Default Image
19, Dec 2023
90 – Al-Balad

90 – Al-Balad

(1) በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡ (1) I do swear by this city [of Makkah] –
(2) አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡ (2) and you are free of restriction [for a while] in this city –
(3) በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡ (3) and by every parent and offspring,
(4) ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡ (4) We have created man in hardship.
(5) በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን? (5) Does he think that none can ever have power over him?
(6) «ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡ (6) He says, “I have squandered enormous wealth!”
(7) አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን? (7) Does he think that no one sees him?
(8) ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን? (8) Have We not given him two eyes,
(9) ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡ (9) and a tongue and two lips,
(10) ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን? (10) and shown him the two ways [of right and wrong]?
(11) ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡ (11) Yet he did not make his way through the steep path,
(12) ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? (12) and how do you know what the steep path is?
(13) (እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡ (13) It is freeing a slave,
(14) ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡ (14) or giving food on a day of hunger,
(15) የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤ (15) to an orphan relative,
(16) ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡ (16) or to a needy person in misery,
(17) (ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡ (17) then [most importantly] to be one of those who believe and exhort one another to patience and exhort one another to compassion.
(18) እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ (18) Such are the people of the Right.
(19) እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ (19) As for those who reject Our signs, they are the people of the Left,
(20) በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡ (20) who will be locked up in the Fire.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

30 – Ar-Room

30 – Ar-Room (1) አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)፡፡ (1) Alif Lām Mīm. (2) ሩም ተሸነፈች፡፡ (2) The Romans have been defeated…

13 – Ar-Ra’d

13 – Ar-Ra’d (1) አ.ለ.መ.ረ (አሊፍ ላም ሚም ራ) ይህች (አናቅጽ) ከመጽሐፉ አንቀጾች ናት፡፡ ያም ከጌታህ ወዳንተ የተወረደው እውነት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም፡፡…

57 – Al-Hadid

57 – Al-Hadid (1) በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፡፡ እርሱም ሁሉን አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ (1) All that is in…