13 – Ar-Ra’d
13 – Ar-Ra’d
| (1) አ.ለ.መ.ረ (አሊፍ ላም ሚም ራ) ይህች (አናቅጽ) ከመጽሐፉ አንቀጾች ናት፡፡ ያም ከጌታህ ወዳንተ የተወረደው እውነት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም፡፡ | (1) Alif Lām Mīm Ra. These are the verses of the Book. That which has been sent down to you [O Prophet] from your Lord is the truth, but most people do not believe. |
| (2) አላህ ያ ሰማያትን የምታዩዋት አዕማድ ሳትኖር ያነሳት ከዚያም በዐርሹ (ዙፋኑ) ላይ (ለሱ ክብር በሚስማማ መልኩ) የተደላደለ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ነው፡፡ ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ፡፡ ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል፡፡ በጌታችሁ መገናኘት ታረጋግጡ ዘንድ ተዓምራቶችን ይዘረዝራል፡፡ | (2) It is Allah Who raised the heavens without any pillars that you can see, then He rose over the Throne. He subjected the sun and the moon, each running its course for an appointed term. He governs all affairs, and explains the signs in detail, so that you may be certain of the meeting with your Lord. |
| (3) እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በሷም ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ምልክቶች አሉ፡፡ | (3) It is He Who spread out the earth and placed therein firm mountains and rivers, and created therein fruits of every kind in pairs. He causes the night to cover the day. Indeed, there are signs in this for people who reflect. |
| (4) በምድርም የተጎራበቱ ቁርጥራጮች አልሉ፡፡ ከወይኖችም አትክልቶች አዝርዕቶችም መንታዎችና መንታዎች ያልኾኑ ዘንባባዎችም አልሉ፡፡ በአንድ ውሃ ይጠጣሉ፤ (በጣዕምም ይለያያሉ)፡፡ ከፊሉዋንም በከፊሉ ላይ በሚበላው ሰብል እናበልጣለን፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ተዓምራት አለበት፡፡ | (4) And on the earth there are neighboring [yet different] tracts of land, and gardens of grapevines, grains and palm trees – some growing in clusters from one root or standing alone. They are all irrigated with the same water, yet We cause some of them excel others in taste. Indeed, there are signs in this for people of understanding. |
| (5) ብትደነቅም ዐፈር በኾንን ጊዜ እና አዲስ ፍጥረት እንኾናለን ማለታቸው (ታላቅ) ድንቅ ነው፡፡ እነዚህ እነዚያ በጌታቸው የካዱት ናቸው፡፡ እነዚህም እንዛዝላዎች በአንገቶቻቸው ላይ ያሉባቸው ናቸው፡፡ እነዚሀም የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ | (5) If you wonder, then wondrous is their saying, “what! When we become dust, will we be created anew?” They are the ones who disbelieve in their Lord, and they are the ones who will have shackles around their necks. Such are the people of the Fire; they will abide therein forever. |
| (6) ከእነሱ በፊት የመሰሎቻቸው ቅጣቶች በእርግጥ ያለፉ ሲኾኑ ከመልካሙ በፊት በመጥፎው ያስቸኩሉሃል፡፡ ጌታህም ለሰዎች ከመበደላቸው ጋር በእርግጥ የምህረት ባለቤት ነው፡፡ ጌታህም በእርግጥ ቅጣተ ብርቱ ነው፡፡ | (6) They ask you [O Prophet] to hasten the punishment before the good, even though there have already been similar punishments before them. But your Lord is indeed forgiving to people despite their wrongdoing, and your Lord is indeed severe in punishment. |
| (7) እነዚያም የካዱት በእርሱ ላይ ከጌታው ተዓምር ለምን አልተወረደለትም ይላሉ፡፡ አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው፡፡ | (7) The disbelievers say, “Why has no sign been sent down to him from his Lord?” You are only a warner, and for every people there is a guide. |
| (8) አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ያውቃል፡፡ ማሕጸኖችም የሚያጎድሉትን የሚጨምሩትንም (ያውቃል)፡፡ ነገሩም ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነው፡፤ | (8) Allah knows what every female bears, and what the wombs may fall short or increase. With Him everything is precisely measured. |
| (9) ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ታላቅ የላቀ ነው፡፡ | (9) He is the Knower of the unseen and the seen, the All-Great, the Most Exalted. |
| (10) ከእናንተ ውስጥ ቃሉን ዝቅ ያደረገ ሰው በእርሱ የጮኸም ሰው እርሱ በሌሊት ተደባቂም በቀን (ተገልጾ) ኺያጅም የኾነ ሰው (እርሱ ዘንድ) እኩል ነው፡፡ | (10) It is the same [to Him] whether one of you speaks secretly or in public, and whether one is hidden in the darkness of the night or walks about openly in the daylight. |
| (11) ለእርሱ (ለሰው) ከስተፊቱም ከኋላውም በአላህ ትዕዛዝ (ከክፉ) የሚጠብቁት ተተካኪዎች (መላእክት) አሉት፡፡ አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን (ኹኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡ አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለውም፡፡ ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸውም፡፡ | (11) For each person there are successive angels in front of him and behind him, guarding him by the command of Allah. Allah does not change the condition of a people until they change their own attitude and conduct. But if Allah intends punishment for a people, then it cannot be averted, nor will there be any protector for them besides Him. |
| (12) እርሱ ያ የምትፈሩና የምትከጅሉም ስትሆኑ ብልጭታን የሚያሳያችሁ ከባዶች ደመናዎችንም የሚያስገኝ ነው፡፡ | (12) It is He Who shows you lightening [causing] fear and hope, and forms heavy clouds. |
| (13) ነጎድጓድም አላህን በማመስገን ያጠራል፡፡ መላእክትም እርሱን ለመፍራት (ያጠሩታል)፡፡ መብረቆችንም ይልካል፡፡ እነርሱም (ከሓዲዎች) በአላህ የሚከራከሩ ሲሆኑ በእርሷ የሚሻውን ሰው ይመታል፡፡ እርሱም ኀይለ ብርቱ ነው፡፡ | (13) The thunder glorifies His praise, and so do the angels in awe of Him. He sends thunderbolts, striking therewith whom He wills, yet they dispute about Allah, Who is severe in might. |
| (14) ለእርሱ (ለአላህ) የእውነት መጥሪያ አለው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚገዙዋቸው (ጣዖታት) ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ ወደ ውሃ መዳፎቹን (በሩቅ ሆኖ) እንደሚዘረጋ (ሰው መልስ) እንጂ ለነርሱ በምንም አይመልሱላቸውም፡፡ እርሱም ወደ አፉ ደራሽ አይደለም፡፡ የከሓዲዎችም ጥሪ በከንቱ እንጂ አይደለም፡፡ | (14) To Him alone should all supplication be addressed. But those whom they supplicate besides Him do not respond to them in any way, except like one who stretches out his hands for water to reach his mouth, but it will never reach it. The supplication of the disbelievers is all in vain. |
| (15) በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ፡ ጥላዎቻቸውም በጧቶችና በሠርኮች ይሰግዳሉ፡፡ | (15) To Allah prostrates whoever is in the heavens and on earth, willingly or unwillingly, and so do their shadows in the morning and evening. |
| (16) «የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡ «አላህ ነው» በል፡፡ «ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትንም የማይችሉን ረዳቶች ከርሱ ሌላ ያዛችሁን» በላቸው፡፡ «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይስተካከላሉን ወይስ ለአላህ እንደርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አደረጉለትና ፍጥረቱ በእነሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን» በል፤ «አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው» በል፡፡ | (16) Say, “Who is the Lord of the heavens and earth?” Say, “Allah.” Say, “Have you taken besides Him protectors, those who have no power to benefit or harm themselves?” Say, “Can the blind person be equal to the seeing, or can the darkness be equal to the light?” Or do they ascribe to Allah partners who created the like of His creation, so they are confused between two creations? Say, “Allah is the Creator of all things, and He is the One, the Subjugator.” |
| (17) ከሰማይ ውሃን አወረደ፡፡ ሸለቆዎቹም በመጠናቸው ፈሰሱ፡፡ ጎርፉም አሰፋፊውን ኮረፋት ተሸከመ፡፡ ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጎት በእርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም (ማዕድን) ብጤው የኾነ ኮረፋት አልለው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለእውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል፡፡ ኮረፋቱማ ግብስብስ ኾኖ ይጠፋል፡፡ ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል፡፡ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልፃል፡፡ | (17) He sends down rain from the sky, causing the valleys to flow, each according to its capacity, and the torrent carries along rising foam, similar to the slag produced from metal that people melt in the fire to make ornaments or tools. This is how Allah compares truth to falsehood: as for the residue, it is then cast away, but that which benefits people remains on the earth. This is how Allah sets forth comparisons. |
| (18) ለእነዚያ ለጌታቸው ለታዘዙት መልካም ነገር (ገነት) አልላቸው፡፡ እነዚያም ለእርሱ ያልታዘዙት ለእነሱ በምድር ያለው ሁሉ ከእርሱም ጋር ብጤው ቢኖራቸው ኖሮ በእርሱ በተበዡበት ነበር፡፡ እነዚያ ለእነሱ ክፉ ምርመራ አለባቸው፡፡ መኖሪያቸውም ገሀነም ናት፡፡ ፍራሻቸውም ከፋች! | (18) Those who respond to their Lord will have the best reward. As for those who do not respond to Him, even if they were to possess all that is on earth and the likes thereof, they would surely offer it to ransom themselves; they will have the worst reckoning, and their abode will be Hell. What a terrible resting place! |
| (19) ከጌታህ ወዳንተ የተወረደው እውነት መኾኑን የሚያውቅ ሰው እንደዚያ እርሱ ዕውር እንደኾነው ሰው ነውን የሚገሠጹት የአእምሮ ባለቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ | (19) Is the one who knows that what has been sent down from your Lord is the truth like the one who is blind? None will take heed except the people of understanding, |
| (20) እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳን የሚሞሉ የጠበቀውንም ኪዳን የማያፈርሱ ናቸው፡፡ | (20) those who fulfill the covenant of Allah and do not break the pledge, |
| (21) እነዚያም አላህ እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቀጥሉ ጌታቸውንም የሚያከብሩ መጥፎንም ቁጥጥር የሚፈሩ ናቸው፡፡ | (21) and those who maintain [the ties] which Allah has ordered to be maintained, and fear their Lord, and are afraid of a terrible reckoning, |
| (22) እነዚያም የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሱ፣ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ፣ እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ኾነ በግልጽ የመጸወቱ፣ ክፉውንም ነገር በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው፡፡ እነዚያ ለእነሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው፡፡ | (22) and those who observe patience, seeking the pleasure of their Lord, and establish prayer, and spend from what We have provided for them, secretly and in public, and repel evil with good – it is they who will have the final abode, |
| (23) (እርሷም) የመኖሪያ ገነቶች ናት፡፡ ይገቡባታል፡፡ ከአባቶቻቸውም፣ ከሚስቶቻቸውም፣ ከዝርያቸውም መልካም የሠራ ሰው (ይገባታል)፡፡ መላእክትም በእነርሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ፡፡ | (23) Gardens of Eternity, which they will enter together with their righteous parents, their spouses and their offspring. Angels will enter upon them from every gate, |
| (24) «ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)፡፡ | (24) “Peace be on you, for what you have patiently endured. How excellent is the final abode!” |
| (25) እነዚያም የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኋላ የሚያፈርሱ አላህም እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ በምድርም ላይ የሚያበላሹ እነዚያ ለነሱ እርግማን አለባቸው፡፡ ለእነሱም መጥፎ አገር (ገሀነም) አላቸው፡፡ | (25) As for those who break the covenant of Allah after it has been ratified, and sever the ties that Allah has commanded to be maintained, and spread corruption in the land – it is they who are cursed, and for them there will be the worst abode. |
| (26) አላህ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ (ከሓዲዎች) በቅርቢቱም ሕይወት ተደሰቱ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱ አንጻር (ትንሽ) መጠቀሚያ እንጂ ምንም አይደለችም፡፡ | (26) Allah extends provision to whom He wills or restricts it. They rejoice in the life of this world, although the life of this world, compared to the Hereafter, is nothing but a fleeting pleasure. |
| (27) እነዚያም የካዱት «በእርሱ ላይ ከጌታው ተዓምር ለምን አልተወረደም» ይላሉ፡፡ «አላህ የሚሻውን ያጠምማል፡፡ የተመለሰውንም ሰው ወደርሱ ይመራል» በላቸው፡፡ | (27) Those who disbelieve say, “Why has no sign been sent down to him from his Lord?” Say, “Allah causes to stray whom He wills and guides to Himself who turns to Him, |
| (28) (እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡ | (28) those who believe and whose hearts find tranquility in the remembrance of Allah, for indeed in the remembrance of Allah do hearts find tranquility. |
| (29) እነዚያ ያመኑትና መልካም ሥራዎችን የሠሩት ለእነሱ ደግ ኑሮ መልካም መመለሻም አላቸው፡፡ | (29) Those who believe and do righteous deeds, for them there will be bliss and a good return.” |
| (30) እንደዚሁ ከበፊትዋ ብዙ ሕዝቦች በእርግጥ ያለፉ ወደኾነችው ሕዝብ እነርሱ በአልረሕማን የሚክዱ ሲኾኑ ያንን ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ፡፡ «እርሱ (አልረሕማን) ጌታዬ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ በርሱ ላይ ተጠጋሁ፡፡ መመለሻየም ወደርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ | (30) Thus did We send you to a community before which other communities had passed away, so that you may recite to them what We have revealed to you, yet they disbelieve in the Most Compassionate. Say, “He is my Lord; none has the right to be worshiped except Him. In Him I put my trust, and to Him is my return.” |
| (31) ቁርኣንም በእርሱ ተራራዎች በተነዱበት ወይም በእርሱ ምድር በተቆራረጠችበት ወይም በእርሱ ሙታን እንዲናገሩ በተደረጉበት ኖሮ (የመካ ከሓዲዎች ባላመኑ ነበር)፡፡ በእውነቱ ነገሩ ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑት ሰዎች እነሆ አላህ በሻ ኖሮ ሰዎችን በመላ በእርግጥ ይመራቸው እንደነበረ አያውቁምን እነዚያም የካዱት በሥራቸው ምክንያት (አጥፊ) ዐደጋ የምታገኛቸው ከመኾን ወይም የአላህ ቀጠሮ እስኪመጣ በአገራቸው አቅራቢያ (አንተ) የምትሰፍርባቸው ከመኾን አይወገዱም፡፡ አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና፡፡ | (31) Even if there were a Qur’an that could cause mountains to move, or split the earth, or cause the dead to speak, [they would still not believe]. To Allah belongs all matters. Do the believers not know that if Allah had willed, He could have guided all humans? Calamities will continue to befall the disbelievers or strike close to their homes because of their deeds, until the promise of Allah comes to pass, for Allah does not fail in His promise. |
| (32) ከአንተ በፊት በነበሩትም መልክተኞች በእርግጥ ተላግጦባቸዋል፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ጊዜን ሰጠኋቸው፡፡ ከዚያም (በቅጣት) ያዝኩዋቸው፡፡ ቅጣቴም እንዴት ነበር! | (32) There were messengers before you who were ridiculed, but I gave respite to those who disbelieved, then I seized them. How [terrible] was My chastisement! |
| (33) እርሱ በነፍስ ሁሉ ላይ በሠራቸው ሥራ ተጠባባቂ የኾነው (አላህ እንደዚህ እንዳልኾነው ጣዖት ብጤ ነውን) ለአላህም ተጋሪዎችን አደረጉ፡፡ ጥሯቸው «አላህን በምድር ውስጥ የማያውቀው ኖሮ ትነግሩታላችሁን ወይስ ከቃል በግልጽ (ፍቺ በሌለው ከንቱ ቃል ተጋሪዎች በማለት ትጠሩዋቸዋላችሁን)» በላቸው፡፡ በእውነቱ ለእነዚያ ለካዱት ተንኮላቸው ተሸለመላቸው፡፡ ከእውነቱ መንገድም ታገዱ፡፡ አላህም ያጠመመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡ | (33) Is He Who watches every soul in whatever it does [like others]? Yet they ascribe partners to Allah. Say, “Name them! Or do you presume to inform Him of something that He does not know on earth, or it is just a show of words?” No, but the falsehood of the disbelievers is made appealing to them, and they are hindered from the [straight] path. Whoever Allah causes to stray, he will have none to guide. |
| (34) ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወት ቅጣት አላቸው፡፡ የመጨረሻይቱም (ዓለም) ቅጣት በጣም የበረታ ነው፡፡ ለእነሱም ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ የላቸውም፡፡ | (34) They will be punished in this life, but the punishment of the Hereafter is more severe, and they will have no protector against Allah. |
| (35) ያች ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት ገነት ምጣኔዋ (እንደሚነገራችሁ ነው)፡፡ ከሥርዋ ወንዞች ይፈስሳሉ፡፡ ምግቧ (ሁልጊዜ) የማይቋረጥ፤ ነው፡፡ ጥላዋም (እንደዚሁ)፡፡ ይህች የእነዚያ የተጠነቀቁት መጨረሻ ናት፡፡ የከሃዲዎችም መጨረሻ እሳት ናት፡፡ | (35) The likeness of Paradise, which is promised to the righteous is that under it rivers flow; its fruit is eternal, so is its shade. Such is the end of those who fear Allah, but the end of the disbelievers is Fire! |
| (36) እነዚያም መጽሐፉን የሰጠናቸው ወዳንተ በተወረደው ይደሰታሉ፡፡ ከአሕዛብም ከፊሉን የሚክዱ ሰዎች አልሉ፡፡ «እኔ የታዘዝኩት አላህን ብቻ እንድገዛ በእርሱም እንደዳላጋራ ነው፡፡ ወደእርሱ እጠራለሁ፤ መመለሻዬም ወደእርሱ ነው» በላቸው፡፡ | (36) Those whom We gave the Scripture rejoice at that which is sent down to you [O Prophet], but there are some factions who deny part of it. Say, “I have only been commanded to worship Allah, and associate none with Him. To Him I call and to Him is my return.” |
| (37) እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲኾን አወረድነው፡፡ ዕውቀቱ ከመጣልህም በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል ከአላህ ቅጣት ምንም ረዳትም ጠባቂም የለህም፡፡ | (37) Thus We have sent it down as a commandment in Arabic. If you were to follow their desires after the knowledge that has come to you, you would have no supporter or protector against Allah. |
| (38) ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ለእነርሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል፡፡ ለማንኛውም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ ተዓምር ሊያመጣ አይገባውም፡፡ ለጊዜው ሁሉ ጽሑፍ አለው፡፡ | (38) We have sent messengers before you and gave them wives and offspring. It was not for any messenger to bring a sign except with Allah’s permission. Every matter has a destined time. |
| (39) አላህ የሚሻውን ያብሳል፤ ያጸድቃልም፡፡ የመጽሐፉ መሠረትም እርሱ ዘንድ ነው፡፡ | (39) Allah eliminates what He wills or affirms it, and with Him is the Master Book. |
| (40) የዚያንም ያስፈራራናቸውን ከፊሉን ብናሳይህ (መልካም ነው)፡፡ ወይም ብንገድልህ (ወቀሳ የለብህም)፡፡ በአንተ ላይ ያለብህ ማድረስ ብቻ ነው፡፡ ምርመራውም በኛ ላይ ነው፡፤ | (40) Whether We show you [O Prophet] part of what We warn them or cause you to die [before that], your duty is only to convey the message, and the reckoning is for Us. |
| (41) እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ኾነን የምንመጣባት መኾናችንን አላዩምን አላህም ይፈርዳል፡፡ ለፍርዱም ገልባጭ የለውም፡፡ እርሱም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ | (41) Do they not see that We advance to the land, diminishing it from its sides? It is Allah Who decrees; there is none to reverse His decree, and He is swift in reckoning. |
| (42) እነዚያም ከእነሱ በፊት የነበሩት በእርግጥ መከሩ፡፡ አዘንግቶም የመያዙ ዘዴ በሙሉ የአላህ ነው፡፡ ነፍስ ሁሉ የምትሠራውን ያውቃል፡፡ ከሓዲዎችም የመጨረሻይቱ አገር ለማን እንደምትኾን ወደፊት ያውቃሉ፡፡ | (42) Those who came before them did devise plans, but Allah has the ultimate plan. He knows what every soul does, and the disbelievers will come to know who will have the final abode. |
| (43) እነዚያም የካዱት ሰዎች «መልክተኛ አይደለህም» ይላሉ፡፡ «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህና እርሱ ዘንድ የመጽሐፉ ዕውቀት ባለው ሰው በቃ» በላቸው፡፡ | (43) Those who disbelieve say, “You are not a messenger.” Say, “Allah is sufficient as a Witness between me and you, as well as those who have knowledge of the Scripture.” |
