Default Image
11, Dec 2023
70 – Al-Ma’aarij

70 – Al-Ma’aarij

(1) ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡(1) A challenger asked for a punishment bound to come
(2) በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡(2) upon the disbelievers, which none can avert,
(3) የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡(3) from Allah, Lord of the pathways of ascent,
(4) መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡(4) by which the angels and the Spirit will ascend to Him on a Day the length of which is fifty thousand years.
(5) መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡(5) So be patient [O Prophet] with beautiful patience.
(6) እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡(6) Indeed, they see this [punishment] far off,
(7) እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡(7) but We see it to be close at hand.
(8) ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡(8) On the Day when the sky will be like molten brass
(9) ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡(9) and the mountains will be like dyed wool,
(10) ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡(10) and no close friend will ask about another,
(11) (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡(11) even though they will see one another. The wicked will wish he could ransom himself from the punishment of that Day by offering his children,
(12) በሚስቱም በወንድሙም፡፡(12) and his wife and his brother,
(13) በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡(13) and his kindred who stood by him,
(14) በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡(14) and everyone on earth, just to save himself.
(15) ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡(15) By no means! It is a raging Flame,
(16) የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡(16) that will strip off the scalps.
(17) (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡(17) It will call everyone who turned their backs and disobeyed,
(18) ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡(18) and amassed and hoarded wealth.
(19) ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡(19) Indeed, man was created impatient:
(20) ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡(20) when evil befalls him, he bewails,
(21) መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡(21) but when good fortune comes his way, he becomes tight-fisted –
(22) ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡(22) except those who pray,
(23) እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡(23) who are steadfast in their prayers;
(24) እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡(24) and who give a due share of their wealth
(25) ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡(25) to the beggar and the dispossessed;
(26) እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡(26) and who firmly believe in the Day of Judgment;
(27) እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡(27) and those who fear the punishment of their Lord –
(28) የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡(28) for none can feel secure from their Lord’s punishment –
(29) እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡(29) and those who guard their private parts,
(30) በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡(30) except from their wives or bondwomen whom they own, for then they are not to be blamed.
(31) ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡(31) But whoever seeks beyond that, it is they who are the transgressors.
(32) እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡(32) and those who fulfill their trusts and pledges;
(33) እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡(33) and who are upright in their testimonies;
(34) እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡(34) and who take due care of their prayers;
(35) እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡(35) they will be honored in gardens.
(36) ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?(36) What is the matter with the disbelievers that they are rushing towards you [O Prophet],
(37) ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡(37) from the right and from the left, in crowds?
(38) ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?(38) Does everyone of them aspire to enter a garden of bliss?
(39) ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡(39) By no means! We have created them from what they know.
(40) በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡(40) I swear by the Lord of the sunrises and sunsets that We are surely Capable
(41) ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡(41) to replace them with others better than them, and none can escape Our decree.
(42) ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡(42) So leave them to engage in their falsehood and amuse themselves until they meet their Day which they are promised;
(43) ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡(43) the Day when they will rush out of their graves as if they are racing towards a goal,
(44) ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡(44) with their eyes downcast and overwhelmed with disgrace. That is the Day that they were promised.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

114 – An-Naas

114 – An-Naas (1) በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ፡፡ (1) Say, “I seek refuge with the Lord of mankind, (2) «የሰዎች…

ሱረቱ አል ተውባ Free Amharic Quran 9 Sura At-Tawba

ሱረቱ አል ተውባ Free Amharic Quran 9 Sura At-Tawba بَرَاءَةٌ مِّنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ إِلَى الَّذِينَ عَاهَدتُّم مِّنَ الْمُشْرِكِينَ التوبة [1]…

ሱረቱል አል-በቀራህ አማርኛ ቅዱስ ቁርአን ምዕራፍ 2 Amharic Quran

ሱረቱል አል-በቀራህ አማርኛ ቅዱስ ቁርአን ምዕራፍ 2 Amharic Quran بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ Bismillah hir rahman nir raheem الم  [1] (1) አ.ለ.መ    (1)…