102 – At-Takaathur
102 – At-Takaathur
| (1) በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡ | (1) Competition for worldly gains distracts you [from Allah], |
| (2) መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡ | (2) until you come to your graves. |
| (3) ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፡፡ | (3) No indeed! You will come to know. |
| (4) ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡ | (4) Again no! You will come to know. |
| (5) በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)፡፡ | (5) No indeed! If only you knew for certain. |
| (6) ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ፡፡ | (6) You will surely see the Blazing Fire, |
| (7) ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፡፡ | (7) Again, you will see it with absolute certainty. |
| (8) ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ፡፡ | (8) Then on that Day you will surely be asked about your worldly pleasures. |
