Skip to content

Amharic Quran

ከመሞትህ በፊት ቁርአንን አንብብ! (Read the holy Quran before you die!)

  • Home
    • ቁርአንን እንረዳው
    • Download
  • ሱራዎች / Surah List
    • አል-ፋቲሐ (Al-Fatiha)
    • አል-በቀራህ (Al-Beqerah)
    • አል-ዒምራን (Al-Imran)
    • አል-ኒሳዕ (An-Nisa)
    • አል-ማዒዳህ (Al-Maidah) 
    • አንዓም (Al-anam)
    • አል አዕራፍ (Al-Aeraf)
    • አል አንፋል (Al-Anfal)
    • አል ተውባ (At-Tawba)
    • አል ዩኑስ (Yunus)
    • አል ሁድ (Al-Hud)
    • ዩሱፍ (Yusuf)
    • 13 – Ar-Ra’d
    • 14 – Ibrahim
    • አል ሒጅር (Al-Hijr)
    • 16 – An-Nahl
    • 17 – Al-Israa
    • ከህፍ (Al-Kahf )
    • 19 Maryam
    • ጧሃ (Taa-Ha)
    • 21 – Al-Anbiyaa
    • አል ሐጅ (Al-Hajj)
    • 23 – Al-Muminoon
    • 24 – An-Noor
    • 25 – Al -Furqan
    • 26 – Ash-Shu’araa
    • 27 – An-Naml
    • 28 – Al-Qasas
    • 29 – Al-Ankaboot
    • 30 – Ar-Room
    • 31 – Luqman
    • 32 – As-Sajda
    • 33 – Al-Ahzaab
    • 34 – Saba
    • 35 – Faatir
    • 36 – Yaseen
    • 37 – As-Saaffaat
    • 38 – Saad
    • 39 – Az-Zumar
    • 40 – Al-Ghaafir
    • 41 – Fussilat
    • 42 – Ash-Shura
    • 43 – Az-Zukhruf
    • 44 – Ad-Dukhaan
    • 45 – Al-Jaathiya
    • 46 – Al-Ahqaf
    • 47 – Muhammad
    • 48 – Al-Fath
    • 49 – Al-Hujuraat
    • 50 – Qaaf
    • 51 – Adh-Dhaariyat
    • 52 – At-Tur
    • 53 – An-Najm
    • 54 – Al-Qamar
    • 55 – Ar-Rahmaan
    • 56 – Al-Waaqia
    • 57 – Al-Hadid
    • 58 – Al-Mujaadila
    • 59 – Al-Hashr
    • 60 – Al-Mumtahana
    • 61 – As-Saff
    • 62 – Al-Jumu’a
    • 63 – Al-Munaafiqoon
    • 64 – At-Taghaabun
    • 65 – At-Talaaq
    • 66 – At-Tahrim
    • 67 – Al-Mulk
    • 68 – Al-Qalam
    • 69 – Al-Haaqqa
    • 70 – Al-Ma’aarij
    • 71 – Nooh
    • 72 – Al-Jinn
    • 73 – Al-Muzzammil
    • 74 – Al-Muddaththir
    • 75 – Al-Qiyaama
    • 76 – Al-Insaan
    • 77 – Al-Mursalaat
    • 78 – An-Naba
    • 79 – An-Naazi’aat
    • 80 – Abasa
    • 81 – At-Takwir
    • 82 – Al-Infitaar
    • 83 – Al-Mutaffifin
    • 84 – Al-Inshiqaaq
    • 85 – Al-Burooj
    • 86 – At-Taariq
    • 87 – Al-A’laa
    • 88 – Al-Ghaashiya
    • 89 – Al-Fajr
    • 90 – Al-Balad
    • 91 – Ash-Shams
    • 92 – Al-Lail
    • 93 – Ad-Dhuhaa
    • 94 – Ash-Sharh
    • 95 – At-Tin
    • 96 – Al-Alaq
    • 97 – Al-Qadr
    • 98 – Al-Bayyina
    • 99 – Az-Zalzala
    • 100 – Al-Aadiyaat
    • 101 – Al-Qaari’a
    • 102 – At-Takaathur
    • 103 – Al-Asr
    • 104 – Al-Humaza
    • 105 – Al-Fil
    • 106 – Quraish
    • 107 – Al-Maa’un
    • 108 – Al-Kawthar
    • 109 – Al-Kaafiroon
    • 110 – An-Nasr
    • 111 – Al-Masad
    • 112 – Al-Ikhlaas
    • 113 – Al-Falaq
    • 114 – An-Naas

44 – Ad-Dukhaan

Posted on December 10, 2023August 5, 2026 By Muhammed No Comments on 44 – Ad-Dukhaan
Amharic Quran, ቁርአንን እንረዳው

44 – Ad-Dukhaan

(1) ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡(1) Hā Mīm.
(2) አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡(2) By the clear Book.
(3) እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡(3) Indeed, We sent it down on a blessed night, We have been warning about.
(4) በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡(4) On that night, every matter of wisdom is determined
(5) ከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡(5) by Our command. We have always sent messengers.
(6) ከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡(6) as a mercy from your Lord. He is indeed the All-Hearing, the All-Knowing,
(7) የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡(7) Lord of the heavens and earth and all that is between them, if only you had sure faith.
(8) ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው፡፡(8) None has the right to be worshiped except Him, Who gives life and causes death – your Lord, and the Lord of your forefathers.
(9) በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲኾኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡(9) But they are in doubt, amusing themselves.
(10) ሰማይም በግልጽ ጭስ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡(10) So wait for a day when the sky will bring forth a visible smoke,
(11) ሰዎችን የሚሸፍን (በኾነ ጭስ) ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው፡፡(11) that will overwhelm the people. This is a painful punishment!
(12) «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን፡፡ እኛ አማኞች እንኾናለንና» (ይላሉም)፡፡(12) [They will cry,] “Our Lord, remove the punishment from us; we will surely believe!”
(13) (ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መግገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል? አስረጅ መልክተኛ የመጣቸው ሲኾን (የካዱም ሲኾኑ)፡፡(13) How will they take heed, when a messenger who explained things clearly has already come to them?
(14) ከዚያም ከእርሱ የዞሩ፤ (ከሰው) «የተሰተማረ ዕብድ ነው» ያሉም ሲኾኑ፡፡(14) Then they turned away from him and said, “[He is] a madman, taught by others.”
(15) እኛ ቅጣቱን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን፡፡ እናንተ (ወደ ክህደታችሁ) በእርግጥ ተመላሾች ናችሁ፡፡(15) We shall hold the punishment back for a while, but you will surely return [to disbelief].
(16) ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን፤ እኛ ተበቃዮች ነን፡፡(16) On the Day when We seize [them] with the greatest assault, We will surely exact retribution.
(17) ከእነርሱም በፊት የፈርዖንን ሕዝቦች በእርግጥ ሞከርን፡፡ ክቡር መልእክተኛም መጣላቸው፡፡(17) Indeed, We tested the people of Pharaoh before them, when a noble messenger came to them,
(18) «የአላህን ባሮች ወደኔ አድርሱ፡፡ እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝና፡፡(18) [saying], “Hand over to me the slaves of Allah. I am indeed a trustworthy messenger to you,
(19) «በአላህም ላይ አትኩሩ፡፡ እኔ ግልጽ የኾነን አስረጅ ያመጣሁላችሁ ነኝና (በማለት መጣላቸው)፡፡(19) and do not be arrogant towards Allah. I have certainly come to you with a clear proof.
(20) «እኔም እንዳትወግሩኝ በጌታየና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ፡፡(20) And I certainly seek refuge with my Lord and your Lord, lest you stone me to death.
(21) «በእኔም ባታምኑ ራቁኝ» (ተዉኝ አለ)፡፡(21) If you do not believe me, then leave me alone.”
(22) ቀጥሎም (ስለ ዛቱበት) «እነዚህ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸው» (አጥፋቸው) ሲል ጌታውን ለመነ፡፡(22) Then he called upon his Lord, “These are a wicked people”.
(23) (ጌታው) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና፡፡(23) [Allah said], “Leave along with My slaves by night; you will surely be pursued.
(24) «ባሕሩንም የተከፈተ ኾኖ ተወው፡፡ እነርሱ የሚሰጥጠሙ ሰራዊት ናቸውና» (አለው)፡፡(24) And leave the sea parted; for they are surely an army destined to drown.”
(25) ከአትክልቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ፡፡(25) [Imagine] how many gardens and springs they left behind,
(26) ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም፡፡(26) and crops and splendid mansions,
(27) በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ተዉ)፡፡(27) and luxuries they used to rejoice therein.
(28) (ነገሩ) እንደዚሁ ኾነ፡፡ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት፡፡(28) So it was; and We made another people inherit all that.
(29) ሰማይና ምድርም በእነርሱ ላይ አላለቀሱም፡፡ የሚቆዩም አልነበሩም፡፡(29) Neither the heaven nor earth wept for them, nor were they given any respite.
(30) የእስራኤልንም ልጆች አዋራጅ ከኾነ ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው፡፡(30) Thus did We save the Children of Israel from the humiliating punishment,
(31) ከፈርዖን፤ እርሱ የኮራ ከወሰን አላፊዎቹ ነበርና፡፡(31) from Pharaoh. He was indeed arrogant who transgressed all bounds.
(32) ከማወቅም ጋር በዓለማት ላይ በእርግጥ መረጥናቸው፡፡(32) We chose them with knowledge above all others.
(33) ከታምራቶችም በውስጡ ግልጽ የኾነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው፡፡(33) And We gave them signs in which there was a clear test.
(34) እነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በእርግጥ ይላሉ፡-(34) Indeed, these [Makkans] say,
(35) እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ አይደለችም፡፡ እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም፡፡(35) “There is nothing after our first death, and we will not be resurrected,
(36) እውነተኞችም እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡልን፡፡(36) then bring back our forefathers if you are truthful.”
(37) እነርሱ በላጮች ናቸውን ወይስ የቱብበዕ ሕዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? አጠፋናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ነበሩና፡፡(37) Are they better [in power] or the people of Tubba‘ and those who were before them? We destroyed them, for they were truly wicked.
(38) ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም፡፡(38) We have not created the heavens and earth and all that is between them for amusement.
(39) ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡(39) We have not created them except for a true purpose, but most of them do not know.
(40) የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡(40) Indeed, the Day of Judgment is the time appointed for them all,
(41) ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይርረዱበት ቀን ነው፡፡(41) the Day when no friend will avail another in the least, nor will they be helped,
(42) አላህ ያዘነለት ሰውና ያመነ ብቻ ሲቀር፡፡ (እርሱስ ይርረዳል)፡፡ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና፡፡(42) except those to whom Allah shows mercy. He is indeed the All-Mighty, the Most Merciful.
(43) የዘቁመ ዛፍ(43) Indeed, the tree of Zaqqūm
(44) የኀጢኣተኛው ምግብ ነው፡፡(44) will be the food of the sinful,
(45) እንደ ዘይት አተላ ነው፡፡ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲኾን፡፡(45) like molten metal that will boil in their bellies
(46) እንደ ገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲኾን)፡፡(46) like the boiling of scalding water.
(47) ያዙት፤ ወደ ገሀነም መካከልም በኀይል ጎትቱት፡፡(47) [It will be said], “Seize him and drag him into the midst of the Blazing Fire.
(48) ከዚያም «ከራሱ በላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት፡፡»(48) Then pour over his head the torment of scalding water.”
(49) «ቅመስ፤ አንተ አሸናፊው ክብሩ ነህና» (ይባላል)፡፡(49) “Taste this. You are surely the mighty and honorable!
(50) «ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡(50) This is what you [all] used to doubt.”
(51) ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡(51) Indeed, the righteous will be in a safe place,
(52) በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡(52) in gardens and springs,
(53) ፊት ለፊት የተቅጣጩ ኾነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ፡፡(53) wearing fine silk and heavy brocade, facing one another.
(54) (ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናማዎች የኾኑን ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡(54) So it will be, and We will marry them to maidens with gorgeous eyes.
(55) በእርሷም ውስጥ የተማመኑ ኾነው፤ ከፍራፍሬ ሁሉ ያዝዛሉ፡፡(55) They will call therein for every kind of fruit, safe and secure.
(56) የፊተኛይቱን ሞት እንጅ (ዳግመኛ) በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም፡፡ የገሀነምንም ቅጣት (አላህ) ጠበቃቸው፡፡(56) They will not taste death therein except the first death, and He will protect them from the punishment of the Blazing Fire,
(57) ከጌታህ በኾነ ችሮታ (ጠበቃቸው)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡(57) as a grace from your Lord. That is the supreme triumph.
(58) (ቁርኣኑን) በቋንቋህም ያገራነው (ሕዝቦችህ) ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው፡፡(58) We have made this [Qur’an] easy in your own language, so that they may take heed.
(59) ተጠባበቅም እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና፡፡(59) Then wait; they too are waiting.
Tags: Amharic Quran Free Amharic Quran quran amharic quran in amharic ምዕራፍ 2 ሱረቱ ተባረክ ሱረቱ አል ሐጅ ሱረቱ አል ከህፍ ሱረቱ አትተውባ ሱረቱ ጡር ሱረቱል ሙልክ ሱረቱል በቀራህ ሱረቱል አል ማዒዳህ ሱረቱል አል-በቀራህ ሱረቱል ከህፍ ቁረአን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ትርጉም ቁርአን በአማርኛ ቅዱስ ቁርአን አልበቀራህ አማርኛ ቁርአን አማርኛ ቅዱስ ቁርአን የቁራን ትርጉም

Post navigation

❮ Previous Post: 43 – Az-Zukhruf
Next Post: 45 – Al-Jaathiya ❯

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ሁሉም ሱራዎች / All Chapters

  1. ሱረቱ አል-ፋቲሃ – Al-Fātihah
  2. ሱረቱ አል-በቀራህ – Al-Baqarah
  3. ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን – Āl-‘Imrān
  4. ሱረቱ አን-ኒሳዕ – An-Nisā’
  5. ሱረቱ አል-ማኢዳህ – Al-Mā’idah
  6. ሱረቱ አል-አንዓም – Al-An‘ām
  7. ሱረቱ አል-አዕራፍ – Al-A‘rāf
  8. ሱረቱ አል-አንፋል – Al-Anfāl
  9. ሱረቱ አት-ተውባህ – At-Tawbah
  10. ሱረቱ ዩኑስ – Yūnus
  11. ሱረቱ ሁድ – Hūd
  12. ሱረቱ ዩኑስ – Yūsuf
  13. ሱረቱ አር-ረዕድ – Ar-Ra‘d
  14. ሱረቱ ኢብራሂም – Ibrāhīm
  15. ሱረቱ አል ሒጅር – Al-Hijr
  16. ሱረቱ አን–ነሕል – An-Nahl
  17. ሱረቱ አል ኢስራዕ – Al-Isrā’
  18. ሱረቱ አል ከህፍ – Al-Kahf
  19. ሱረቱ መርየም – Maryam
  20. ሱረቱ ጣሃ – Tā-ha
  21. ሱረቱ አል አንቢያ – Al-Anbiyā’
  22. ሱረቱ አል ሐጅ – Al-Hajj
  23. ሱረቱ አል–ሙዕሚኑን – Al-Mu’minūn
  24. ሱረቱ አልን ኑር – An-Noor
  25. ሱረቱ አል ፉርቃን – Al-Furqān
  26. ሱረቱ አሽ ሹዐራእ – Ash-Shu‘arā’
  27. ሱረቱ አን ነምል – An-Naml
  28. ሱረቱ አል ቀሰስ – Al-Qasas
  29. ሱረቱ አል ዐንከቡት – Al-‘Ankabūt
  30. ሱረቱ አር ሩም – Ar-Rūm
  31. ሱረቱ አል ሉቅማን – Luqmān
  32. ሱረቱ አስ ሰጅደህ – As-Sajdah
  33. ሱረቱ አል አሕዛብ – Al-Ahzāb
  34. ሱረቱ ሰበእ – Saba’
  35. ሱረቱ ፋጢር – Fātir
  36. ሱረቱ ያሲን – Yā-Sīn
  37. ሱረቱ አስ ሷፋት – As-Sāffāt
  38. ሱረቱ ሷድ – Sād
  39. ሱረቱ አዝ ዙመር – Az-Zumar
  40. ሱረቱ ጋፊር – Ghāfir
  41. ሱረቱ ፉሲለት – Fussilat
  42. ሱረቱ አሽ ሹራ – Ash-Shūra
  43. ሱረቱ አዝ ዙኽሩፍ – Az-Zukhruf
  44. ሱረቱ አድ ዱኻን – Ad-Dukhān
  45. ሱረቱ አል ጃሲያህ – Al-Jāthiyah
  46. ሱረቱ አል አህቃፍ – Al-Ahqāf
  47. ሱረቱ ሙሐመድ – Muhammad
  48. ሱረቱ አል ፈትህ – Al-Fat’h
  49. ሱረቱ አል ሑጅራት – Al-Hujurāt
  50. ሱረቱ ቃፍ – Qāf
  51. ሱረቱ አዝ ዛሪያት – Adh-Dhāriyāt
  52. ሱረቱ አጥ ጡር – At-Toor
  53. ሱረቱ አን ነጅም – An-Najm
  54. ሱረቱ አል ቀመር – Al-Qamar
  55. ሱረቱ አር ረሕማን – Ar-Rahmān
  56. ሱረቱ አል ዋቂዓህ – Al-Wāqi‘ah
  57. ሱረቱ አል ሐዲድ – Al-Hadīd
  58. ሱረቱ አል ሙጃደላ – Al-Mujādalah
  59. ሱረቱ አል ሐሽር – Al-Hashr
  60. ሱረቱ አል ሙምተሂና – Al-Mumtahanah
  61. ሱረቱ አስ ሶፍ – As-Saff
  62. ሱረቱ አል ጁሙዓህ – Al-Jumu‘ah
  63. ሱረቱ አል ሙናፊቁን – Al-Munāfiqūn
  64. ሱረቱ አት ተጋቡን – At-Taghābun
  65. ሱረቱ አጥ ጠላቅ – At-Talāq
  66. ሱረቱ አት ተህሪም – At-Tahrīm
  67. ሱረቱ አል ሙልክ – Al-Mulk
  68. ሱረቱ አል ቀለም – Al-Qalam
  69. ሱረቱ አል ሓቃህ – Al-Hāqqah
  70. ሱረቱ አል መዓሪጅ – Al-Ma‘ārij
  71. ሱረቱ ኑህ – Nūh
  72. ሱረቱ አል ጂን – Al-Jinn
  73. ሱረቱ አል ሙዘሚል – Al-Muzzammil
  74. ሱረቱ አል ሙደሲር – Al-Muddaththir
  75. ሱረቱ አል ቂያማህ – Al-Qiyāmah
  76. ሱረቱ አል ኢንሳን – Al-Insān
  77. ሱረቱ አል ሙርሰላት – Al-Mursalāt
  78. ሱረቱ አን ነበእ – An-Naba’
  79. ሱረቱ አን ናዚዓት – An-Nāzi‘āt
  80. ሱረቱ ዐበሰ – ‘Abasa
  81. ሱረቱ አት ተክዊር – At-Takwīr
  82. ሱረቱ አል ኢንፊጣር – Al-Infitār
  83. ሱረቱ አል ሙጠፊፊን – Al-Mutaffifīn
  84. ሱረቱ አል ኢንሺቃቅ – Al-Inshiqāq
  85. ሱረቱ አል ቡሩጅ – Al-Burūj
  86. ሱረቱ አጥ ጣሪቅ – At-Tāriq
  87. ሱረቱ አል አዕላ – Al-A‘lā
  88. ሱረቱ አል ጋሺያህ – Al-Ghāshiyah
  89. ሱረቱ አል ፈጅር – Al-Fajr
  90. ሱረቱ አል በለድ – Al-Balad
  91. ሱረቱ አሽ ሸምስ – Ash-Shams
  92. ሱረቱ አል ለይል – Al-Layl
  93. ሱረቱ አድ ዱሓ – Ad-Duhā
  94. ሱረቱ አሽ ሸርህ – Ash-Sharh
  95. ሱረቱ አት ቲን – At-Teen
  96. ሱረቱ አል ዐለቅ – Al-‘Alaq
  97. ሱረቱ አል ቀድር – Al-Qadr
  98. ሱረቱ አል–በይናህ – Al-Bayyinah
  99. ሱረቱ አል ዘልዘላህ – Az-Zalzalah
  100. ሱረቱ አል ዓዲያት – Al-‘Ādiyāt
  101. ሱረቱ አል ቃሪዓሕ – Al-Qāri‘ah
  102. ሱረቱ አት ተካሱር – At-Takāthur
  103. ሱረቱ አል ዓስር – Al-‘Asr
  104. ሱረቱ አል ሁመዛህ – Al-Humazah
  105. ሱረቱ አል ፊል – Al-Feel
  106. ሱረቱ ቁረይሽ – Quraysh
  107. ሱረቱ አል ማዑን – Al-Mā‘ūn
  108. ሱረቱ አል ከውሰር – Al-Kawthar
  109. ሱረቱ አል ካፊሩን – Al-Kāfirūn
  110. ሱረቱ አን ነስር – An-Nasr
  111. ሱረቱ አል መሰድ – Al-Masad
  112. ሱረቱ አል ኢኽላስ – Al-Ikhlās
  113. ሱረቱ አል ፈለቅ – Al-Falaq
  114. ሱረቱ አን ናስ – An-Nās

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ!
ይህ ዌየብሳይት ገና በመበልጸግ ላይ ያለ ስለሆነ ብዙ ስህተቶችን ልታገኙበት ትችላላችሁ። ስለዚህ እባካችሁ የምታገኟቸውን ስህተቶች በኮመንት ላይ እንዲታሳውቁን ስንል በአላህ ስም እንጠይቃለን።

Copyright © 2026 Amharic Quran.

Theme: Oceanly by ScriptsTown