላቸው። «እርሷ በትንሣኤ ቀን ለእነዚያ ላመኑት ብቻ ስትኾን በቅርቢቱ ሕይወት ተገቢያቸው ናት» በላቸው። እንደዚሁ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን።

(32) Say, “Who has forbidden the adornments and lawful provisions that Allah has brought forth for His slaves?” Say, “They are for the believers in the life of this world, and they will be exclusively for them on the Day of Resurrection. This is how We make the verses clear for people who have knowledge.”

قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَالْإِثْمَ وَالْبَغْيَ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَأَن تُشْرِكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ  [33]

(33) «ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን (ጣዖት) በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው» በላቸው።

(33) Say, “My Lord has forbidden shameful acts done openly or in secret, sinfulness, unjustified aggression, associating partners with Allah for which He has not sent down any authority, and saying about Allah that of which you have no knowledge.”

وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ  [34]

(34) ለሕዝብም ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው። ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም። (ከጊዜያቱ) አይቀደሙምም።

(34) Each nation has its appointed time. When their appointed time comes, they cannot delay it for a moment or bring it forward.

يَا بَنِي آدَمَ إِمَّا يَأْتِيَنَّكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي ۙ فَمَنِ اتَّقَىٰ وَأَصْلَحَ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ  [35]

(35) የአዳም ልጆች ሆይ! ከእናንተ ውስጥ በናንተ ላይ አንቀጾቼን የሚያነቡ መልከተኞች ቢመጧችሁ ከእናንተ ክሕደትን የተጠነቀቁና መልካምንም የሠሩ በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም። እነሱም አያዝኑም።

(35) O children of Adam, when there come to you messengers from among you, reciting My verses to you – then whoever fears Allah and mends his ways, they will have no fear, nor will they grieve.

وَالَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَاسْتَكْبَرُوا عَنْهَا أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ  [36]

(36) እነዚያም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው። እነሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው።

(36) But those who reject Our verses and show arrogance towards them, they are the people of the Fire, they will abide therein forever.

فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِآيَاتِهِ ۚ أُولَٰئِكَ يَنَالُهُمْ نَصِيبُهُم مِّنَ الْكِتَابِ ۖ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَتْهُمْ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوْنَهُمْ قَالُوا أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ ۖ قَالُوا ضَلُّوا عَنَّا وَشَهِدُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا كَافِرِينَ  [37]

(37) በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ከአስዋሸ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው እነዚያ (ከተጻፈላቸው) ከመጽሐፉ ውስጥ ሲኾን ዕድላቸው ያገኛቸዋል። (የሞት) መልክተኞቻችንም የሚገድሏቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ «ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ» ይሏቸዋል። «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ። እነርሱም ከሃዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ።

(37) Who does greater wrong than the one who fabricates lies against Allah or rejects His verses? They will receive the share that is destined for them, until when Our angel-messengers come to take their souls, saying, “Where are those whom you used to invoke besides Allah?” They will say, “They are lost from us,” and they will testify against themselves that they were disbelievers.

قَالَ ادْخُلُوا فِي أُمَمٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِكُم مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ فِي النَّارِ ۖ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا ۖ حَتَّىٰ إِذَا ادَّارَكُوا فِيهَا جَمِيعًا قَالَتْ أُخْرَاهُمْ لِأُولَاهُمْ رَبَّنَا هَٰؤُلَاءِ أَضَلُّونَا فَآتِهِمْ عَذَابًا ضِعْفًا مِّنَ النَّارِ ۖ قَالَ لِكُلٍّ ضِعْفٌ وَلَٰكِن لَّا تَعْلَمُونَ  [38]

(38) «ከጋኔንም ከሰውም ከእናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ሕዝቦች ጋር ኾናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ» ይላቸዋል። አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር (ያሳሳተቻትን) ብጤዋን ትረግማለች። መላውም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙም ጊዜ የኋለኛይቱ ለመጀመሪያይቱ (ተከታዮች ለአስከታዮች) «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን። ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው» ትላለች። (አላህም)፡- ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም ይላቸዋል።

(38) Allah will say, “Enter the Fire along with nations of jinn and humans who have passed on before you.” Every time a nation enters, it will curse the preceding one until they are all gathered inside, the followers will say about their leaders, “Our Lord, they have led us astray, so give them a double punishment of the Fire.” He will say, “Each will have a double punishment, but you do not know.”

وَقَالَتْ أُولَاهُمْ لِأُخْرَاهُمْ فَمَا كَانَ لَكُمْ عَلَيْنَا مِن فَضْلٍ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْسِبُونَ  [39]

(39) «መጀመሪያይቱም ለኋለኛይቱ ለእናንተ በእኛ ላይ ምንም ብልጫ አልነበራችሁም» ትላለች። «ትሠሩትም በነበራችሁት ቅጣቱን ቅመሱ» (ይላቸዋል)።

(39) The leaders will say to their followers, “You were no better than us, so taste the punishment for what you used to do.”

إِنَّ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَاسْتَكْبَرُوا عَنْهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمْ أَبْوَابُ السَّمَاءِ وَلَا يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ الْجَمَلُ فِي سَمِّ الْخِيَاطِ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُجْرِمِينَ  [40]

(40) እነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም። ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ ገነትን አይገቡም። እንደዚሁም አጋሪዎችን እንቀጣለን።

(40) Those who reject Our verses and show arrogance towards them, the gates of heaven will not be opened for them, nor will they enter Paradise until a camel can pass through the eye of a needle. This is how We recompense the wicked.

لَهُم مِّن جَهَنَّمَ مِهَادٌ وَمِن فَوْقِهِمْ غَوَاشٍ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الظَّالِمِينَ  [41]

(41) ለእነርሱ ከገሀነም እሳት (በሥራቸው) ምንጣፍ ከበላያቸውም (የእሳት) መሸፈኛዎች አሏቸው። እንደዚሁም በደለኞችን እንቀጣለን።

(41) Hell will be their resting place and above them will be coverings [of fire]. This is how We recompense the wrongdoers.

وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ  [42]

(42) እነዚያም ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድምና፤ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው። እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው።

(42) As for those who believe and do righteous deeds – We do not burden a soul more than what it can bear – they are the people of Paradise, they will abide therein forever.

وَنَزَعْنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنْ غِلٍّ تَجْرِي مِن تَحْتِهِمُ الْأَنْهَارُ ۖ وَقَالُوا الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي هَدَانَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهْتَدِيَ لَوْلَا أَنْ هَدَانَا اللَّهُ ۖ لَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُ رَبِّنَا بِالْحَقِّ ۖ وَنُودُوا أَن تِلْكُمُ الْجَنَّةُ أُورِثْتُمُوهَا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ  [43]

(43) በደረቶቻቸው ውስጥ ያለውንም ጥላቻ እናስወግዳለን። ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ። «ለዚያም ወደዚህ (ላደረሰን ሥራ) ለመራን አላህ ምስጋና ይገባው። አላህ ባልመራንም ኖሮ አንመራም ነበር። የጌታችን መልክተኞች በእውነት ላይ ሲኾኑ በእርግጥ መጥተውልናል» ይላሉ። ይህች ገነት ትሠሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ።

(43) We will remove all ill feelings from their hearts and rivers will flow beneath them. They will say, “All praise be to Allah Who has guided us to this, for We would not have been guided to this if Allah had not guided us. The messengers of our Lord came with the truth.” They will be called, “This is Paradise that you are made to inherit for what you used to do.”

وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ  [44]

(44) የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎች «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን። ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን» ሲሉ ይጣራሉ። «አዎን አገኘን» ይላሉ። በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል።

(44) The people of Paradise will call out to the people of Hell, “We have surely found our Lord’s promise to be true. Have you also found your Lord’s promise to be true?” They will say, “Yes.” Then a caller will announce among them, “May Allah’s curse be upon the wrongdoers,

الَّذِينَ يَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ وَيَبْغُونَهَا عِوَجًا وَهُم بِالْآخِرَةِ كَافِرُونَ  [45]

(45) (በደለኞች) እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚከለክሉ፣ (የአላህም መንገድ) እንድትጣመምም የሚፈልጉዋት፣ እነርሱም በመጨረሻዋ ዓለም ከሓዲዎች የኾኑ ናቸው።

(45) those who prevent [people] from the way of Allah, seeking to make it crooked, and who disbelieve in the Hereafter.”

وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ ۚ وَعَلَى الْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّا بِسِيمَاهُمْ ۚ وَنَادَوْا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَن سَلَامٌ عَلَيْكُمْ ۚ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُونَ  [46]

(46) በመካከላቸውም ግርዶሽ አልለ። በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አልሉ። የገነትንም ሰዎች ሰላም ለናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ። እነርሱም (የአዕራፍ ሰዎች) የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም።

(46) Between them there will be a barrier, and on its Heights there will be men who will recognize each group by their marks. They will call out to the people of Paradise, “Peace be on you.” They will not have entered it, yet they will eagerly hope [to enter].

وَإِذَا صُرِفَتْ أَبْصَارُهُمْ تِلْقَاءَ أَصْحَابِ النَّارِ قَالُوا رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا مَعَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ  [47]

(47) ዓይኖቻቸውም ወደ እሳት ሰዎች አቅጣጫ በተዞሩ ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! ከበደለኞች ጋር አታድርገን» ይላሉ።

(47) And when their eyes are turned towards the people of Hell, they will say, “Our Lord, do not join us with the wrongdoing people.”

وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْأَعْرَافِ رِجَالًا يَعْرِفُونَهُم بِسِيمَاهُمْ قَالُوا مَا أَغْنَىٰ عَنكُمْ جَمْعُكُمْ وَمَا كُنتُمْ تَسْتَكْبِرُونَ  [48]

(48) የአዕራፍም ሰዎች በምልክታቸው የሚያውቁዋቸውን (ታላላቅ) ሰዎች ይጣራሉ። «ስብስባችሁና በብዛታችሁ የምትኮሩ መኾናችሁም ከእናንተ ምንም አልጠቀማችሁ» ይሏቸዋል።

(48) The people of the Heights will call out to some men whom they recognize by their marks, saying, “Neither your great numbers, nor your arrogance were of any avail to you.”

أَهَٰؤُلَاءِ الَّذِينَ أَقْسَمْتُمْ لَا يَنَالُهُمُ اللَّهُ بِرَحْمَةٍ ۚ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ لَا خَوْفٌ عَلَيْكُمْ وَلَا أَنتُمْ تَحْزَنُونَ  [49]

(49) እነዚያ አላህ በችሮታው አያገኛቸውም ብላችሁ የማላችሁት (ደካሞች) እነዚህ ናቸውን «ገነትን ግቡ ፍርሃት የለባችሁም እናንተም አታዝኑም» (ተባሉ ይሏቸዋል)።

(49) “Are these the ones whom you swore that Allah would never grant mercy?” “Enter Paradise; you will have no fear, nor will you grieve.”

وَنَادَىٰ أَصْحَابُ النَّارِ أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَنْ أَفِيضُوا عَلَيْنَا مِنَ الْمَاءِ أَوْ مِمَّا رَزَقَكُمُ اللَّهُ ۚ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ حَرَّمَهُمَا عَلَى الْكَافِرِينَ  [50]

(50) የእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎች «በእኛ ላይ ከውሃ አፍስሱብን ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ (ጣሉልን)» ብለው ጠሩዋቸዋል። እነርሱም «አላህ በከሓዲዎች ላይ እርም አድርጓቸዋል» ይሏቸዋል።

(50) The people of the Fire will call out to the people of Paradise, “Send down to us some water or any provision that Allah has given you.” They will say, “Allah has forbidden both to the disbelievers,

الَّذِينَ اتَّخَذُوا دِينَهُمْ لَهْوًا وَلَعِبًا وَغَرَّتْهُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا ۚ فَالْيَوْمَ نَنسَاهُمْ كَمَا نَسُوا لِقَاءَ يَوْمِهِمْ هَٰذَا وَمَا كَانُوا بِآيَاتِنَا يَجْحَدُونَ  [51]

(51) እነዚያ ሃይማኖታቸውን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው የያዙ የቅርቢቱም ሕይወት ያታለለቻቸው ይህንን ቀናቸውን መገናኘትን እንደረሱ በተአምራታችንም ይክዱ እንደነበሩ ዛሬ እንረሳቸዋልን።

(51) those who took their religion as amusement and play, and were deceived by the life of this world. Today We will ignore them just as they ignored their meeting of this Day and because they used to reject Our verses.”

وَلَقَدْ جِئْنَاهُم بِكِتَابٍ فَصَّلْنَاهُ عَلَىٰ عِلْمٍ هُدًى وَرَحْمَةً لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ  [52]

(52) ከዕውቀት ጋርም የዘረዘርነው የኾነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ሕዝቦች መምሪያና እዝነት ሲኾን በእርግጥ አመጣንላቸው።

(52) We have brought them a Book which We have explained in detail on the basis of knowledge, as guidance and mercy for people who believe.

هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا تَأْوِيلَهُ ۚ يَوْمَ يَأْتِي تَأْوِيلُهُ يَقُولُ الَّذِينَ نَسُوهُ مِن قَبْلُ قَدْ جَاءَتْ رُسُلُ رَبِّنَا بِالْحَقِّ فَهَل لَّنَا مِن شُفَعَاءَ فَيَشْفَعُوا لَنَا أَوْ نُرَدُّ فَنَعْمَلَ غَيْرَ الَّذِي كُنَّا نَعْمَلُ ۚ قَدْ خَسِرُوا أَنفُسَهُمْ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ  [53]

(53) (የዛቻውን) ፍጻሜውን እንጂ ሌላ አይጠባበቁም። ፍጻሜው በሚመጣበት ቀን እነዚያ ከመምጣቱ በፊት የረሱት ሰዎች «የጌታችን መልክተኞች በእርግጥ በውነት መጥተዋል። ለእኛ ያማልዱም ዘንድ አማላጆች አልሉን ወይስ ከዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላን ሥራ እንሠራ ዘንድ (ወደ ምድረ ዓለም) እንመለሳለን» ይላሉ። ነፍሶቻቸውን በእርግጥ አከሰሩ። ይቀጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ጠፋቸው።

(53) Are they waiting except for the fulfillment [of its warning]? On the Day when it is fulfilled, those who ignored it before will say, “The messengers of our Lord surely came with the truth. Are there any intercessors who can intercede on our behalf? Or can we be sent back so that we may do other than what we used to do?” In fact, they will have ruined themselves and all that they used to fabricate will be lost from them.

إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ يَطْلُبُهُ حَثِيثًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ وَالنُّجُومَ مُسَخَّرَاتٍ بِأَمْرِهِ ۗ أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ ۗ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ  [54]

(54) ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው። ከዚያም (ለክብሩ በምስማማ መልኩ) በዐርሹ ላይ ተደላደለ። (አላህ) ሌሊትን በቀን ፈጥኖ የሚፈልገው ሲኾን ይሸፍናል። ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ (ፈጠራቸው)። ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው። የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ።

(54) Your Lord is Allah, Who created the heavens and earth in six days, and then rose over [istawa] the Throne. He makes the night and day overlap in rapid succession. He made the sun, the moon, and the stars – all subservient to His command. Behold, His is the creation and the command. Blessed is Allah, the Lord of the worlds.

ادْعُوا رَبَّكُمْ تَضَرُّعًا وَخُفْيَةً ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ  [55]

(55) ጌታችሁን ተዋርዳችሁ በድብቅም ለምኑት። እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና።

(55) Call upon your Lord with humility and in private, for He does not like the transgressors.

وَلَا تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَاحِهَا وَادْعُوهُ خَوْفًا وَطَمَعًا ۚ إِنَّ رَحْمَتَ اللَّهِ قَرِيبٌ مِّنَ الْمُحْسِنِينَ  [56]

(56) በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ። ፈርታችሁና ከጅላችሁም ተገዙት። የአላህ ችሮታ ከበጎ አድራጊዎች ቅርብ ነውና።

(56) Do not spread corruption on earth after it has been set aright, but call upon Him with fear and hope. Indeed, the mercy of Allah is close to those who do good.

وَهُوَ الَّذِي يُرْسِلُ الرِّيَاحَ بُشْرًا بَيْنَ يَدَيْ رَحْمَتِهِ ۖ حَتَّىٰ إِذَا أَقَلَّتْ سَحَابًا ثِقَالًا سُقْنَاهُ لِبَلَدٍ مَّيِّتٍ فَأَنزَلْنَا بِهِ الْمَاءَ فَأَخْرَجْنَا بِهِ مِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ ۚ كَذَٰلِكَ نُخْرِجُ الْمَوْتَىٰ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ  [57]

(57) እርሱም ያ ነፋሶችን ከችሮታው (ከዝናም) በፊት አብሳሪዎች አድርጎ የሚልክ ነው። ከባዳዎችንም ደመናዎች በተሸከሙ ጊዜ ሙት ወደ ኾነ አገር እንነዳዋለን። በእርሱም ውሃን እናወርዳለን። ከፍሬዎችም ሁሉ በእርሱ እናወጣለን። እንደዚሁ ትገነዘቡ ዘንድ ሙታንን (ከመቃብር) እናወጣለን።

(57) It is He Who sends the winds as glad tidings ahead of His Mercy, until when they bear heavy clouds, We drive them to a lifeless land then We send down rain from it, producing thereby every kind of fruit. This is how We raise the dead, so that you may take heed.

وَالْبَلَدُ الطَّيِّبُ يَخْرُجُ نَبَاتُهُ بِإِذْنِ رَبِّهِ ۖ وَالَّذِي خَبُثَ لَا يَخْرُجُ إِلَّا نَكِدًا ۚ كَذَٰلِكَ نُصَرِّفُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَشْكُرُونَ  [58]

(58) መልካሙም አገር በጌታው ፈቃድ በቃዩ (ያማረ ኾኖ) ይወጣል። ያም መጥፎ የኾነው (በቃዩ) ደካማ ኾኖ እንጂ አይወጣም። እንደዚሁ ለሚያመሰግኑ ሕዝቦች ታምራትን እናብራራለን።

(58) The good land produces its vegetation by the Will of its Lord, but the bad land only produces poor and scanty vegetation. This is how We diversify the signs for people who give thanks.

لَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ  [59]

(59) ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው። አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ። ለእናንተ ከርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም። እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።»

(59) Indeed, We sent Noah to his people. He said, “O my people, worship Allah; you have no god other than Him. I fear for you the punishment of a momentous Day.”

قَالَ الْمَلَأُ مِن قَوْمِهِ إِنَّا لَنَرَاكَ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ  [60]

(60) ከሕዝቦቹ (የካዱት) መሪዎቹ፡- «እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾነህ በእርግጥ እናይሃለን» አሉት።

(60) The chiefs of his people said, “We certainly see that you are clearly misguided.”

قَالَ يَا قَوْمِ لَيْسَ بِي ضَلَالَةٌ وَلَٰكِنِّي رَسُولٌ مِّن رَّبِّ الْعَالَمِينَ  [61]

(61) አላቸው «ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም። ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልእክተኛ ነኝ።»

(61) He said, “O my people, I am not misguided, but I am a messenger from the Lord of the worlds.

أُبَلِّغُكُمْ رِسَالَاتِ رَبِّي وَأَنصَحُ لَكُمْ وَأَعْلَمُ مِنَ اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ  [62]

(62) «የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ። ለእናንተም እመክራችኋለሁ። ከአላህም በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ።»

(62) I convey to you the messages of my Lord and give you sincere advice, and I know from Allah what you do not know.

أَوَعَجِبْتُمْ أَن جَاءَكُمْ ذِكْرٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَلَىٰ رَجُلٍ مِّنكُمْ لِيُنذِرَكُمْ وَلِتَتَّقُوا وَلَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ  [63]

(63) «አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከእናንተው (ጎሳ) በኾነ ሰው ላይ እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ቢመጣላችሁ ትደነቃላችሁን» (አላቸው)።

(63) Are you surprised that a reminder should come to you from your Lord through a man from among yourselves, so that he may warn you and you may fear Allah, and so that you may be shown mercy?”

فَكَذَّبُوهُ فَأَنجَيْنَاهُ وَالَّذِينَ مَعَهُ فِي الْفُلْكِ وَأَغْرَقْنَا الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمًا عَمِينَ  [64]

(64) ወዲያውም አስተባበሉት። እርሱንና እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያሉትን (አማኞች) በታንኳዋ ውስጥ አዳንናቸው። እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን አሰጠምን። እነርሱ (ልበ) ዕውራን ሕዝቦች ነበሩና።

(64) But they rejected him, so We delivered him and those who were with him in the Ark, and We drowned those who rejected Our signs. They were indeed people who were blind [to the truth].

وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ  [65]

(65) ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን። «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ። ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም። (የአላህን ቅጣት) አትፈሩምን» አላቸው።

(65) To the people of ‘Ād We sent their brother Hūd. He said, “O my people, worship Allah; you have no god other than Him. Will you not then fear Him?”

قَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن قَوْمِهِ إِنَّا لَنَرَاكَ فِي سَفَاهَةٍ وَإِنَّا لَنَظُنُّكَ مِنَ الْكَاذِبِينَ  [66]

(66) ከሕዝቦቹ እነዚያ የካዱት መሪዎች «እኛ በሞኝነት ላይ ኾነህ በእርግጥ እናይሃለን። እኛም ከውሸተኞቹ ነህ ብለን እንጠረጥርሃለን» አሉት።

(66) The disbelieving chiefs of his people said, “Indeed, we see you as foolish, and we think you are one of the liars.”

قَالَ يَا قَوْمِ لَيْسَ بِي سَفَاهَةٌ وَلَٰكِنِّي رَسُولٌ مِّن رَّبِّ الْعَالَمِينَ  [67]

(67) (እርሱም) አላቸው «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ሞኝነት የለብኝም። ግን እኔ ከዓለማት ጌታ የተላክሁ ነኝ።»

(67) He said, “O my people, there is no foolishness in me, but I am a messenger from the Lord of the worlds,

أُبَلِّغُكُمْ رِسَالَاتِ رَبِّي وَأَنَا لَكُمْ نَاصِحٌ أَمِينٌ  [68]

(68) «የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ። እኔም ለእናንተ ታማኝ መካሪ ነኝ።»

(68) I convey to you the messages of my Lord, and I am your sincere adviser.

أَوَعَجِبْتُمْ أَن جَاءَكُمْ ذِكْرٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَلَىٰ رَجُلٍ مِّنكُمْ لِيُنذِرَكُمْ ۚ وَاذْكُرُوا إِذْ جَعَلَكُمْ خُلَفَاءَ مِن بَعْدِ قَوْمِ نُوحٍ وَزَادَكُمْ فِي الْخَلْقِ بَسْطَةً ۖ فَاذْكُرُوا آلَاءَ اللَّهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ  [69]

(69) «ከጌታችሁ የኾነ ግሣጼ ከእናንተው ውስጥ ባንድ ሰው ላይ ያስጠነቀቃችሁ ዘንድ ቢመጣባችሁ ትደነቃላችሁን ከኑሕም ሕዝቦች በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በፍጠረትም ግዙፍነትን በጨመረላችሁ ጊዜ አስታውሱ። የሻችሁትንም ታገኙ ዘንድ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ።»

(69) Are you surprised that a reminder should come to you from your Lord through a man from among yourselves? Remember when He made you successors after the people of Noah and increased you amply in stature. Remember Allah’s favors, so that you may be successful.”

قَالُوا أَجِئْتَنَا لِنَعْبُدَ اللَّهَ وَحْدَهُ وَنَذَرَ مَا كَانَ يَعْبُدُ آبَاؤُنَا ۖ فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَا إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ  [70]

(70) «አላህን ብቻውን እንድንገዛ አባቶቻችንም ይገዙት የነበረውን (አማልክት) እንድንተው መጣህብን ከውነተኞች ከኾንክ የምታስፈራብንን (ቅጣት) አምጣብን» አሉ።

(70) They said, “Have you come to tell us that we should worship Allah alone and abandon what our forefathers used to worship? Bring upon us what you are threatening us with, if you are truthful.”

قَالَ قَدْ وَقَعَ عَلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ رِجْسٌ وَغَضَبٌ ۖ أَتُجَادِلُونَنِي فِي أَسْمَاءٍ سَمَّيْتُمُوهَا أَنتُمْ وَآبَاؤُكُم مَّا نَزَّلَ اللَّهُ بِهَا مِن سُلْطَانٍ ۚ فَانتَظِرُوا إِنِّي مَعَكُم مِّنَ الْمُنتَظِرِينَ  [71]

(71) «ከጌታችሁ የኾነ ቅጣትና ቁጣ በእናንተ ላይ በእውነት ተረጋገጠ። እናንተና አባቶቻችሁም (አማልክት ብላችሁ) በጠራችኋቸው ስሞች አላህ በእርሷ ምንም ማስረጃ ያላወረደባት ስትኾን ትከራከሩኛላችሁን ተጠባባቁም እኔ ከእናንተ ጋር ከተጠባባቂዎቹ ነኝና» አለ።

(71) He said, “You are definitely going to be subjected to the punishment and wrath of your Lord. Do you dispute with me concerning mere names that you and your forefathers have made up which Allah has never authorized? Then wait. I am too waiting with you.”

فَأَنجَيْنَاهُ وَالَّذِينَ مَعَهُ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَقَطَعْنَا دَابِرَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۖ وَمَا كَانُوا مُؤْمِنِينَ  [72]

(72) እርሱንና እነዚያንም አብረውት የነበሩትን ከእኛ በኾነው ችሮታ (ከቅጣት) አዳንናቸው። የእነዚያንም በተአምራታችን ያስተባበሉትንና አማኞች ያልነበሩትን መሠረት ቆረጥን።

(72) Then We saved him and those who were with him by Our mercy, and exterminated all those who rejected Our signs, for they would not believe.

وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ قَدْ جَاءَتْكُم بَيِّنَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ هَٰذِهِ نَاقَةُ اللَّهِ لَكُمْ آيَةً ۖ فَذَرُوهَا تَأْكُلْ فِي أَرْضِ اللَّهِ ۖ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ  [73]

(73) ወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን። አላቸው «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ። ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም። (እውነተኛ ለመኾኔ) ከጌታችሁ የኾነች ምልክት በእርግጥ መጥታላችኋለች። ይህች ለእናንተ ተዓምር ስትኾን የአላህ ግመል ናትና ተዋት። በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ፤ (ትጠጣም)። በክፉ አትንኳትም። አሳማሚ ቅጣት ይይዛችኋልና።»

(73) And to the people of Thamūd [We sent] their brother, Sālih. He said, “O my people, worship Allah; you have no god other than Him. There has come to you a clear proof from your Lord: this is a she-camel of Allah, as a sign to you. So leave her to graze in Allah’s land, and do not harm her in any way, or else a painful punishment will seize you.

وَاذْكُرُوا إِذْ جَعَلَكُمْ خُلَفَاءَ مِن بَعْدِ عَادٍ وَبَوَّأَكُمْ فِي الْأَرْضِ تَتَّخِذُونَ مِن سُهُولِهَا قُصُورًا وَتَنْحِتُونَ الْجِبَالَ بُيُوتًا ۖ فَاذْكُرُوا آلَاءَ اللَّهِ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ  [74]

(74) «ከዓድም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ ባስቀመጣችሁ ጊዜ አስታውሱ። ከሜዳዎቿ (ሸክላ) ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ። ከተራራዎችም ቤቶችን ትጠርባላችሁ። ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ። በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ።»

(74) Remember when He made you successors after ‘Ād and settled you in the land; you make palaces on its plains and carve homes in the mountains. So remember the bounties of Allah, and do not spread corruption in the land.”

قَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ اسْتَكْبَرُوا مِن قَوْمِهِ لِلَّذِينَ اسْتُضْعِفُوا لِمَنْ آمَنَ مِنْهُمْ أَتَعْلَمُونَ أَنَّ صَالِحًا مُّرْسَلٌ مِّن رَّبِّهِ ۚ قَالُوا إِنَّا بِمَا أُرْسِلَ بِهِ مُؤْمِنُونَ  [75]

(75) ከወገኖቹ እነዚያ የኮሩት መሪዎች ለእነዚያ ለተሸነፉት ከነሱ ላመኑት፡- «ሷሊህ ከጌታው መላኩን ታውቃላችሁን» አሏቸው። « (አዎን)፡- እኛ እርሱ በተላከበት ነገር አማኞች ነን» አሉ።

(75) The arrogant chiefs of his people said to those believers who were oppressed, “Do you really know that Sālih has been sent by his Lord?” They said, “We surely believe in what he has been sent with.”

قَالَ الَّذِينَ اسْتَكْبَرُوا إِنَّا بِالَّذِي آمَنتُم بِهِ كَافِرُونَ  [76]

(76) እነዚያ የኮሩት፡- «እኛ በዚያ እናንተ በርሱ ባመናችሁበት ከሓዲዎች ነን» አሉ።

(76) Those who were arrogant said, “As for us, we surely disbelieve in what you believe.”

فَعَقَرُوا النَّاقَةَ وَعَتَوْا عَنْ أَمْرِ رَبِّهِمْ وَقَالُوا يَا صَالِحُ ائْتِنَا بِمَا تَعِدُنَا إِن كُنتَ مِنَ الْمُرْسَلِينَ  [77]

(77) ወዲያውም ግመሊቱን ወጓት። ከጌታቸውም ትዕዛዝ ወጡ። አሉም፡- «ሷሊህ ሆይ! ከመልክተኞቹ እንደኾንክ የምታስፈራራብንን (ቅጣት) አምጣብን።»

(77) Then they killed the she-camel and defied their Lord’s command, and said, “Bring us what you are threatening us, if you are indeed one of the messengers.”

فَأَخَذَتْهُمُ الرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا فِي دَارِهِمْ جَاثِمِينَ  [78]

(78) ወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው። በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ።

(78) Then an earthquake seized them, and they fell lifeless in their homes.

فَتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَا قَوْمِ لَقَدْ أَبْلَغْتُكُمْ رِسَالَةَ رَبِّي وَنَصَحْتُ لَكُمْ وَلَٰكِن لَّا تُحِبُّونَ النَّاصِحِينَ  [79]

(79) (ሷሊህ) ከእነርሱም ዞረ። (እንዲህም) አለ «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልክት በእርግጥ አደረስኩላችሁ። ለእናንተም መከርኳችሁ። ግን መካሪዎችን አትወዱም።»

(79) So he turned away from them, saying, “O my people, I did convey my Lord’s message to you and gave you sincere advice, but you do not like sincere advisers.”

وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ  [80]

(80) ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)። «አስቀያሚን ሥራ ትሠራላችሁን በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም።»

(80) And [We sent] Lot, when he said to his people, “Do you commit such a shameful act that nobody has ever done before you?

إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ شَهْوَةً مِّن دُونِ النِّسَاءِ ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ مُّسْرِفُونَ  [81]

(81) «እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል በእርግጥ ትመጡባቸዋላችሁ። በእውነቱ እናንተ ወሰንን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ።»

(81) For you approach men lustfully instead of women; you are but a transgressing people.”

وَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِ إِلَّا أَن قَالُوا أَخْرِجُوهُم مِّن قَرْيَتِكُمْ ۖ إِنَّهُمْ أُنَاسٌ يَتَطَهَّرُونَ  [82]

(82) የሕዝቦቹም መልስ « (ሎጥንና ተከታዮቹን) ከከተማችሁ አውጧቸው። እነሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።

(82) The only reply his people gave was to say, “Drive them out of your town, for they are people who keep themselves pure!”

فَأَنجَيْنَاهُ وَأَهْلَهُ إِلَّا امْرَأَتَهُ كَانَتْ مِنَ الْغَابِرِينَ  [83]

(83) እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳንናቸው ሚስቱ ብቻ ስትቀር። እርሷ (ለጥፋት) ከቀሩት ኾነች።

(83) So We saved him and his family except his wife; she was one of those who remained behind.

وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُجْرِمِينَ  [84]

(84) በእነሱም ላይ (የእሳት) ዝናብን አዘነብንባቸው። የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት።

(84) And We rained down upon them a rain [of brimstone]. So see how was the end of the evildoers.

وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ قَدْ جَاءَتْكُم بَيِّنَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ فَأَوْفُوا الْكَيْلَ وَالْمِيزَانَ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَاحِهَا ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ  [85]

(85) ወደ መድየንም (ምድያን) ወንድማቸውን ሹዓይብን (ላክን)፤ አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ። ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም። ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ በእርግጥ መጥታላችኋለች። ስፍርንና ሚዛንን ሙሉ። ሰዎችንም አንዳቾቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) አታጉድሉባቸው። በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ። ይህ ምእምናን እንደኾናችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው።»

(85) And to the people of Midian [We sent] their brother Shu‘ayb. He said, “O my people, worship Allah; you have no god other than Him. There has come to you a clear proof from your Lord. Give full measure and weight, and do not defraud people of their property, and do not spread corruption in the land after it has been set aright. That is best for you, if you are [truly] believers.

وَلَا تَقْعُدُوا بِكُلِّ صِرَاطٍ تُوعِدُونَ وَتَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ مَنْ آمَنَ بِهِ وَتَبْغُونَهَا عِوَجًا ۚ وَاذْكُرُوا إِذْ كُنتُمْ قَلِيلًا فَكَثَّرَكُمْ ۖ وَانظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُفْسِدِينَ  [86]

(86) « (ሰዎችን) የምታስፈራሩና ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱ መጥመሟንም የምትፈልጉዋት ኾናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ። ጥቂቶችም በነበራችሁና ባበዛችሁ ጊዜ አስታውሱ። የአጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።»

(86) Do not lie in wait on every path, threatening and preventing from Allah’s path those who believe in Him, and seeking to make it crooked. Remember when you were few, then He increased you in number. See how was the end of those who spread corruption.

وَإِن كَانَ طَائِفَةٌ مِّنكُمْ آمَنُوا بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ وَطَائِفَةٌ لَّمْ يُؤْمِنُوا فَاصْبِرُوا حَتَّىٰ يَحْكُمَ اللَّهُ بَيْنَنَا ۚ وَهُوَ خَيْرُ الْحَاكِمِينَ  [87]

(87) «ከእናንተም በዚያ እኔ በእርሱ በተላክሁበት ያመኑ ጭፍሮችና ያላመኑ ጭፍሮችም ቢኖሩ በመካከላችን አላህ እስከሚፈርድ ታገሱ። እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።»

(87) If there are some among you who believe in what I have been sent with, while others do not believe, then be patient until Allah judges between us, and He is the Best of Judges.”

قَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ اسْتَكْبَرُوا مِن قَوْمِهِ لَنُخْرِجَنَّكَ يَا شُعَيْبُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَكَ مِن قَرْيَتِنَا أَوْ لَتَعُودُنَّ فِي مِلَّتِنَا ۚ قَالَ أَوَلَوْ كُنَّا كَارِهِينَ  [88]

(88) ከሕዝቦቹ እነዚያ የኮሩት መሪዎች፡- «ሹዓይብ ሆይ! አንተንና እነዚያን ከአንተጋር ያመኑትን ከከተማችን በእርግጥ እናስወጣችኋለን። ወይም ወደ ሃይማኖታችን መመለስ አለባችሁ አሉ። የጠላንም ብንኾን» አላቸው።

(88) The arrogant chiefs of his people said, “O Shu‘ayb, we will surely drive you and those who believe with you out of our town unless you return to our faith.” He said, “Even if we detest it?

قَدِ افْتَرَيْنَا عَلَى اللَّهِ كَذِبًا إِنْ عُدْنَا فِي مِلَّتِكُم بَعْدَ إِذْ نَجَّانَا اللَّهُ مِنْهَا ۚ وَمَا يَكُونُ لَنَا أَن نَّعُودَ فِيهَا إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّنَا ۚ وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَيْءٍ عِلْمًا ۚ عَلَى اللَّهِ تَوَكَّلْنَا ۚ رَبَّنَا افْتَحْ بَيْنَنَا وَبَيْنَ قَوْمِنَا بِالْحَقِّ وَأَنتَ خَيْرُ الْفَاتِحِينَ  [89]

(89) «አላህ ከእርሷ ከአዳነን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ በእርግጥ ውሸትን ቀጠፍን። አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ለእኛ ወደእርሷ ልንመለስ አይገባንም። ጌታችን ዕውቀቱ ሁሉን ነገር ሰፋ። በአላህ ላይ ተጠጋን። ጌታችን ሆይ! በኛና በወገኖቻችን መካከል በውነት ፍረድ። አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህ» (አለ)

(89) We would be fabricating lies against Allah if we were to return to your faith after Allah has saved us from it. We will not return to it unless Our Lord Allah so wills. Our Lord has full knowledge of everything. In Allah we put our trust. Our Lord, judge between us and our people with truth, for You are the Best of the Judges.”

وَقَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن قَوْمِهِ لَئِنِ اتَّبَعْتُمْ شُعَيْبًا إِنَّكُمْ إِذًا لَّخَاسِرُونَ  [90]

(90) ከወገኖቹም እነዚያ የካዱት መሪዎች «ሹዓይብን ብትከተሉ እናንተ ያን ጊዜ ከሳሪዎች ናችሁ» አሉ።

(90) The disbelieving chiefs of his people said, “If you follow Shu‘ayb, you will certainly be losers.”

فَأَخَذَتْهُمُ الرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا فِي دَارِهِمْ جَاثِمِينَ  [91]

(91) ወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው። በከተማቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ።

(91) Then they were seized by the earthquake and they fell lifeless in their homes.

الَّذِينَ كَذَّبُوا شُعَيْبًا كَأَن لَّمْ يَغْنَوْا فِيهَا ۚ الَّذِينَ كَذَّبُوا شُعَيْبًا كَانُوا هُمُ الْخَاسِرِينَ  [92]

(92) እነዚያ ሹዓይብን ያሰተባበሉት በእርሷ እንዳልነበሩባት ኾኑ። እነዚ ሹዓይብን ያስተባበሉት እነርሱ ከሳሪዎች ኾኑ።

(92) Those who rejected Shu‘ayb became as if they had never lived there. Those who rejected Shu‘ayb were themselves the losers.

فَتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَا قَوْمِ لَقَدْ أَبْلَغْتُكُمْ رِسَالَاتِ رَبِّي وَنَصَحْتُ لَكُمْ ۖ فَكَيْفَ آسَىٰ عَلَىٰ قَوْمٍ كَافِرِينَ  [93]

(93) ከእነርሱም (ትቷቸው) ዞረ፡- «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልክቶች በእርግጥ አደረስኩላችሁ። ለእናንተም መከርኩ። ታዲያ በከሓዲዎች ሰዎች ላይ እንዴት አዝናለሁ» አለም።

(93) So he turned away from them and said, “O my people, I did convey to you the messages of my Lord, and gave you sincere advice. Why should I grieve for a disbelieving people?”

وَمَا أَرْسَلْنَا فِي قَرْيَةٍ مِّن نَّبِيٍّ إِلَّا أَخَذْنَا أَهْلَهَا بِالْبَأْسَاءِ وَالضَّرَّاءِ لَعَلَّهُمْ يَضَّرَّعُونَ  [94]

(94) በከተማ አንድንም ነቢይ አልላክንም ሰዎችዋን ይዋደቁ ዘንድ በድህነትና በጉዳት የያዝናቸው ብንኾን እንጂ።

(94) We have not sent any prophet to a town, but We seized its people with poverty and adversity, so that they may humble themselves.

ثُمَّ بَدَّلْنَا مَكَانَ السَّيِّئَةِ الْحَسَنَةَ حَتَّىٰ عَفَوا وَّقَالُوا قَدْ مَسَّ آبَاءَنَا الضَّرَّاءُ وَالسَّرَّاءُ فَأَخَذْنَاهُم بَغْتَةً وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ  [95]

(95) ከዚያም እስከበዙና «አባቶቻችንን ድህነትና በሺታ በእርግጥ ነክቷቸዋል። (ይኽም የጊዜ ልማድ ነው)» እስካሉ ድረስ በመጥፎው ስፍራ በጎውን ለወጥን። ወዲያውም እነርሱ የማያውቁ ኾነው በድንገት ያዝናቸው።

(95) Then We changed their adversity into prosperity until they flourished and said, “Our forefathers were also afflicted with hardship and ease.” Then We seized them by surprise while they were unaware.

وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْقُرَىٰ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَفَتَحْنَا عَلَيْهِم بَرَكَاتٍ مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ وَلَٰكِن كَذَّبُوا فَأَخَذْنَاهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ  [96]

(96) የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር። ግን አስተባበሉ። ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው።

(96) If only the people of the towns had believed and feared Allah, We would have certainly opened for them blessings from the heaven and earth. But they disbelieved, so We seized them for what they earned.

أَفَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَىٰ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا بَيَاتًا وَهُمْ نَائِمُونَ  [97]

(97) የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የተኙ ኾነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን

(97) Do the people of the towns feel secure that Our punishment will not befall them by night while they are asleep?

أَوَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَىٰ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا ضُحًى وَهُمْ يَلْعَبُونَ  [98]

(98) የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የሚጫወቱ ኾነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋድ ሊመጣባቸው አይፈሩምን

(98) Or do the people of the towns feel secure that Our punishment will not befall them by day while they are at play?

أَفَأَمِنُوا مَكْرَ اللَّهِ ۚ فَلَا يَأْمَنُ مَكْرَ اللَّهِ إِلَّا الْقَوْمُ الْخَاسِرُونَ  [99]

(99) የአላህንም ማዘናጋት አይፈሩምን የአላህንም ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር የሚተማመን የለም።

(99) Do they feel secure from the plan of Allah? None can feel secure from the plan of Allah except the people who are losers.

أَوَلَمْ يَهْدِ لِلَّذِينَ يَرِثُونَ الْأَرْضَ مِن بَعْدِ أَهْلِهَا أَن لَّوْ نَشَاءُ أَصَبْنَاهُم بِذُنُوبِهِمْ ۚ وَنَطْبَعُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَسْمَعُونَ  [100]

(100) ለእነዚያ ምድርን ከባለቤቶችዋ (ጥፋት) በኋላ ለሚወርሱት ብንሻ ኖሮ በኃጢኣቶቻቸው የምንቀጣቸው መኾናችን አልተገለጸላቸውምን በልቦቻቸውም ላይ እናትማለን። ስለዚህ እነርሱ አይሰሙም።

(100) Is it not clear to those who inherit the land after its former people that, if We so willed, We could punish them for their sins and seal up their hearts so that they do not hear?

تِلْكَ الْقُرَىٰ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَائِهَا ۚ وَلَقَدْ جَاءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِالْبَيِّنَاتِ فَمَا كَانُوا لِيُؤْمِنُوا بِمَا كَذَّبُوا مِن قَبْلُ ۚ كَذَٰلِكَ يَطْبَعُ اللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِ الْكَافِرِينَ  [101]

(101) እነዚህ ከተሞች (ከኑሕ እስከ ሹዓይብ ሰዎች የተነገሩት) ከወሬዎቻቸው ባንተ ላይ እንተርካለን። መልክተኞቻቸውም በግልጽ ተዓምራት በእርግጥ መጥተዋቸዋል። ከመምጣታቸው በፊት ባስተባበሉትም ነገር የሚያምኑ አልኾኑም። እንደዚሁ አላህ በከሓዲያን ልቦች ላይ ያትማል።

(101) These are the towns, some of whose stories We relate to you. Their messengers came to them with clear proofs, but they were not about to believe in what they had already rejected. This is how Allah seals up the hearts of the disbelievers.

وَمَا وَجَدْنَا لِأَكْثَرِهِم مِّنْ عَهْدٍ ۖ وَإِن وَجَدْنَا أَكْثَرَهُمْ لَفَاسِقِينَ  [102]

(102) ለብዙዎቻቸውም በቃል ኪዳናቸው መሙላትን አላገኘንም። አብዛኞቻቸውንም በእርግጥ አመጸኞች ኾነው አገኘናቸው።

(102) We did not find most of them committed to their covenant; rather We found most of them rebellious.

ثُمَّ بَعَثْنَا مِن بَعْدِهِم مُّوسَىٰ بِآيَاتِنَا إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِ فَظَلَمُوا بِهَا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُفْسِدِينَ  [103]

(103) ከዚያም ከበኋላቸው ሙሳን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቶቹ በተዓምራታችን ላክነው። በእርሷም ካዱ። ያጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት።

(103) Then We sent after them Moses with Our signs to Pharaoh and his chiefs, but they wrongfully rejected them. See how was the end of those who spread corruption.

وَقَالَ مُوسَىٰ يَا فِرْعَوْنُ إِنِّي رَسُولٌ مِّن رَّبِّ الْعَالَمِينَ  [104]

(104) ሙሳም አለ፡- «ፈርዖን ሆይ! እኔ ከዓለማት ጌታ የተላክሁ መልክተኛ ነኝ።»

(104) Moses said, “O Pharaoh, I am a messenger from the Lord of the worlds.

حَقِيقٌ عَلَىٰ أَن لَّا أَقُولَ عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ ۚ قَدْ جِئْتُكُم بِبَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ فَأَرْسِلْ مَعِيَ بَنِي إِسْرَائِيلَ  [105]

(105) «»በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው። ከጌታችሁ በተዓምር በእርግጥ መጣኋችሁ። የእስራኤልንም ልጆች ከእኔ ጋር ልቀቅ።

(105) I am obliged to say nothing concerning Allah except the truth. I have come to you with a clear proof from your Lord, so let the Children of Israel go with me.”

قَالَ إِن كُنتَ جِئْتَ بِآيَةٍ فَأْتِ بِهَا إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ  [106]

(106) (ፈርዖንም «በተዓምር የመጣህ እንደኾንክ ከውነተኞቹ ከኾንክ እርሷን አምጣት» አለው።

(106) Pharaoh said, “If you have brought a sign, then bring it forth if you are truthful.”

فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعْبَانٌ مُّبِينٌ  [107]

(107) በትሩንም ጣለ። እርስዋም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ኾነች።

(107) So he threw his staff, and it suddenly became a real serpent.

وَنَزَعَ يَدَهُ فَإِذَا هِيَ بَيْضَاءُ لِلنَّاظِرِينَ  [108]

(108) እጁንም አወጣ። እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ ኾነች።

(108) And he drew out his hand, and it was shining white to the beholders.

قَالَ الْمَلَأُ مِن قَوْمِ فِرْعَوْنَ إِنَّ هَٰذَا لَسَاحِرٌ عَلِيمٌ  [109]

(109) ከፈርዖን ሰዎች መማክርቶቹ፡- «ይህ በእርግጥ ዐዋቂ ድግምተኛ ነው» አሉ።

(109) The chiefs among Pharaoh’s people said, “This is indeed a learned magician!

يُرِيدُ أَن يُخْرِجَكُم مِّنْ أَرْضِكُمْ ۖ فَمَاذَا تَأْمُرُونَ  [110]

(110) «ከምድራችሁ ሊያወጣችሁ ይሻል» (አሉ)። «ታዲያ ምን ታዛላችሁ» (አለ)

(110) He seeks to drive you out of your land. [Pharaoh said], “So what do you advise?”

قَالُوا أَرْجِهْ وَأَخَاهُ وَأَرْسِلْ فِي الْمَدَائِنِ حَاشِرِينَ  [111]

(111) (እነርሱም) አሉ «እርሱንና ወንድሙን አቆይ። ወደ ከተሞቹም ሁሉ ሰብሳቢዎችን (ዘበኞች) ላክ።»

(111) They said, “let him and his brother wait for a while, and send heralds to the cities

يَأْتُوكَ بِكُلِّ سَاحِرٍ عَلِيمٍ  [112]

(112) «ዐዋቂ ድግምተኛ የኾነን ሁሉ ያመጡልሃልና።»

(112) to bring you every learned magician.”

وَجَاءَ السَّحَرَةُ فِرْعَوْنَ قَالُوا إِنَّ لَنَا لَأَجْرًا إِن كُنَّا نَحْنُ الْغَالِبِينَ  [113]

(113) ድግምተኞቹም ወደ ፈርዖን መጡ። «እኛ አሸናፊዎች ብንኾን ለእኛ በእርግጥ ዋጋ አለን» አሉ።

(113) The magicians came to Pharaoh and said, “Will we have a reward if we prevail?”

قَالَ نَعَمْ وَإِنَّكُمْ لَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ  [114]

(114) «አዎን እናንተም በእርግጥ ከባለሟሎቹ ትኾናላችሁ» አላቸው።

(114) He said, “Yes, and you will surely be of those who are close to me.”

قَالُوا يَا مُوسَىٰ إِمَّا أَن تُلْقِيَ وَإِمَّا أَن نَّكُونَ نَحْنُ الْمُلْقِينَ  [115]

(115) «ሙሳ ሆይ (በትርህን) ወይም (በፊት) ትጥላለህ ወይም እኛ ጣዮች እንኾናለን» አሉት።

(115) They said, “O Moses, will you throw first or will we be the first to throw?”

قَالَ أَلْقُوا ۖ فَلَمَّا أَلْقَوْا سَحَرُوا أَعْيُنَ النَّاسِ وَاسْتَرْهَبُوهُمْ وَجَاءُوا بِسِحْرٍ عَظِيمٍ  [116]

(116) «ጣሉ» አላቸው። (ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸው። አስፈራሩዋቸውም። ትልቅ ድግምትንም አመጡ።

(116) He said, “You throw first.” So when they threw, they enchanted the eyes of the people and struck terror into them, and produced a powerful magic.

وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنْ أَلْقِ عَصَاكَ ۖ فَإِذَا هِيَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَ  [117]

(117) ወደ ሙሳም፡- «በትርህን ጣል» ስንል ላክን። (ጣላትም) ወዲያውኑም የሚቀጣጥፉትን (ማታለያ) ትውጣለች።

(117) We inspired Moses, “Throw your staff,” and it suddenly swallowed up all their illusionary devices.

فَوَقَعَ الْحَقُّ وَبَطَلَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ  [118]

(118) እውነቱም ተገለጸ። ይሠሩት የነበሩትም (ድግምት) ተበላሸ።

(118) Thus the truth prevailed, and all what they did was proven to be false.

فَغُلِبُوا هُنَالِكَ وَانقَلَبُوا صَاغِرِينَ  [119]

(119) እዚያ ዘንድ ተሸነፉም። ወራዶችም ኾነው ተመለሱ።

(119) They were defeated right there and were utterly humiliated.

وَأُلْقِيَ السَّحَرَةُ سَاجِدِينَ  [120]

(120) ድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ።

(120) The magicians fell down in prostration,

قَالُوا آمَنَّا بِرَبِّ الْعَالَمِينَ  [121]

(121) አሉ፡- «በዓለማት ጌታ አመንን።»

(121) and said, “We believe in the Lord of the worlds,

رَبِّ مُوسَىٰ وَهَارُونَ  [122]

(122) «በሙሳና በሃሩን ጌታ።»

(122) the Lord of Moses and Aaron.”

قَالَ فِرْعَوْنُ آمَنتُم بِهِ قَبْلَ أَنْ آذَنَ لَكُمْ ۖ إِنَّ هَٰذَا لَمَكْرٌ مَّكَرْتُمُوهُ فِي الْمَدِينَةِ لِتُخْرِجُوا مِنْهَا أَهْلَهَا ۖ فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ  [123]

(123) ፈርዖን አለ፡- «እኔ ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በእርሱ አመናችሁን ይህ በከተማይቱ ውስጥ ሰዎቿን ከእርሷ ለማውጣት በእርግጥ የተስማማችሁበት ተንኮል ነው። ወደፊትም (የሚደርስባችሁን) ታውቃላችሁ።»

(123) Pharaoh said, “How dare you believe in him before I give you permission! This is indeed a plot that you devised in the city to drive out its people, but you will soon come to know.

لَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُم مِّنْ خِلَافٍ ثُمَّ لَأُصَلِّبَنَّكُمْ أَجْمَعِينَ  [124]

(124) «እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ በእርግጥ እቆራርጣለሁ። ከዚያም ሁላችሁንም በእርግጥ እሰቅላችኋለሁ።»

(124) I will surely cut off your hands and feet on opposite sides, then I will crucify you all together.”

قَالُوا إِنَّا إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ  [125]

(125) አሉ፡- «እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን።»

(125) They said, “We are surely returning to our Lord.

وَمَا تَنقِمُ مِنَّا إِلَّا أَنْ آمَنَّا بِآيَاتِ رَبِّنَا لَمَّا جَاءَتْنَا ۚ رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَتَوَفَّنَا مُسْلِمِينَ  [126]

(126) «የጌታችንም ተዓምራቶች በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በቀር ከእኛ አትጠላም። ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ። ሙስሊሞች ኾነን ግደለን።»

(126) Your only vengeance against us is because we believed in the signs of our Lord when they came to us. Our Lord, shower upon us patience and let us die as Muslims, submitting to You.”

وَقَالَ الْمَلَأُ مِن قَوْمِ فِرْعَوْنَ أَتَذَرُ مُوسَىٰ وَقَوْمَهُ لِيُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ وَيَذَرَكَ وَآلِهَتَكَ ۚ قَالَ سَنُقَتِّلُ أَبْنَاءَهُمْ وَنَسْتَحْيِي نِسَاءَهُمْ وَإِنَّا فَوْقَهُمْ قَاهِرُونَ  [127]

(127) ከፈርዖንም ሰዎች ታላላቆቹ (ለፈርዖን) «ሙሳንና ሰዎቹን በምድር ላይ እንዲያበላሹና (ሙሳም) አንተንና አማልክቶችህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን» አሉ። «ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን። ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን። እኛም ከበላያቸው ነን። አሸናፊዎች (ነን)» አለ።

(127) The chiefs among Pharaoh’s people said, “Will you leave Moses and his people to spread corruption in the land, and abandon you and your gods?” He said, “We will kill their sons and spare their women, for we have full dominance over them.”

قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ اسْتَعِينُوا بِاللَّهِ وَاصْبِرُوا ۖ إِنَّ الْأَرْضَ لِلَّهِ يُورِثُهَا مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ ۖ وَالْعَاقِبَةُ لِلْمُتَّقِينَ  [128]

(128) ሙሳ ለሰዎቹ፡- «ለአላህ ተገዙ ታገሱም። ምድር ለአላህ ናትና። ከባሮቹ ለሚሻው ያወርሳታል። ምሰጉንዋም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት» አላቸው።

(128) Moses said to his people, “Seek help from Allah and be patient. The earth belongs to Allah; He gives it as an inheritance to whom He wills of His slaves, but the outcome is for those who fear Allah.”

قَالُوا أُوذِينَا مِن قَبْلِ أَن تَأْتِيَنَا وَمِن بَعْدِ مَا جِئْتَنَا ۚ قَالَ عَسَىٰ رَبُّكُمْ أَن يُهْلِكَ عَدُوَّكُمْ وَيَسْتَخْلِفَكُمْ فِي الْأَرْضِ فَيَنظُرَ كَيْفَ تَعْمَلُونَ  [129]

(129) «ከመምጣትህም በፊት ከመጣኽልንም በኋላ ተሰቃየን» አሉት። «ጌታችሁ ጠላቶቻችሁን ሊያጠፋ እንዴት እንደምትሠሩም ይመለከት ዘንድ በምድር ላይ ሊተካችሁ ይሻል» አላቸው።

(129) They said, “We were oppressed before you came to us and after you came.” He said, “It may be that your Lord will destroy your enemy and make you successors in the land to see how you will do.”

وَلَقَدْ أَخَذْنَا آلَ فِرْعَوْنَ بِالسِّنِينَ وَنَقْصٍ مِّنَ الثَّمَرَاتِ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ  [130]

(130) የፈርዖንንም ቤተሰቦች እንዲገሰጹ በድርቅ ዓመታትና ከፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ ያዝናቸው።

(130) We afflicted the people of Pharaoh with famine and poor harvests, so that they may take heed.

فَإِذَا جَاءَتْهُمُ الْحَسَنَةُ قَالُوا لَنَا هَٰذِهِ ۖ وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ يَطَّيَّرُوا بِمُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُ ۗ أَلَا إِنَّمَا طَائِرُهُمْ عِندَ اللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ  [131]

(131) ደጊቱም ነገር (ምቾት) በመጣችላቸው ጊዜ «ይህች ለእኛ (ተገቢ) ናት» ይላሉ። ክፉትም ብታገኛቸው በሙሳና አብረውት ባሉት ገደቢስነት ያመካኛሉ። ንቁ! ገደቢስነታቸው አላህ ዘንድ ብቻ ነው። ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም።

(131) When prosperity came their way, they said, “This is what we deserve,” but when adversity befell them, they ascribed it to the misfortune of Moses and those who were with him. Indeed, their misfortune is decreed by Allah, but most of them do not know.

وَقَالُوا مَهْمَا تَأْتِنَا بِهِ مِنْ آيَةٍ لِّتَسْحَرَنَا بِهَا فَمَا نَحْنُ لَكَ بِمُؤْمِنِينَ  [132]

(132) (ለሙሳም) «በማንኛይቱም ተዓምር በእርሷ ልትደግምብን ብትመጣብን እኛ ለአንተ የምናምንልህ አይደለንም» አሉ።

(132) They said, “No matter what sign you may bring to enchant us, we are not going to believe in you.”

فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ  [133]

(133) ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም ነቀዝንም እንቁራሪቶችንም ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ።

(133) So We sent upon them flood, locusts, lice, frogs and blood – as clear signs, yet they persisted in arrogance and were a wicked people.

وَلَمَّا وَقَعَ عَلَيْهِمُ الرِّجْزُ قَالُوا يَا مُوسَى ادْعُ لَنَا رَبَّكَ بِمَا عَهِدَ عِندَكَ ۖ لَئِن كَشَفْتَ عَنَّا الرِّجْزَ لَنُؤْمِنَنَّ لَكَ وَلَنُرْسِلَنَّ مَعَكَ بَنِي إِسْرَائِيلَ  [134]

(134) በእነርሱም ላይ ቅጣቱ በወደቀባቸው ጊዜ «ሙሳ ሆይ! ጌታህን ላንተ ቃል ኪዳን በገባልህ ነገር ለእኛ ለምንልን። ከእኛ ቅጣቱን ብታነሳልን ለአንተ በእርግጥ እናምንልሃለን። የእስራኤልንም ልጆች ከአንተ ጋር በእርግጥ እንለቃለን፤» አሉ።

(134) When a scourge befell them, they said, “O Moses, call upon your Lord for us by virtue of the covenant He has made to you; if you remove the scourge from us, we will surely believe in you and will let the Children of Israel go with you.”

فَلَمَّا كَشَفْنَا عَنْهُمُ الرِّجْزَ إِلَىٰ أَجَلٍ هُم بَالِغُوهُ إِذَا هُمْ يَنكُثُونَ  [135]

(135) እነርሱም ደራሾቹ እኾኑበት ጊዜ ድረስ ቅጣትን ከእነሱ ላይ ባነሳን ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ቃላቸውን ያፈርሳሉ።

(135) But when We removed the scourge from them until an appointed term that they were bound to reach, they broke their promise.

فَانتَقَمْنَا مِنْهُمْ فَأَغْرَقْنَاهُمْ فِي الْيَمِّ بِأَنَّهُمْ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَكَانُوا عَنْهَا غَافِلِينَ  [136]

(136) እነርሱ በተዓምራታችን ስለአስተባበሉም ከእርሷ ዘንጊዎች ስለኾኑም፤ ከእነሱ ተበቀልን። በባሕርም ውስጥ አሰጠምናቸው።

(136) So We subjected them to retribution, and drowned them in the sea because they rejected Our signs and were heedless of them.

وَأَوْرَثْنَا الْقَوْمَ الَّذِينَ كَانُوا يُسْتَضْعَفُونَ مَشَارِقَ الْأَرْضِ وَمَغَارِبَهَا الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا ۖ وَتَمَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ الْحُسْنَىٰ عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ بِمَا صَبَرُوا ۖ وَدَمَّرْنَا مَا كَانَ يَصْنَعُ فِرْعَوْنُ وَقَوْمُهُ وَمَا كَانُوا يَعْرِشُونَ  [137]

(137) እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምሥራቆችዋንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው። የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች። ፈርዖንና ሰዎቹም ይሠሩት የነበረውን (ሕንጻ) ዳስ ያደርጉትም የነበረውን አፈረስን።

(137) And We made the people who had been oppressed to inherit the lands of the east and west that We had blessed. The good word of your Lord was fulfilled for the Children of Israel because of what they endured patiently, and We destroyed what Pharaoh and his people used to make and what they used to construct.

وَجَاوَزْنَا بِبَنِي إِسْرَائِيلَ الْبَحْرَ فَأَتَوْا عَلَىٰ قَوْمٍ يَعْكُفُونَ عَلَىٰ أَصْنَامٍ لَّهُمْ ۚ قَالُوا يَا مُوسَى اجْعَل لَّنَا إِلَٰهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ ۚ قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ  [138]

(138) የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሻገርናቸው። ለእነርሱ በኾኑ ጣዖታት (መገዛት) ላይ በሚዘወትሩ ሕዝቦች ላይ አለፉም። «ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን» አሉት። «እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ፤» አላቸው።

(138) We led the Children of Israel across the sea, then they came upon a people who were devoted to their idols. They said, “O Moses, make for us a god just as they have gods.” He said, “You are indeed an ignorant people.

إِنَّ هَٰؤُلَاءِ مُتَبَّرٌ مَّا هُمْ فِيهِ وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ  [139]

(139) «እነዚህ እነርሱ በውስጡ ያሉበት ነገር ጠፊ ነው። ይሰሩት የነበሩትም ብልሹ ነው» (አላቸው)፤

(139) Indeed, what they follow is doomed to destruction and what they do is worthless.”

قَالَ أَغَيْرَ اللَّهِ أَبْغِيكُمْ إِلَٰهًا وَهُوَ فَضَّلَكُمْ عَلَى الْعَالَمِينَ  [140]

(140) «ከአላህ ሌላ እርሱ ከዓለማት ያበለጣችሁ ሲኾን (የምትገዙት) አምላክን እፈልግላችኋለሁን» አለ።

(140) He said, “Shall I seek for you a god other than Allah, when He has favored you above the worlds?”

وَإِذْ أَنجَيْنَاكُم مِّنْ آلِ فِرْعَوْنَ يَسُومُونَكُمْ سُوءَ الْعَذَابِ ۖ يُقَتِّلُونَ أَبْنَاءَكُمْ وَيَسْتَحْيُونَ نِسَاءَكُمْ ۚ وَفِي ذَٰلِكُم بَلَاءٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَظِيمٌ  [141]

(141) ከፈርዖንም ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሱዋችሁ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚገድሉ ሴቶቻችሁንም የሚተዉ ሲኾኑ ባዳናችሁ ጊዜ (አስታውሱ)። በዚህም ውስጥ ከጌታችሁ ዘንድ የኾነ ከባድ ፈተና አለበት።

(141) And [remember] when We saved you from the people of Pharaoh, who were afflicting you with the worst punishment – killing your sons and sparing your women. That was a great trial from your Lord.

وَوَاعَدْنَا مُوسَىٰ ثَلَاثِينَ لَيْلَةً وَأَتْمَمْنَاهَا بِعَشْرٍ فَتَمَّ مِيقَاتُ رَبِّهِ أَرْبَعِينَ لَيْلَةً ۚ وَقَالَ مُوسَىٰ لِأَخِيهِ هَارُونَ اخْلُفْنِي فِي قَوْمِي وَأَصْلِحْ وَلَا تَتَّبِعْ سَبِيلَ الْمُفْسِدِينَ  [142]

(142) ሙሳንም ሰላሳን ሌሊት (ሊጾምና ልናነጋግረው) ቀጠርነው። በዐስርም (ሌሊት) ሞላናት። የጌታውም ቀጠሮ አርባ ሌሊት ሲኾን ተፈጸመ። ሙሳም ለወንድሙ ሃሩን «በሕዝቦቼ ላይ ተተካኝ። አሳምርም የአጥፊዎችንም መንገድ አትከተል» አለው።

(142) We appointed for Moses thirty nights, and completed it with ten more, whereby the term of forty nights set by Allah was fulfilled. Moses said to his brother Aaron, “Take my place among my people in my absence, keep things right, and do not follow the way of those who spread corruption.”

وَلَمَّا جَاءَ مُوسَىٰ لِمِيقَاتِنَا وَكَلَّمَهُ رَبُّهُ قَالَ رَبِّ أَرِنِي أَنظُرْ إِلَيْكَ ۚ قَالَ لَن تَرَانِي وَلَٰكِنِ انظُرْ إِلَى الْجَبَلِ فَإِنِ اسْتَقَرَّ مَكَانَهُ فَسَوْفَ تَرَانِي ۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا ۚ فَلَمَّا أَفَاقَ قَالَ سُبْحَانَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُؤْمِنِينَ  [143]

(143) ሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! (ነፍስህን) አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ። (አላህም)፡- «በፍጹም አታየኝም ግን ወደ ተራራው ተመልከት። በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ» አለው። ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው። ሙሳም ጮሆ ወደቀ። በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ። ወዳንተ ተመለስኩ። እኔም (በወቅቱ) የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ።

(143) When Moses came at Our appointed time and his Lord spoke to him, he said, “My Lord, reveal Yourself to me so that I may look at You.” Allah said, “You will not be able to see Me. But look at the mountain; if it stays firm in its place, only then will you see Me.” When his Lord appeared to the mountain, it was leveled to dust and Moses fell unconscious. When he recovered, he said, “Glory be to You! I repent to You and I am the first of the believers.”

قَالَ يَا مُوسَىٰ إِنِّي اصْطَفَيْتُكَ عَلَى النَّاسِ بِرِسَالَاتِي وَبِكَلَامِي فَخُذْ مَا آتَيْتُكَ وَكُن مِّنَ الشَّاكِرِينَ  [144]

(144) (አላህም) አለው፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ በመልክቶቼና በማናገሬ በሰዎች ላይ መረጥኩህ። የሰጡህንም ያዝ። ከአመስጋኞቹም ኹን።»

(144) He said, “O Moses, I have chosen you above other people, by giving you My messages and speaking to you. So hold fast to what I have given you, and be of those who are grateful.”

وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ مَّوْعِظَةً وَتَفْصِيلًا لِّكُلِّ شَيْءٍ فَخُذْهَا بِقُوَّةٍ وَأْمُرْ قَوْمَكَ يَأْخُذُوا بِأَحْسَنِهَا ۚ سَأُرِيكُمْ دَارَ الْفَاسِقِينَ  [145]

(145) ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት። (አልንም) በብርታትም ያዛት። ሕዝቦችህንም በመልካሟ እንዲይዙ እዘዛቸው። የአመጸኞቹን አገር በእርግጥ አሳያችኋለሁ።

(145) We inscribed for him in the Tablets admonition of all things and explanation of everything. “Hold fast to them and ask your people to follow the best of it. I will show you the home of the rebellious.

سَأَصْرِفُ عَنْ آيَاتِيَ الَّذِينَ يَتَكَبَّرُونَ فِي الْأَرْضِ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَإِن يَرَوْا كُلَّ آيَةٍ لَّا يُؤْمِنُوا بِهَا وَإِن يَرَوْا سَبِيلَ الرُّشْدِ لَا يَتَّخِذُوهُ سَبِيلًا وَإِن يَرَوْا سَبِيلَ الْغَيِّ يَتَّخِذُوهُ سَبِيلًا ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَكَانُوا عَنْهَا غَافِلِينَ  [146]

(146) እነዚያን ያለአግባብ በምድር ላይ የሚኮሩትን ከአንቀጾቼ በእርግጥ አዞራቸዋለሁ። ተዓምርንም ሁሉ ቢያዩ በርሷ አያምኑም። ቅንንም መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው አይዙትም። ግን የጥመትን መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው ይይዙታል። ይህ እነርሱ በአንቀጾቻችን ስለአስተባበሉና ከእርሷም ዘንጊዎች ስለኾኑ ነው።

(146) I will turn away from My signs those who are arrogant in the land without any right. Even if they see every sign, they will still not believe in it; if they see the way of guidance, they will not follow it, but if they see the way of misguidance, they will follow it as their way. That is because they have rejected Our signs and were heedless of them.

وَالَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَلِقَاءِ الْآخِرَةِ حَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ ۚ هَلْ يُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ  [147]

(147) እነዚያም በአንቀጾቻችንና መጨረሻይቱን ዓለም በመገናኘት ያስተባበሉት ሥራዎቻቸው ተበላሹ። ይሠሩት የነበረውን እንጂ ይመነዳሉን

(147) Those who reject Our signs and the meeting of the Hereafter, their deeds will become worthless. Will they not be recompensed except for what they used to do?

وَاتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِن بَعْدِهِ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ ۚ أَلَمْ يَرَوْا أَنَّهُ لَا يُكَلِّمُهُمْ وَلَا يَهْدِيهِمْ سَبِيلًا ۘ اتَّخَذُوهُ وَكَانُوا ظَالِمِينَ  [148]

(148) የሙሳም ሕዝቦች ከእርሱ (መኼድ) በኋላ ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለርሱ ማግሳት ያለውን (አምላክ አድርገው) ያዙ። እርሱ የማያናግራቸው መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን (አምላክ አድርገው) ያዙት። በዳዮችም ኾኑ።

(148) In his absence, the people of Moses took for worship an image of calf made from their jewelry that made a lowing sound. Did they not see that it could neither speak to them nor could it guide them to any [straight] way? Yet they took it for worship and they were wrongdoers.

وَلَمَّا سُقِطَ فِي أَيْدِيهِمْ وَرَأَوْا أَنَّهُمْ قَدْ ضَلُّوا قَالُوا لَئِن لَّمْ يَرْحَمْنَا رَبُّنَا وَيَغْفِرْ لَنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ  [149]

(149) በተጸጸቱና እነሱም በእርግጥ የተሳሳቱ መኾናቸውን ባዩ ጊዜ፡- «ጌታችን ባያዝንልንና ባይምረን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ።

(149) When they became remorseful and realized that they had gone astray, they said, “If our Lord does not have mercy upon us and forgive us, we will certainly be among the losers.”

وَلَمَّا رَجَعَ مُوسَىٰ إِلَىٰ قَوْمِهِ غَضْبَانَ أَسِفًا قَالَ بِئْسَمَا خَلَفْتُمُونِي مِن بَعْدِي ۖ أَعَجِلْتُمْ أَمْرَ رَبِّكُمْ ۖ وَأَلْقَى الْأَلْوَاحَ وَأَخَذَ بِرَأْسِ أَخِيهِ يَجُرُّهُ إِلَيْهِ ۚ قَالَ ابْنَ أُمَّ إِنَّ الْقَوْمَ اسْتَضْعَفُونِي وَكَادُوا يَقْتُلُونَنِي فَلَا تُشْمِتْ بِيَ الْأَعْدَاءَ وَلَا تَجْعَلْنِي مَعَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ  [150]

(150) ሙሳም እየተቆጣና እያዘነ ወደ ሕዝቦቹ በተመለሰ ጊዜ «ከእኔ በኋላ በእኔ ላይ የተካችሁት ነገር ከፋ! የጌታችሁን ትእዛዝ ተቻኮላችሁን» አላቸው። ሰሌዳዎቹንም ጣላቸው። የወንድሙንም ራስ (ጸጉር) ወደርሱ የሚጎትተው ሲኾን ያዘ። (ወንድሙም)፡- «የናቴ ልጅ ሆይ! ሕዝቦቹ ናቁኝ። ሊገድሉኝም ተቃራቡ። ስለዚህ በእኔ ጠላቶችን አታስደስትብኝ። ከአመጸኞች ሕዝቦችም ጋር አታድርገኝ» አለው።

(150) When Moses returned to his people, furious and grieved, he said, “What an evil thing you did in my absence! Did you seek to hasten the command of your Lord?” He threw the Tablets and grabbed his brother by the hair, dragging him towards himself. Aaron said, “O son of my mother, the people overpowered me and were about to kill me. Do not make my enemies rejoice over me, nor count me among the people of wrongdoing.”

قَالَ رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِأَخِي وَأَدْخِلْنَا فِي رَحْمَتِكَ ۖ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ  [151]

(151) (ሙሳም)፡- «ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወንድሜም ማር። በእዝነትህም ውስጥ አግባን። አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» አለ።

(151) Moses said, “My Lord, forgive me and my brother, and admit us into Your mercy, for You are the Most Merciful of those who show mercy.”

إِنَّ الَّذِينَ اتَّخَذُوا الْعِجْلَ سَيَنَالُهُمْ غَضَبٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَذِلَّةٌ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُفْتَرِينَ  [152]

(152) እነዚያ ወይፈኑን (አምላክ አድርገው) የያዙ ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ፤ በቅርቢቱም ሕይወት ውርደት በእርግጥ ያገኛቸዋል። እንዲሁም ቀጣፊዎችን እንቀጣለን።

(152) As for those who took the calf for worship, they will certainly be afflicted with wrath from their Lord and disgrace in the life of this world. This is how We recompense those who invent falsehood.

وَالَّذِينَ عَمِلُوا السَّيِّئَاتِ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِهَا وَآمَنُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ  [153]

(153) እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም ከእርሷ በኋላ የተጸጸቱ ያመኑም ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው።

(153) But those who commit evil deeds, then repent thereafter and [truly] believe, then your Lord is indeed All-Forgiving, Most Merciful.

وَلَمَّا سَكَتَ عَن مُّوسَى الْغَضَبُ أَخَذَ الْأَلْوَاحَ ۖ وَفِي نُسْخَتِهَا هُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلَّذِينَ هُمْ لِرَبِّهِمْ يَرْهَبُونَ  [154]

(154) ከሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን በግልባጫቸው ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚፈሩ ለኾኑት መምሪያና እዝነት ያለባቸው ሲኾኑ ያዘ።

(154) When Moses’ fury calmed down, he picked up the Tablets; in their inscription there was guidance and mercy for those who fear their Lord.

وَاخْتَارَ مُوسَىٰ قَوْمَهُ سَبْعِينَ رَجُلًا لِّمِيقَاتِنَا ۖ فَلَمَّا أَخَذَتْهُمُ الرَّجْفَةُ قَالَ رَبِّ لَوْ شِئْتَ أَهْلَكْتَهُم مِّن قَبْلُ وَإِيَّايَ ۖ أَتُهْلِكُنَا بِمَا فَعَلَ السُّفَهَاءُ مِنَّا ۖ إِنْ هِيَ إِلَّا فِتْنَتُكَ تُضِلُّ بِهَا مَن تَشَاءُ وَتَهْدِي مَن تَشَاءُ ۖ أَنتَ وَلِيُّنَا فَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا ۖ وَأَنتَ خَيْرُ الْغَافِرِينَ  [155]

(155) ሙሳም ከሕዝቦቹ ውስጥ ለቀጠሮዋችን ሰባን ሰዎች መረጠ። ብርቱ የምድር እንቅጥቃጤ በያዘቻቸውም ጊዜ ሙሳ አለ «ጌታዬ ሆይ! በሻህ ኖሮ ከአሁን በፊት በአጠፋሃቸው ነበር። እኔንም (ባጠፋኸኝ ነበር)። ከእኛ ቂሎቹ በሠሩት ነገር ታጠፋናለህን እርሷ (ፈተናይቱ) ያንተ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም። በእርሷ የምትሻውን ታሳስታለህ። የምትሻውንም ታቀናለህ። አንተ ረዳታችን ነህና ለእኛ ምሕረት አድርግልን። እዘንልንም። አንተም ከመሓሪዎች ሁሉ በላጭ ነህ።»

(155) Moses chose seventy men from among his people for Our appointment. When the earthquake seized them, he said, “My Lord, had it been Your will, You could have destroyed them earlier, and me too; will You destroy us for what the fools among us have done? This is not but a trial from You, by which You cause to stray whom you will and guide whom You will. You are our Guardian, so forgive us and have mercy upon us, for You are the Best of Forgivers.

وَاكْتُبْ لَنَا فِي هَٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ إِنَّا هُدْنَا إِلَيْكَ ۚ قَالَ عَذَابِي أُصِيبُ بِهِ مَنْ أَشَاءُ ۖ وَرَحْمَتِي وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ ۚ فَسَأَكْتُبُهَا لِلَّذِينَ يَتَّقُونَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَالَّذِينَ هُم بِآيَاتِنَا يُؤْمِنُونَ  [156]

(156) «ለእኛም በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም (መልካሟን) ጻፍልን። እኛ ወደ አንተ ተመለስን።» (ሲል ሙሳ ጸለየ፤ አላህም) አለ፡- «ቅጣቴ በእርሱ የምሻውን ሰው እቀጣበታለሁ። ችሮታየም ነገሩን ሁሉ ሰፋች። ለእነዚያም ለሚጠነቀቁ፣ ዘካንም ለሚሰጡ፣ ለእነዚያም እነሱ በአንቀጾቻችን ለሚያምኑ በእርግጥ» እጽፋታለሁ።

(156) Ordain for us good in this life and in the Hereafter, for We have turned to You in repentance.” Allah said, “As for my punishment, I will afflict with it whom I will, but My mercy encompasses everything; I will ordain it for those who fear Me, and give zakah, and those who believe in Our verses,

الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الرَّسُولَ النَّبِيَّ الْأُمِّيَّ الَّذِي يَجِدُونَهُ مَكْتُوبًا عِندَهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَالْإِنجِيلِ يَأْمُرُهُم بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَاهُمْ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ وَيَضَعُ عَنْهُمْ إِصْرَهُمْ وَالْأَغْلَالَ الَّتِي كَانَتْ عَلَيْهِمْ ۚ فَالَّذِينَ آمَنُوا بِهِ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَاتَّبَعُوا النُّورَ الَّذِي أُنزِلَ مَعَهُ ۙ أُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ  [157]

(157) ለእነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት (በእርግጥ እጽፍለታለሁ)። በበጎ ሥራ ያዛቸዋል። ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል። መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል። መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል። ከእነሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንዛዝላዎች (ከባድ ሕግጋቶች) ያነሳላቸዋል። እነዚያም በእርሱ ያመኑ ያከበሩትም የረዱትም ያንንም ከእርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚያድኑ ናቸው።

(157) those who follow the Messenger – the unlettered Prophet – whose description they find in their Torah and the Gospel. He enjoins them to do what is good and forbids them from what is evil; he makes lawful for them what is pure and makes unlawful for them what is impure; he relieves them of their burden and the shackles that were on them. So those who believe in him, they honor and support him, and follow the light which is sent down with him – it is they who will be successful.”

قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ جَمِيعًا الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ ۖ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ النَّبِيِّ الْأُمِّيِّ الَّذِي يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَكَلِمَاتِهِ وَاتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ  [158]

(158) (ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደናንተ ወደሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ። (እርሱም) ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ የኾነ ነው። እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም። ሕያው ያደርጋል። ይገድላልም። በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ። ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት።»

(158) Say [O Prophet], “O people, I am the Messenger of Allah to you all. To Him belongs the dominion of the heavens and earth; none has the right to be worshiped except Him; He gives life and causes death.” So believe in Allah and His Messenger, the unlettered Prophet, who believes in Allah and His words, and follow him, so that you may be guided.

وَمِن قَوْمِ مُوسَىٰ أُمَّةٌ يَهْدُونَ بِالْحَقِّ وَبِهِ يَعْدِلُونَ  [159]

(159) ከሙሳም ሕዝቦች በእውነት የሚመሩት በእርሱም (ፍርድን) የሚያስተካክሉ ጭፍሮች አሉ።

(159) Among the people of Moses there is a community which guides others with truth and establish justice therewith.

وَقَطَّعْنَاهُمُ اثْنَتَيْ عَشْرَةَ أَسْبَاطًا أُمَمًا ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ إِذِ اسْتَسْقَاهُ قَوْمُهُ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْحَجَرَ ۖ فَانبَجَسَتْ مِنْهُ اثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا ۖ قَدْ عَلِمَ كُلُّ أُنَاسٍ مَّشْرَبَهُمْ ۚ وَظَلَّلْنَا عَلَيْهِمُ الْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْهِمُ الْمَنَّ وَالسَّلْوَىٰ ۖ كُلُوا مِن طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ ۚ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَٰكِن كَانُوا أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ  [160]

(160) ዐሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው። ወደ ሙሳም ወገኖቹ መጠጣትን በፈለጉበት ጊዜ «ድንጋዩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክን። (መታውም) ከእርሱ ዐሥራ ሁለት ምንጮችም ፈለቁ። ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ ዐወቁ። በእነሱም ላይ ደመናን አጠለልን። በእነሱም ላይ መናንና ድርጭትን አወረድን። «ከሰጠናችሁም መልካም ሲሳይ ብሉ» (አልን፤ ጸጋችንን በመካዳቸው) አልበደሉንምም። ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ።

(160) We divided them into twelve tribes, each as a community, and We inspired Moses when his people asked him for water, “Strike the rock with your staff.” There gushed forth from it twelve springs; each tribe knew the place of its drinking. We shaded them with clouds and sent down to them manna and quails, “Eat of the good things We have provided for you.” They did not wrong Us, but it was themselves that they wronged.

وَإِذْ قِيلَ لَهُمُ اسْكُنُوا هَٰذِهِ الْقَرْيَةَ وَكُلُوا مِنْهَا حَيْثُ شِئْتُمْ وَقُولُوا حِطَّةٌ وَادْخُلُوا الْبَابَ سُجَّدًا نَّغْفِرْ لَكُمْ خَطِيئَاتِكُمْ ۚ سَنَزِيدُ الْمُحْسِنِينَ  [161]

(161) ለእነርሱም በተባሉ ጊዜ (አስታውስ) «በዚህች ከተማ ተቀመጡ። ከእርሷም በሻችሁት ስፍራ ብሉ። (የምንፈልገው) የኃጢኣታችንን መርገፍ ነው በሉም። የከተማይቱንም በር አጎንብሳችሁ ግቡ። ኃጢኣቶቻችሁን ለእናንተ እንምራለንና። በጎ ለሠሩት በእርግጥ እንጨምራለን።»

(161) When it was said to them, “Live in this city [of Jerusalem], and eat from wherever you please, and say, ‘Absolve us,’ and enter the gate bowing with humility; We will forgive you your sins, and increase the reward of those who do good.”

فَبَدَّلَ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْهُمْ قَوْلًا غَيْرَ الَّذِي قِيلَ لَهُمْ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ رِجْزًا مِّنَ السَّمَاءِ بِمَا كَانُوا يَظْلِمُونَ  [162]

(162) ከእነሱም ውስጥ እነዚያ (ራሳቸውን) የበደሉት ሰዎች ከዚያ ለእነርሱ ከተባለው ሌላ የኾነን ቃል ለወጡ። በእነርሱም ላይ ይበድሉ በነበሩት በደል መዐትን ከሰማይ ላክንባቸው።

(162) But the wrongdoers among them altered the words to something other than what they were told; so We sent down upon them a scourge from the heaven for their wrongdoing.

وَاسْأَلْهُمْ عَنِ الْقَرْيَةِ الَّتِي كَانَتْ حَاضِرَةَ الْبَحْرِ إِذْ يَعْدُونَ فِي السَّبْتِ إِذْ تَأْتِيهِمْ حِيتَانُهُمْ يَوْمَ سَبْتِهِمْ شُرَّعًا وَيَوْمَ لَا يَسْبِتُونَ ۙ لَا تَأْتِيهِمْ ۚ كَذَٰلِكَ نَبْلُوهُم بِمَا كَانُوا يَفْسُقُونَ  [163]

(163) ከዚያችም በባህሩ ዳርቻ ከነበረችው ከተማ በቅዳሜ (ቀን) ወሰን ባለፉ ጊዜ በሰንበታቸው ቀን ዐሳዎቻቸው የተከማቹ ኾነው በሚመጡላቸው ጊዜ (የኾነውን) ጠይቃቸው። ሰንበትንም በማያከብሩበት (በሌላው) ቀን አይመጡላቸውም። እንደዚሁ ያምጹበት በነበሩት ምክንያት እንሞክራቸዋለን።

(163) Ask them [O Prophet] about the town which was by the sea and how they broke the Sabbath. The fish would come to them appearing on the surface of the water on Sabbath days, but when it was not Sabbath, they would not come. This is how We tested them for their rebelliousness.

وَإِذْ قَالَتْ أُمَّةٌ مِّنْهُمْ لِمَ تَعِظُونَ قَوْمًا ۙ اللَّهُ مُهْلِكُهُمْ أَوْ مُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا ۖ قَالُوا مَعْذِرَةً إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ  [164]

(164) ከእነሱም (ከፊሎቹ) ሕዝቦች «አላህ አጥፊያቸው ወይም በብርቱ ቅጣት ቀጪአቸው የኾኑትን ሕዝቦች ለምን ትገስፃጻላችሁ» ባሉ ጊዜ (ገሳጮቹ) «ወደ ጌታችሁ በቂ ምክንያት እንዲኾንና እነርሱም ቢከለከሉ ብለን ነው» አሉ።

(164) When a group of them said, “Why are you admonishing a people whom Allah will destroy or punish severely?” They said, “To excuse ourselves before your Lord, and perhaps they may fear Allah.”

فَلَمَّا نَسُوا مَا ذُكِّرُوا بِهِ أَنجَيْنَا الَّذِينَ يَنْهَوْنَ عَنِ السُّوءِ وَأَخَذْنَا الَّذِينَ ظَلَمُوا بِعَذَابٍ بَئِيسٍ بِمَا كَانُوا يَفْسُقُونَ  [165]

(165) በእርሱም የተገሰጹበትን ነገር በተዉ ጊዜ እነዚያን ከክፉ የሚከለከሉትን አዳንን፤ እነዚያንም የበደሉትን ያምጹ በነበሩት ምክንያት በብርቱ ቅጣት ያዝናቸው።

(165) When they ignored the admonition they were given, We saved those who forbade evil and seized the wrongdoers with a grievous punishment for their defiant disobedience.

فَلَمَّا عَتَوْا عَن مَّا نُهُوا عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ  [166]

(166) ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነሱ «ወረዶች ዝንጀሮች ኹኑ አልን፤» (ኾኑም)።

(166) When they persistently violated what they were forbidden to do, We said to them, “Be despised apes.”

وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكَ لَيَبْعَثَنَّ عَلَيْهِمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ مَن يَسُومُهُمْ سُوءَ الْعَذَابِ ۗ إِنَّ رَبَّكَ لَسَرِيعُ الْعِقَابِ ۖ وَإِنَّهُ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ  [167]

(167) ጌታህም እስከ ትንሣኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን ሰው በነሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መኾኑን ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሳቸው)። ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው። እርሱም በእርግጥ እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው።

(167) And [remember] when your Lord declared that He would send against them those who would afflict them with a terrible punishment until the Day of Resurrection. Your Lord is Swift in Punishment, but He also is All-Forgiving, Most Merciful.

وَقَطَّعْنَاهُمْ فِي الْأَرْضِ أُمَمًا ۖ مِّنْهُمُ الصَّالِحُونَ وَمِنْهُمْ دُونَ ذَٰلِكَ ۖ وَبَلَوْنَاهُم بِالْحَسَنَاتِ وَالسَّيِّئَاتِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ  [168]

(168) (የእስራኤልን ልጆች) በምድር ላይ የተለያዩ ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው። ከእነሱ መልካሞች አሉ። ከእነሱም ከዚያ ሌላ አልሉ። ይመለሱ ዘንድም በተድላዎችም በመከራዎችም ሞከርናቸው።

(168) We scattered them through the land in communities – some of them were righteous and others were less so. We tested them with both prosperity and adversity, so that they would return [to Allah’s Obedience].

فَخَلَفَ مِن بَعْدِهِمْ خَلْفٌ وَرِثُوا الْكِتَابَ يَأْخُذُونَ عَرَضَ هَٰذَا الْأَدْنَىٰ وَيَقُولُونَ سَيُغْفَرُ لَنَا وَإِن يَأْتِهِمْ عَرَضٌ مِّثْلُهُ يَأْخُذُوهُ ۚ أَلَمْ يُؤْخَذْ عَلَيْهِم مِّيثَاقُ الْكِتَابِ أَن لَّا يَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ وَدَرَسُوا مَا فِيهِ ۗ وَالدَّارُ الْآخِرَةُ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ يَتَّقُونَ ۗ أَفَلَا تَعْقِلُونَ  [169]

(169) ከኋላቸውም፡- መጽሐፉን የወረሱ መጥፎ ምትኮች ተተኩ። የዚህን የቅርቡን ጠፊ ጥቅም ይይዛሉ። ብጤውም ጥቅም ቢመጣላቸው የሚይዙት ሲኾኑ « (በሠራነው)፡- ለኛ ምሕረት ይደረግልናል» ይላሉ። በአላህ ላይ ከእውነት በቀር እንዳይናገሩ በእነርሱ ላይ የመጽሐፉ ቃል ኪዳን አልተያዘባቸውምን በእርሱ ውስጥ ያለውንም አላነበቡምን የመጨረሻይቱም አገር ለእነዚያ ጌታቸውን ለሚፈሩት በላጭ ናት። አታውቁምን

(169) They were then succeeded by other generations who inherited the Scripture, opting for the lowly gains, and saying, “We will be forgiven.” Yet if a similar gain comes their way, they will seize it. Was not a covenant of the Scripture taken from them that they should not say about Allah except the truth, and they had studied its teachings? But the Home of the Hereafter is better for those who fear Allah. Do you not understand?

وَالَّذِينَ يُمَسِّكُونَ بِالْكِتَابِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجْرَ الْمُصْلِحِينَ  [170]

(170) እነዚያም መጽሐፉን ጠብቀው የሚይዙ ሶላትንም በደንቡ የሰገዱ እኛ የመልካም ሠሪዎችን ዋጋ አናጠፋም።

(170) As for those who hold fast to the Scripture and establish prayer, We will not let the reward of those who seek righteousness to be lost.

وَإِذْ نَتَقْنَا الْجَبَلَ فَوْقَهُمْ كَأَنَّهُ ظُلَّةٌ وَظَنُّوا أَنَّهُ وَاقِعٌ بِهِمْ خُذُوا مَا آتَيْنَاكُم بِقُوَّةٍ وَاذْكُرُوا مَا فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ  [171]

(171) የጡርን ተራራ ነቅለን ከበላያቸው እንደ ጥላ ኾኖ በአነሳነውና እርሱም በነሱ ላይ ወዳቂ መኾኑን ባረጋገጡ ጊዜ (አስታውስ)። «የሰጠናችሁን በብርታት ያዙ። ትጠነቀቁም ዘንድ በውስጡ ያለውን ተገንዘቡ» (አልን)።

(171) And [remember] when We raised the mountain over them as if it were a dark cloud, and they thought that it would fall upon them, “Hold fast to what We have given you and observe its teachings, so that you may fear Allah.”

وَإِذْ أَخَذَ رَبُّكَ مِن بَنِي آدَمَ مِن ظُهُورِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَأَشْهَدَهُمْ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَلَسْتُ بِرَبِّكُمْ ۖ قَالُوا بَلَىٰ ۛ شَهِدْنَا ۛ أَن تَقُولُوا يَوْمَ الْقِيَامَةِ إِنَّا كُنَّا عَنْ هَٰذَا غَافِلِينَ  [172]

(172) ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና «ጌታችሁ አይደለሁምን» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)። «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ። «በትንሣኤ ቀን ከዚህ (ኪዳን) ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ።»

(172) And [remember] when your Lord brought forth from the loins of the children of Adam their offspring and made them testify about themselves [asking], “Am I not your Lord?” They said, “Yes indeed; We testify.” [We did so] lest you should say on the Day of Resurrection, “We were unaware of this,”

أَوْ تَقُولُوا إِنَّمَا أَشْرَكَ آبَاؤُنَا مِن قَبْلُ وَكُنَّا ذُرِّيَّةً مِّن بَعْدِهِمْ ۖ أَفَتُهْلِكُنَا بِمَا فَعَلَ الْمُبْطِلُونَ  [173]

(173) ወይም «(ጣዖታትን) ያጋሩት ከእኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን ብቻ ናቸው። እኛም ከእነሱ በኋላ የኾን ዘሮች ነበርን። አጥፊዎቹ በሠሩት ታጠፋናለህን» እንዳትሉ (አስመሰከርናችሁ)።

(173) Or that you say, “It was our forefathers before us who associated partners with Allah, and we are their offspring who came after them. Will you then destroy us for the falsehood that they invented?”

وَكَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ وَلَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ  [174]

(174) እንደዚሁም (እንዲያስቡ) እንዲመለሱም አንቀጾችን እናብራራለን።

(174) This is how We make the verses clear, so that they may return.

وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ الَّذِي آتَيْنَاهُ آيَاتِنَا فَانسَلَخَ مِنْهَا فَأَتْبَعَهُ الشَّيْطَانُ فَكَانَ مِنَ الْغَاوِينَ  [175]

(175) የዚያንም ተዓምራታችንን የሰጠነውንና ከእርሷ የወጣውን ሰይጣንም ያስከተለውን ከጠማሞቹም የኾነውን ሰው ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው።

(175) And relate to them [O Prophet] the story of the one whom We gave knowledge of Our revelations, but he abandoned it, so Satan took hold of him and he became one of the deviants.

وَلَوْ شِئْنَا لَرَفَعْنَاهُ بِهَا وَلَٰكِنَّهُ أَخْلَدَ إِلَى الْأَرْضِ وَاتَّبَعَ هَوَاهُ ۚ فَمَثَلُهُ كَمَثَلِ الْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ۚ ذَّٰلِكَ مَثَلُ الْقَوْمِ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۚ فَاقْصُصِ الْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ  [176]

(176) በሻንም ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር። እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ። ፍላጎቱንም ተከተለ። ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ ውሻ ነው። ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው። ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው።

(176) If We had willed, We could have elevated him thereby, but he clung to the [life of the] earth and followed his desires. His likeness is that of a dog: if you attack it, it pants with its tongue lolling, and if you leave it, it still pants. Such is the example of the people who reject Our revelations. Therefore, relate the stories, so that they may reflect.

سَاءَ مَثَلًا الْقَوْمُ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَأَنفُسَهُمْ كَانُوا يَظْلِمُونَ  [177]

(177) የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትና ነፍሶቻቸውን ይበድሉ የነበሩት ሰዎች ምሳሌ ከፋ!

(177) How evil is the likeness of people who rejected Our verses, and it is themselves that they have wronged.

مَن يَهْدِ اللَّهُ فَهُوَ الْمُهْتَدِي ۖ وَمَن يُضْلِلْ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ  [178]

(178) አላህ የሚያቀናው ሰው ቅን እርሱ ነው። የሚያጠመውም ሰው እነዚያ ከሳሪዎቹ እነሱ ናቸው።

(178) Whoever Allah guides is rightly guided; and whoever He causes to stray, it is they who are the losers.

وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ ۖ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُونَ  [179]

(179) ከጋኔንም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን። ለእነርሱ በርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው። ለእነሱም በሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው። ለእነሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው። እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው። ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው። እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው፤

(179) We have surely created for Hell many jinn and humans. They have hearts with which they do not understand, eyes with which they do not see, and ears with which they do not hear. They are like cattle, rather, they are more astray. It is they who are the heedless.

وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَا ۖ وَذَرُوا الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي أَسْمَائِهِ ۚ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ  [180]

(180) ለአላህም መልካም ስሞች አሉት። (ስትጸልዩ) በእርሷም ጥሩት። እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው። ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይምመነዳሉ።

(180) Allah has the Most Beautiful Names, so call upon Him by them, and leave those who deviate concerning His Names. They will be recompensed for what they used to do.

وَمِمَّنْ خَلَقْنَا أُمَّةٌ يَهْدُونَ بِالْحَقِّ وَبِهِ يَعْدِلُونَ  [181]

(181) ከፈጠርናቸውም ሰዎች በእውነት የሚመሩ በእርሱም (ፍርድን) የሚያስተካክሉ ሕዝቦች አልሉ።

(181) And among those whom We created is a group that guides others with the truth and establishes justice therewith.

وَالَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا سَنَسْتَدْرِجُهُم مِّنْ حَيْثُ لَا يَعْلَمُونَ  [182]

(182) እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን ከማያውቁት ስፍራ ቀስ በቀስ (ምቾትን በመጨመር) እናዘነጋቸዋለን።

(182) As for those who reject Our signs, We will gradually lead them to destruction without them realizing it.

وَأُمْلِي لَهُمْ ۚ إِنَّ كَيْدِي مَتِينٌ  [183]

(183) ለእነርሱም ጊዜ እሰጣቸዋለሁ ጥበቤ ብርቱ ነውና።

(183) I will give them respite, but My plan is firm.

أَوَلَمْ يَتَفَكَّرُوا ۗ مَا بِصَاحِبِهِم مِّن جِنَّةٍ ۚ إِنْ هُوَ إِلَّا نَذِيرٌ مُّبِينٌ  [184]

(184) በነቢያቸው (በሙሐመድ) ምንም ዕብደት የሌለበት መኾኑን አያስተውሉምን እርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ እንጅ ሌላ አይደለም።

(184) Have they not reflected that their fellow [Prophet] is not insane? He is none but a clear warner.

أَوَلَمْ يَنظُرُوا فِي مَلَكُوتِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا خَلَقَ اللَّهُ مِن شَيْءٍ وَأَنْ عَسَىٰ أَن يَكُونَ قَدِ اقْتَرَبَ أَجَلُهُمْ ۖ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَهُ يُؤْمِنُونَ  [185]

(185) በሰማያትና በምድር ግዛት ውስጥ ከማንኛው ነገር አላህ በፈጠረውም ሁሉ የሞት ጊዜያቸውም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መኾኑን አያስተውሉምን ከእርሱም (ከቁርኣን) ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ።

(185) Have they not observed the dominions of the heavens and earth and all that Allah has created, and that the end of their term might be near? In what message after this [Qur’an] will they then believe?

مَن يُضْلِلِ اللَّهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ ۚ وَيَذَرُهُمْ فِي طُغْيَانِهِمْ يَعْمَهُونَ  [186]

(186) አላህ የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኝ የለውም። በጥምመታቸውም ውስጥ እየዋለሉ ይተዋቸዋል።

(186) Whoever Allah causes to stray, there is none to guide him; He will leave them to wander blindly in their transgression.

يَسْأَلُونَكَ عَنِ السَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَاهَا ۖ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ رَبِّي ۖ لَا يُجَلِّيهَا لِوَقْتِهَا إِلَّا هُوَ ۚ ثَقُلَتْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ لَا تَأْتِيكُمْ إِلَّا بَغْتَةً ۗ يَسْأَلُونَكَ كَأَنَّكَ حَفِيٌّ عَنْهَا ۖ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ اللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ  [187]

(187) ከሰዓቲቱ መቼ እንደምትረጋ (እንደምትመጣ) ይጠይቁሃል። «ዕውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ነው። በጊዜዋ እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጣትም። በሰማያትና በምድርም ከበደች። በድንገት ቢኾን እንጂ አትመጣችሁም» በላቸው። ከእርሷ አጥብቀህ እንደ ተረዳህ አድርገው ይጠይቁሃል። «ዕውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው። ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው።

(187) They ask you [O Prophet] about the Hour, “When will it come to pass?” Say, “Its knowledge is only with my Lord. None can reveal its due time except Him. It will be heavy on the heavens and earth; it will only come to you by surprise.” They ask you as if you are well-aware of it. Say, “Its knowledge is only with Allah, but most people do not know.”

قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ الْغَيْبَ لَاسْتَكْثَرْتُ مِنَ الْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِيَ السُّوءُ ۚ إِنْ أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ  [188]

(188) «አላህ የሻውን በስተቀር ለእራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም። ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር። እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው።

(188) Say, “I have no power to benefit or harm myself, except what Allah wills. If I had knowledge of the unseen, I would have acquired much good, and no evil would have touched me. I am only a warner and bearer of glad tidings for people who believe.”

هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَجَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا لِيَسْكُنَ إِلَيْهَا ۖ فَلَمَّا تَغَشَّاهَا حَمَلَتْ حَمْلًا خَفِيفًا فَمَرَّتْ بِهِ ۖ فَلَمَّا أَثْقَلَت دَّعَوَا اللَّهَ رَبَّهُمَا لَئِنْ آتَيْتَنَا صَالِحًا لَّنَكُونَنَّ مِنَ الشَّاكِرِينَ  [189]

(189) እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁ ከእርሷም መቀናጆዋን ወደርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው። በተገናኛትም ጊዜ ቀላልን እርግዝና አረገዘች። እርሱንም (ፅንሱን) ይዛው ኼደች። በከበደችም ጊዜ «ደግን ልጅ ብትሰጠን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንኾናለን፤» ሲሉ ጌታቸውን አላህን ለመኑ።

(189) It is He Who created you from a single soul, and from it He made its spouse, so that he may find comfort in her. When he covered her, she conceived a light burden carrying it with ease. Then when she grew heavy, they called upon Allah, their Lord, “If you give us a healthy child, we will certainly be grateful.”

فَلَمَّا آتَاهُمَا صَالِحًا جَعَلَا لَهُ شُرَكَاءَ فِيمَا آتَاهُمَا ۚ فَتَعَالَى اللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ  [190]

(190) መልካም ልጅ በሰጣቸውም ጊዜ በሰጣቸው ልጅ (ስም) ለእርሱ ተጋሪዎችን አደረጉለት። አላህም ከሚያጋሩት ሁሉ ላቀ።

(190) But when He gave them a healthy child, they ascribed partners to Him in that which He had given them. Exalted is Allah far above what they ascribe to Him.

أَيُشْرِكُونَ مَا لَا يَخْلُقُ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ  [191]

(191) ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ) ያጋራሉን

(191) Do they ascribe to Him partners who cannot create anything, but are themselves created?

وَلَا يَسْتَطِيعُونَ لَهُمْ نَصْرًا وَلَا أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ  [192]

(192) ለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን)

(192) They cannot help them, nor can they help themselves.

وَإِن تَدْعُوهُمْ إِلَى الْهُدَىٰ لَا يَتَّبِعُوكُمْ ۚ سَوَاءٌ عَلَيْكُمْ أَدَعَوْتُمُوهُمْ أَمْ أَنتُمْ صَامِتُونَ  [193]

(193) (ጣዖቶቹን) ወደ ቅን መንገድ ብትጠሩዋቸውም አይከተሉዋችሁም። ብትጠሩዋቸው ወይም እናንተ ዝምተኞችም ብትኾኑ በእናንተ ላይ እኩል ነው።

(193) If you call them to guidance, they will not follow you; it is the same whether you call them or remain silent.

إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ  [194]

(194) እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገ³ቸው ብጤዎቻችሁ ተገዢዎች ናቸው። እውነተኞችም እንደኾናችሁ ጥሩዋቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ፤ (መመለስ ግን አይችሉም)።

(194) Those whom you supplicate besides Allah are slaves like you; supplicate them and let them respond to you if you are truthful.

أَلَهُمْ أَرْجُلٌ يَمْشُونَ بِهَا ۖ أَمْ لَهُمْ أَيْدٍ يَبْطِشُونَ بِهَا ۖ أَمْ لَهُمْ أَعْيُنٌ يُبْصِرُونَ بِهَا ۖ أَمْ لَهُمْ آذَانٌ يَسْمَعُونَ بِهَا ۗ قُلِ ادْعُوا شُرَكَاءَكُمْ ثُمَّ كِيدُونِ فَلَا تُنظِرُونِ  [195]

(195) ለእነርሱ በእርሳቸው የሚኼዱባቸው እግሮች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በርሳቸው የሚጨብጡባቸው እጆች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በእርሳቸው የሚያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በእርሳቸው የሚሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸውን «ያጋራችኋቸውን ጥሩ ከዚያም ተተናኮሉኝ። ጊዜም አትስጡኝ፤ (አልፈራችሁም)» በላቸው።

(195) Do they have feet to walk with? Or hands to grasp with? Or eyes to see with? Or ears to hear with? Say [O Prophet], “Call your idols then conspire against me and give me no respite!

إِنَّ وَلِيِّيَ اللَّهُ الَّذِي نَزَّلَ الْكِتَابَ ۖ وَهُوَ يَتَوَلَّى الصَّالِحِينَ  [196]

(196) «የእኔ ረዳቴ ያ መጽሐፉን (ቁርኣንን) ያወረደልኝ አላህ ነውና፤ እርሱም መልካም ሠሪዎችን ይረዳል» (በላቸው)።

(196) My Protector is Allah Who has sent down the Book, for it is He Who protects the righteous.

وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَا أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ  [197]

(197) እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትገ³ቸው ሊረÇችሁ አይችሉም። ነፍሶቻቸውንም አይረዱም።

(197) But those whom you supplicate besides Him cannot help you, nor can they help themselves.”

وَإِن تَدْعُوهُمْ إِلَى الْهُدَىٰ لَا يَسْمَعُوا ۖ وَتَرَاهُمْ يَنظُرُونَ إِلَيْكَ وَهُمْ لَا يُبْصِرُونَ  [198]

(198) «ወደ ቅንም መንገድ (እንዲመሩዋችሁ) ብትጠሩዋቸው አይሰሙም፤» (በላቸው)። እነርሱንም የማያዩ ሲኾኑ ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ።

(198) If you call them to guidance, they do not hear, and you see them looking at you, but they do not see.

خُذِ الْعَفْوَ وَأْمُرْ بِالْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ الْجَاهِلِينَ  [199]

(199) ገርን ጠባይ ያዝ። በመልካምም እዘዝ። ባለጌዎቹንም ተዋቸው።

(199) Be gracious, enjoin what is right and turn away from those who are ignorant.

وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ  [200]

(200) ከሰይጣንም (በኩል) ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ። እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና።

(200) If you are tempted by Satan, seek refuge with Allah, for He is All-Hearing, All-Knowing.

إِنَّ الَّذِينَ اتَّقَوْا إِذَا مَسَّهُمْ طَائِفٌ مِّنَ الشَّيْطَانِ تَذَكَّرُوا فَإِذَا هُم مُّبْصِرُونَ  [201]

(201) እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ። ወዲያውም እነሱ ተመልካቾች ይኾናሉ።

(201) Those who fear Allah, when an evil whisper comes to them from Satan, they remember Him and immediately come back to their senses.

وَإِخْوَانُهُمْ يَمُدُّونَهُمْ فِي الْغَيِّ ثُمَّ لَا يُقْصِرُونَ  [202]

(202) ወንድሞቻቸውም ጥመትን ይጨምሩላቸዋል፤ ከዚያም (እነርሱ) አይገቱም።

(202) But the devils plunge their [human] brothers deeper into sin, sparing no effort.

وَإِذَا لَمْ تَأْتِهِم بِآيَةٍ قَالُوا لَوْلَا اجْتَبَيْتَهَا ۚ قُلْ إِنَّمَا أَتَّبِعُ مَا يُوحَىٰ إِلَيَّ مِن رَّبِّي ۚ هَٰذَا بَصَائِرُ مِن رَّبِّكُمْ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ  [203]

(203) በተዓምርም ባልመጣሃቸው ጊዜ (በራስህ) «ለምን አትፈጥራትም» ይላሉ። ከጌታዬ ወደኔ የተወረደውን ብቻ እከተላለሁ። ይህ (ቁርኣን) ከጌታችሁ ሲኾን ለሚያምኑ ሕዝቦች መረጃዎችና መምሪያ እዝነትም ነው በላቸው።

(203) When you do not bring them a sign, they say, “Why do you not improvise one?” Say, “I only follow what is revealed to me from my Lord. This [Qur’an] is an insight from your Lord, and a guidance and mercy for people who believe.”

وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ  [204]

(204) ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ። ጸጥም በሉ። ይታዘንላችኋልና።

(204) When the Qur’an is recited, listen to it attentively and maintain silence, so that you may receive mercy.

وَاذْكُر رَّبَّكَ فِي نَفْسِكَ تَضَرُّعًا وَخِيفَةً وَدُونَ الْجَهْرِ مِنَ الْقَوْلِ بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ الْغَافِلِينَ  [205]

(205) ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው። ከዘንጊዎቹም አትኹን።

(205) And remember your Lord within yourself with humility and fear, without raising your voice, in the morning and evening, and do not be of those who are heedless.

إِنَّ الَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيُسَبِّحُونَهُ وَلَهُ يَسْجُدُونَ ۩  [206]

(206) እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም። ያወድሱታልም። ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ።

(206) Indeed, those [angels] who are near to your Lord do not disdain to worship Him; they glorify Him, and to Him they prostrate.

   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   
   

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

ሱረቱል አል ማዒዳህ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran 

ሱረቱል አል ማዒዳህ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا…

ሱረቱል አንዓም አማርኛ ቁርአን 6 Al anam Amharic Quran

ሱረቱል አንዓም አማርኛ ቁርአን 6 Al anam Amharic Quran الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَجَعَلَ الظُّلُمَاتِ وَالنُّورَ ۖ ثُمَّ الَّذِينَ…