| (1) እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች ከአጋሪዎቹም የካዱት ግልጹ አስረጅ እስከ መጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት ላይ) ተወጋጆች አልነበሩም፡፡ |
(1) Those who disbelieve from the People of the Book and the polytheists were not going to desist [from disbelief] until there came to them clear proof, |
| (2) (አስረጁም) ከአላህ የኾነ መልክተኛ የተጥራሩን መጽሐፎች የሚያነብ ነው፡፡ |
(2) a messenger from Allah, reciting pure pages |
| (3) በውስጧ ቀጥተኛ የኾኑ ጽሑፎች ያሉባት የኾነችን፡፡ |
(3) containing upright commandments. |
| (4) እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች ግልጽ አስረጅ ከመጣላቸው በኋላ እንጅ አልተለያዩም፡፡ |
(4) Yet those who were given the Scripture did not disagree except after the clear proof came to them, |
| (5) አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡ |
(5) although they were commanded only to worship Allah with sincere devotion to Him, being inclined to true faith, and to establish prayer and give zakah; that is the true religion. |
| (6) እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት፣ አጋሪዎቹም በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡ |
(6) Those who disbelieve from the People of the Book and the polytheists will be in the fire of Hell, abiding therein forever. It is they who are the worst of creatures. |
| (7) እነዚያ ያመኑትና መልካሞችንም የሠሩት፣ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ ናቸው፡፡ |
(7) As for those who believe and do righteous deeds – it is they who are the best of creatures. |
| (8) በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች ነው፡፡ በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ (ይገቡባቸወል)፡፡ አላህ ከእነርሱ ወደደ፡፡ ከእርሱም ወደዱ፡፡ ይህ ጌታውን ለፈራ ሰው ነው፡፡ |
(8) Their reward with their Lord is Gardens of Eternity under which rivers flow, abiding therein forever. Allah is pleased with them and they are pleased with Him. This is for those who fear their Lord. |