Default Image
10, Dec 2023
25 – Al -Furqan

25 Al -Furqan

(1) ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡(1) Blessed is the One Who has sent down the Criterion to His slave, so that he may be a warner to the worlds,
(2) (እርሱ) ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ የኾነ፣ ልጅንም ያልያዘ፣ በንግሥናውም(2) He to Whom belongs the dominion of the heavens and earth, Who has never begotten a son, and has no partner in His dominion. He has created everything and measured it precisely.
(3) (ከሓዲዎች) ከእርሱም ሌላ ምንንም የማይፈጥሩን፣ እነርሱም የሚፈጠሩን፣ ለነፍሶቻቸውም ጉዳትን ለመከላከል ጥቅምንም ለማምጣት የማይችሉን ሞትንና ሕይወትንም መቀስቀስንም የማይችሉን፣ አማልክት ያዙ፡፡(3) They have taken besides Him other gods who can create nothing but are themselves created. Nor do they have power to harm or benefit themselves, nor do they have power to cause death, give life or resurrect the dead.
(4) እነዚያም የካዱት ይህ (ቁርኣን ሙሐመድ) የቀጠፈው በእርሱም ላይ ሌሎች ሕዝቦች ያገዙት የኾነ ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም አሉ፡፡ በእርግጥም በደልንና እብለትን ሠሩ፡፡(4) Those who disbelieve say, “This [Qur’an] is nothing but a lie which he has fabricated, with the help of other people.” What they claim is totally unjust and false.
(5) አሉም «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናት፡፡ አስጻፋት፡፡ እርሷም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች፡፡»(5) And they say, “Ancient fables which he has written down; they are dictated to him morning and evening.”
(6) «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡(6) Say, “It has been sent down by the One Who knows the secrets of the heavens and earth. He is All-Forgiving, Most Merciful.”
(7) ለዚህም መልክተኛ ምግብን የሚበላ፣ በገበያዎችም የሚኼድ ሲኾን ምን (መልክተኛነት) አለው ከርሱ ጋር አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ወደርሱ መልአክ (ገሃድ) አይወረድም ኖሯልን አሉ፡፡(7) And they say, “What kind of messenger is this who eats food and walks in the markets? If only an angel had been sent down to him to be a warner with him,
(8) «ወይም ወደእርሱ ድልብ አይጣልለትምን ወይም ከእርሷ የሚበላላት አትክልት ለእርሱ አትኖረውምን» (አሉ)፡፡ በዳዮቹም (ላመኑት) «የተደገመበትን ሰው እንጂ ሌላ አትከተሉም» አሉ፡፡(8) or a treasure had been cast down to him, or he had a garden to eat from it.” The wrongdoers say, “You are following none but a bewitched man.”
(9) ላንተ ምሳሌዎችን እንዴት እንዳደረጉልህና እንደተሳሳቱ ተመልከት፡፡ (ወደ እውነት ለመድረስ) መንገድንም አይችሉም፡፡(9) See how they call you names. Thus they have gone astray and cannot find a way.
(10) ያ ቢሻ ከዚህ (ካሉት) የተሻለን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን አትክልቶች ላንተ የሚያደርግልህ ሕንጻ ቤቶችንም ላንተ የሚያደርግልህ ጌታ ችሮታው በዛ፡፡(10) Blessed is He Who, if He wills, could give you better than that: gardens under which rivers flow, and could give you palaces.
(11) ይልቁንም በትንሣኤ አስተባበሉ፡፡ በትንሣኤ ላስተባበለም ሰው ሁሉ ነዳጅን እሳት አዘጋጅተናል፡፡(11) But they deny the Hour, and We have prepared for those who deny the Hour a Blazing Fire.
(12) ከሩቅ ስፍራ ባየቻቸው ጊዜ ለእርሷ የቁጭት መገንፈልንና ማናፋትን ይሰማሉ፡፡(12) When it sees them from a far distance, they will hear its raging and roaring.
(13) እጅ ከፍንጅ የታሠሩ ኾነውም ከእርሷ በጠባብ ስፍራ በተጣሉ ጊዜ በዚያ ስፍራ ጥፋትን ይጠራሉ፤ (ዋ ጥፋታችን ይላሉ)፡፡(13) And when they are thrown into a narrow space therein, chained together, they will cry out for death.
(14) ፡-ዛሬ አንድን ጥፋት ብቻ አትጥሩ ብዙንም ጥፋት ጥሩ (ይባላሉ)፡፡(14) Do not cry out this Day for death only once, but cry out many times.”
(15) (እንዲህ) በላቸው «ይህ የተሻለ ነውን ወይስ ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት የዘለዓለሟ ገነት» ለእነርሱ ምንዳና መመለሻ ኾነች፡፡(15) Say, “Is that better or the Eternal Paradise which has been promised to the righteous?” It will be as a reward for them and as a final destination.
(16) ለእነሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ኾነው የሚፈልጉት ሁሉ አልላቸው፡፡ (ይህም) ተስፋ ከጌታህ ተለማኝ ተስፋ ነው፡፡(16) They will have there whatever they wish for, abiding therein forever. That is a promise that your Lord has taken upon Himself.”
(17) እነርሱንና ከአላህ ሌላ የሚግገዟቸውንም የሚሰበስብባቸውንና «እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን ወይስ እነሱው መንገድን ሳቱ» የሚልበትን ቀን (አስታውስ)፡፡(17) On the Day when He will gather them along with those whom they worshiped besides Allah, He will say, “Did you mislead these slaves of Mine, or did they stray from the right way on their own?”
(18) «ጥራት ይገባህ፤ ካንተ ሌላ ረዳቶችን ልንይዝ ለእኛ ተገቢያችን አልነበረም፡፡ ግን እነርሱንም አባቶቻቸውንም መገንዘብን እስከተዉ ድረስ አጣቀምካቸው፡፡ ጠፊ ሕዝቦችም ኾኑ» ይላሉ፡፡(18) They will say, “Glory be to You! It was not for us to take besides You any guardians. But You provided for them and their forefathers pleasures, until they forgot the message, for they were a ruined people.”
(19) በምትሉትም (አማልክቶቻችሁ) አስዋሹዋችሁ፡፡ ቅጣቴን መገፍተርንም መርዳትንም አትችሉም፡፡ ከእናንተም የሚበድለውን ታላቅን ቅጣት እናቀምሰዋለን፤ (ይባላሉ)፡፡(19) Thus they [the idols] will deny all what you say, so you cannot avert [punishment] nor can you get any help. Whoever among you does wrong, We will make him taste a great punishment.
(20) ከአንተ በፊትም ከመልክተኞች እነሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚኼዱ ኾነው በስተቀር አልላክንም፡፡ ከፊላችሁንም ለከፊሉ ፈተና አድርገናል፡፡ ትታገሳላችሁን ጌታህም ተመልካች ነው፡፡(20) We did not send any messengers before you [O Prophet] except that they ate food and walked in the markets. We have made some of you as a trial for others. Will you have patience? For your Lord is All-Seeing.
(21) እነዚያም መገናኘታችንን የማይፈሩት በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም፡፡ ወይም ጌታችንን ለምን አናይም አሉ፡ በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ፡፡ ታላቅንም አመጽ አመፁ፡፡(21) Those who do not expect to meet Us say, “Why are angels not sent down to us or why do we not see our Lord?” They have been too proud of themselves, and have transgressed immensely.
(22) መላእክትን በሚያዩበት ቀን በዚያ ጊዜ ለአመጸኞች ምስራች የላቸውም፡፡ «የተከለከለ ክልክልም አድርገን» ይላሉ፡፡(22) On the Day when they see the angels, there will be no glad tidings for the wicked, and [the angels] will say, “Absolutely forbidden for you.”
(23) ከሥራም ወደ ሠሩት እናስባለን፡፡ የተበተነ ትቢያም እናደርገዋለን፡፡(23) We will turn to whatever deeds they did and turn them into scattered dust.
(24) የገነት ሰዎች በዚያ ቀን በመርጊያ የተሻሉ በማረፊያም በጣም ያማሩ ናቸው፡፡(24) On that Day the people of Paradise will have the best abode and the finest resting place.
(25) ሰማይም በደመና የምትቀደድበትንና መላእክትም መወረድን የሚወርድበትን ቀን (አስታውስ)፡፡(25) On the Day when the sky will split asunder with clouds, and the angels will be sent down in succession.
(26) እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአልራሕማን ብቻ ነው፡፡ በከሓዲዎችም ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡(26) The true dominion on that Day belongs to the Most Compassionate, and it will be a hard day for the disbelievers.
(27) በዳይም «ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ!» እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)፡፡(27) On that Day, the wrongdoer will bite his hands saying, “Would that I had taken a way with the Messenger!
(28) «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡፡(28) Woe to me! Would that I had not taken so-and-so as a close friend!
(29) (የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ» (ይላል)፡፡ ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነው፡፡(29) He led me astray from the Reminder after it had come to me.” Satan always betrays man.
(30) መልክተኛውም «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት» አለ፡፡(30) The Messenger said, “O my Lord, my people have taken this Qur’an as a thing to be abandoned.”
(31) እንደዚሁም ለነቢዩ ሁሉ ከአመጸኞች የኾነ ጠላትን አድርገናል፡፡ መሪና ረዳትም በጌታህ በቃ፡፡(31) Thus did we assign for every prophet an enemy from among the wicked, but your Lord is sufficient as a Guide and Helper.
(32) እነዚያ የካዱትም «ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም» አሉ፡፡ እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ (ከፋፍለን አወረድነው)፡፡ ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው፡፡(32) Those who disbelieve say, “Why was the Qur’an not sent down to him all at once?” [We sent it] in this way so that We may strengthen your heart thereby, and We have revealed it in a gradual manner.
(33) በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን (መልስ) መልካምን ፍችም የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ፡፡(33) Whenever they bring you an argument, We bring you the truth and the best explanation.
(34) እነዚያ በፊቶቻቸው ለይ (እየተጎተቱ) ወደ ገሀነም የሚሰበሰቡ ናቸው፡፡ እነዚያ ስፍራቸው የከፋ መንገዳቸውም የጠመመ ናቸው፡፡(34) Those who will be dragged on their faces to Hell – they will be in the worst position and farthest astray from the right path.
(35) በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት፡፡(35) We gave Moses the Scripture and appointed with him his brother Aaron as a helper.
(36) «ወደእነዚያም በተዓምራቶቻችን ወደ አስተባበሉት ሕዝቦች ኺዱ» አልናቸው፡፡ (አስዋሿቸውም) ማጥፋትንም አጠፋናቸው፡፡(36) We said, “Go, both of you, to the people who have rejected Our signs.” Then We destroyed them utterly.
(37) የኑሕን ሰዎችም መልክተኞችን ባስተባበሉ ጊዜ አሰጠምናቸው፡፡ ለሰዎችም መገሰጫ አደረግናለቸው፡፡ ለበደለኞችም አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል፡፡(37) Also the people of Noah, when they rejected the messengers, We drowned them and made them an example for mankind. And We have prepared for the wrongdoers a painful punishment.
(38) ዓድንም ሰሙድንም የረስን ሰዎችም በዚህ መካከል የነበሩትንም ብዙን የክፍለ ዘመናት ሕዝቦች (አጠፋን)፡፡(38) Also [We destroyed] ‘Ād and Thamūd, and the people of the Well, and many generations between them.
(39) ሁሉንም (ገሠጽን) ለእነሱ ምሳሌዎችን ገለጽን፡፡ ሁሉንም ማጥፋትን አጠፋናቸውም፡፡(39) To each We gave examples [of the previous nations], and each We destroyed completely.
(40) በዚያችም ክፉ ዝናምን በተዘነመችው ከተማ ላይ (የመካ ከሐዲዎች) በእርግጥ መጥተዋል፡፡ የሚያዩዋት አልነበሩምን በእውነቱ መቀስቀስን የማይፈሩ ነበሩ፡፡(40) They have surely passed by the town that was destroyed by a terrible rain [of stones]. Have they not seen it? But they do not expect to be resurrected.
(41) ባዩህም ጊዜ ያ አላህ መልእክተኛ አድርጎ የላከው ይህ ነውን እያሉ መሳለቂያ እንጂ ሌላ አያደርጉህም፡፡(41) When they see you [O Prophet], they only ridicule you, “Is this the one whom Allah has sent as a messenger?
(42) «እነሆ በእርሷ ላይ መታገሳችን ባልነበረ ኖሮ ከአማልክቶቻችን ሊያሳስተን ቀርቦ ነበር» (ሲሉም ይሳለቃሉ)፡፡ ወደፊትም ቅጣቱን በሚያዩ ጊዜ መንገድን በጣም ተሰሳቹ ማን እንደኾነ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡(42) He would have almost led us astray from our gods, if we had not been so devoted to them.” But when they see the punishment, they will come to know who is further astray from the right way.
(43) ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን(43) Have you [O Prophet] seen the one who takes his desire as his god, will you then be a keeper over him?
(44) ይልቁንም አብዛኛዎቻቸው የሚሰሙ ወይም የሚያውቁ መኾናቸውን ታስባለህን እነርሱ እንደ እንስሳዎች እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡ ከቶውንም እነሱ ይልቅ መንገድን የተሳሳቱ ናቸው፡፡(44) Do you think that most of them hear or understand? They are just like livestock, rather they are further astray from the right way.
(45) ወደ ጌታህ (ሥራ) ጥላን እንዴት እንደ ዘረጋ አላየህምን በሻም ኖሮ የረጋ ባደረገው ነበር፡፡ ከዚያም ፀሐይን በእርሱ ላይ ምልክት አደረግን፡፡(45) Do you not see how your Lord extends the shade? If He had willed, He could have made it still. Then We made the sun an indication for it.
(46) ከዚያም ቀስ በቀስ ወደእኛ ሰብሰብነው፡፡(46) Then We gradually draw it towards Us [as the sun climbs up]?
(47) እርሱም ያ ለእናንተ ሌሊትን ልብስ እንቅልፍንም ማረፊያ ያደረገ፤ ቀንንም መበተኛ ያደረገላችሁ ነው፡፡(47) It is He Who has made the night as a garment for you, and made sleep for rest; and has made daytime for returning to life.
(48) እርሱም ያ ነፋሶችን አብሳሪዎች ሲኾኑ ከዝናሙ በስተፊት የላከ ነው፡፡ ከሰማይም አጥሪ ውሃን አወረድን፡፡(48) It is He Who sends the winds as harbingers before His mercy, and We send down from the sky pure water,
(49) በእርሱ የሞተችን አገር ሕያው ልናደርግበት ከፈጠርነውም ፍጡር እንስሳዎችንና ብዙ ሰዎችንም ልናጠጣው (አወረድነው)፡፡(49) so that We may revive therewith a dead land, and quench the thirst of countless beasts and humans We have created.
(50) (ጸጋችንን) ይገነዘቡም ዘንድ በመካከላቸው ከፋፈልነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ክህደትን እንጂ እንቢ አሉ፡፡(50) We distribute it among them so that they may take heed, but most people persist in their ingratitude.
(51) በሻንም ኖሮ በየከተማይቱ አስፈራሪን በላክን ነበር፡፡(51) If We had willed, We could have sent to each town a warner.
(52) ከሓዲዎችንም አትታዘዛቸው፡፡ በእርሱም (በቁርኣን) ታላቅን ትግል ታገላቸው፡፡(52) So do not obey the disbelievers, but strive against them with this [Qur’an] a great striving.
(53) እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች አጎራብቶ የለቀቀ ነው፡፡ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፡፡ ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፡፡ በመካከላቸውም (ከመቀላቀል) መለያንና የተከለለን ክልል ያደረገ ነው፡፡(53) It is He Who merges the two bodies of water: one fresh and palatable and the other salty and bitter, and He has made between them a barrier and an insurmountable partition.
(54) እርሱም ያ ከውሃ ሰውን የፈጠረ፣ የዝምድናና የአማችም ባለቤት ያደረገው ነው፡፡ ጌታህም ቻይ ነው፡፡(54) It is He Who created human beings from water, then made between them bonds of kinship and marriage, for your Lord is Most Capable.
(55) ከአላህም ሌላ የማይጠቅማቸውንና የማይጎዳቸውን ይግገዛሉ፤ ከሓዲም በጌታው ላይ (በማመጽ ለሰይጣን) ረዳት ነው፡፡(55) Yet they worship besides Allah that which can neither benefit nor harm them; the disbeliever always collaborates against his Lord.
(56) አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን እንጂ አልላክንህም፡፡(56) We have not sent you [O Prophet] except as a bearer of glad tidings and a warner.
(57) «በእርሱ ላይ ዋጋን በፍጹም አልጠይቃችሁም፡፡ ግን ወደ ጌታው (መልካም) መንገድን ለመያዝ የሻ ሰው (ይሥራ)» በላቸው፡፡(57) Say, “I do not ask you for any reward for it, except that anyone who wishes to take a path to his Lord.”
(58) በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡(58) Put your trust in the Ever-Living Who never dies, and glorify Him with praise. He is Sufficient as All-Aware of the sins of His slaves –
(59) ያ ሰማያትና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ፣ ከዚያም በዐርሹ ላይ (ለሱ ክብር በምስማማ መልኩ) የተደላደለ አልረሕማን ነው፡፡ ከእርሱም ዐዋቂን ጠይቅ፡፡(59) it is He Who created the heavens and earth and all that is between them in six Days, then rose over the Throne. He is the Most Compassionate, so ask about Him the One Who is All-Aware.
(60) ለእነርሱም ለአልረሕማን ስገዱ በተባሉ ጊዜ አልረሕማን ማነው ለምታዘን (እና ለማናውቀው) እንሰግዳለን ይላሉ፡፡ (ይህ) መራቅንም ጨመራቸው፡፡(60) When it is said to them, “Prostrate to the Most Compassionate,” they say, “What is ‘the Most Compassionate?’ Shall we prostrate to what you order us?” And it only increases them in aversion.
(61) ያ በሰማይ ቡሩጆችን ያደረገና በእርሷም አንጸባራቂን (ፀሐይ) አብሪ ጨረቃንም ያደረገ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ፡፡(61) Blessed is He Who placed in the sky constellations, and placed therein a radiant lamp and a luminous moon.
(62) እርሱም ያ (ያመለጠውን ሥራ) ማስታወስን ለሚፈልግ ወይም ማመስገንን ለሚፈልግ ሰው ሌሊትንና ቀንን ተተካኪ ያደረገ ነው፡፡(62) It is He Who made the night and the day to follow each other so that everyone who wishes may reflect or become grateful.
(63) የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡(63) The slaves of the Most Compassionate are those who walk on earth humbly, and when the ignorant address them, they only say words of peace;
(64) እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው፡፡(64) and those who spend the night prostrating and standing before their Lord;
(65) እነዚያም «ጌታችን ሆይ! የገሀነምን ቅጣት ከእኛ ላይ መልስልን ቅጣቷ የማይለቅ ነውና» የሚሉት ናቸው፡፡(65) and those who say, “Our Lord, turn the punishment of Hell away from us, for its punishment is unrelenting.”
(66) እርሷ መርጊያና መቀመጫ በመኾን ከፋች! (ይላሉ)፡፡(66) It is an evil place to settle and an evil abode.”
(67) እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑ የማይቆጥቡትም ናቸው፡፡ በዚህም መካከል (ልግስናቸው) ትክክለኛ የኾነ ነው፡፡(67) And those who neither spend wastefully nor stingily, but are moderate between them;
(68) እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል፡፡(68) and those who do not invoke besides Allah another god, and who do not kill a soul whom Allah has forbidden, except in the course of justice, and who do not commit adultery, for whoever does any of this will face the penalty,
(69) በትንሣኤ ቀን ቅጣቱ ለእርሱ ይደራረባል፡፡ በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ኾኖ ይኖራል፡፡(69) the punishment will be doubled for him on the Day of Resurrection, wherein he will remain disgraced forever,
(70) ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡(70) except those who repent and believe, and do righteous deeds; for them Allah will change their evil deeds into good deeds, for Allah is All-Forgiving, Most Merciful.
(71) ተጸጽቶ የተመለሰም ሰው መልካምንም የሠራ እርሱ የተወደደን መመለስ ወደ አላህ ይመለሳል፡፡(71) Whoever repents and does righteous deeds has turned to Allah with sincere repentance.
(72) እነዚያም እብለትን የማይመሰክሩ፤ በውድቅ ቃልም (ተናጋሪ አጠገብ) ባለፉ ጊዜ የከበሩ ኾነው የሚያልፉት ናቸው፡፡(72) And those who do not witness falsehood, and when they pass by futility, they pass by with dignity;
(73) እነዚያም በጌታቸው አንቀጾች በተገሰጹ ጊዜ (የተረዱ ተቀባዮች ኾነው እንጂ) ደንቆሮዎችና ዕውሮች ኾነው በእርሷ ላይ የማይደፉት ናቸው፡፡(73) and those who, when they are reminded with the verses of their Lord, they do not turn a deaf ear or a blind eye to them;
(74) እነዚያም «ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያን ለእኛ ስጠን፡፡ አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን» የሚሉት ናቸው፡፡(74) and those who say, “Our Lord, let our spouses and children be a source of joy for us, and make us good examples for the righteous.”
(75) እነዚያ በመታገሳቸው የገነትን ሰገነቶች ይምመነዳሉ፡፡ በእርሷም ውስጥ ውዳሴንና ሰላምታን ይስሰጣሉ፡፡(75) It is they who will be rewarded with high palaces [in Paradise] for their perseverance, and they will be received therein with salutations and greetings of peace,
(76) በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ኾነው (ይስሰጣሉ)፡፡ መርጊያና መኖሪያይቱ አማረች፡፡(76) abiding therein forever. What an excellent abode and a resting place!
(77) «ጸሎታችሁ ባልነበረ ኖሮ ጌታዬ እናንተን ከምንም አይቆጥራችሁም ነበር፡፡ በእርግጥም አስተባበላችሁ፤ ወደ ፊትም (ቅጣቱ) ያዣችሁ ይኾናል» በላቸው፡፡(77) Say [O Prophet], “My Lord would not care at all about you, were it not for your supplication. Now since you have rejected [the truth], the inevitable is bound to come.”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

23 – Al-Muminoon

23 – Al-Muminoon (1) ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡ (1) The believers have attained true success: (2) እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው…

106 – Quraish

106 – Quraish (1) ቁረይሽን ለማላመድ (ባለዝሆኖቹን አጠፋ)፡፡ (1) For the accustomed security of the Quraysh, (2) የብርድና የበጋን ወራት ጉዞ…

51 – Adh-Dhaariyat

51 – Adh-Dhaariyat (1) መበተንን በታኞች በኾኑት (ነፋሶች)፡፡ (1) By the winds that scatters [dust], (2) ከባድ (ዝናምን) ተሸካሚዎች በኾኑትም (ደመናዎች)፡፡ (2) and by the…