Default Image
17, Dec 2023
83 – Al-Mutaffifin

83 – Al-Mutaffifin

(1) ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡(1) Woe to the defrauders,
(2) ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡(2) those who take full measure when they take from others,
(3) ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡(3) but they give less when they measure or weigh for them.
(4) እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን?(4) Do they really not think that they will be resurrected
(5) በታላቁ ቀን፡፡(5) for a momentous Day,
(6) ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡(6) a Day when people will stand before the Lord of the worlds?
(7) በእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡(7) No indeed! The record of the wicked is surely in Sijjīn.
(8) ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?(8) How do you know what Sijjīn is?
(9) የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡(9) It is a clearly inscribed Record.
(10) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡(10) Woe on that Day to the deniers,
(11) ለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡(11) those who deny the Judgment Day!
(12) በእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡(12) None denies it except every sinful transgressor.
(13) አንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡(13) When Our verses are recited to him, he says, “Ancient fables!”
(14) ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡(14) No indeed! Their hearts have been stained by what they used to commit!
(15) ይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡(15) No indeed! On that Day they will be barred from seeing their Lord.
(16) ከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡(16) They will then surely enter the Blazing Fire,
(17) ከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡(17) then they will be told, “This is what you used to deny.”
(18) በእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡(18) No indeed! The record of the righteous is certainly in ‘illiyyīn –
(19) ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?(19) and how do you know what ‘illiyyūn is? –
(20) የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡(20) It is a record inscribed,
(21) ባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡(21) witnessed by those who are close to Allah.
(22) እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡(22) Indeed, the righteous will be in Bliss,
(23) በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡(23) seated on the couches, gazing in wonder.
(24) በፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡(24) You will see on their faces the radiance of bliss.
(25) ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡(25) They will be served to drink pure wine from a sealed container,
(26) ማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡(26) whose last sip is musk – let those who strive, strive for that –
(27) መበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡(27) and it will be mixed with water from the spring of Tasnīm,
(28) ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡(28) a spring from which those who are close to Allah will drink.
(29) እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡(29) Indeed, the wicked used to laugh at the believers;
(30) በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡(30) when they passed by them, they would wink at one another,
(31) ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡(31) and when they went back to their people, they would return exulting.
(32) ባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡(32) When they saw the believers, they would say, “These people are truly misguided,”
(33) በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡(33) although they were not sent as their keepers.
(34) ዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡(34) So Today the believers will laugh at the disbelievers,
(35) በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡(35) while sitting on the couches, gazing around.
(36) ከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡(36) Have the disbelievers been rewarded except for what they used to do?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

62 – Al-Jumu’a

62 – Al-Jumu’a (1) በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ፣ ቅዱስ፣ አሸናፊ፣ ጥበበኛ ለኾነው ያሞግሳል፡፡ (1) All that is…

ግደሉ የሚለው ቁርአን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ?

ግደሉ የሚለው ቁርአን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ? የግድያ መፅሀፍ የሚመስለው ቅዱስ ቁርአን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ? እስኪ ከመፅሀፍ ቅዱስ ጀምረን እንየው:- ግደል…

66 – At-Tahrim

66 – At-Tahrim (1) አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትኾን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ? አላህም እጅግ…