Skip to content

Amharic Quran

ከመሞትህ በፊት ቁርአንን አንብብ! (Read the holy Quran before you die!)

  • Home
    • ቁርአንን እንረዳው
    • Download
  • ሱራዎች / Surah List
    • አል-ፋቲሐ (Al-Fatiha)
    • አል-በቀራህ (Al-Beqerah)
    • አል-ዒምራን (Al-Imran)
    • አል-ኒሳዕ (An-Nisa)
    • አል-ማዒዳህ (Al-Maidah) 
    • አንዓም (Al-anam)
    • አል አዕራፍ (Al-Aeraf)
    • አል አንፋል (Al-Anfal)
    • አል ተውባ (At-Tawba)
    • አል ዩኑስ (Yunus)
    • አል ሁድ (Al-Hud)
    • ዩሱፍ (Yusuf)
    • 13 – Ar-Ra’d
    • 14 – Ibrahim
    • አል ሒጅር (Al-Hijr)
    • 16 – An-Nahl
    • 17 – Al-Israa
    • ከህፍ (Al-Kahf )
    • 19 Maryam
    • ጧሃ (Taa-Ha)
    • 21 – Al-Anbiyaa
    • አል ሐጅ (Al-Hajj)
    • 23 – Al-Muminoon
    • 24 – An-Noor
    • 25 – Al -Furqan
    • 26 – Ash-Shu’araa
    • 27 – An-Naml
    • 28 – Al-Qasas
    • 29 – Al-Ankaboot
    • 30 – Ar-Room
    • 31 – Luqman
    • 32 – As-Sajda
    • 33 – Al-Ahzaab
    • 34 – Saba
    • 35 – Faatir
    • 36 – Yaseen
    • 37 – As-Saaffaat
    • 38 – Saad
    • 39 – Az-Zumar
    • 40 – Al-Ghaafir
    • 41 – Fussilat
    • 42 – Ash-Shura
    • 43 – Az-Zukhruf
    • 44 – Ad-Dukhaan
    • 45 – Al-Jaathiya
    • 46 – Al-Ahqaf
    • 47 – Muhammad
    • 48 – Al-Fath
    • 49 – Al-Hujuraat
    • 50 – Qaaf
    • 51 – Adh-Dhaariyat
    • 52 – At-Tur
    • 53 – An-Najm
    • 54 – Al-Qamar
    • 55 – Ar-Rahmaan
    • 56 – Al-Waaqia
    • 57 – Al-Hadid
    • 58 – Al-Mujaadila
    • 59 – Al-Hashr
    • 60 – Al-Mumtahana
    • 61 – As-Saff
    • 62 – Al-Jumu’a
    • 63 – Al-Munaafiqoon
    • 64 – At-Taghaabun
    • 65 – At-Talaaq
    • 66 – At-Tahrim
    • 67 – Al-Mulk
    • 68 – Al-Qalam
    • 69 – Al-Haaqqa
    • 70 – Al-Ma’aarij
    • 71 – Nooh
    • 72 – Al-Jinn
    • 73 – Al-Muzzammil
    • 74 – Al-Muddaththir
    • 75 – Al-Qiyaama
    • 76 – Al-Insaan
    • 77 – Al-Mursalaat
    • 78 – An-Naba
    • 79 – An-Naazi’aat
    • 80 – Abasa
    • 81 – At-Takwir
    • 82 – Al-Infitaar
    • 83 – Al-Mutaffifin
    • 84 – Al-Inshiqaaq
    • 85 – Al-Burooj
    • 86 – At-Taariq
    • 87 – Al-A’laa
    • 88 – Al-Ghaashiya
    • 89 – Al-Fajr
    • 90 – Al-Balad
    • 91 – Ash-Shams
    • 92 – Al-Lail
    • 93 – Ad-Dhuhaa
    • 94 – Ash-Sharh
    • 95 – At-Tin
    • 96 – Al-Alaq
    • 97 – Al-Qadr
    • 98 – Al-Bayyina
    • 99 – Az-Zalzala
    • 100 – Al-Aadiyaat
    • 101 – Al-Qaari’a
    • 102 – At-Takaathur
    • 103 – Al-Asr
    • 104 – Al-Humaza
    • 105 – Al-Fil
    • 106 – Quraish
    • 107 – Al-Maa’un
    • 108 – Al-Kawthar
    • 109 – Al-Kaafiroon
    • 110 – An-Nasr
    • 111 – Al-Masad
    • 112 – Al-Ikhlaas
    • 113 – Al-Falaq
    • 114 – An-Naas

54 – Al-Qamar

Posted on December 10, 2023August 5, 2026 By Muhammed No Comments on 54 – Al-Qamar
Amharic Quran, ቁርአንን እንረዳው

54 – Al-Qamar

(1) ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡(1) The Hour has drawn near and the moon has split asunder.
(2) ተዓምርንም ቢያዩ (ከእምነት) ይዞራሉ፡፡ (ይህ) «ዘውታሪ ድግምት ነውም» ይላሉ፡፡(2) Whenever they see a sign, they turn away and say, “Same old magic!”
(3) አስተባበሉም፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፡፡ ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው)፤ ረጊ ነው፡፡(3) They deny [the truth] and follow their desires, but every matter will reach its inevitable end.
(4) ከዜናዎችም በእርሱ ውስጥ መገሰጥ ያለበት ነገር በእርግጥ መጣላቸው፡፡(4) There have already come to them stories [of destroyed nations] that are sufficient to deter them,
(5) ሙሉ የኾነች ጥበብ (መጣቻቸው) ግን አስፈራሪዎቹ አያብቃቁም፡፡(5) which contain extensive wisdom, but the warnings are of no avail.
(6) ከነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው (መልአክ) ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን (አስታውስ)፡፡(6) So turn away from them [O Prophet]. On the Day when the caller will summon them to a horrific event,
(7) ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ኾነው፤ ፍጹም የተበተነ አንበጣ መስለው ከመቃብሮቹ ይወጣሉ፡፡(7) with eyes downcast, they will come out of the graves like scattered locusts,
(8) ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎች ቸኳዮች ኾነው (ይወጣሉ)፡፡ ከሓዲዎቹ (ያን ጊዜ ምን ይላሉ?) «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ፡፡(8) rushing headlong towards the caller. The disbelievers will say, “This is a hard Day!”
(9) ከእነርሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች፡፡ ባሪያችንንም (ኑሕን) አስተባበሉ፡፡ «ዕብድ ነውም» አሉ፡፡ ተገላመጠም፡፡(9) The people of Noah rejected [the truth] before them; they rejected Our slave and said, “He is a madman,” and he was rebuked.
(10) ጌታውንም «እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ጠራ፡፡(10) So he called upon his Lord, “I am overpowered, so help me!”
(11) ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን፡፡(11) So We opened the gates of the sky with water pouring down in torrents,
(12) የምድርንም ምንጮች አፈነዳን፡፡ ውሃውም (የሰማዩና የምድሩ) በእርግጥ በተወሰነ ኹነታ ላይ ተገናኘ፡፡(12) and We caused the earth to burst forth with springs, then the waters met for a preordained purpose.
(13) ባለ ሳንቃዎችና ባለሚስማሮች በኾነችም ታንኳ ላይ ጫንነው፡፡(13) We carried him on an [Ark made] of planks and nails,
(14) በጥበቃችን ስር ኾና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረው ሰው ምንዳ (ይህንን ሠራን)፡፡(14) sailing under Our [watchful] Eyes; as a reward for the one [they] denied.
(15) ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት፡፡ ከተገሳጭም አልለን?(15) We have certainly left it as a sign; is there anyone to take heed?
(16) ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?(16) Then how were My punishment and My warnings?
(17) ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን?(17) We have certainly made the Qur’an easy to understand and remember; is there anyone to take heed?
(18) ዓድ አስተባበለች፡፡ ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ!(18) ‘Ād disbelieved. Then how were My punishment and My warnings?
(19) እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በኾነ ቀን በኀይል የምትንሻሻ ነፋስን ላክንባቸው፡፡(19) We sent against them a furious wind on a day of continuous misfortune,
(20) ሰዎቹን ልክ ከሥሮቻቸው የተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው (ከተደበቁበት) ትነቅላቸዋለች፡፡(20) sweeping people away, as if they were trunks of uprooted palm trees.
(21) ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?(21) Then how were My punishment and My warnings?
(22) ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን?(22) We have certainly made the Qur’an easy to understand and remember; is there anyone to take heed?
(23) ሰሙድ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች፡፡(23) Thamūd rejected the warnings,
(24) «ከእኛ የኾነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያን ጊዜ በስህተትና በዕብደት ውስጥ ነን» አሉ፡፡(24) They said, “Shall we follow a single human being from among us? Then we would surely be in error and insanity!
(25) «ከኛ መካከል በእርሱ ላይ (ብቻ) ማስገንዘቢያ (ራእይ) ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» (አሉ)፡፡(25) Has the revelation been sent down upon him out of all of us? Rather, he is an insolent liar.”
(26) ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደኾነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡(26) Tomorrow they will know who the insolent liar is.
(27) እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትኾን ዘንድ ላኪዎች ነን፡፡ ተጠባበቃቸውም፡፡ ታገስም፡፡(27) We are sending the she-camel as a test for them, so watch them [O Sālih] and be patient,
(28) ውሃውንም በመካከላቸው የተከፈለ መኾኑን ንገራቸው፡፡ ከውሃ የኾነ ፋንታ ሁሉ (ተረኞቹ) የሚጣዱት ነው፡፡(28) and tell them that the water is to be shared between them; each should take its drink in turn.
(29) ጓደኛቸውንም ጠሩ፡፡ ወዲያውም (ሰይፍን) ተቀበለ፡፡ ወጋትም፡፡(29) But they called their companion, and he undertook the task and hamstrung her.
(30) ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?(30) Then how [terrible] My punishment and My warnings were!
(31) እኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው፡፡ ወዲያውም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ ርግጋፊ ኾኑ፡፡(31) We sent against them a single blast, leaving them like trampled hedge-building twigs.
(32) ቁርኣንንም ለመገንዘብ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን?(32) We have certainly made the Qur’an easy to understand and remember; is there anyone to take heed?
(33) የሉጥ ሕዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች፡፡(33) The people of Lot rejected the warnings.
(34) እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ (እነርሱንስ) በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው፡፡(34) We sent against them a storm of pebbles, except the family of Lot whom We saved before dawn,
(35) ከእኛ በኾነ ጸጋ (አዳንናቸው)፡፡ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን፡፡(35) as a blessing from Us. Thus do We reward those who give thanks.
(36) ብርቱይቱን አያያዛችንንም በእርግጥ አስጠነቀቃቸው፡፡ በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ፡፡(36) He had already warned them of Our punishing assault, but they doubted the warnings.
(37) ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት፡፡ ወዲያውም ዓይኖቻቸውን አበስን፡፡ «ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱ» (አልናቸው)፡፡(37) They even demanded that he let them have their way with his angel-guests, so We blinded their eyes, [saying], “Taste My punishment and My warnings!”
(38) በማለዳም ዘውታሪ የኾነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው፡፡(38) By the early morning a lasting torment overtook them.
(39) «ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱ» (ተባሉ)፡፡(39) Taste My punishment and My warnings!
(40) ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን?(40) We have certainly made the Qur’an easy to understand and remember; is there anyone to take heed?
(41) የፈርዖንንም ቤተሰቦች ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጡዋቸው፡፡(41) Indeed, warnings came to the people of Pharaoh.
(42) በተዓምራቶቻችን በሁሏም አስተባበሉ፡፡ የብርቱ ቻይንም አያያዝ ያዝናቸው፡፡(42) But they rejected all of Our signs, so We seized them with the grip of the All-Mighty, Most Powerful.
(43) ከሓዲዎቻችሁ ከእነዚህ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለናንተ በመጽሐፎች ውስጥ (የተነገረ) ነፃነት አላችሁን?(43) Are your disbelievers [O Makkans] superior than those, or have you been granted immunity in divine Scriptures?
(44) ወይስ «እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን» ይላሉን?(44) Or do they say, “We are a united front, bound to prevail.”?
(45) ክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይምመታሉ፡፡ ጀርባዎችንም ያዞራሉ፡፡(45) Soon their united front will be defeated, and they will flee.
(46) ይልቁንም ሰዓቲቱ (ትንሣኤ) ቀጠሮዋቸው ናት፡፡ ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት፡፡(46) But the Hour is their appointed time, and the Hour is more catastrophic and more bitter.
(47) አመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው፡፡(47) Indeed, the wicked are in error and will be in blazes.
(48) በእሳት ውስጥ በፊቶቻቸው በሚጎተቱበት ቀን «የሰቀርን መንካት ቅመሱ» (ይባላሉ)፡፡(48) On the Day when they will be dragged into the Fire on their faces, [they will be told], “Taste the agony of Hell!”
(49) እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡(49) Indeed, We have created everything according to a determined measure.
(50) ትእዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት አንዲት (ቃል) እንጅ ሌላ አይደለም፡፡(50) Our command is but a single word, which is fulfilled in the blink of an eye.
(51) ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፡፡ ተገሳጭም አልለን?(51) We have destroyed many like you [O Makkans]; is there anyone to take heed?
(52) የሠሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው፡፡(52) Everything they did is in the written records,
(53) ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተጻፈ ነው፡፡(53) and everything, small or big, is written down.
(54) አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው፡፡(54) Indeed, the righteous will be in gardens and rivers,
(55) (እነርሱም ውድቅ ቃልና መውወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ቻይ የሆነው ንጉሥ ዘንድ ናቸው፡፡(55) seated in honor in the presence of the Most Powerful Sovereign.
Tags: Amharic Quran Free Amharic Quran quran amharic quran in amharic ምዕራፍ 2 ሱረቱ ተባረክ ሱረቱ አል ሐጅ ሱረቱ አል ከህፍ ሱረቱ አትተውባ ሱረቱ ጡር ሱረቱል ሙልክ ሱረቱል በቀራህ ሱረቱል አል ማዒዳህ ሱረቱል አል-በቀራህ ሱረቱል ከህፍ ቁረአን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ትርጉም ቁርአን በአማርኛ ቅዱስ ቁርአን አልበቀራህ አማርኛ ቁርአን አማርኛ ቅዱስ ቁርአን የቁራን ትርጉም

Post navigation

❮ Previous Post: 53 – An-Najm
Next Post: 55 – Ar-Rahmaan ❯

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ሁሉም ሱራዎች / All Chapters

  1. ሱረቱ አል-ፋቲሃ – Al-Fātihah
  2. ሱረቱ አል-በቀራህ – Al-Baqarah
  3. ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን – Āl-‘Imrān
  4. ሱረቱ አን-ኒሳዕ – An-Nisā’
  5. ሱረቱ አል-ማኢዳህ – Al-Mā’idah
  6. ሱረቱ አል-አንዓም – Al-An‘ām
  7. ሱረቱ አል-አዕራፍ – Al-A‘rāf
  8. ሱረቱ አል-አንፋል – Al-Anfāl
  9. ሱረቱ አት-ተውባህ – At-Tawbah
  10. ሱረቱ ዩኑስ – Yūnus
  11. ሱረቱ ሁድ – Hūd
  12. ሱረቱ ዩኑስ – Yūsuf
  13. ሱረቱ አር-ረዕድ – Ar-Ra‘d
  14. ሱረቱ ኢብራሂም – Ibrāhīm
  15. ሱረቱ አል ሒጅር – Al-Hijr
  16. ሱረቱ አን–ነሕል – An-Nahl
  17. ሱረቱ አል ኢስራዕ – Al-Isrā’
  18. ሱረቱ አል ከህፍ – Al-Kahf
  19. ሱረቱ መርየም – Maryam
  20. ሱረቱ ጣሃ – Tā-ha
  21. ሱረቱ አል አንቢያ – Al-Anbiyā’
  22. ሱረቱ አል ሐጅ – Al-Hajj
  23. ሱረቱ አል–ሙዕሚኑን – Al-Mu’minūn
  24. ሱረቱ አልን ኑር – An-Noor
  25. ሱረቱ አል ፉርቃን – Al-Furqān
  26. ሱረቱ አሽ ሹዐራእ – Ash-Shu‘arā’
  27. ሱረቱ አን ነምል – An-Naml
  28. ሱረቱ አል ቀሰስ – Al-Qasas
  29. ሱረቱ አል ዐንከቡት – Al-‘Ankabūt
  30. ሱረቱ አር ሩም – Ar-Rūm
  31. ሱረቱ አል ሉቅማን – Luqmān
  32. ሱረቱ አስ ሰጅደህ – As-Sajdah
  33. ሱረቱ አል አሕዛብ – Al-Ahzāb
  34. ሱረቱ ሰበእ – Saba’
  35. ሱረቱ ፋጢር – Fātir
  36. ሱረቱ ያሲን – Yā-Sīn
  37. ሱረቱ አስ ሷፋት – As-Sāffāt
  38. ሱረቱ ሷድ – Sād
  39. ሱረቱ አዝ ዙመር – Az-Zumar
  40. ሱረቱ ጋፊር – Ghāfir
  41. ሱረቱ ፉሲለት – Fussilat
  42. ሱረቱ አሽ ሹራ – Ash-Shūra
  43. ሱረቱ አዝ ዙኽሩፍ – Az-Zukhruf
  44. ሱረቱ አድ ዱኻን – Ad-Dukhān
  45. ሱረቱ አል ጃሲያህ – Al-Jāthiyah
  46. ሱረቱ አል አህቃፍ – Al-Ahqāf
  47. ሱረቱ ሙሐመድ – Muhammad
  48. ሱረቱ አል ፈትህ – Al-Fat’h
  49. ሱረቱ አል ሑጅራት – Al-Hujurāt
  50. ሱረቱ ቃፍ – Qāf
  51. ሱረቱ አዝ ዛሪያት – Adh-Dhāriyāt
  52. ሱረቱ አጥ ጡር – At-Toor
  53. ሱረቱ አን ነጅም – An-Najm
  54. ሱረቱ አል ቀመር – Al-Qamar
  55. ሱረቱ አር ረሕማን – Ar-Rahmān
  56. ሱረቱ አል ዋቂዓህ – Al-Wāqi‘ah
  57. ሱረቱ አል ሐዲድ – Al-Hadīd
  58. ሱረቱ አል ሙጃደላ – Al-Mujādalah
  59. ሱረቱ አል ሐሽር – Al-Hashr
  60. ሱረቱ አል ሙምተሂና – Al-Mumtahanah
  61. ሱረቱ አስ ሶፍ – As-Saff
  62. ሱረቱ አል ጁሙዓህ – Al-Jumu‘ah
  63. ሱረቱ አል ሙናፊቁን – Al-Munāfiqūn
  64. ሱረቱ አት ተጋቡን – At-Taghābun
  65. ሱረቱ አጥ ጠላቅ – At-Talāq
  66. ሱረቱ አት ተህሪም – At-Tahrīm
  67. ሱረቱ አል ሙልክ – Al-Mulk
  68. ሱረቱ አል ቀለም – Al-Qalam
  69. ሱረቱ አል ሓቃህ – Al-Hāqqah
  70. ሱረቱ አል መዓሪጅ – Al-Ma‘ārij
  71. ሱረቱ ኑህ – Nūh
  72. ሱረቱ አል ጂን – Al-Jinn
  73. ሱረቱ አል ሙዘሚል – Al-Muzzammil
  74. ሱረቱ አል ሙደሲር – Al-Muddaththir
  75. ሱረቱ አል ቂያማህ – Al-Qiyāmah
  76. ሱረቱ አል ኢንሳን – Al-Insān
  77. ሱረቱ አል ሙርሰላት – Al-Mursalāt
  78. ሱረቱ አን ነበእ – An-Naba’
  79. ሱረቱ አን ናዚዓት – An-Nāzi‘āt
  80. ሱረቱ ዐበሰ – ‘Abasa
  81. ሱረቱ አት ተክዊር – At-Takwīr
  82. ሱረቱ አል ኢንፊጣር – Al-Infitār
  83. ሱረቱ አል ሙጠፊፊን – Al-Mutaffifīn
  84. ሱረቱ አል ኢንሺቃቅ – Al-Inshiqāq
  85. ሱረቱ አል ቡሩጅ – Al-Burūj
  86. ሱረቱ አጥ ጣሪቅ – At-Tāriq
  87. ሱረቱ አል አዕላ – Al-A‘lā
  88. ሱረቱ አል ጋሺያህ – Al-Ghāshiyah
  89. ሱረቱ አል ፈጅር – Al-Fajr
  90. ሱረቱ አል በለድ – Al-Balad
  91. ሱረቱ አሽ ሸምስ – Ash-Shams
  92. ሱረቱ አል ለይል – Al-Layl
  93. ሱረቱ አድ ዱሓ – Ad-Duhā
  94. ሱረቱ አሽ ሸርህ – Ash-Sharh
  95. ሱረቱ አት ቲን – At-Teen
  96. ሱረቱ አል ዐለቅ – Al-‘Alaq
  97. ሱረቱ አል ቀድር – Al-Qadr
  98. ሱረቱ አል–በይናህ – Al-Bayyinah
  99. ሱረቱ አል ዘልዘላህ – Az-Zalzalah
  100. ሱረቱ አል ዓዲያት – Al-‘Ādiyāt
  101. ሱረቱ አል ቃሪዓሕ – Al-Qāri‘ah
  102. ሱረቱ አት ተካሱር – At-Takāthur
  103. ሱረቱ አል ዓስር – Al-‘Asr
  104. ሱረቱ አል ሁመዛህ – Al-Humazah
  105. ሱረቱ አል ፊል – Al-Feel
  106. ሱረቱ ቁረይሽ – Quraysh
  107. ሱረቱ አል ማዑን – Al-Mā‘ūn
  108. ሱረቱ አል ከውሰር – Al-Kawthar
  109. ሱረቱ አል ካፊሩን – Al-Kāfirūn
  110. ሱረቱ አን ነስር – An-Nasr
  111. ሱረቱ አል መሰድ – Al-Masad
  112. ሱረቱ አል ኢኽላስ – Al-Ikhlās
  113. ሱረቱ አል ፈለቅ – Al-Falaq
  114. ሱረቱ አን ናስ – An-Nās

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ!
ይህ ዌየብሳይት ገና በመበልጸግ ላይ ያለ ስለሆነ ብዙ ስህተቶችን ልታገኙበት ትችላላችሁ። ስለዚህ እባካችሁ የምታገኟቸውን ስህተቶች በኮመንት ላይ እንዲታሳውቁን ስንል በአላህ ስም እንጠይቃለን።

Copyright © 2026 Amharic Quran.

Theme: Oceanly by ScriptsTown