101 – Al-Qaari’a
| (1) ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤ | (1) The Striking Calamity! |
| (2) ምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት! | (2) What is the Striking Calamity? |
| (3) ቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? | (3) How do you know what the Striking Calamity is? |
| (4) ሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤ | (4) On that Day people will be like scattered moths, |
| (5) ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡) | (5) and the mountains will be like carded wool. |
| (6) ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤ | (6) Then the one whose scales of good deeds are heavy, |
| (7) እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡ | (7) will have a pleasant life. |
| (8) ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤ | (8) But the one whose scales of good deeds are light, |
| (9) መኖሪያው ሃዊያህ ናት | (9) his abode will be the abyss. |
| (10) እርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? | (10) And how do you know what it is? |
| (11) (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡ | (11) It is a Blazing Fire. |