Skip to content

Amharic Quran

ከመሞትህ በፊት ቁርአንን አንብብ! (Read the holy Quran before you die!)

  • Home
    • ቁርአንን እንረዳው
    • Download
  • ሱራዎች / Surah List
    • አል-ፋቲሐ (Al-Fatiha)
    • አል-በቀራህ (Al-Beqerah)
    • አል-ዒምራን (Al-Imran)
    • አል-ኒሳዕ (An-Nisa)
    • አል-ማዒዳህ (Al-Maidah) 
    • አንዓም (Al-anam)
    • አል አዕራፍ (Al-Aeraf)
    • አል አንፋል (Al-Anfal)
    • አል ተውባ (At-Tawba)
    • አል ዩኑስ (Yunus)
    • አል ሁድ (Al-Hud)
    • ዩሱፍ (Yusuf)
    • 13 – Ar-Ra’d
    • 14 – Ibrahim
    • አል ሒጅር (Al-Hijr)
    • 16 – An-Nahl
    • 17 – Al-Israa
    • ከህፍ (Al-Kahf )
    • 19 Maryam
    • ጧሃ (Taa-Ha)
    • 21 – Al-Anbiyaa
    • አል ሐጅ (Al-Hajj)
    • 23 – Al-Muminoon
    • 24 – An-Noor
    • 25 – Al -Furqan
    • 26 – Ash-Shu’araa
    • 27 – An-Naml
    • 28 – Al-Qasas
    • 29 – Al-Ankaboot
    • 30 – Ar-Room
    • 31 – Luqman
    • 32 – As-Sajda
    • 33 – Al-Ahzaab
    • 34 – Saba
    • 35 – Faatir
    • 36 – Yaseen
    • 37 – As-Saaffaat
    • 38 – Saad
    • 39 – Az-Zumar
    • 40 – Al-Ghaafir
    • 41 – Fussilat
    • 42 – Ash-Shura
    • 43 – Az-Zukhruf
    • 44 – Ad-Dukhaan
    • 45 – Al-Jaathiya
    • 46 – Al-Ahqaf
    • 47 – Muhammad
    • 48 – Al-Fath
    • 49 – Al-Hujuraat
    • 50 – Qaaf
    • 51 – Adh-Dhaariyat
    • 52 – At-Tur
    • 53 – An-Najm
    • 54 – Al-Qamar
    • 55 – Ar-Rahmaan
    • 56 – Al-Waaqia
    • 57 – Al-Hadid
    • 58 – Al-Mujaadila
    • 59 – Al-Hashr
    • 60 – Al-Mumtahana
    • 61 – As-Saff
    • 62 – Al-Jumu’a
    • 63 – Al-Munaafiqoon
    • 64 – At-Taghaabun
    • 65 – At-Talaaq
    • 66 – At-Tahrim
    • 67 – Al-Mulk
    • 68 – Al-Qalam
    • 69 – Al-Haaqqa
    • 70 – Al-Ma’aarij
    • 71 – Nooh
    • 72 – Al-Jinn
    • 73 – Al-Muzzammil
    • 74 – Al-Muddaththir
    • 75 – Al-Qiyaama
    • 76 – Al-Insaan
    • 77 – Al-Mursalaat
    • 78 – An-Naba
    • 79 – An-Naazi’aat
    • 80 – Abasa
    • 81 – At-Takwir
    • 82 – Al-Infitaar
    • 83 – Al-Mutaffifin
    • 84 – Al-Inshiqaaq
    • 85 – Al-Burooj
    • 86 – At-Taariq
    • 87 – Al-A’laa
    • 88 – Al-Ghaashiya
    • 89 – Al-Fajr
    • 90 – Al-Balad
    • 91 – Ash-Shams
    • 92 – Al-Lail
    • 93 – Ad-Dhuhaa
    • 94 – Ash-Sharh
    • 95 – At-Tin
    • 96 – Al-Alaq
    • 97 – Al-Qadr
    • 98 – Al-Bayyina
    • 99 – Az-Zalzala
    • 100 – Al-Aadiyaat
    • 101 – Al-Qaari’a
    • 102 – At-Takaathur
    • 103 – Al-Asr
    • 104 – Al-Humaza
    • 105 – Al-Fil
    • 106 – Quraish
    • 107 – Al-Maa’un
    • 108 – Al-Kawthar
    • 109 – Al-Kaafiroon
    • 110 – An-Nasr
    • 111 – Al-Masad
    • 112 – Al-Ikhlaas
    • 113 – Al-Falaq
    • 114 – An-Naas

የእስልምና ታሪክ መበደል

Posted on May 1, 2025July 24, 2026 By Amharic Quran 1 Comment on የእስልምና ታሪክ መበደል
የእስልምና ታሪክ

የእስልምና ታሪክ መበደል

መግቢያ
የእስልምና ታሪክን ለማጠልሸት የቻሉ ክፍሎች

ኢማሙ አል-ጠበሪይ ታሪክን ከሰበሰቡበት እለት ጀምሮ የእስልምናን ታሪክን አስቦ የሚነሳበት አዋቂ ባይጠፋም አንዳንዱ አደገኛነቱን ባለመገንዘብ ሳያጣራ ያገኘውን ሲጽፍ ሌላው ደግሞ አስቦበት እንደ ራፊዷ ያሉና ሌሎችም ለእስልምና ቅን መንፈስ የሌላቸው ተንኮለኛች በወገንተኝነት በእስልምና ታሪክ ውስጥ ያስገቡትን ቅጥፈት ከአል-ጠበሪ የታሪክ መጽሐፍ በመውስድና እንዲሁም ከተመሳሳይ መጻሕፍት በደካማ መረጃ የተደገፈ ቅጥፈትን ለአንባቢ እውነት አስመስለው ለማቅረብ ችለዋል።

እንደ ምእራባውያን ያሉ ጸሐፊዎች ደግሞ ስለእስልምና ታሪክ ለመጻፍ በሚፈልጉበት ጊዜ ታሪኩን ከራሳችን የታሪክ መጻሕፍት በመውሰድ ታሪካችንን በርዘውና ከልሰው ይጽፉልንናል ። እነዚህም ምእራባውያን በኦሬንታሊስት ስም ሲታወቁ አብዛኞቹ የእስልምና ታሪክን የሚያጎድፈውን በመምረጥ ከእነሱ የመነጨ ታሪክ ጋር ቀላቅለው ያቀርቡታል። ኦሬንታሊስት የሚባሉትም ከምእራብ የፈረንጅ አገሮች ወደ ምሥራቅ የአረብ አገሮች ሄደው ስለ እስልምና ታሪክ የሚያጠኑ ሲሆኑ ብዙዎቹ በታሪክ አጻጻፋቸው ላይ ታማኝነት የሌላቸው ሆነው ይታያሉ። በተጨማሪም ኦሬንታሊስቶች የራሳቸውን አስተያየት በመጨመር የሚጽፉት የተሳሳተ ታሪክ በየገበያው በየቋንቋው ታትሞ ይሸጣል። የኦሬንታሊስት የተሳሳተ የእስልምናን ታሪክ መጻፍ ብቻ ሳይጎዳ በዘመናችን የበለጠ አስከፊ የሆነው ነገር በአንዳንድ ሙስሊም ናቸው የተባሉ ጸሐፊዎች የሚታየው ምእራባውያን ከሚጽፉት መጽሐፍ እንደ መረጃና ዋቢ አድርገው በመውሰድ ታሪካችንን ለማጠልሸት መቻላቸው ነው።

ከሊፋ ዑስማን ብን ዓፋንን (ረዐ) ገድለው በሶሓባዎች (ረዐ) መካከል የእርስበርስ ጦርነት እንዲነሳ ለማድረግ የቻሉ በሙስሊም ስምና በሙስሊሞች መካከል ተሰግስገው የሚገኙ የኢስላም ጠላቶች እስከ አሁንም ድረስ ታሪካችንን በማጠልሸት ከሶሓባዎች (ረዐ) ጋር እንድንቃቃር ለማድረግ ሞከራቸውን አላቋረጡም። ከነዚህ አጥፊዎች መካከል ዋነኞቹ እንደ ራፊዷዎች ያሉ በቅጥፈት ከሚጽፉት ታሪክ ለምሳሌ ብናቀርብ እንደ እናታችን ዓኢሻ (ረዐ) ያሉትን በዓልይ አቢ ጣሊብ (ረዐ) ላይ ጦርነት አስነስተዋል በማለት የታሪክን መልክ ለመቀየር ችለዋል።

እንዲሁም የዓልይና (ረዐ) የሙዓውያ (ረ.ዐ) ጦርነት ምክንያት የነበረው የዑስማን (ረዐ) ገዳዮችን እንዳልሆኑ አድርገው በማጥፋፋት በመካከላቸው የሥልጣን ሽሚያ እንደነበርና ሙዓውያ (ረዐ) ከዓልይ (ረዐ) ሥልጣናቸውን ለመንጠቅ የተደረገ ጦርነት አስመስለው በማስወራት መንስኤው የአሚር አል-ሙእሚኒን የዑስማን (ረዐ) በአመጸኞች መገደል እንዳልሆነ በማስመሰል ፍጹም የታሪክን መልክ በመቀየር ብዙሃኑን ለማሳመን ችለዋል።

ይህን ያደረጉበት ዋነኛ ምክንያትም የአመጸኞቹን ተንኮል ለመሸፈንና የዑስማን (ረዐ) ገዳዮችን የፊትና እሳት ጫሪዎች መሆናቸው እንዳይታወቅ ለማጥፋፋት ያደረጉት ሴራ እንጅ ዓልይን (ረዐ) ለመደገፍ ያደረጉት ቅጥፈት ፍጹም አልነበረም ። እንዲሁም በዓልይ (ረዐ) በሙዓውያ (ረዐ) የውጊያ ማቆም ስምምነት ምክንያት ከሁለቱም ወገን ለአስታራቂነት የተመረጡ ሶሓቦችን ስም በማጥፋት አንዱን ሶሓብይ ጮሌላና አታላይ ሲያስመስሉ ሌላውን ቂላቂልና በቀላሉ የሚታለል በማስመሰል እርቁ እንዲፈርስ ያደረጉ አመጽኞቹ እንዳልሆኑ አድርገው ብዙዎቻችንን ሊያሳምኑ ችለዋል።

ይህን የመሳሰለ ልዩ የሆነ ቅጥፈት በመቅጠፍ ታሪክን በመበረዝ ሰላምና እርቅ እንዳይሰፍን ለማደፍረስ ሆን ተብሎ ታስቦበት ከዑስማን (ረዐ) መገደል በኋላ ያለው ታሪካችን ብዙ ብልሽት የገባበት በመሆኑ በብርቱ ጥንቃቄና በቂ መረጃዎች እየተመረጡ ለማስተካከል በዘመናችን ሙስሊሞች የታሪክ አዋቂዎች ጥረት እያደረጉ ጥሩ ውጤት እያሳየ ነው። ይህን ጥፋት ያዘለ ታሪክ ግን እስካሁንም በሺዓዎች በኩል ከፍተኛ ክንክን ተሰጥቶት በየሚዲያው በየመጻፍሕፍቱ በየሑሰይንያው (የሺዓዎች መሰብሰቢያ ሌሎች የሱና ተከታይ ሙስሊሞች የማይቀላቀሉበት ሶሓባዎች በየደቂቃው የሚሰደቡበትና የሚረገሙበት ቦታ) በየጊዜው እንደ ከቁርአን የበልጥ ይነበባል።

በተለይ የመጀመሪያዎቹ የፊትና አባቶችና የኢስላም ጠላቶች የነበሩትን የሠሩትን እርኩስ ተግባር ሁሉ በመሸፈን እንዲሁም ጀብዱ ሥራ የሠሩ አድርገው በማጋነን እነሱን ለማወደስ ራፊዷዎች የሚያፍሩበት ነገር ሆኖ አልተገኘም። በአንጻሩ ግን የነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ሶሓቦችን (ረ.ዐ) በማዋረድና በማናናቅ ያለ አንዳች ፍራቻ ሲቀጥፉ ይታያሉ ።

በዚህ አይነት ራፊዷዎች በቅጥፈት ያስገቡትን የታሪክ ጠለሸት ብዙ ጸሐፊዎች ሳያጣሩ የጻፉት በአህለል ሱና ኪታቦች ውስጥ በመገኘቱ ብዙዎቻችንን እውነተኛ ታሪክ መስሎ ሊያሳምነን ችሏል ። ራፊዷዎች ታሪክን በማዛወር እኛን ለማሳመን ከሚሞክሩበት አንዱ የሑሰይን ብን ዓልይ ብን አቢ ጣሊብ (ረዐ) መገድልን የሚያወሳውን ታሪክ በመቀያየር ነው።

ራሳቸውን የሑሰይን (ረዐ) ደጋፊዎች በማድረግ የሱና ተከታዮችን ደግሞ ገዳዮች እንደሆኑ አድርገው በማስወራታቸው በማናቀው ነገር በየትኛውም ዘመን በማንኛውም ሺዓ ነኝ በሚሉ ሰዎች አይን በጥላቻ እንድንታይ አድርጎናል።

ነገር ግን ትክክል ያልሆነ ታሪክን በመከተል ለሑሴን (ረዐ) መገደል ምክንያት አህለል ሱናዎች እንደሆኑ አድርገው እንደጠላት ሲያዩ ዓልይን (ረዐ) የገደለ ከራሳቸው ሺዓ (ደጋፊ ወይም ተከታይ) በነበረ በከዋሪጅ እጅ መሆኑን እምብዛም የቆጫቸው አይመስልም ከዋሪጆችም የዓልይ (ረዐ) ሺዓ እንደነበሩ ፍጹም ለመጥቀስ ፍጹም አይሞክሩም።

በተለይም ራፊዷዎች ሃቅን እንደሚደብቁ ልናውቅ የሚያስችለን ነገርና የኢስላም ጠላት የሚያስመስላቸው በዑስማን (ረዐ) ገደላ ሴራ ተሳትፈው የነበሩ ወንጀለኞች የነበሩ እንደ አል-አሽተርና ሙሐመድ አቡ በከር ወዘተ.. ያሉትን ቀንደኞች የፊትና እሳት ቆስቋሾች የነበሩትን በመልካም ነገር ካልሆነ በስተቀር ማንም ሰው በመጥፎ እንዲያነሳቸው ያለመፍቀዳቸው ነው።

በአንጻሩ ግን የከሊፋ ዑስማን (ረዐ) በግፍ መገደል እንኳንና ሊቆጫቸው ዑስማንን (ረዐ) ጥፋተኛ ለማድረግ ብዙ የቅጥፈት ታሪኮችን ፈብርከው ይገኛሉ። ከዚህም አልፈው ዑስማንን (ረዐ) የገደሉ ሶሓቦች ናቸው ለማለት አላፈሩም። ይባስ ብሎ እናታችን ዓኢሻን (ረዐ) የዑስማን (ረዐ) ገዳዮች ተባባሪ እንደነበሩ አድርገው የሚያስወሩ የአላህ ፍራቻ የሌላቸው የራፊዷዎችን ተንኮል በመረጃ ለአንባቢዎች ኢንሻአህ እናቀርባለን።
ይቀጥላል

በአህመድ ሰ. አል-ከሽዓን የተዘጋጀ (https://www.facebook.com/islamawitarik )

Tags: Amharic Quran quran amharic quran in amharic ሱረቱል በቀራህ ሱረቱል ከህፍ ቁረአን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ትርጉም ቁርአን በአማርኛ የቁራን ትርጉም የእስልምና ታሪክ የእስልምና ታሪክ መበደል

Post navigation

❮ Previous Post: Quran in Afaan Orormo
Next Post: ክርስቲያኖችም ተሰደው ሲመጡ ተቀበለናቸዋል! በአህመዲን ጀበል ❯

One thought on “የእስልምና ታሪክ መበደል”

  1. 4 says:
    July 9, 2026 at 5:08 pm

    4

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ሁሉም ሱራዎች / All Chapters

  1. ሱረቱ አል-ፋቲሃ – Al-Fātihah
  2. ሱረቱ አል-በቀራህ – Al-Baqarah
  3. ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን – Āl-‘Imrān
  4. ሱረቱ አን-ኒሳዕ – An-Nisā’
  5. ሱረቱ አል-ማኢዳህ – Al-Mā’idah
  6. ሱረቱ አል-አንዓም – Al-An‘ām
  7. ሱረቱ አል-አዕራፍ – Al-A‘rāf
  8. ሱረቱ አል-አንፋል – Al-Anfāl
  9. ሱረቱ አት-ተውባህ – At-Tawbah
  10. ሱረቱ ዩኑስ – Yūnus
  11. ሱረቱ ሁድ – Hūd
  12. ሱረቱ ዩኑስ – Yūsuf
  13. ሱረቱ አር-ረዕድ – Ar-Ra‘d
  14. ሱረቱ ኢብራሂም – Ibrāhīm
  15. ሱረቱ አል ሒጅር – Al-Hijr
  16. ሱረቱ አን–ነሕል – An-Nahl
  17. ሱረቱ አል ኢስራዕ – Al-Isrā’
  18. ሱረቱ አል ከህፍ – Al-Kahf
  19. ሱረቱ መርየም – Maryam
  20. ሱረቱ ጣሃ – Tā-ha
  21. ሱረቱ አል አንቢያ – Al-Anbiyā’
  22. ሱረቱ አል ሐጅ – Al-Hajj
  23. ሱረቱ አል–ሙዕሚኑን – Al-Mu’minūn
  24. ሱረቱ አልን ኑር – An-Noor
  25. ሱረቱ አል ፉርቃን – Al-Furqān
  26. ሱረቱ አሽ ሹዐራእ – Ash-Shu‘arā’
  27. ሱረቱ አን ነምል – An-Naml
  28. ሱረቱ አል ቀሰስ – Al-Qasas
  29. ሱረቱ አል ዐንከቡት – Al-‘Ankabūt
  30. ሱረቱ አር ሩም – Ar-Rūm
  31. ሱረቱ አል ሉቅማን – Luqmān
  32. ሱረቱ አስ ሰጅደህ – As-Sajdah
  33. ሱረቱ አል አሕዛብ – Al-Ahzāb
  34. ሱረቱ ሰበእ – Saba’
  35. ሱረቱ ፋጢር – Fātir
  36. ሱረቱ ያሲን – Yā-Sīn
  37. ሱረቱ አስ ሷፋት – As-Sāffāt
  38. ሱረቱ ሷድ – Sād
  39. ሱረቱ አዝ ዙመር – Az-Zumar
  40. ሱረቱ ጋፊር – Ghāfir
  41. ሱረቱ ፉሲለት – Fussilat
  42. ሱረቱ አሽ ሹራ – Ash-Shūra
  43. ሱረቱ አዝ ዙኽሩፍ – Az-Zukhruf
  44. ሱረቱ አድ ዱኻን – Ad-Dukhān
  45. ሱረቱ አል ጃሲያህ – Al-Jāthiyah
  46. ሱረቱ አል አህቃፍ – Al-Ahqāf
  47. ሱረቱ ሙሐመድ – Muhammad
  48. ሱረቱ አል ፈትህ – Al-Fat’h
  49. ሱረቱ አል ሑጅራት – Al-Hujurāt
  50. ሱረቱ ቃፍ – Qāf
  51. ሱረቱ አዝ ዛሪያት – Adh-Dhāriyāt
  52. ሱረቱ አጥ ጡር – At-Toor
  53. ሱረቱ አን ነጅም – An-Najm
  54. ሱረቱ አል ቀመር – Al-Qamar
  55. ሱረቱ አር ረሕማን – Ar-Rahmān
  56. ሱረቱ አል ዋቂዓህ – Al-Wāqi‘ah
  57. ሱረቱ አል ሐዲድ – Al-Hadīd
  58. ሱረቱ አል ሙጃደላ – Al-Mujādalah
  59. ሱረቱ አል ሐሽር – Al-Hashr
  60. ሱረቱ አል ሙምተሂና – Al-Mumtahanah
  61. ሱረቱ አስ ሶፍ – As-Saff
  62. ሱረቱ አል ጁሙዓህ – Al-Jumu‘ah
  63. ሱረቱ አል ሙናፊቁን – Al-Munāfiqūn
  64. ሱረቱ አት ተጋቡን – At-Taghābun
  65. ሱረቱ አጥ ጠላቅ – At-Talāq
  66. ሱረቱ አት ተህሪም – At-Tahrīm
  67. ሱረቱ አል ሙልክ – Al-Mulk
  68. ሱረቱ አል ቀለም – Al-Qalam
  69. ሱረቱ አል ሓቃህ – Al-Hāqqah
  70. ሱረቱ አል መዓሪጅ – Al-Ma‘ārij
  71. ሱረቱ ኑህ – Nūh
  72. ሱረቱ አል ጂን – Al-Jinn
  73. ሱረቱ አል ሙዘሚል – Al-Muzzammil
  74. ሱረቱ አል ሙደሲር – Al-Muddaththir
  75. ሱረቱ አል ቂያማህ – Al-Qiyāmah
  76. ሱረቱ አል ኢንሳን – Al-Insān
  77. ሱረቱ አል ሙርሰላት – Al-Mursalāt
  78. ሱረቱ አን ነበእ – An-Naba’
  79. ሱረቱ አን ናዚዓት – An-Nāzi‘āt
  80. ሱረቱ ዐበሰ – ‘Abasa
  81. ሱረቱ አት ተክዊር – At-Takwīr
  82. ሱረቱ አል ኢንፊጣር – Al-Infitār
  83. ሱረቱ አል ሙጠፊፊን – Al-Mutaffifīn
  84. ሱረቱ አል ኢንሺቃቅ – Al-Inshiqāq
  85. ሱረቱ አል ቡሩጅ – Al-Burūj
  86. ሱረቱ አጥ ጣሪቅ – At-Tāriq
  87. ሱረቱ አል አዕላ – Al-A‘lā
  88. ሱረቱ አል ጋሺያህ – Al-Ghāshiyah
  89. ሱረቱ አል ፈጅር – Al-Fajr
  90. ሱረቱ አል በለድ – Al-Balad
  91. ሱረቱ አሽ ሸምስ – Ash-Shams
  92. ሱረቱ አል ለይል – Al-Layl
  93. ሱረቱ አድ ዱሓ – Ad-Duhā
  94. ሱረቱ አሽ ሸርህ – Ash-Sharh
  95. ሱረቱ አት ቲን – At-Teen
  96. ሱረቱ አል ዐለቅ – Al-‘Alaq
  97. ሱረቱ አል ቀድር – Al-Qadr
  98. ሱረቱ አል–በይናህ – Al-Bayyinah
  99. ሱረቱ አል ዘልዘላህ – Az-Zalzalah
  100. ሱረቱ አል ዓዲያት – Al-‘Ādiyāt
  101. ሱረቱ አል ቃሪዓሕ – Al-Qāri‘ah
  102. ሱረቱ አት ተካሱር – At-Takāthur
  103. ሱረቱ አል ዓስር – Al-‘Asr
  104. ሱረቱ አል ሁመዛህ – Al-Humazah
  105. ሱረቱ አል ፊል – Al-Feel
  106. ሱረቱ ቁረይሽ – Quraysh
  107. ሱረቱ አል ማዑን – Al-Mā‘ūn
  108. ሱረቱ አል ከውሰር – Al-Kawthar
  109. ሱረቱ አል ካፊሩን – Al-Kāfirūn
  110. ሱረቱ አን ነስር – An-Nasr
  111. ሱረቱ አል መሰድ – Al-Masad
  112. ሱረቱ አል ኢኽላስ – Al-Ikhlās
  113. ሱረቱ አል ፈለቅ – Al-Falaq
  114. ሱረቱ አን ናስ – An-Nās

Copyright © 2026 Amharic Quran.

Theme: Oceanly by ScriptsTown