Skip to content

Amharic Quran

ከመሞትህ በፊት ቁርአንን አንብብ! (Read the holy Quran before you die!)

  • Home
    • ቁርአንን እንረዳው
    • Download
  • ሱራዎች / Surah List
    • አል-ፋቲሐ (Al-Fatiha)
    • አል-በቀራህ (Al-Beqerah)
    • አል-ዒምራን (Al-Imran)
    • አል-ኒሳዕ (An-Nisa)
    • አል-ማዒዳህ (Al-Maidah) 
    • አንዓም (Al-anam)
    • አል አዕራፍ (Al-Aeraf)
    • አል አንፋል (Al-Anfal)
    • አል ተውባ (At-Tawba)
    • አል ዩኑስ (Yunus)
    • አል ሁድ (Al-Hud)
    • ዩሱፍ (Yusuf)
    • 13 – Ar-Ra’d
    • 14 – Ibrahim
    • አል ሒጅር (Al-Hijr)
    • 16 – An-Nahl
    • 17 – Al-Israa
    • ከህፍ (Al-Kahf )
    • 19 Maryam
    • ጧሃ (Taa-Ha)
    • 21 – Al-Anbiyaa
    • አል ሐጅ (Al-Hajj)
    • 23 – Al-Muminoon
    • 24 – An-Noor
    • 25 – Al -Furqan
    • 26 – Ash-Shu’araa
    • 27 – An-Naml
    • 28 – Al-Qasas
    • 29 – Al-Ankaboot
    • 30 – Ar-Room
    • 31 – Luqman
    • 32 – As-Sajda
    • 33 – Al-Ahzaab
    • 34 – Saba
    • 35 – Faatir
    • 36 – Yaseen
    • 37 – As-Saaffaat
    • 38 – Saad
    • 39 – Az-Zumar
    • 40 – Al-Ghaafir
    • 41 – Fussilat
    • 42 – Ash-Shura
    • 43 – Az-Zukhruf
    • 44 – Ad-Dukhaan
    • 45 – Al-Jaathiya
    • 46 – Al-Ahqaf
    • 47 – Muhammad
    • 48 – Al-Fath
    • 49 – Al-Hujuraat
    • 50 – Qaaf
    • 51 – Adh-Dhaariyat
    • 52 – At-Tur
    • 53 – An-Najm
    • 54 – Al-Qamar
    • 55 – Ar-Rahmaan
    • 56 – Al-Waaqia
    • 57 – Al-Hadid
    • 58 – Al-Mujaadila
    • 59 – Al-Hashr
    • 60 – Al-Mumtahana
    • 61 – As-Saff
    • 62 – Al-Jumu’a
    • 63 – Al-Munaafiqoon
    • 64 – At-Taghaabun
    • 65 – At-Talaaq
    • 66 – At-Tahrim
    • 67 – Al-Mulk
    • 68 – Al-Qalam
    • 69 – Al-Haaqqa
    • 70 – Al-Ma’aarij
    • 71 – Nooh
    • 72 – Al-Jinn
    • 73 – Al-Muzzammil
    • 74 – Al-Muddaththir
    • 75 – Al-Qiyaama
    • 76 – Al-Insaan
    • 77 – Al-Mursalaat
    • 78 – An-Naba
    • 79 – An-Naazi’aat
    • 80 – Abasa
    • 81 – At-Takwir
    • 82 – Al-Infitaar
    • 83 – Al-Mutaffifin
    • 84 – Al-Inshiqaaq
    • 85 – Al-Burooj
    • 86 – At-Taariq
    • 87 – Al-A’laa
    • 88 – Al-Ghaashiya
    • 89 – Al-Fajr
    • 90 – Al-Balad
    • 91 – Ash-Shams
    • 92 – Al-Lail
    • 93 – Ad-Dhuhaa
    • 94 – Ash-Sharh
    • 95 – At-Tin
    • 96 – Al-Alaq
    • 97 – Al-Qadr
    • 98 – Al-Bayyina
    • 99 – Az-Zalzala
    • 100 – Al-Aadiyaat
    • 101 – Al-Qaari’a
    • 102 – At-Takaathur
    • 103 – Al-Asr
    • 104 – Al-Humaza
    • 105 – Al-Fil
    • 106 – Quraish
    • 107 – Al-Maa’un
    • 108 – Al-Kawthar
    • 109 – Al-Kaafiroon
    • 110 – An-Nasr
    • 111 – Al-Masad
    • 112 – Al-Ikhlaas
    • 113 – Al-Falaq
    • 114 – An-Naas

56 – Al-Waaqia

Posted on December 11, 2023August 5, 2026 By Muhammed No Comments on 56 – Al-Waaqia
Amharic Quran, ቁርአንን እንረዳው

56 – Al-Waaqia

(1) መከራይቱ በወደቀች ጊዜ፡፡(1) When the Inevitable Event comes to pass,
(2) ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም፡፡(2) there will be none to deny its occurrence;
(3) ዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ ናት፡፡(3) it will bring some low and raise others up.
(4) ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ፡፡(4) When the earth will be shaken violently,
(5) ተራራዎችም መፍፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በኾኑ ጊዜ)፡፡(5) and the mountains crushed to pieces,
(6) የተበተነ ብናኝ በኾኑም ጊዜ(6) and turn to scattered dust,
(7) ሦስት ዓይነቶችም በኾናችሁ ጊዜ (ታዋርዳለች፤ ታነሳለችም)፡፡(7) then you are sorted into three groups:
(8) የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡(8) the people of the right – how blessed will be the people of the right!
(9) የግራ ጓዶችም ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው፡፡(9) The people of the left – how miserable will be the people of the left!
(10) (ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡(10) And the forerunners [in faith] are the forerunners [in Paradise].
(11) እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡(11) They are the nearest ones [to Allah],
(12) በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ፡፡(12) in Gardens of Bliss,
(13) ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡(13) many from the early generations,
(14) ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡(14) and a few from the later generations.
(15) በተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡(15) [They will be seated] on jeweled couches,
(16) በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ፡፡(16) reclining on them, facing one another.
(17) በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡(17) They will be served by immortal youths
(18) ከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ)፡፡(18) with cups, pitchers, and glasses [of wine] from a flowing spring,
(19) ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡(19) which will neither cause any headache nor intoxication,
(20) ከሚመርጡትም ዓይነት በእሸቶች፡፡(20) along with fruits of their choice,
(21) ከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡(21) and flesh of birds that they may desire.
(22) ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡(22) And [they will have] maidens with wide gorgeous eyes,
(23) ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡(23) like pristine pearls,
(24) በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡(24) as a reward for what they used to do.
(25) በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም፡፡(25) They will not hear therein any idle talk or sinful speech,
(26) ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡(26) except the words of peace, peace.
(27) የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች!(27) The people of the right – how blessed will be the people of the right!
(28) በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡(28) [They will be] amid thornless lote trees,
(29) (ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡(29) and clusters of bananas,
(30) በተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡(30) and shade long-extended,
(31) በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡(31) and flowing water,
(32) ብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም፡፡(32) and abundant fruit –
(33) የማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡(33) neither ceasing nor restricted –
(34) ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡(34) and mattresses raised high [on beds].
(35) እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው፡፡(35) Indeed, We have perfectly created them [their spouses],
(36) ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡(36) and have made them virgins,
(37) ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡(37) loving and of equal age,
(38) ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡(38) for the people of the right,
(39) ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡(39) many from the earlier generations,
(40) ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡(40) and many from the later generations.
(41) የግራ ጓደኞችም ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው፡፡(41) And the people of the left – how wretched will be the people of the left!
(42) በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡(42) [They will be] in scorching wind and scalding water,
(43) ከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡(43) in the shade of black smoke,
(44) ቀዝቃዛም መልካምም ያልኾነ፡፡(44) neither cool nor refreshing.
(45) እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና፡፡(45) Indeed, they used to be in luxuries before,
(46) በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና፡፡(46) and persisted in the gravest sin [of polytheism].
(47) ይሉም ነበሩ፡- «በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን?(47) They used to say, “When we die and become dust and bones, will we really be raised again?
(48) «የፊተኞቹ አባቶቻችንም?»(48) And our forefathers as well?”
(49) በላቸው፡- «ፊተኞቹም ኋለኞቹም፡፡(49) Say, [O Prophet], “Indeed, the former and later generations
(50) «በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው፡፡(50) will be gathered on a predetermined Day.
(51) «ከዚያም እናንተ ጠማሞች አስተባባዮች ሆይ!(51) Then you, O misguided deniers,
(52) « ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ፡፡(52) will surely eat from the tree of zaqqūm,
(53) «ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ፡፡(53) filling your bellies with it,
(54) «በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችሁ፡፡(54) and drinking scalding water on top of it,
(55) «የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡»(55) drinking like thirsty camels do.”
(56) ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው፡፡(56) This will be their welcome on the Day of Judgment.
(57) እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን?(57) It is We Who created you; will you not then believe [in resurrection]?
(58) (በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁን?(58) Have you thought about the semen that you emit?
(59) እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን?(59) Is it you who create it, or is it We Who are the Creators?
(60) እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡(60) We have ordained death among you, and nothing can overcome us
(61) ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)፡፡(61) from transforming you and recreating you in forms that you do not know.
(62) የፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡ አትገነዘቡምን?(62) You are well aware of the first creation; why do you not then take heed?
(63) የምትዘሩትንም አያችሁን?(63) Have you thought about what you sow?
(64) እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?(64) Is it you who cause it grow, or is it We Who make it grow?
(65) ብነሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በኾናችሁ ነበር፡፡(65) If We willed, We could reduce your harvest to crumble, leaving you to wonder and lament,
(66) «እኛ በዕዳ ተያዦች ነን፡፡(66) “We suffered loss,
(67) «በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን» (ትሉ ነበር)፡፡(67) rather, we are deprived.”
(68) ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አየችሁን?(68) Have you thought about the water that you drink?
(69) እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?(69) Is it you who bring it down from the clouds, or is it We Who bring it down?
(70) ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን?(70) If We willed, We could make it salty; will you not then give thanks?
(71) ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?(71) Have you thought about the fire that you kindle?
(72) እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን?(72) Is it you who produced its trees, or is it We Who produced it?
(73) እኛ (ለገሀናም) ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት፡፡(73) We made it a reminder [of the Hellfire] and a benefit for the travelers.
(74) የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡(74) So glorify the Name of your Lord, the Most Great.
(75) በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡(75) I do swear by the positions of the stars –
(76) እርሱም ብታወቁ ታላቅ መሓላ ነው፡፡(76) and this is indeed a great oath, if only you knew –
(77) እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡(77) that this is indeed a noble Qur’an,
(78) በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡(78) in a well-preserved Record,
(79) የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡(79) that none can touch except the purified [angels] –
(80) ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡(80) a revelation from the Lord of the worlds.
(81) በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?(81) Do you take this discourse lightly,
(82) ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን?(82) and instead [of thanking Allah] for the provision you are given, you show ingratitude?
(83) (ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡(83) Then why [are you helpless] when the soul reaches the throat,
(84) እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ፡፡(84) while you are looking on,
(85) እኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን፡፡(85) when We are closer to him than you, but you do not see?
(86) የማትዳኙም ከኾናችሁ፡፡(86) If you are not subject to retribution, then why do you not
(87) እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም፡፡(87) bring that [soul] back, if you are truthful?
(88) (ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ፡፡(88) If that dying person is one of those who will be brought near to Allah,
(89) (ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው፡፡(89) then [he will have] comfort, fragrance, and a Garden of Bliss.
(90) ከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡(90) If he is one of the people of the right,
(91) ከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡(91) [He will be told], “Peace be to you, for being one of the people of the right.”
(92) ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡(92) But if he is one of the misguided deniers,
(93) ከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡(93) then he will be welcomed with scalding water,
(94) በገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡(94) and he will burn in Blazing Fire.
(95) ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡(95) This is indeed the absolute truth.
(96) የታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡(96) So glorify the name of your Lord, the Most Great.
Tags: Amharic Quran Free Amharic Quran quran amharic quran in amharic ምዕራፍ 2 ሱረቱ ተባረክ ሱረቱ አል ሐጅ ሱረቱ አል ከህፍ ሱረቱ አትተውባ ሱረቱ ጡር ሱረቱል ሙልክ ሱረቱል በቀራህ ሱረቱል አል ማዒዳህ ሱረቱል አል-በቀራህ ሱረቱል ከህፍ ቁረአን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ትርጉም ቁርአን በአማርኛ ቅዱስ ቁርአን አልበቀራህ አማርኛ ቁርአን አማርኛ ቅዱስ ቁርአን የቁራን ትርጉም

Post navigation

❮ Previous Post: 55 – Ar-Rahmaan
Next Post: 57 – Al-Hadid ❯

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ሁሉም ሱራዎች / All Chapters

  1. ሱረቱ አል-ፋቲሃ – Al-Fātihah
  2. ሱረቱ አል-በቀራህ – Al-Baqarah
  3. ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን – Āl-‘Imrān
  4. ሱረቱ አን-ኒሳዕ – An-Nisā’
  5. ሱረቱ አል-ማኢዳህ – Al-Mā’idah
  6. ሱረቱ አል-አንዓም – Al-An‘ām
  7. ሱረቱ አል-አዕራፍ – Al-A‘rāf
  8. ሱረቱ አል-አንፋል – Al-Anfāl
  9. ሱረቱ አት-ተውባህ – At-Tawbah
  10. ሱረቱ ዩኑስ – Yūnus
  11. ሱረቱ ሁድ – Hūd
  12. ሱረቱ ዩኑስ – Yūsuf
  13. ሱረቱ አር-ረዕድ – Ar-Ra‘d
  14. ሱረቱ ኢብራሂም – Ibrāhīm
  15. ሱረቱ አል ሒጅር – Al-Hijr
  16. ሱረቱ አን–ነሕል – An-Nahl
  17. ሱረቱ አል ኢስራዕ – Al-Isrā’
  18. ሱረቱ አል ከህፍ – Al-Kahf
  19. ሱረቱ መርየም – Maryam
  20. ሱረቱ ጣሃ – Tā-ha
  21. ሱረቱ አል አንቢያ – Al-Anbiyā’
  22. ሱረቱ አል ሐጅ – Al-Hajj
  23. ሱረቱ አል–ሙዕሚኑን – Al-Mu’minūn
  24. ሱረቱ አልን ኑር – An-Noor
  25. ሱረቱ አል ፉርቃን – Al-Furqān
  26. ሱረቱ አሽ ሹዐራእ – Ash-Shu‘arā’
  27. ሱረቱ አን ነምል – An-Naml
  28. ሱረቱ አል ቀሰስ – Al-Qasas
  29. ሱረቱ አል ዐንከቡት – Al-‘Ankabūt
  30. ሱረቱ አር ሩም – Ar-Rūm
  31. ሱረቱ አል ሉቅማን – Luqmān
  32. ሱረቱ አስ ሰጅደህ – As-Sajdah
  33. ሱረቱ አል አሕዛብ – Al-Ahzāb
  34. ሱረቱ ሰበእ – Saba’
  35. ሱረቱ ፋጢር – Fātir
  36. ሱረቱ ያሲን – Yā-Sīn
  37. ሱረቱ አስ ሷፋት – As-Sāffāt
  38. ሱረቱ ሷድ – Sād
  39. ሱረቱ አዝ ዙመር – Az-Zumar
  40. ሱረቱ ጋፊር – Ghāfir
  41. ሱረቱ ፉሲለት – Fussilat
  42. ሱረቱ አሽ ሹራ – Ash-Shūra
  43. ሱረቱ አዝ ዙኽሩፍ – Az-Zukhruf
  44. ሱረቱ አድ ዱኻን – Ad-Dukhān
  45. ሱረቱ አል ጃሲያህ – Al-Jāthiyah
  46. ሱረቱ አል አህቃፍ – Al-Ahqāf
  47. ሱረቱ ሙሐመድ – Muhammad
  48. ሱረቱ አል ፈትህ – Al-Fat’h
  49. ሱረቱ አል ሑጅራት – Al-Hujurāt
  50. ሱረቱ ቃፍ – Qāf
  51. ሱረቱ አዝ ዛሪያት – Adh-Dhāriyāt
  52. ሱረቱ አጥ ጡር – At-Toor
  53. ሱረቱ አን ነጅም – An-Najm
  54. ሱረቱ አል ቀመር – Al-Qamar
  55. ሱረቱ አር ረሕማን – Ar-Rahmān
  56. ሱረቱ አል ዋቂዓህ – Al-Wāqi‘ah
  57. ሱረቱ አል ሐዲድ – Al-Hadīd
  58. ሱረቱ አል ሙጃደላ – Al-Mujādalah
  59. ሱረቱ አል ሐሽር – Al-Hashr
  60. ሱረቱ አል ሙምተሂና – Al-Mumtahanah
  61. ሱረቱ አስ ሶፍ – As-Saff
  62. ሱረቱ አል ጁሙዓህ – Al-Jumu‘ah
  63. ሱረቱ አል ሙናፊቁን – Al-Munāfiqūn
  64. ሱረቱ አት ተጋቡን – At-Taghābun
  65. ሱረቱ አጥ ጠላቅ – At-Talāq
  66. ሱረቱ አት ተህሪም – At-Tahrīm
  67. ሱረቱ አል ሙልክ – Al-Mulk
  68. ሱረቱ አል ቀለም – Al-Qalam
  69. ሱረቱ አል ሓቃህ – Al-Hāqqah
  70. ሱረቱ አል መዓሪጅ – Al-Ma‘ārij
  71. ሱረቱ ኑህ – Nūh
  72. ሱረቱ አል ጂን – Al-Jinn
  73. ሱረቱ አል ሙዘሚል – Al-Muzzammil
  74. ሱረቱ አል ሙደሲር – Al-Muddaththir
  75. ሱረቱ አል ቂያማህ – Al-Qiyāmah
  76. ሱረቱ አል ኢንሳን – Al-Insān
  77. ሱረቱ አል ሙርሰላት – Al-Mursalāt
  78. ሱረቱ አን ነበእ – An-Naba’
  79. ሱረቱ አን ናዚዓት – An-Nāzi‘āt
  80. ሱረቱ ዐበሰ – ‘Abasa
  81. ሱረቱ አት ተክዊር – At-Takwīr
  82. ሱረቱ አል ኢንፊጣር – Al-Infitār
  83. ሱረቱ አል ሙጠፊፊን – Al-Mutaffifīn
  84. ሱረቱ አል ኢንሺቃቅ – Al-Inshiqāq
  85. ሱረቱ አል ቡሩጅ – Al-Burūj
  86. ሱረቱ አጥ ጣሪቅ – At-Tāriq
  87. ሱረቱ አል አዕላ – Al-A‘lā
  88. ሱረቱ አል ጋሺያህ – Al-Ghāshiyah
  89. ሱረቱ አል ፈጅር – Al-Fajr
  90. ሱረቱ አል በለድ – Al-Balad
  91. ሱረቱ አሽ ሸምስ – Ash-Shams
  92. ሱረቱ አል ለይል – Al-Layl
  93. ሱረቱ አድ ዱሓ – Ad-Duhā
  94. ሱረቱ አሽ ሸርህ – Ash-Sharh
  95. ሱረቱ አት ቲን – At-Teen
  96. ሱረቱ አል ዐለቅ – Al-‘Alaq
  97. ሱረቱ አል ቀድር – Al-Qadr
  98. ሱረቱ አል–በይናህ – Al-Bayyinah
  99. ሱረቱ አል ዘልዘላህ – Az-Zalzalah
  100. ሱረቱ አል ዓዲያት – Al-‘Ādiyāt
  101. ሱረቱ አል ቃሪዓሕ – Al-Qāri‘ah
  102. ሱረቱ አት ተካሱር – At-Takāthur
  103. ሱረቱ አል ዓስር – Al-‘Asr
  104. ሱረቱ አል ሁመዛህ – Al-Humazah
  105. ሱረቱ አል ፊል – Al-Feel
  106. ሱረቱ ቁረይሽ – Quraysh
  107. ሱረቱ አል ማዑን – Al-Mā‘ūn
  108. ሱረቱ አል ከውሰር – Al-Kawthar
  109. ሱረቱ አል ካፊሩን – Al-Kāfirūn
  110. ሱረቱ አን ነስር – An-Nasr
  111. ሱረቱ አል መሰድ – Al-Masad
  112. ሱረቱ አል ኢኽላስ – Al-Ikhlās
  113. ሱረቱ አል ፈለቅ – Al-Falaq
  114. ሱረቱ አን ናስ – An-Nās

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ!
ይህ ዌየብሳይት ገና በመበልጸግ ላይ ያለ ስለሆነ ብዙ ስህተቶችን ልታገኙበት ትችላላችሁ። ስለዚህ እባካችሁ የምታገኟቸውን ስህተቶች በኮመንት ላይ እንዲታሳውቁን ስንል በአላህ ስም እንጠይቃለን።

Copyright © 2026 Amharic Quran.

Theme: Oceanly by ScriptsTown