87 – Al-A’laa
| (1) ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ | (1) Glorify the name of your Lord, the Most High, |
| (2) የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡ | (2) Who created and fashioned in due proportion, |
| (3) የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡ | (3) and Who determined [the creation] then guided them, |
| (4) የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡ | (4) and Who brings forth the pasture, |
| (5) (ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡ | (5) then makes it into withered chaff. |
| (6) (ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡ | (6) We will teach you [the Qur’an], so you will not forget, |
| (7) አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ | (7) except what Allah wills, for indeed He knows what is manifest and what is hidden. |
| (8) ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡ | (8) We will guide you to the easy way. |
| (9) ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡ | (9) So remind, if the reminder should benefit. |
| (10) (አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡ | (10) He who fears Allah will take heed, |
| (11) መናጢውም ይርቃታል፡፡ | (11) but the wretched will avoid it, |
| (12) ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡ | (12) who will enter the Great Fire, |
| (13) ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡ | (13) wherein he will neither die nor live. |
| (14) የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡ | (14) Indeed, he who purifies himself will attain success, |
| (15) የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡ | (15) and remembers his Lord’s Name and prays. |
| (16) ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡ | (16) But you prefer the life of this world, |
| (17) መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡ | (17) even though the Hereafter is better and more lasting. |
| (18) ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡ | (18) Indeed, this was in the earlier Scriptures, |
| (19) በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡ | (19) the Scriptures of Abraham and Moses. |