33 – Al-Ahzaab
33 – Al-Ahzaab
| (1) አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህን ፍራ፡፡ ከሓዲዎችንና መናፍቃንንም አትታዘዝ፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡ | (1) O Prophet, fear Allah and do not obey the disbelievers and the hypocrites. Indeed, Allah is All-Knowing, All-Wise. |
| (2) ከጌታህም ወደ አንተ የሚወረደውን ተከተል፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውሰጠ አዋቂ ነውና፡፡ | (2) Follow what is revealed to you from your Lord. Indeed, Allah is All-Aware of what you do. |
| (3) በአላህም ላይ ተመካ፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡ | (3) Put your trust in Allah; sufficient is Allah as a Disposer of Affairs. |
| (4) አላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም፡፡ ሚስቶቻችሁንም እነዚያን ከእነርሱ እንደናቶቻችሁ ጀርባዎች ይሁኑብን የምትሏቸውን እናቶቻችሁ አላደረገም፡፡ ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውንም ልጆቻችሁ አላደረገም፡፡ ይህ በአፎቻችሁ የምትሉት ነው፡፡ አላህም እውነቱን ይናገራል፡፡ እርሱም ትክክለኛውን መንገድ ይመራል፡፡ | (4) Allah has not made for any man two hearts inside him, nor has he made your wives – whom you declare unlawful – your real mothers, nor has he made your adopted sons your real sons. These are only words that you utter, but Allah speaks the truth and He guides to the right way. |
| (5) ለአባቶቻቸው (በማስጠጋት) ጥሯቸው፡፡ እርሱ አላህ ዘንድ ትክክለኛ ነው፡፡ አባቶቻቸውንም ባታውቁ በሃይማኖት ወንድሞቻችሁና ዘመዶቻችሁ ናቸው፡፡ በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት (ኀጢአት | (5) Call them [adopted sons] by their real fathers’ names; that is more equitable before Allah. But if you do not know their fathers, then they are your brothers in faith and your patronized associates. There is no blame on you if you make a mistake in that regard, but only for what your hearts intend. And Allah is All-Forgiving, Most Merciful. |
| (6) ነቢዩ በምእምናን ከነፍሶቻቸው ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው፡፡ የዝምድና ባለቤቶችም ከፊላቸው በከፊሉ (ውርስ) በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ከምእምናንና ከስደተኞቹ ይልቅ የተገባቸው ናቸው፡፡ግን ወደ ወዳጆቻችሁ (በኑዛዜ) መልካምን ብትሰሩ (ይፈቀዳል)፡፡ ይህ በመጽሐፉ ውሰጥ የተመዘገበ ነው፡፡ | (6) The Prophet has a greater claim over the believers than their own selves, and his wives are their mothers. And blood relatives are more entitled [to inheritance] than other believers and emigrants according to the Book of Allah, unless you do good to your close associates [through bequest]. This is written in the Record. |
| (7) ከነቢዮችም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም ከመርየም ልጅ ዒሳም በያዝን ጊዜ (አስታወስ)፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ | (7) And [remember] when We took from the prophets their covenant and from you [O Prophet], and from Noah, Abraham, Moses, and Jesus, son of Mary; We took from them a solemn covenant |
| (8) (አላህ) እውነተኞችን ከውነታቸው ሊጠይቅ (ይህንን ሠራ)፡፡ ለከሓዲዎችም አሳማሚን ቅጣት አዘጋጀ፡፡ | (8) so that He may question the truthful about their truthfulness, and He has prepared for the disbelievers a painful punishment. |
| (9) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ብዙ ሰራዊት በመጣችባችሁና በእነርሱ ላይ ነፋስንና ያላያችኋትን ሰራዊት በላክን ጊዜ በእናንተ ላይ (ያደረገላችሁን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ | (9) O you who believe, remember Allah’s favor upon you when [enemy] forces came against you, but We sent against them a violent wind and forces that you could not see. And Allah is All-Seeing of what you do. |
| (10) ከበላያችሁም ከናንተ በታችም በመጡባችሁ ጊዜ፣ ዓይኖችም በቃበዙ፣ ልቦችም ላንቃዎች በደረሱና በአላህም ጥርጣሬዎችን በጠረጠራችሁ ጊዜ (ያደረገላችሁን አስታውሱ)፡፡ | (10) [Remember] when they came upon you from above you and from below you, and your eyes grew wild [in horror], and the hearts reached the throats, and you began to entertain various thoughts about Allah. |
| (11) እዚያ ዘንድ ምእምናን ተሞከሩ፡፡ ብርቱን መንቀጥቀጥም ተንቀጠቀጡ፡፡ | (11) There the believers were tested and were severely shaken. |
| (12) መናፍቆችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸውም «አላህና መልክተኛው ማታለልን እንጂ ሌላን አልቀጠሩንም» በሚሉ ጊዜ (ያደረገላችሁን አስታውሱ)፡፡ | (12) And [remember] when the hypocrites and those with sickness in their hearts said, “Allah and His Messenger did not promise us but delusion!” |
| (13) ከእነርሱም የሆኑ ጭፍሮች «የየስሪብ ሰዎች ሆይ! ለእናንተ ስፍራ የላችሁምና ተመለሱ» ባሉ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ ከእነርሱም «ከፊሎቹ እርሷ ነውረኛ ሳትሆን ቤቶቻችን ነውረኛ ናቸው» የሚሉ ሆነው ነቢዩን (ከጦሩ ለመመለስ) ፈቃድን ይጠይቃሉ፡፡ መሸሽን እንጂ ሌላ አይፈልጉም፡፡ | (13) And [remember] when a group of them said, “O people of Yathrib, you cannot withstand [the enemy attack], so go back.” Another group of them asked the Prophet’s permission to leave, saying, “Our homes are exposed,” even though they were not exposed; they only wanted to flee. |
| (14) በእነርሱም ላይ (ቤቶቻቸው) ከየቀበሌዋ በተገባባት ከዚያም ከኢስላም መመለስን በተጠየቁ ኖሮ በሠሯት ነበር፡፡ በእርሷም ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር፡፡ | (14) If the enemy were to enter the town upon them from all sides, and they were asked to abandon faith, they would have done it and would not have shown hesitation in it except a little. |
| (15) ጀርባዎችንም ላያዞሩ ከዚያ በፊት በእርግጥ አላህን ቃል ኪዳን የተጋቡ ነበሩ፡፡ የአላህም ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ነው፡፡ | (15) They had already made a covenant with Allah earlier that they would not turn and flee, and the covenant of Allah will surely be questioned about. |
| (16) ከሞት ወይም ከመገደል ብትሸሹ መሸሻችሁ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም፡፡ ያን ጊዜም ጥቂትን እንጂ የምትጣቀሙ አትደረጉም በላቸው፡፡ | (16) Say, “Fleeing will never benefit you if you try to flee from death or killing, even then you will only be left to enjoy life except for a little while.” |
| (17) «(አላህ) በእናንተ ክፉን ነገር ቢሻ ያ ከአላህ የሚጠብቃችሁ ማነው? ወይም ለእናንተ ችሮታን ቢሻ፤ (በክፉ የሚነካችሁ ማነው?)» በላቸው፤ ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ወዳጅም ረዳትም አያገኙም፡፡ | (17) Say, “Who is there that can protect you from Allah if He intends to harm you or show you mercy?” They will not find besides Allah any protector or helper. |
| (18) ከእናንተ ውስጥ የሚያሳንፉትን፣ ለወንድሞቻቸውም «ወደኛ ኑ» የሚሉትን፣ ውጊያንም ጥቂትን እንጂ የማይመጡትን በእርግጥ አላህ ያውቃቸዋል፡፡ | (18) Allah knows well those among you who discourage others and those [hypocrites] who say to their brothers, “Come and join us,” and they hardly take part in the battle. |
| (19) በእናንተ ላይ (እርዳታን) የነፈጉ ሆነው እንጅ (የማይመጡትን)፣ ሽብሩም በመጣ ጊዜ እንደዚያ ከሞት (መከራ) በርሱ ላይ የሚሸፍን ዐደጋ እንደወደቀበት ዓይኖቻቸው ወዲያና ወዲህ የምትዞር ኾና ወዳንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ ሽብሩም በኼደ ጊዜ በገንዘብ ላይ የሚሳሱ ኾነው በተቡ ምላሶች ይነድፏችኋል፡፡ እነዚያ አላመኑም፡፡ ስለዚህ አላህ ሥራዎቻቸውን አበላሸ፡፡ ይህም በአላህ ላይ ገርነው፡፡ | (19) They are niggardly towards you. When danger comes, you see them looking at you with their eyes rolling like someone in the throes of death. But when danger is over, they slash you with sharp tongues, in greed for gains. Such people have not truly believed, so Allah will render their deeds worthless. That is easy for Allah. |
| (20) (መናፍቆች) አሕዛብን አልኼዱም ብለው ያስባሉ፡፡ አሕዛቦቹም ቢመጡ እነርሱ በዘላኖች ውስጥ በገጠር (የራቁ) ሊሆኑ ይመኛሉ፡፡ ከወሬዎቻችሁ ይጠይቃሉ፡፡ በእናንተ ውስጥ በነበሩም ኖሮ ጥቂትን እንጂ አይዋጉም ነበር፡ | (20) They think that the confederates have not yet gone. If the confederates were to come again, they would wish that they were away in the desert with Bedouins, asking for news of you. Even if they were among you, they would hardly take part in the fight. |
| (21) ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡ | (21) Indeed, in the Messenger of Allah you have an excellent example for those who look forward to Allah and the Last Day, and remember Allah much. |
| (22) አማኞቹም አሕዛብን ባዩ ጊዜ «ይህ አላህና መልክተኛው የቀጠሩን ነው፡፡ አላህና መልክተኛውም እውነትን ተናገሩ» አሉ፡፡ (ይህ) እምነትንና መታዘዝንም እንጂ ሌላን አልጨመረላቸውም፡፡ | (22) When the believers saw the confederates, they said, “This is what Allah and His messenger had promised us, and Allah and His messenger have told the truth.” And it only increased them in faith and submission. |
| (23) ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አልሉ፡፡ ከነርሱም ስለቱን የፈጸመ (ለሃይማኖቱ የተገደለ) አልለ፤ ከነርሱም ገና የሚጠባበቅ አልለ፡፡ (የገቡበትን ቃል) መለወጥንም አልለወጡም፡፡ | (23) Among the believers there are men who have been true to their pledge with Allah. Some of them have fulfilled their pledge, and others are still waiting, and they have not changed in the least. |
| (24) አላህ እውነተኞችን በውነተኛነታቸው ሊመነዳ መናፍቃንንም ቢሻ ሊቀጣ ወይም (ቢመለሱ) በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን ሊቀበል (ይህን አደረገ)፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ | (24) [It all happened] so that Allah may reward the truthful for their truthfulness, and punish the hypocrites if He wills, or accept their repentance. Indeed, Allah is All-Forgiving, Most Merciful. |
| (25) እነዚያንም የካዱትን በቁጭታቸው የተመሉ መልካምን ነገር ያላገኙ ሆነው አላህ | (25) Allah has repelled the disbelievers in their rage without gaining any good. And Allah spared the believers from fighting, and Allah is All-Powerful, All-Mighty. |
| (26) እነዚያንም ከመጽሐፉ ባለቤቶች (አሕዛቦችን) የረዷቸውን (ቁረይዟን) ከምሽጎቻቸው አወረዳቸው፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ መባባትን ጣለባቸው፡፡ ከፊሉን ትገድላላችሁ፡፡ ከፊሉንም ትማርካላችሁ፡፡ | (26) And He brought down those of the People of the Book who supported them from their fortresses, and cast horror into their hearts: you killed some and took others as captives. |
| (27) ምድራቸውንም፣ ቤቶቻቸውንም፣ ገንዘቦቻቸውንም ገና ያልረገጣችኋትንም ምድር አወረሳችሁ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ | (27) He also made you inherit their land, their homes and their wealth, and a land on which you have not yet set foot. And Allah is Most Capable of all things. |
| (28) አንተ ነቢይ ሆይ! ለሚስቶችህ (እንዲህ) በላቸው «ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የምትፈልጉ እንደ ሆናችሁ ኑ፤ አጣቅማችኋለሁና፡፡ መልካምንም ማሰማራት (በመፍታት) አሰማራችኋለሁና፡፡ | (28) O Prophet, tell your wives, “If you seek the life of this world and its embellishments, then come, I will give you provision and release you graciously. |
| (29) «አላህንና መልክተኛውን የመጨረሻይቱን አገርም የምትፈልጉ ብትሆኑም፤ እነሆ አላህ ከእናንተ ለመልካም ሠሪዎቹ ትልቅን ምንዳ አዘጋጅቷል፡፡» | (29) But if you seek Allah and His Messenger and the Final Abode, then Allah has prepared for those who do good among you a great reward.” |
| (30) የነቢዩ ሴቶች ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ግልጽ የሆነን መጥፎ ሥራ የምትሠራ ለእርሷ ቅጣቱ ሁለት እጥፍ ሆኖ ይነባበርባታል፡፡ ይህም በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ | (30) O wives of the Prophet, if anyone from among you were to commit a clear shameful act, the punishment would be doubled for her. That is easy for Allah. |
| (31) ከእናንተም ለአላህና ለመልክተኛው የምትታዘዝ መልካም ሥራንም የምትሠራ ምንዳዋን ሁለት ጊዜ እንሰጣታለን፡፡ ለእርሷም የከበረን ሲሳይ አዘጋጅተንላታል፡፡ | (31) But whoever among you devoutly obeys Allah and His Messenger and does righteous deeds, We will give her a double reward, and We have prepared for her an honorable provision. |
| (32) የነቢዩ ሴቶች ሆይ! ከሴቶች እንደማናቸው አይደላችሁም፡፡ አላህን ብትፈሩ (ትበልጣላችሁ)፡፡ ያ በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር አትለስልሱም፡፡ መልካምንም ንግግር ተናገሩ፡፡ | (32) O wives of the Prophet, you are not like any other women: if you fear Allah, do not be complaisant in your speech, lest those with sickness in their hearts should be moved with desire; but speak in an appropriate manner. |
| (33) በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፡፡ እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገለጥም በማጌጥ አትገለጡ፡፡ ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ የነቢዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው ከእናንተ ላይ እርክሰትን ሊያስወግድና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው፡፡ | (33) Stay in your homes and do not display your charms as was done in the former days of ignorance; establish prayer and give Zakah; and obey Allah and His Messenger. Allah only intends to keep evil away from you, O members of the [Prophet’s] household, and to completely purify you. |
| (34) ከአላህ አንቀጾችና ከጥበቡም በቤቶቻችሁ የሚነበበውን አስታውሱ፡፡ አላህ እዝነቱ ረቂቅ ውስጠ ዐዋቂ ነውና፡፡ | (34) And remember what is recited in your homes of Allah’s verses and [prophetic] wisdom. Allah is Most Subtle, All-Aware. |
| (35) ሙስሊሞች ወንዶችና ሙስሊሞች ሴቶች፣ ምእምናንና ምእምናትም፣ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፣ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፣ ታጋሾች ወንዶችና ታጋሾች ሴቶችም፣ አላህን ፈሪዎች ወንዶችና አላህን ፈሪዎች ሴቶችም፣ መጽዋቾች ወንዶችና መጽዋቾች ሴቶችም፣ ጿሚዎች ወንዶችና ጿሚዎች ሴቶችም፣ (ካልተፈቀደ ሥራ) ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ | (35) Muslim men and women, believing men and women, obedient men and women, truthful men and women, patient men and women, humble men and women, charitable men and women, fasting men and women, and the men and women who guard their chastity, and men and women who remember Allah much – Allah has prepared for them forgiveness and a great reward. |
| (36) አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡ | (36) It is not for a believing man or woman – when Allah and His Messenger have decided a matter – to have any other choice in their matter. Whoever disobeys Allah and His Messenger has clearly gone astray. |
| (37) ለእዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና (አንተም ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው (ለዘይድ) አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ባንተ ዘንድ ያዝ፤ (ከመፍታት) አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጉዋቸው (ሰዎች) ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ (በማግባት) ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን አጋባንህ፡፡ የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው፡፡ | (37) And [remember, O Prophet] when you were saying to the one who was favored by Allah and favored by you, “Keep your wife and fear Allah.” You were concealing in your heart what Allah was going to reveal, and you were fearing people, while it was more fitting that you should fear Allah. When Zayd no longer had desire for her, We gave her to you in marriage, so that there would be no restraint for the believers in marrying the ex-wives of their adopted sons when they no longer have desire for them. And Allah’s decree is bound to be fulfilled. |
| (38) በነቢዩ ላይ አላህ ለእርሱ በፈረደው ነገር ምንም ችግር ሊኖርበት አይገባም፡፡ በእነዚያ ከዚያ በፊት ባለፉት (ነቢያት) አላህ ደነገገው፡፡ የአላህም ትእዛዝ የተፈረደ ፍርድ ነው፡፡ | (38) There is no blame on the Prophet concerning what Allah has made lawful for him. Such was the way of Allah with those [prophets] who came before. And Allah’s command is a decree firmly determined, |
| (39) ለእነዚያ የአላህን መልእክቶች ለሚያደርሱና ለሚፈሩት ከአላህ በስተቀርም አንድንም ለማይፈሩት (ተደነገገ)፡፡ ተቆጣጣሪም በአላህ በቃ፡፡ | (39) those who convey the messages of Allah and fear Him, and they do not fear anyone except Allah. And sufficient is Allah as a Reckoner. |
| (40) ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ | (40) Muhammad is not the father of any of your men, but he is the Messenger of Allah and the seal of the prophets. And Allah is All-Knowing of everything. |
| (41) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት፡፡ | (41) O you who believe, remember Allah much, |
| (42) በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አጥሩት፡፡ | (42) and glorify Him morning and evening. |
| (43) እርሱ ያ በእናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው፡፡ መላእክቶቹም (እንደዚሁ ምሕረትን የሚለምኑላችሁ ናቸው)፡፡ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣችሁ ዘንድ (ያዝንላችኋል)፡፡ ለአማኞችም በጣም አዛኝ ነው፡፡ | (43) It is He Who confers blessings upon you, and His angels pray for you, so that He may bring you out of the depths of darkness into the light. And He is Most Merciful to the believers. |
| (44) በሚገናኙት ቀን መከባበሪያቸው ሰላም መባባል ነው፡፡ ለእነርሱም የከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ | (44) Their greeting on the Day they meet Him will be, “Peace,” and He has prepared for them a generous reward. |
| (45) አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን ላክንህ፡፡ | (45) O prophet, We have sent you as a witness, a bearer of glad tidings and a warner, |
| (46) ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ፣ አብሪ ብርሃንም (አድርገን ላክንህ)፡፡ | (46) and a caller to [the way of] Allah by His command, and as a lamp spreading light. |
| (47) አማኞችንም ከአላህ ዘንድ ለእነርሱ ታላቅ ችሮታ ያላቸው መኾኑን አብስራቸው፡፡ | (47) And give glad tidings to the believers that they will have a great bounty from Allah. |
| (48) ከሓዲዎችንና መናፍቃንንም አትታዘዛቸው፡፡ ማሰቃየታቸውንም (ለአላህ) ተው፡፡ በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ መጠጊያም በአላህ በቃ፡፡ | (48) Do not yield to the disbelievers and the hypocrites, and pay no heed to their annoyances. Put your trust in Allah, for Allah is sufficient as a Trustee of affairs. |
| (49) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ምእምናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኩዋቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለእናንተ በእነርሱ ላይ የምትቆጥሩዋት ዒዳ ምንም የላችሁም፡፡ አጣቅሟቸውም፤ (ጉርሻ ስጧቸው)፡፡ መልካም ማሰናበትንም አሰናብቷቸው፡፡ | (49) O you who believe, when you marry believing women and then divorce them before the marriage is consummated, you have no reason to ask them to observe any waiting period, so give them a compensation and release them in a pleasant manner. |
| (50) አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን፣ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች፣ እነዚያንም ከአንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎትህን ሴቶች ልጆች፣ የአክስቶችህንም ሴቶች ልጆች፣ የየሹማህንም ሴቶች ልጆች፣ የየሹሜዎችህንም ሴቶች ልጆች (ማግባትን) ለአንተ ፈቅደንልሃል፡፡ የአመነችንም ሴት ነፍሷን (ራሷን) ለነቢዩ ብትሰጥ ነቢዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ኾነ ከምእምናን ሌላ ላንተ ብቻ የጠራች ስትኾን (ፈቀድንልህ)፡፡ በእነርሱ (በምእምናን) ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው በጨበጧቸው (ባሮች ነገር) ግዴታ ያደረግንባቸውን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር (ያለፉትን ፈቀድንልህ)፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ | (50) O Prophet, We have made lawful for you your wives whose dowries you have paid; any bondwomen you may own from the prisoners of war whom Allah has bestowed upon you; daughters of your paternal uncle, daughters of your paternal aunts, daughters of your maternal uncle, daughters of your maternal aunts who have migrated with you; and a believing woman who offers herself to the Prophet [without dowry] if the Prophet wishes to marry her, [this is] exclusively for you, not for the rest of the believers. We know well what We have ordained for them concerning their marriages and the bondwomen they may own, so that there would be no discomfort for you. And Allah is All-Forgiving, Most Merciful. |
| (51) ከእነርሱ የምትሻትን ታቆያለህ፡፡ የምትሻውንም ወደ አንተ ታስጠጋለህ፡፡ (በመፍታት) ከአራቅሃትም የፈለግሃትን (በመመለስ ብታስጠጋ) በአንተ ላይ ኀጢአት የለብህም፡፡ ይህ ዓይኖቻቸው ወደ መርጋት፣ ወደ አለማዘናቸውም፣ ለሁሉም በሰጠሃቸው ነገር ወደ መውደዳቸውም በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ አላህም ዐዋቂ ታጋሽ ነው፡፡ | (51) You [O Prophet] may postpone [the turn of] whoever you wish [of your wives], and you may share your time with whoever of them you wish, and there is no blame on you if you call back any of those whose turn you have set aside. That is more likely that they will be content and not distressed, and that they will be satisfied with what you give them all. Allah knows what is in your hearts, and Allah is All-Knowing, Most Forbearing. |
| (52) ከእነዚህ በኋላ እጅህ ከጨበጠቻቸው (ባሮች) በስተቀር ሴቶች ለአንተ አይፈቀዱልህም፡፡ ከሚስቶችም መልካቸው ቢደንቅህም እንኳ በእነርሱ ልታላውጥ (አይፈቀደልህም)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ | (52) It is not lawful for you [O Prophet] to marry more women henceforth, nor can you replace any of them with others, even if their beauty may please you, except those bondwomen whom you own. And Allah is ever Watchful over all things. |
| (53) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መድረሱን የማትጠባበቁ ስትኾኑ ወደ ምግብ ካልተፈቀደላችሁ በስተቀር የነቢዩን ቤቶች (በምንም ጊዜ) አትግቡ፡፡ ግን በተጠራችሁ ጊዜ ግቡ፡፡ በተመገባችሁም ጊዜ ወዲያውኑ ተበተኑ፡፡ ለወግ የምትጫወቱ ኾናችሁም (አትቆዩ)፡፡ ይህ ነቢዩን በእርግጥ ያስቸግራል፡፡ ከእናንተም ያፍራል፡፡ ግን አላህ ከእውነት አያፍርም፡፡ ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጠይቋቸው፡፡ ይህ ለልቦቻችሁ፤ ለልቦቻቸውም የበለጠ ንጽሕና ነው፡፡ የአላህንም መልክተኛ ልታስቸግሩ ሚስቶቹንም ከእርሱ በኋላ ምንጊዜም ልታገቡ ለእናንተ አይገባችሁም፡፡ ይህ አላህ ዘንድ ከባድ (ኀጢአት) ነው፡፡ | (53) O you who believe, do not enter the houses of the Prophet, unless you are given permission for a meal; not so early as to wait for the meal to be prepared. But if you are invited, then enter, and when you have eaten, then disperse, without lingering for conversation. Such [behavior] causes annoyance to the Prophet; he is too shy to express it to you, but Allah is not shy of [telling] the truth. And if you ask his wives for something, ask them from behind a screen; that is purer for your hearts and their hearts. It is not lawful for you to cause annoyance to Allah’s Messenger, or to ever marry his wives after him, for that is indeed an enormous sin before Allah. |
| (54) ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት (በርሱ ይመነዳችኋል)፡፡ አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡ | (54) Whether you reveal something or conceal it, Allah is All-Knowing of everything. |
| (55) (የነቢዩ ሚስቶች) በአባቶቻቸው፣ በወንዶች ልጆቻቸውም፣ በወንድሞቻቸውም፣ ወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ በእኅቶቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ (ምእምናት በኾኑት) በሴቶቻቸውም፣ እጆቻቸው በጨበጧቸውም ባሮች (አጠገብ በመገለጥ) በእነርሱ ላይ ኃጢአት የለባቸውም፡፡ (ሴቶች ሆይ! ታዘዙ) አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነውና፡፡ | (55) There is no blame on the Prophet’s wives [if they are seen unveiled] by their fathers, their sons, their brothers, their brothers’ sons, their sisters’ sons, their fellow [Muslim] women, and their slaves whom they own. And fear Allah [O Prophet’s wives], for Allah is Witness over all things. |
| (56) አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ | (56) Indeed, Allah sends His blessings upon the Prophet, and His angels pray for him. O you who believe, invoke Allah’s blessings upon him, and send him greetings of peace. |
| (57) እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚያስከፉ በቅርቢቱ ዓለም በመጨረሻይቱም አላህ ረግሟቸዋል፡፡ ለእነርሱም አዋራጅን ቅጣት ደግሶላቸዋል፡፡ | (57) Those who offend Allah and His Messenger are cursed by Allah in this world and in the Hereafter, and He has prepared for them a humiliating punishment. |
| (58) እነዚያንም ምእምናንንና ምእምናነትን ባልሰሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ፡፡ | (58) Those who abuse believing men and women for something they did not commit, they will bear the burden of slander and flagrant sin. |
| (59) አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ | (59) O Prophet, tell your wives and your daughters, and the believing women to draw their outer garments over themselves; that is more likely that they will be known [as chaste women] and will not be harassed. And Allah is All-Forgiving, Most Merciful. |
| (60) መናፍቃንና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ (የአመንዝራነት) በሽታ ያለባቸው በመዲናም ውሰጥ (በወሬ) አሸባሪዎቹ (ከዚህ ሥራቸው) ባይከለከሉ በእነርሱ ላይ በእርግጥ እንቀሰቅስሃለን፡፡ ከዚያም በእርሷ ውስጥ ጥቂትን እንጂ አይጎራበቱህም፡፡ | (60) If the hypocrites and those who have sickness in their hearts, and the rumormongers in Madinah do not desist, We will surely instruct you [O Prophet] to overpower them, then they will not remain in the city with you except for a short while. |
| (61) የተረገሙ ኾነው እንጂ (አይጎራበቱህም)፡፡ በየትም ስፍራ ቢገኙ ይያዛሉ፡፡ መገደልንም ይገደላሉ፡፡ | (61) They are cursed; wherever they are found they should be seized and killed outright. |
| (62) (ይህቺ) በእነዚያ በፊት ባለፉት (ላይ የደነገጋት) የአላህ ድንጋጌ ናት፡፡ ለአላህም ድንጋጌ ፈጽሞ መለወጥን አታገኝም፡፡ | (62) Such was Allah’s way with those [hypocrites] who came before, and you will find no change in Allah’s way. |
| (63) ሰዎች ከሰዓቲቱ ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀትዋ አላህ ዘንደ ብቻ ነው፤» በላቸው፡፡ የሚያሳወቅህም ምንድን ነው! ሰዓቲቱ በቅርብ ጊዜ ልትኾን ይከጀላል፡፡ | (63) People ask you [O Prophet] concerning the Hour. Say, “Its knowledge is only with Allah.” How could you know? Perhaps the Hour is near. |
| (64) አላህ ከሓዲዎችን በእርግጥ ረግሟቸዋል፡፡ ለእነርሱም የተጋጋመችን እሳት አዘጋጅቷል፡፡ | (64) Indeed, Allah has cursed the disbelievers and has prepared for them a Blazing Fire, |
| (65) በእርሷ ውስጥ ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ፤ ወዳጅም ረዳትም አያገኙም፡፡ | (65) abiding therein forever, never will they find any protector or helper. |
| (66) ፊቶቻቸው በእሳት ውሰጥ በሚገለባበጡ ቀን «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ፡፡ | (66) On the Day when their faces are turned over in the Fire, they will say, “Would that we had obeyed Allah and obeyed the Messenger!” |
| (67) ይላሉም «ጌታችን ሆይ! እኛ ጌቶቻችንንና ታላላቆቻችንን ታዘዝን፡፡ መንገዱንም አሳሳቱን፡፡ | (67) They will say, “Our Lord, we obeyed our chiefs and our elders, but they led us astray from the [right] way. |
| (68) «ጌታችን ሆይ! ከቅጣቱ እጥፍን ስጣቸው፡፡ ታላቅን እርግማንም እርገማቸው፡፡» | (68) Our Lord, give them a double punishment and curse them with a mighty curse.” |
| (69) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደእነዚያ ሙሳን እንዳሰቃዩት ሰዎች አትኹኑ፡፡ ካሉትም ነገር ሁሉ አላህ አጠራው፡፡ አላህም ዘንድ ባለሞገስ ነበር፡፡ | (69) O you who believe, do not be like those who maligned Moses, but Allah cleared him of what they said; he was highly honored before Allah. |
| (70) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ፡፡ | (70) O you who believe, fear Allah and say what is right, |
| (71) ሥራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና፡፡ ኀጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል፡፡ አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ፡፡ | (71) He will guide you to righteous deeds and forgive your sins. Whoever obeys Allah and His Messenger will surely achieve a supreme triumph. |
| (72) እኛ አደራን በሰማያትና በምድር፣ በተራራዎችም ላይ አቀረብናት፡፡ መሸከሟንም እንቢ አሉ፡፡ ከእርሷም ፈሩ፡፡ ሰውም ተሸከማት፡፡ እርሱ በጣም በደለኛ ተሳሳች ነውና፡፡ | (72) Indeed, We offered the Trust to the heavens, the earth, and the mountains, yet they refused to bear it and were afraid of it. But man assumed it; he is indeed wrongful and ignorant. |
| (73) መናፍቃንንና መናፍቃትን፣ ወንዶች አጋሪዎችንና ሴቶች አጋሪዎችንም አላህ ሊቀጣና በምእምናንና በምእምናትም ላይ አላህ ንስሓን ሊቀበል (አደራዋን ሰው ተሸከማት)፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ | (73) [As a result of that] Allah will punish the hypocrite men and women, and the polytheist men and women, and Allah will accept the repentance of the believing men and women, for Allah is All-Forgiving, Most Merciful. |
| (1) አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህን ፍራ፡፡ ከሓዲዎችንና መናፍቃንንም አትታዘዝ፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡ | (1) O Prophet, fear Allah and do not obey the disbelievers and the hypocrites. Indeed, Allah is All-Knowing, All-Wise. |
