Default Image
20, Nov 2023
ሱረቱ አል ዩኑስ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran 10 Yunus

ሱረቱ አል ዩኑስ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran 10 Yunus

الر ۚ تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ الْحَكِيمِ  [1]

(1) አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ) ይህቺ (ሱራ) ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ (ከቁርኣን) አንቀጾች ናት።

(1) Alif Lām Ra. These are the verses of the Book of wisdom.

أَكَانَ لِلنَّاسِ عَجَبًا أَنْ أَوْحَيْنَا إِلَىٰ رَجُلٍ مِّنْهُمْ أَنْ أَنذِرِ النَّاسَ وَبَشِّرِ الَّذِينَ آمَنُوا أَنَّ لَهُمْ قَدَمَ صِدْقٍ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ قَالَ الْكَافِرُونَ إِنَّ هَٰذَا لَسَاحِرٌ مُّبِينٌ  [2]

(2) «ሰዎችን አስፈራራ። እነዚያንም ያመኑትን ለእነሱ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን አብስር» በማለት ከነርሱው ወደ ኾነ አንድ ሰው ራእይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ኾነባቸውን ከሓዲዎቹ፡- «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምተኛ ነው» አሉ።

(2) Is it surprising to people that We have sent revelation to a man from among themselves to warn people and give glad tidings to those who believe, that they will have a noble position with their Lord? But the disbelievers say, “This man is a clear magician!”

إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۖ يُدَبِّرُ الْأَمْرَ ۖ مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ  [3]

(3) ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው። ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲኾን በዐርሹ ላይ (ለሱ ክብር በምስማማ መልኩ) ተደላደለ። ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም። እነሆ! አላህ ጌታችሁ ነውና ተገዙት፤ አትገሰጹምን

(3) Allah is your Lord Who created the heavens and earth in six Days, and then rose over the Throne, governing all affairs. None can intercede except by His permission. Such is Allah your Lord, so worship Him. Will you not then take heed?

إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًا ۖ وَعْدَ اللَّهِ حَقًّا ۚ إِنَّهُ يَبْدَأُ الْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُ لِيَجْزِيَ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ بِالْقِسْطِ ۚ وَالَّذِينَ كَفَرُوا لَهُمْ شَرَابٌ مِّنْ حَمِيمٍ وَعَذَابٌ أَلِيمٌ بِمَا كَانُوا يَكْفُرُونَ  [4]

(4) ሁላችሁም ኾናችሁ መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው። (ይህም) የተረጋገጠ የአላህ ቃል ኪዳን ነው፤ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል። ከዚያም እነዚያን ያመኑትንና መልካም የሠሩትን በትክክል ይመነዳ ዘንድ ይመልሰዋል። እነዚያ የካዱትም ይክዱት በነበሩት ነገር ለነርሱ ከፈላ ውሃ የኾነ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አላቸው።

(4) To Him is your return all together. Allah’s promise will surely come true. He originates the creation then brings it back, so that He may justly reward those who believe and do righteous deeds. But for those who disbelieve there will be a drink of scalding water and a painful punishment because of their disbelief.

هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ ۚ مَا خَلَقَ اللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِالْحَقِّ ۚ يُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ  [5]

(5) እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው። የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው። አላህ ይህንን በእውነት እንጂ (በከንቱ) አልፈጠረውም። ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል።

(5) It is He Who made the sun a radiant light and the moon a reflected light, and precisely determined its phases, so that you may know the number of years and account [of time]. Allah has not created all of this except for a true purpose. He makes the signs clear for people who know.

إِنَّ فِي اخْتِلَافِ اللَّيْلِ وَالنَّهَارِ وَمَا خَلَقَ اللَّهُ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَّقُونَ  [6]

(6) ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህም በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ምልክቶች አሉ።

(6) Indeed, in the alternation of the night and day, and in what Allah has created in the heavens and earth, there are signs for people who fear Him.

إِنَّ الَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَاءَنَا وَرَضُوا بِالْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَاطْمَأَنُّوا بِهَا وَالَّذِينَ هُمْ عَنْ آيَاتِنَا غَافِلُونَ  [7]

(7) እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩ ቅርቢቱንም ሕይወት የወደዱ በእሷም የረኩ እነዚያም እነሱ ከአንቀጾቻችን ዘንጊዎች የኾኑ።

(7) Those who do not expect to meet Us, and are pleased and content with the life of this world, and those who are heedless of Our signs,

أُولَٰئِكَ مَأْوَاهُمُ النَّارُ بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ  [8]

(8) እነዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መኖሪያቸው በእሳት ውስጥ ነው።

(8) their abode will be the Fire, for what they used to earn.

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ يَهْدِيهِمْ رَبُّهُم بِإِيمَانِهِمْ ۖ تَجْرِي مِن تَحْتِهِمُ الْأَنْهَارُ فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ  [9]

(9) እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ጌታቸው በእምነታቸው ምክንያት (የገነትን መንገድ) ይመራቸዋል። ከሥራቸው ወንዞች ይፈስሳሉ። በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ይኖራሉ።

(9) As for those who believe and do righteous deeds, their Lord will guide them by virtue of their faith. Rivers will flow beneath them in the Gardens of Bliss.

دَعْوَاهُمْ فِيهَا سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَتَحِيَّتُهُمْ فِيهَا سَلَامٌ ۚ وَآخِرُ دَعْوَاهُمْ أَنِ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ  [10]

(10) በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ (ማለት) ነው። በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸውም ሰላም መባባል ነው፤ የመጨረሻ ጸሎታቸውም ምስጋና ለዓለማት ጌታ ይሁን (ማለት) ነው።

(10) Their prayer will be, “Glorify be to You, O Allah,” and their greeting will be, “Peace,” and the closing of their prayer will be, “All praise be to Allah, the Lord of the worlds.”

وَلَوْ يُعَجِّلُ اللَّهُ لِلنَّاسِ الشَّرَّ اسْتِعْجَالَهُم بِالْخَيْرِ لَقُضِيَ إِلَيْهِمْ أَجَلُهُمْ ۖ فَنَذَرُ الَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَاءَنَا فِي طُغْيَانِهِمْ يَعْمَهُونَ  [11]

(11) አላህ ለሰዎች ደግን ነገር ለማግኘት እንደ መቻኮላቸው (አጥፋን ሲሉት) ክፉን ነገር ቢያስቸኩል ኖሮ ጊዜያቸው ወደነሱ በተፈጸመ ነበር። እነዚያንም መገናኘታችንን የማይፈሩትን በጥመታቸው ውስጥ የሚዋልሉ ሲኾኑ እንተዋቸዋለን።

(11) If Allah were to hasten evil to the people, just as they seek to hasten good, they would have been ruined. But We leave those who do not expect to meet Us to wander blindly in their transgression.

وَإِذَا مَسَّ الْإِنسَانَ الضُّرُّ دَعَانَا لِجَنبِهِ أَوْ قَاعِدًا أَوْ قَائِمًا فَلَمَّا كَشَفْنَا عَنْهُ ضُرَّهُ مَرَّ كَأَن لَّمْ يَدْعُنَا إِلَىٰ ضُرٍّ مَّسَّهُ ۚ كَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِلْمُسْرِفِينَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ  [12]

(12) ሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ በጎኑ ላይ ተጋድሞ ወይም ተቀምጦ ወይም ቆሞ ይለምነናል። ጉዳቱንም ከእሱ ላይ በገለጥንለት ጊዜ ወደ አገኘው ጉዳት እንዳልጠራን ሆኖ ያልፋል። እንደዚሁ ለድንበር አላፊዎች ይሠሩት የነበሩት ሥራ ተሸለመላቸው።

(12) When hardship befalls man, he calls upon Us, whether lying on his side, sitting or standing. But when We remove his hardship, he turns a blind eye as though he had never called upon Us to remove his hardship. This is how the misdeeds of the transgressors are made appealing to them.

وَلَقَدْ أَهْلَكْنَا الْقُرُونَ مِن قَبْلِكُمْ لَمَّا ظَلَمُوا ۙ وَجَاءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِالْبَيِّنَاتِ وَمَا كَانُوا لِيُؤْمِنُوا ۚ كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْقَوْمَ الْمُجْرِمِينَ  [13]

(13) ከእናንተ በፊት የነበሩትንም የክፍለ ዘመናት ሰዎች መልክተኞቻቸው በማስረጃዎች የመጧቸው ሲኾኑ በበደሉና የማያምኑም በኾኑ ጊዜ በእርግጥ አጠፋናቸው። እንደዚሁ ተንኮለኞችን ሕዝቦች እንቀጣለን።

(13) We destroyed the generations before you when they indulged in wrongdoing, and their messengers came to them with clear proofs, but they would not believe. This is how We recompense the wicked people.

ثُمَّ جَعَلْنَاكُمْ خَلَائِفَ فِي الْأَرْضِ مِن بَعْدِهِمْ لِنَنظُرَ كَيْفَ تَعْمَلُونَ  [14]

(14) ከዚያም እንዴት እንደምትሠሩ ልንመለከት ከእነሱ በኋላ በምድር ላይ ምትኮች አደረግናችሁ።

(14) Then We made you their successors in the land to see how you would behave.

وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ ۙ قَالَ الَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَاءَنَا ائْتِ بِقُرْآنٍ غَيْرِ هَٰذَا أَوْ بَدِّلْهُ ۚ قُلْ مَا يَكُونُ لِي أَنْ أُبَدِّلَهُ مِن تِلْقَاءِ نَفْسِي ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰ إِلَيَّ ۖ إِنِّي أَخَافُ إِنْ عَصَيْتُ رَبِّي عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ  [15]

(15) አንቀጾቻችንም ግልጽ ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው ይላሉ። እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም። ወደእኔ የሚወርደውን እንጂ አልከተልም። እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ በላቸው።

(15) When Our verses are recited to them clearly, those who do not expect to meet Us say, “Bring us a different Qur’an, or make changes in it.” Say, “It is not for me to change it on my own accord; I only follow what is revealed to me. If I were to disobey my Lord, I fear the punishment of a momentous Day.”

قُل لَّوْ شَاءَ اللَّهُ مَا تَلَوْتُهُ عَلَيْكُمْ وَلَا أَدْرَاكُم بِهِ ۖ فَقَدْ لَبِثْتُ فِيكُمْ عُمُرًا مِّن قَبْلِهِ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ  [16]

(16) አላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባለነበብኩትም (አላህ) እርሱን ባላሳወቃችሁም ነበር። በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት (ምንም ሳልል) ብዙን ዕድሜ በእርግጥ ኖሬአለሁ፤ አታውቁምን

(16) Say, “If Allah had willed, I would not have recited it to you, nor would He have made it known to you. I have spent a lifetime among you before this. Do you not then understand?”

فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِآيَاتِهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الْمُجْرِمُونَ  [17]

(17) በአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ከአስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው እነሆ አመጸኞች አይድኑም።

(17) Who does greater wrong than he who fabricates lies against Allah or rejects His verses? Indeed, the wicked will never succeed.

وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ ۚ قُلْ أَتُنَبِّئُونَ اللَّهَ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ  [18]

(18) ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ። «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ። «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው። ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም።

(18) They worship besides Allah those who can neither harm nor benefit them, saying, “These are our intercessors with Allah.” Say, “Do you inform Allah of what He does not know in the heavens or on the earth? Glorified and Exalted is He far above what they associate [with Him]!”

وَمَا كَانَ النَّاسُ إِلَّا أُمَّةً وَاحِدَةً فَاخْتَلَفُوا ۚ وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيْنَهُمْ فِيمَا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ  [19]

(19) ሰዎችም አንድ ሕዝብ እንጂ ሌላ አልነበሩም። ተለያዩም። ከጌታህ ያለፈች ቃልም ባልነበረች ኖሮ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ (በቶሎ) በተፈረደ ነበር።

(19) The whole mankind was but a single community, then they differed. If it had not been for a prior decree from your Lord, a decisive judgment would have been passed between them concerning their differences.

وَيَقُولُونَ لَوْلَا أُنزِلَ عَلَيْهِ آيَةٌ مِّن رَّبِّهِ ۖ فَقُلْ إِنَّمَا الْغَيْبُ لِلَّهِ فَانتَظِرُوا إِنِّي مَعَكُم مِّنَ الْمُنتَظِرِينَ  [20]

(20) በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ። «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው። ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው።

(20) They say, “Why has no sign been sent down to him from his Lord?” Say [O Prophet], “The unseen belongs to Allah alone. Wait then; I too am waiting with you.”

وَإِذَا أَذَقْنَا النَّاسَ رَحْمَةً مِّن بَعْدِ ضَرَّاءَ مَسَّتْهُمْ إِذَا لَهُم مَّكْرٌ فِي آيَاتِنَا ۚ قُلِ اللَّهُ أَسْرَعُ مَكْرًا ۚ إِنَّ رُسُلَنَا يَكْتُبُونَ مَا تَمْكُرُونَ  [21]

(21) ሰዎችንም ካገኛቸው ጉዳት በኋላ እዝነትን (ዝናብና ምቾትን) ባቀመስናቸው ጊዜ ወዲያውኑ ለእነሱ በተዓምራቶቻችን (በማላገጥ) ተንኮል ይኖራቸዋል። አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው። «መልክተኞቻችን የምትመክሩትን ነገር በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው።

(21) When We give people a taste of mercy after being afflicted with adversity, they start plotting against Our verses. Say, “Allah is swifter in planning [retribution]. Our angel-messengers record whatever you plot.”

هُوَ الَّذِي يُسَيِّرُكُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ ۖ حَتَّىٰ إِذَا كُنتُمْ فِي الْفُلْكِ وَجَرَيْنَ بِهِم بِرِيحٍ طَيِّبَةٍ وَفَرِحُوا بِهَا جَاءَتْهَا رِيحٌ عَاصِفٌ وَجَاءَهُمُ الْمَوْجُ مِن كُلِّ مَكَانٍ وَظَنُّوا أَنَّهُمْ أُحِيطَ بِهِمْ ۙ دَعَوُا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ لَئِنْ أَنجَيْتَنَا مِنْ هَٰذِهِ لَنَكُونَنَّ مِنَ الشَّاكِرِينَ  [22]

(22) እርሱ (አላህ) ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው። በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በርሷ የተደሰቱ ኾነው (መርከቦቹ) በተንሻለሉ ጊዜ ኀይለኛ ነፋስ ትመጣባታለች። ከየስፍራውም ማዕበል ይመጣባቸዋል። እነሱም (ለጥፋት) የተከበቡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። (ያን ጊዜ) አላህን ከዚህች (ጭንቀት) ብታድነን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን ሲሉ ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይለምኑታል።

(22) It is He Who enables you to travel through the land and sea, until when you are in the ships and they sail with those on board and rejoicing in a favorable wind, then suddenly a stormy wind comes, with waves crashing into them on all sides, and they feel that there is no escape. Then they cry out to Allah with sincere devotion to Him, “If You save us from this, we will surely be among those who are grateful.”

فَلَمَّا أَنجَاهُمْ إِذَا هُمْ يَبْغُونَ فِي الْأَرْضِ بِغَيْرِ الْحَقِّ ۗ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّمَا بَغْيُكُمْ عَلَىٰ أَنفُسِكُم ۖ مَّتَاعَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ ثُمَّ إِلَيْنَا مَرْجِعُكُمْ فَنُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ  [23]

(23) በአዳናቸውም ጊዜ እነሱ ወዲያውኑ ያለ አግባብ በምድር ላይ ወሰን ያልፋሉ። እናንተ ሰዎች ሆይ! ወሰን ማለፋችሁ (ጥፋቱ) በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው። (እርሱም) የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው። ከዚያም መመለሻችሁ ወደኛ ነው። ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እንነግራችኋለን።

(23) However, when He saves them, they start transgressing in the land unjustly. O people, your transgression is against your own souls. Take your little enjoyment in this life; then to Us is your return, and We will inform you of what you used to do.

إِنَّمَا مَثَلُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا كَمَاءٍ أَنزَلْنَاهُ مِنَ السَّمَاءِ فَاخْتَلَطَ بِهِ نَبَاتُ الْأَرْضِ مِمَّا يَأْكُلُ النَّاسُ وَالْأَنْعَامُ حَتَّىٰ إِذَا أَخَذَتِ الْأَرْضُ زُخْرُفَهَا وَازَّيَّنَتْ وَظَنَّ أَهْلُهَا أَنَّهُمْ قَادِرُونَ عَلَيْهَا أَتَاهَا أَمْرُنَا لَيْلًا أَوْ نَهَارًا فَجَعَلْنَاهَا حَصِيدًا كَأَن لَّمْ تَغْنَ بِالْأَمْسِ ۚ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ  [24]

(24) የቅርቢቱ ሕይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ፣ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት (እንደ ፋፋ) ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋም በርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መኾናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትእዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው። እንደዚሁም ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን።

(24) The likeness of the life of this world is that of the rain that We send down from the sky, and it mixes with the plants of the earth, from which both humans and livestock eat. Then when the earth is in its splendor and its fairest appearance, and its owners feel that they have full control over it, Our command comes to it, by night or by day, and We reduce it to stubble, as if it had not flourished the day before. This is how We make the signs clear for people who reflect.

وَاللَّهُ يَدْعُو إِلَىٰ دَارِ السَّلَامِ وَيَهْدِي مَن يَشَاءُ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ  [25]

(25) አላህም ወደ ሰላም አገር ይጠራል። የሚሻውንም ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል።

(25) Allah invites to the Home of Peace and guides whom He wills to a straight path.

لِّلَّذِينَ أَحْسَنُوا الْحُسْنَىٰ وَزِيَادَةٌ ۖ وَلَا يَرْهَقُ وُجُوهَهُمْ قَتَرٌ وَلَا ذِلَّةٌ ۚ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ  [26]

(26) ለእነዚያ መልካም ለሠሩት መልካም ነገርና ጭማሪም አላቸው። ፊቶቻቸውንም ጥቁረትና ውርደት አይሸፍናቸውም። እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው። እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው።

(26) For those who do good there will be the best reward and more – neither gloom nor humiliation will cover their faces. It is they who are the people of Paradise, they will abide therein forever.

وَالَّذِينَ كَسَبُوا السَّيِّئَاتِ جَزَاءُ سَيِّئَةٍ بِمِثْلِهَا وَتَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ ۖ مَّا لَهُم مِّنَ اللَّهِ مِنْ عَاصِمٍ ۖ كَأَنَّمَا أُغْشِيَتْ وُجُوهُهُمْ قِطَعًا مِّنَ اللَّيْلِ مُظْلِمًا ۚ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ  [27]

(27) ለእነዚያም ኃጢአቶችን ለሠሩት የኃጢኣቲቱ ቅጣት በብጤዋ አለቻቸው። ውርደትም ትሸፍናቸዋለች። ለእነሱ ከአላህ (ቅጣት) ጠባቂ የላቸውም። ፊቶቻቸው ከጨለመ ሌሊት ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይኾናሉ። እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው። እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው።

(27) As for those who commit evil deeds, the recompense of an evil deed is the like thereof, and humiliation will cover them – there will be none to protect them from Allah – as if their faces were covered with patches of the darkest night. It is they who are the people of the Fire, they will abide therein forever.

وَيَوْمَ نَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ نَقُولُ لِلَّذِينَ أَشْرَكُوا مَكَانَكُمْ أَنتُمْ وَشُرَكَاؤُكُمْ ۚ فَزَيَّلْنَا بَيْنَهُمْ ۖ وَقَالَ شُرَكَاؤُهُم مَّا كُنتُمْ إِيَّانَا تَعْبُدُونَ  [28]

(28) ሁሉንም የምንሰበስባቸውን ከዚያም ለእነዚያ ለአጋሩት እናንተም ተጋሪዎችሁም ስፍራችሁን ያዙ የምንልበትን ተጋሪዎቻቸውም እኛን ትገዙ አልነበራችሁም የሚሉዋቸው ሲኾኑ በመካከላቸው የምንለይበትን ቀን (አስታውስ)።

(28) On the Day when We gather them all together, then We will say to those who associated partners with Us, “Stay where you are, you and your [so-called] partners!” Then We will separate them, and their partners will say, “It was not us that you used to worship!

فَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ إِن كُنَّا عَنْ عِبَادَتِكُمْ لَغَافِلِينَ  [29]

(29) «(ጣዖታቶቹ ለእኛ) ከመገዛታችሁ በእርግጥ ዘንጊዎች ለመኾናችንም በእኛና በእናንተ መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ» (ይሏቸዋል)።

(29) Allah is sufficient as a Witness between us and you that we were completely unaware of your worship.”

هُنَالِكَ تَبْلُو كُلُّ نَفْسٍ مَّا أَسْلَفَتْ ۚ وَرُدُّوا إِلَى اللَّهِ مَوْلَاهُمُ الْحَقِّ ۖ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ  [30]

(30) በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች። (አጋሪዎች) ወደ አላህም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ። ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ይጠፋቸዋል።

(30) Thereupon, every soul will realize what it did in the past. They will be brought back to Allah, their True Guardian, and all [false gods] that they fabricated will vanish from them.

قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ أَمَّن يَمْلِكُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَمَن يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ الْمَيِّتَ مِنَ الْحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ الْأَمْرَ ۚ فَسَيَقُولُونَ اللَّهُ ۚ فَقُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ  [31]

(31) «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው። «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል። «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው።

(31) Say, “Who provides for you from the heaven and earth? Or who owns [your] hearing and sight? Who brings forth the living from the dead and the dead from the living? Who controls all things?” They will say, “Allah.” Say, “Do you not then fear Him?

فَذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمُ الْحَقُّ ۖ فَمَاذَا بَعْدَ الْحَقِّ إِلَّا الضَّلَالُ ۖ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ  [32]

(32) እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው። ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ (ከውነት) እንዴት ትዞራላችሁ

(32) Such is Allah, your True Lord. What is beyond the truth except falsehood? So how could you be averted [from the truth]?”

كَذَٰلِكَ حَقَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ عَلَى الَّذِينَ فَسَقُوا أَنَّهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ  [33]

(33) እንደዚሁ የጌታህ ቃል በእነዚያ ባመጹት ላይ እነርሱ የማያምኑ መሆናቸው ተረጋገጠች።

(33) Thus the decree of your Lord has come true against the wicked, that they will never believe.

قُلْ هَلْ مِن شُرَكَائِكُم مَّن يَبْدَأُ الْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُ ۚ قُلِ اللَّهُ يَبْدَأُ الْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ  [34]

(34) «ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ውስጥ መፍጠርን የሚጀምር ከዚም የሚመልሰው አለን» በላቸው። «አላህ መፍጠርን ይጀምራል፤ ከዚያም ይመልሰዋል። ታዲያ (ከእምነት) እንዴት ትዞራላችሁ» በላቸው።

(34) Say, “Can any of your [so-called] partners originate creation then repeat it?” Say, “Allah originates creation and then repeats it. How are you then deluded [from the truth]?”

قُلْ هَلْ مِن شُرَكَائِكُم مَّن يَهْدِي إِلَى الْحَقِّ ۚ قُلِ اللَّهُ يَهْدِي لِلْحَقِّ ۗ أَفَمَن يَهْدِي إِلَى الْحَقِّ أَحَقُّ أَن يُتَّبَعَ أَمَّن لَّا يَهِدِّي إِلَّا أَن يُهْدَىٰ ۖ فَمَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ  [35]

(35) «ከምታጋሩዋቸው፤ ወደ እውነት የሚመራ አለን» በላቸው። «አላህ ወደ እውነቱ ይመራል። ወደ እውነት የሚመራው ሊከተሉት የተገባው ነውን ወይስ ካልተመራ በስተቀር የማይመራው ለእናንተም ምን (አስረጅ) አላችሁ እንዴት (በውሸት) ትፈርዳላችሁ» በላቸው።

(35) Say, “Can any of your [so-called] partners guide to the truth?” Say, “Allah guides to the truth.” Who is then more worthy to be followed: the One Who guides to the truth, or he who has no guidance unless he himself is guided? What is the matter with you, that you judge so?

وَمَا يَتَّبِعُ أَكْثَرُهُمْ إِلَّا ظَنًّا ۚ إِنَّ الظَّنَّ لَا يُغْنِي مِنَ الْحَقِّ شَيْئًا ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ بِمَا يَفْعَلُونَ  [36]

(36) አብዛኞቻቸውም ጥርጣሬን እንጂ አይከተሉም። ጥርጣሬ ከእውነት ምንም አያብቃቃም። አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው።

(36) Most of them follow nothing but assumptions. However, assumptions are of no avail against the truth. Indeed, Allah is All-Knowing of what they do.

وَمَا كَانَ هَٰذَا الْقُرْآنُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ  [37]

(37) ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ (ከሆነ ፍጡር) የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም። ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ (የተወረደ) ነው።

(37) This Qur’an could not possibly have been produced by anyone other than Allah. It is a confirmation of what came before it and an explanation of the Scripture, and is undoubtedly from the Lord of the worlds.

أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ ۖ قُلْ فَأْتُوا بِسُورَةٍ مِّثْلِهِ وَادْعُوا مَنِ اسْتَطَعْتُم مِّن دُونِ اللَّهِ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ  [38]

(38) በእውነትም «(ሙሐመድ) ቀጣጠፈው» ይላሉን «ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ። ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ። እውነተኞች እንደሆናችሁ (ተጋግዛችሁ አምጡ)» በላቸው።

(38) Or do they say, “He fabricated it?” Say, “Produce then one chapter like it, and call upon whoever you can other than Allah, if you are truthful!”

بَلْ كَذَّبُوا بِمَا لَمْ يُحِيطُوا بِعِلْمِهِ وَلَمَّا يَأْتِهِمْ تَأْوِيلُهُ ۚ كَذَٰلِكَ كَذَّبَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الظَّالِمِينَ  [39]

(39) ይልቁንም (ከቁርኣን) እውቀቱን ባላደረሱት ፍቹም ገና ባልመጣቸው ነገር አስተባበሉ። እንደዚሁ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል። የበዳዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት።

(39) But they rejected that which they did not comprehend, and its warning has not yet been fulfilled against them. Similarly, those who came before them refused to believe. Then see how was the end of the wrongdoers!

وَمِنْهُم مَّن يُؤْمِنُ بِهِ وَمِنْهُم مَّن لَّا يُؤْمِنُ بِهِ ۚ وَرَبُّكَ أَعْلَمُ بِالْمُفْسِدِينَ  [40]

(40) ከእነርሱም ውስጥ (ወደፊት) በርሱ የሚያምኑ አልሉ። ከእነርሱም በእርሱ የማያምኑ አልሉ። ጌታህም አጥፊዎቹን በጣም ዐዋቂ ነው።

(40) There are some among them who will believe in it and others will not. And your Lord knows best those who spread corruption.

وَإِن كَذَّبُوكَ فَقُل لِّي عَمَلِي وَلَكُمْ عَمَلُكُمْ ۖ أَنتُم بَرِيئُونَ مِمَّا أَعْمَلُ وَأَنَا بَرِيءٌ مِّمَّا تَعْمَلُونَ  [41]

(41) «ቢያስተባብሉህም ለእኔ ሥራዬ አለኝ። ለእናንተም ሠራችሁ አላችሁ። እናንተ ከምሠራው ነገር ንጹሕ ናችሁ። እኔም ከምትሠሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው።

(41) If they reject you, then say, “My deeds are mine and your deeds are yours. You are not responsible for what I do, nor am I responsible for what you do.”

وَمِنْهُم مَّن يَسْتَمِعُونَ إِلَيْكَ ۚ أَفَأَنتَ تُسْمِعُ الصُّمَّ وَلَوْ كَانُوا لَا يَعْقِلُونَ  [42]

(42) ከእነሱም ወደ አንተ የሚያዳምጡ (እና የማያምኑ) አልሉ። አንተ ደንቆሮዎችን የማያውቁ ቢኾኑም ታሰማለህን

(42) Among them are some who listen to you, but can you make the deaf hear, even though they have no understanding?

وَمِنْهُم مَّن يَنظُرُ إِلَيْكَ ۚ أَفَأَنتَ تَهْدِي الْعُمْيَ وَلَوْ كَانُوا لَا يُبْصِرُونَ  [43]

(43) ከእነሱም ወደ አንተ የሚመለከቱ አልሉ። አንተ (ልበ) ዕውራንን የማያዩ ቢኾኑም ትመራለህን

(43) And among them are some who look at you, but can you guide the blind even though they have no sight?

إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ النَّاسَ شَيْئًا وَلَٰكِنَّ النَّاسَ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ  [44]

(44) አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም። ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ።

(44) Allah does not wrong people in the least, but it is people who wrong themselves.

وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ كَأَن لَّمْ يَلْبَثُوا إِلَّا سَاعَةً مِّنَ النَّهَارِ يَتَعَارَفُونَ بَيْنَهُمْ ۚ قَدْ خَسِرَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِلِقَاءِ اللَّهِ وَمَا كَانُوا مُهْتَدِينَ  [45]

(45) (ከሓዲዎችን) ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ እንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው የሚተዋወቁ ሲሆኑ በምንሰበስባቸው ቀን (አስታውስ)። እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉት በእርግጥ ከሰሩ የተመሩም አልነበሩም።

(45) On the Day when He will gather them, it will be as if they had not stayed [in this world] except for an hour of a day, they will recognize one another. Those who denied the meeting of Allah will be losers, for they did not follow guidance.

وَإِمَّا نُرِيَنَّكَ بَعْضَ الَّذِي نَعِدُهُمْ أَوْ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِلَيْنَا مَرْجِعُهُمْ ثُمَّ اللَّهُ شَهِيدٌ عَلَىٰ مَا يَفْعَلُونَ  [46]

(46) የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን (በሕይወትህ) ብናሳይህ (መልካም ነው)። ወይም (ሳናሳይህ) ብንገድልህ መመለሻቸው ወደ እኛ ነው። ከዚያም አላህ በሚሠሩት ስራ ላይ ዐዋቂ ነው።

(46) Whether We show you [O Prophet] some of that [punishment] of which We warn them, or We cause you to die, to Us is their return, and Allah is a Witness to all what they do.

وَلِكُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولٌ ۖ فَإِذَا جَاءَ رَسُولُهُمْ قُضِيَ بَيْنَهُم بِالْقِسْطِ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ  [47]

(47) ለሕዝቦችም ሁሉ መልክተኛ አላቸው። መልክተኛውም በመጣ ጊዜ (ሲያስተባብሉ) በመካከላቸው በትክክል ይፈረዳል። እነርሱም አይበደሉም።

(47) For every people there is a messenger. When their messenger comes, it will be judged between them with justice, and they will not be wronged.

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا الْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ  [48]

(48) «እውነተኞችም ከሆናችሁ ይህ (የቅጣቱ) ቀጠሮ መቼ ነው» ይላሉ።

(48) They say, “When will this warning come to pass, if you are truthful?”

قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي ضَرًّا وَلَا نَفْعًا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۗ لِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ ۚ إِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ فَلَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ  [49]

(49) «ለራሴ ጉዳትንም ጥቅምንም አላህ ከሻው በስተቀር አልችልም። ለሕዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አልላቸው። ጊዜያቸው በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም» በላቸው።

(49) Say, “I have no power to harm or benefit myself, except by the Will of Allah.” For every people there is an appointed term; when their time comes, they can neither delay it for a moment, nor can they bring it forward.

قُلْ أَرَأَيْتُمْ إِنْ أَتَاكُمْ عَذَابُهُ بَيَاتًا أَوْ نَهَارًا مَّاذَا يَسْتَعْجِلُ مِنْهُ الْمُجْرِمُونَ  [50]

(50) «ቅጣቱ በሌሊት ወይም በቀን ቢመጣባችሁ፤ አጋሪዎቹ ከርሱ የሚቻኮሉበት ነገር ምንድን ነው ንገሩኝ» በላቸው።

(50) Say, “What do you think, if His punishment were to overtake you by night or by day, what part of it would the wicked seek to hasten?

أَثُمَّ إِذَا مَا وَقَعَ آمَنتُم بِهِ ۚ آلْآنَ وَقَدْ كُنتُم بِهِ تَسْتَعْجِلُونَ  [51]

(51) «ከዚያም (ቅጣቱ) በወደቀ ጊዜ በእርሱ አመናችሁበትን በእርግጥ በእርሱ የምትቻኮሉ የነበራችሁ ስትሆኑ አሁን» (ይባላሉ)።

(51) Will you believe in it only after it befalls you? Now! While you used to seek its hastening?”

ثُمَّ قِيلَ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا ذُوقُوا عَذَابَ الْخُلْدِ هَلْ تُجْزَوْنَ إِلَّا بِمَا كُنتُمْ تَكْسِبُونَ  [52]

(52) ከዚያም ለእነዚያ ለበደሉት፡- «ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ ትሠሩት የነበረችሁትን ዋጋ እንጂ አትመነዱም» ይባላሉ።

(52) Then the wrongdoers will be told, “Taste the everlasting punishment! Are you being recompensed except for what you used to earn?”

وَيَسْتَنبِئُونَكَ أَحَقٌّ هُوَ ۖ قُلْ إِي وَرَبِّي إِنَّهُ لَحَقٌّ ۖ وَمَا أَنتُم بِمُعْجِزِينَ  [53]

(53) እርሱም «እውነት ነውን» (ሲሉ) ይጠይቁሃል። «አዎን፤ በጌታዬ እምላለሁ፤ እርሱ እውነት ነው። እናንተም አምላጮች አይደላችሁም፤» በላቸው።

(53) They ask you, “Is it true?” Say, “Yes, by my Lord. It is certainly true, and you cannot escape it.”

وَلَوْ أَنَّ لِكُلِّ نَفْسٍ ظَلَمَتْ مَا فِي الْأَرْضِ لَافْتَدَتْ بِهِ ۗ وَأَسَرُّوا النَّدَامَةَ لَمَّا رَأَوُا الْعَذَابَ ۖ وَقُضِيَ بَيْنَهُم بِالْقِسْطِ ۚ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ  [54]

(54) ለበደለችም ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሁሉ ቢኖራት ኖሮ በእርግጥ በተበዠችበት ነበር። ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይገልጻሉ። በመካከላቸውም በትክክል ይፈረዳል። እነርሱም አይበደሉም።

(54) If every wrongdoer were to possess all that is on earth, he would surely offer it to ransom himself. They will hide their remorse when they see the punishment. They will be judged in all fairness, and they will not be wronged.

أَلَا إِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ أَلَا إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ  [55]

(55) ንቁ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው። ንቁ! የአላህ ተስፋ ቃል እርግጥ ነው። ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም።

(55) Indeed, to Allah belongs all that is in the heavens and earth. Allah’s promise is certainly true, but most of them do not know.

هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ  [56]

(56) እርሱ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ።

(56) It is He Who gives life and causes death, and to Him you will all be returned.

يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ  [57]

(57) እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ።

(57) O people, there has come to you an exhortation from your Lord, a cure for [illness] of the hearts, a guidance and mercy for the believers.

قُلْ بِفَضْلِ اللَّهِ وَبِرَحْمَتِهِ فَبِذَٰلِكَ فَلْيَفْرَحُوا هُوَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ  [58]

(58) «በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)። በዚህም ምክንያት ይደሰቱ። እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው።

(58) Say, “By Allah’s grace and His mercy let them therefore rejoice. It is much better than what they accumulate.”

قُلْ أَرَأَيْتُم مَّا أَنزَلَ اللَّهُ لَكُم مِّن رِّزْقٍ فَجَعَلْتُم مِّنْهُ حَرَامًا وَحَلَالًا قُلْ آللَّهُ أَذِنَ لَكُمْ ۖ أَمْ عَلَى اللَّهِ تَفْتَرُونَ  [59]

(59) «አላህ ከሲሳይ ለእናንተ ያወረደውን ከእርሱም እርምና የተፈቀደ ያደረጋችሁትን አያችሁን» በላቸው። «አላህ (ይህንን) ለእናንተ ፈቀደላችሁን ወይስ በአላህ ላይ ትቀጣጥፋላችሁ» በላቸው።

(59) Say [to the pagans], “What do you think about the provision that Allah has sent down to you, of which you made some unlawful and some lawful.” Say, “Has Allah given you permission or are you fabricating lies against Allah?”

وَمَا ظَنُّ الَّذِينَ يَفْتَرُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى النَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَشْكُرُونَ  [60]

(60) የእነዚያም በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ (ሰዎች) በትንሣኤ ቀን (በአላህ) ጥርጣሬያቸው ምንድን ነው (አይቀጡም ይመስላቸዋልን) አላህ በሰዎች ላይ (ቅጣትን ባለማቻኮል) የልግስና ባለቤት ነው። ግን አብዛኛዎቹ አያመሰግኑም።

(60) What do those who fabricate lies against Allah think of it on the Day of Judgment? Indeed, Allah is bountiful to people, yet most of them are ungrateful.

وَمَا تَكُونُ فِي شَأْنٍ وَمَا تَتْلُو مِنْهُ مِن قُرْآنٍ وَلَا تَعْمَلُونَ مِنْ عَمَلٍ إِلَّا كُنَّا عَلَيْكُمْ شُهُودًا إِذْ تُفِيضُونَ فِيهِ ۚ وَمَا يَعْزُبُ عَن رَّبِّكَ مِن مِّثْقَالِ ذَرَّةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي السَّمَاءِ وَلَا أَصْغَرَ مِن ذَٰلِكَ وَلَا أَكْبَرَ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ  [61]

(61) (ሙሐመድ ሆይ!) በማንኛውም ነገር ላይ አትሆንም፣ ከርሱም ከቁርኣን አታነብም፣ ማንኛውንም ሥራ (አንተም ሰዎቹም) አትሠሩም በገባችሁበት ጊዜ በናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ብንሆን እንጂ። በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል ከጌታህ (ዕውቀት) አይርቅም። ከዚያም ያነሰ የተለቀም የለም፤ በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ።

(61) Whatever matter you [O Prophet] may be engaged in, and whatever portion of the Qur’an you may recite, and whatever deed you [O people] may do, We are a Witness over you when you are engaged in it. Nothing is hidden from your Lord, not even an atom’s weight on earth nor in heaven, nor anything smaller or greater than that, except that it is [written] in a clear Record.

أَلَا إِنَّ أَوْلِيَاءَ اللَّهِ لَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ  [62]

(62) ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም።

(62) Indeed, the allies of Allah will have no fear, nor will they grieve.

الَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ  [63]

(63) (እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው።

(63) Those who believe and fear Allah.

لَهُمُ الْبُشْرَىٰ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ ۚ لَا تَبْدِيلَ لِكَلِمَاتِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ  [64]

(64) ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው።

(64) For them are glad tidings in the life of this world and in the Hereafter; there is no change in Allah’s words. That is the supreme triumph.

وَلَا يَحْزُنكَ قَوْلُهُمْ ۘ إِنَّ الْعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا ۚ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ  [65]

(65) ንግግራቸውም አያሳዝንህ። ኀይል ሁሉ በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና። እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነው።

(65) Do not let their words grieve you. Indeed, all power belongs to Allah. He is the All-Hearing, the All-Knowing.

أَلَا إِنَّ لِلَّهِ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ ۗ وَمَا يَتَّبِعُ الَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ شُرَكَاءَ ۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَإِنْ هُمْ إِلَّا يَخْرُصُونَ  [66]

(66) ንቁ! በሰማያት ያሉትና በምድርም ያሉት ሁሉ በእርግጥ የአላህ ናቸው፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ ተጋሪዎችን የሚጠሩ ምንን ይከተላሉ ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አይከተሉም። እነርሱም የሚዋሹ እንጂ አይደሉም።

(66) Indeed, to Allah belongs all those who are in the heavens and all those who are on earth. Those who invoke [so-called] partners besides Allah follow nothing but conjecture and they do nothing but lie.

هُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ اللَّيْلَ لِتَسْكُنُوا فِيهِ وَالنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَسْمَعُونَ  [67]

(67) እርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ)፤ ቀንንም (ልትሠሩበት) ብርሃን ያደረገላችሁ ነው። በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ።

(67) It is He Who made the night for you to rest therein and the day bright. Indeed, there are signs in this for people who listen.

قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا ۗ سُبْحَانَهُ ۖ هُوَ الْغَنِيُّ ۖ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۚ إِنْ عِندَكُم مِّن سُلْطَانٍ بِهَٰذَا ۚ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ  [68]

(68) «አላህ ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ። (ከሚሉት) ጥራት ተገባው። እርሱ ተብቃቂ ነው። በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ነው። እናንተ ዘንድ በዚህ (በምትሉት) ምንም አስረጅ የላችሁም። በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን

(68) They say, “Allah has taken a son.” Glory be to Him! He is the Self-Sufficient. To Him belongs all that is in the heavens and all that is on earth. You have no proof for this. Do you say about Allah something that you do not know?

قُلْ إِنَّ الَّذِينَ يَفْتَرُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ لَا يُفْلِحُونَ  [69]

(69) «እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ፈጽሞ አይድኑም፤» በላቸው።

(69) Say, “Those who fabricate lies against Allah will never succeed.”

مَتَاعٌ فِي الدُّنْيَا ثُمَّ إِلَيْنَا مَرْجِعُهُمْ ثُمَّ نُذِيقُهُمُ الْعَذَابَ الشَّدِيدَ بِمَا كَانُوا يَكْفُرُونَ  [70]

(70) (እነሱ) በቅርቢቱ ዓለም መጠቀም አላቸው። ከዚያም መመለሻቸው ወደእኛ ነው። ከዚያም ይክዱ በነበሩት ምክንያት ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን።

(70) A short enjoyment in this life, then to Us is their return, then We will make them taste the severe punishment because of their disbelief.

وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ نُوحٍ إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ إِن كَانَ كَبُرَ عَلَيْكُم مَّقَامِي وَتَذْكِيرِي بِآيَاتِ اللَّهِ فَعَلَى اللَّهِ تَوَكَّلْتُ فَأَجْمِعُوا أَمْرَكُمْ وَشُرَكَاءَكُمْ ثُمَّ لَا يَكُنْ أَمْرُكُمْ عَلَيْكُمْ غُمَّةً ثُمَّ اقْضُوا إِلَيَّ وَلَا تُنظِرُونِ  [71]

(71) የኑሕንም ወሬ በእነሱ ላይ አንብብላቸው። ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)። «ሕዝቦቼ ሆይ! በእናንተ ውስጥ ብዙ ጊዜ መቆየቴ በአላህም ተዓምራት ማስታወሴ በእናንተ ላይ የከበደ ቢሆን፤ በአላህ ላይ ተጠግቻለሁ። ነገራችሁንም ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ጋር ሆናችሁ ቁረጡ። ከዚያም ነገራችሁ በእናንተ ላይ ድብቅ አይሁን (ግለጹት)። ከዚያም (የሻችሁትን) ወደእኔ አድርሱ። ጊዜም አትስጡኝ (ከምንም አልቆጥራችሁም)።»

(71) Relate to them the story of Noah when he said to his people, “O my People, if my presence among you and my reminding you of Allah’s signs have become unbearable to you, then in Allah I have put my trust. So gather all your schemes, you and your [so-called] partners, leaving no room for uncertainty, then carry it out against me, and give me no respite.

فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَمَا سَأَلْتُكُم مِّنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَى اللَّهِ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُسْلِمِينَ  [72]

(72) «ብትሸሹም (አትጎዱኝም)። ከምንዳ ምንንም አልለምናችሁምና። ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም። ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ።»

(72) But if you turn away, then I have not asked you for any reward. My reward is only with Allah, and I have been commanded to be among those who submit to Allah [as Muslims].”

فَكَذَّبُوهُ فَنَجَّيْنَاهُ وَمَن مَّعَهُ فِي الْفُلْكِ وَجَعَلْنَاهُمْ خَلَائِفَ وَأَغْرَقْنَا الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُنذَرِينَ  [73]

(73) አስተባበሉትም። እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትንም በታንኳይቱ ውስጥ አዳንናቸው። (ለጠፉት) ምትኮችም አደረግናቸው። እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን አሰጠምን። የተስፈራሩትም ሕዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት።

(73) But they rejected him, so We saved him and those who were with him in the Ark, and made them successors; and We drowned those who rejected Our signs. Then see how was the end of those who were warned.

ثُمَّ بَعَثْنَا مِن بَعْدِهِ رُسُلًا إِلَىٰ قَوْمِهِمْ فَجَاءُوهُم بِالْبَيِّنَاتِ فَمَا كَانُوا لِيُؤْمِنُوا بِمَا كَذَّبُوا بِهِ مِن قَبْلُ ۚ كَذَٰلِكَ نَطْبَعُ عَلَىٰ قُلُوبِ الْمُعْتَدِينَ  [74]

(74) ከዚያም ከእርሱ በኋላ መልክተኞችን ወደየሕዝቦቻቸው ላክን። በግልጽ ማስረጃዎችም መጧቸው። (ከመላካቸው) በፊት በእርሱ ባስተባበሉበትም ነገር፤ የሚያምኑ አልሆኑም። እንደዚሁ በወሰን አላፊዎች ልቦች ላይ እናትማለን።

(74) Then We sent after him messengers to their [own] peoples; they came to them with clear proofs, but they would not believe in what they had already rejected beforehand. This is how We seal the hearts of the transgressors.

ثُمَّ بَعَثْنَا مِن بَعْدِهِم مُّوسَىٰ وَهَارُونَ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِ بِآيَاتِنَا فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ  [75]

(75) ከዚያም ከእነሱ ኋላ ሙሳንና ሃሩንን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቱ በተዓምራታችን ላክን። ኮሩም ትዕቢተኞች ሕዝቦችም ነበሩ።

(75) Then We sent after them Moses and Aaron with Our signs to Pharaoh and his chiefs, but they showed arrogance and were wicked people.

فَلَمَّا جَاءَهُمُ الْحَقُّ مِنْ عِندِنَا قَالُوا إِنَّ هَٰذَا لَسِحْرٌ مُّبِينٌ  [76]

(76) ከእኛም ዘንድ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ።

(76) So when the truth came to them from Us, they said, “This is indeed a clear magic!”

قَالَ مُوسَىٰ أَتَقُولُونَ لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَكُمْ ۖ أَسِحْرٌ هَٰذَا وَلَا يُفْلِحُ السَّاحِرُونَ  [77]

(77) ሙሳ አለ፡- «እውነቱን በመጣላችሁ ጊዜ ድግምተኞች የማይድኑ ሲኾኑ (እርሱ ድግምት ነው) ትላላችሁን ይህ ድግምት ነውን»

(77) Moses said, “Do you say this about the truth after it has come to you? Can this be magic? But magicians will never succeed.”

قَالُوا أَجِئْتَنَا لِتَلْفِتَنَا عَمَّا وَجَدْنَا عَلَيْهِ آبَاءَنَا وَتَكُونَ لَكُمَا الْكِبْرِيَاءُ فِي الْأَرْضِ وَمَا نَحْنُ لَكُمَا بِمُؤْمِنِينَ  [78]

(78) (እነርሱም) አሉ፡- «አባቶቻችንን በእርሱ ላይ ካገኘንበት ሃይማኖት ልታዞረን ለእናንተም በምድር ውስጥ ኩራት (ሹመት) ልትኖራችሁ መጣህብን እኛም ለእናንተ አማኞች አይደለንም።»

(78) They said, “Have you come to turn us away from what we found our forefathers following, so that you two might become supreme in the land? We will never believe in you!”

وَقَالَ فِرْعَوْنُ ائْتُونِي بِكُلِّ سَاحِرٍ عَلِيمٍ  [79]

(79) ፈርዖንም፡- «ዐዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ» አለ።

(79) Pharaoh said, “Bring me all learned magicians.”

فَلَمَّا جَاءَ السَّحَرَةُ قَالَ لَهُم مُّوسَىٰ أَلْقُوا مَا أَنتُم مُّلْقُونَ  [80]

(80) ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ሙሳ ለእነርሱ፡- «እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ» አላቸው።

(80) When the magicians came, Moses said to them, “Cast whatever you have to cast.”

فَلَمَّا أَلْقَوْا قَالَ مُوسَىٰ مَا جِئْتُم بِهِ السِّحْرُ ۖ إِنَّ اللَّهَ سَيُبْطِلُهُ ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُصْلِحُ عَمَلَ الْمُفْسِدِينَ  [81]

(81) (ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ ሙሳ አለ፡- «ያ በርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው። አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል። አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና።»

(81) When they did, Moses said, “All what you have brought is mere magic; Allah will surely make it useless, for Allah does not let the work of the mischief-makers to thrive.

وَيُحِقُّ اللَّهُ الْحَقَّ بِكَلِمَاتِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُجْرِمُونَ  [82]

(82) አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል።

(82) And Allah establishes the truth by His Words, even though the wicked abhor it.”

فَمَا آمَنَ لِمُوسَىٰ إِلَّا ذُرِّيَّةٌ مِّن قَوْمِهِ عَلَىٰ خَوْفٍ مِّن فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِمْ أَن يَفْتِنَهُمْ ۚ وَإِنَّ فِرْعَوْنَ لَعَالٍ فِي الْأَرْضِ وَإِنَّهُ لَمِنَ الْمُسْرِفِينَ  [83]

(83) ለሙሳም ከፈርዖንና ከሹማምንቶቻቸው ማሰቃየትን ከመፍራት ጋር ከወገኖቹ የኾኑ ጥቂቶች ትውልዶች እንጂ አላመኑለትም። ፈርዖንም በምድር ላይ በእርግጥ የኮራ ነበር። እርሱም በእርግጥ ወሰን ካለፉት ነበር።

(83) But none believed in Moses except some youth of his own people, despite their fear that Pharaoh and their own chiefs might persecute them. Pharaoh was indeed a tyrant in the land and he was truly one of the transgressors.

وَقَالَ مُوسَىٰ يَا قَوْمِ إِن كُنتُمْ آمَنتُم بِاللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُوا إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ  [84]

(84) ሙሳም አለ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ። ታዛዦች እንደ ሆናችሁ (በአላህ ላይ ትመካላችሁ)።»

(84) Moses said, “O my people, if you have faith in Allah, then put your trust in Him, if you have truly submitted.”

فَقَالُوا عَلَى اللَّهِ تَوَكَّلْنَا رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا فِتْنَةً لِّلْقَوْمِ الظَّالِمِينَ  [85]

(85) አሉም፡- «በአላህ ላይ ተጠጋን። ጌታችን ሆይ! ለበደለኞች ሕዝቦች መፈተኛ አታድርገን።»

(85) They said, “In Allah we put our trust. Our Lord, do not subject us to the persecution of the oppressive people,

وَنَجِّنَا بِرَحْمَتِكَ مِنَ الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ  [86]

(86) በእዝነትህም ከከሓዲዎች ሕዝቦች አድነን።

(86) and save us by Your mercy from the disbelieving people.”

وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ وَأَخِيهِ أَن تَبَوَّآ لِقَوْمِكُمَا بِمِصْرَ بُيُوتًا وَاجْعَلُوا بُيُوتَكُمْ قِبْلَةً وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ  [87]

(87) ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡- «ለሕዝቦቻችሁ በምስር ቤቶችን ሥሩ። ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ። ሶላትንም በደንቡ ስገዱ። (ለሙሳ) ምእምናኖቹንም አብስር» ስንል ላክን።

(87) We inspired Moses and his brother, “Provide houses for your people in Egypt, and make your houses face the qiblah direction, establish prayer, and give glad tidings to the believers.”

وَقَالَ مُوسَىٰ رَبَّنَا إِنَّكَ آتَيْتَ فِرْعَوْنَ وَمَلَأَهُ زِينَةً وَأَمْوَالًا فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا رَبَّنَا لِيُضِلُّوا عَن سَبِيلِكَ ۖ رَبَّنَا اطْمِسْ عَلَىٰ أَمْوَالِهِمْ وَاشْدُدْ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُوا حَتَّىٰ يَرَوُا الْعَذَابَ الْأَلِيمَ  [88]

(88) ሙሳም አለ፡- «ጌታችን ሆይ! አንተ ለፈርዖንና ለሹሞቹ በቅርቢቱ ሕይወት ጌጥን ብዙ ገንዘቦችንም በእርግጥ ሰጠህ። ጌታችን ሆይ! ከመንገድህ ያሳስቱ ዘንድ (ሰጠሃቸው)። ጌታችን ሆይ! ገንዘቦቻቸውን አጥፋ። በልቦቻቸውም ላይ አትም። አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ አያምኑምና።»

(88) Moses said, “Our Lord, You have given Pharaoh and his chiefs splendor and wealth in the life of this world. Our Lord, they may lead people astray from Your way. Our Lord, destroy their wealth and harden their hearts, so that they will not believe until they see the painful punishment.”

قَالَ قَدْ أُجِيبَت دَّعْوَتُكُمَا فَاسْتَقِيمَا وَلَا تَتَّبِعَانِّ سَبِيلَ الَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ  [89]

(89) (አላህም) «ጸሎታችሁ በእርግጥ ተሰምታለች። ቀጥም በሉ። የእነዚያንም የማያውቁትን ሰዎች መንገድ አትከተሉ» አላቸው።

(89) Allah said [to Moses and Aaron], “Your prayer is answered, so be steadfast on the straight path, and do not follow the way of those who do not know.”

وَجَاوَزْنَا بِبَنِي إِسْرَائِيلَ الْبَحْرَ فَأَتْبَعَهُمْ فِرْعَوْنُ وَجُنُودُهُ بَغْيًا وَعَدْوًا ۖ حَتَّىٰ إِذَا أَدْرَكَهُ الْغَرَقُ قَالَ آمَنتُ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا الَّذِي آمَنَتْ بِهِ بَنُو إِسْرَائِيلَ وَأَنَا مِنَ الْمُسْلِمِينَ  [90]

(90) የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው። ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው። መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- «አመንኩ። እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም። እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ።

(90) We led the Children of Israel across the sea, then Pharaoh and his soldiers pursued them out of transgression and tyranny, until when he was drowning, he said, “I believe that none has the right to be worshiped except He in whom the Children of Israel believe, and I am one of those who submit to Allah.”

آلْآنَ وَقَدْ عَصَيْتَ قَبْلُ وَكُنتَ مِنَ الْمُفْسِدِينَ  [91]

(91) ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክ ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን (አመንኩ ትላለህ)

(91) [He was told], “Now [you believe]? You had always been disobedient, and were one of the mischief-makers!

فَالْيَوْمَ نُنَجِّيكَ بِبَدَنِكَ لِتَكُونَ لِمَنْ خَلْفَكَ آيَةً ۚ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ النَّاسِ عَنْ آيَاتِنَا لَغَافِلُونَ  [92]

(92) ዛሬማ ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ (ከባሕሩ) እናወጣሃለን (ተባለ)። ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዓምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው።

(92) So today We will preserve your body, so that you will be an example for those who come after you, yet most people are heedless of Our signs.”

وَلَقَدْ بَوَّأْنَا بَنِي إِسْرَائِيلَ مُبَوَّأَ صِدْقٍ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ فَمَا اخْتَلَفُوا حَتَّىٰ جَاءَهُمُ الْعِلْمُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ يَقْضِي بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ  [93]

(93) የእስራኤልንም ልጆች ምስጉንን ስፍራ በእርግጥ አሰፈርናቸው። ከመልካም ሲሳዮችም ሰጠናቸው። ዕውቀትም (ቁርኣን) እስከመጣቸው ድረስ አልተለያዩም። ጌታህ በርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል።

(93) We settled the Children of Israel in a blessed land, and provided good things for their sustenance. They did not differ until after knowledge had come to them. Your Lord will judge between them on the Day of Resurrection concerning that over which they used to differ.

فَإِن كُنتَ فِي شَكٍّ مِّمَّا أَنزَلْنَا إِلَيْكَ فَاسْأَلِ الَّذِينَ يَقْرَءُونَ الْكِتَابَ مِن قَبْلِكَ ۚ لَقَدْ جَاءَكَ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُمْتَرِينَ  [94]

(94) ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ። እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል። ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን።

(94) If you are in doubt about what We have sent down to you [O Prophet], then ask those who read the Scripture before you. The truth has surely come to you from your Lord, so never be of those who doubt,

وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ الْخَاسِرِينَ  [95]

(95) ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን። ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና።

(95) and never be of those who reject the signs of Allah, for then you would be among the losers.

إِنَّ الَّذِينَ حَقَّتْ عَلَيْهِمْ كَلِمَتُ رَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ  [96]

(96) እነዚያ በእነርሱ ላይ የጌታህ ቃል የተረጋገጠባቸው አያምኑም።

(96) Indeed, those upon whom the decree of Allah is passed will not believe,

وَلَوْ جَاءَتْهُمْ كُلُّ آيَةٍ حَتَّىٰ يَرَوُا الْعَذَابَ الْأَلِيمَ  [97]

(97) ተዓምር ሁሉ ብትመጣላቸውም አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ ድረስ (አያምኑም)።

(97) even if every sign were to come to them, until they see the painful punishment.

فَلَوْلَا كَانَتْ قَرْيَةٌ آمَنَتْ فَنَفَعَهَا إِيمَانُهَا إِلَّا قَوْمَ يُونُسَ لَمَّا آمَنُوا كَشَفْنَا عَنْهُمْ عَذَابَ الْخِزْيِ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَمَتَّعْنَاهُمْ إِلَىٰ حِينٍ  [98]

(98) (ከዩኑስ በፊት ካለፉት ከተሞች) ያመነችና እምነትዋ የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም ግን የዩኑስ ሕዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው። እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው።

(98) There had never been any town that believed [after seeing the punishment] and benefited from its faith except the people of Jonah. When they believed, We removed from them the punishment of disgrace in the life of this world, and let them enjoy themselves for a while.

وَلَوْ شَاءَ رَبُّكَ لَآمَنَ مَن فِي الْأَرْضِ كُلُّهُمْ جَمِيعًا ۚ أَفَأَنتَ تُكْرِهُ النَّاسَ حَتَّىٰ يَكُونُوا مُؤْمِنِينَ  [99]

(99) ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር። ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን

(99) Had your Lord willed, all those on earth would have believed altogether. Will you then compel people to become believers?

وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تُؤْمِنَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَيَجْعَلُ الرِّجْسَ عَلَى الَّذِينَ لَا يَعْقِلُونَ  [100]

(100) ለማንኛዋም ነፍስ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ልታምን (ችሎታ) የላትም። (አላህ ለከፊሎቹ እምነትን ይሻል)። በእነዚያም በማያውቁት ላይ ርክሰትን ያደርጋል።

(100) No soul can believe except by Allah’s will, and He will bring disgrace upon those who do not use their intellect.

قُلِ انظُرُوا مَاذَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَا تُغْنِي الْآيَاتُ وَالنُّذُرُ عَن قَوْمٍ لَّا يُؤْمِنُونَ  [101]

(101) «በሰማያትና በምድር ያለውን (ተዓምር) ተመልከቱ» በላቸው። ተዓምራቶችና አስፈራሪዎችም ለማያምኑ ሕዝቦች አይጠቅሙም።

(101) Say, “Look at what is in the heavens and earth.” But the signs and warnings are of no avail to those who do not believe.

فَهَلْ يَنتَظِرُونَ إِلَّا مِثْلَ أَيَّامِ الَّذِينَ خَلَوْا مِن قَبْلِهِمْ ۚ قُلْ فَانتَظِرُوا إِنِّي مَعَكُم مِّنَ الْمُنتَظِرِينَ  [102]

(102) የእነዚያን ከእነሱ በፊት ያለፉትን ሕዝቦች ቀኖች ብጤ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን «ተጠባበቁ፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው።

(102) Are they waiting except for the same punishment that befell those who came before them? Say, “Then wait. I too am waiting with you.”

ثُمَّ نُنَجِّي رُسُلَنَا وَالَّذِينَ آمَنُوا ۚ كَذَٰلِكَ حَقًّا عَلَيْنَا نُنجِ الْمُؤْمِنِينَ  [103]

(103) ከዚያም መልክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን እናድናለን። እንደዚሁም ምእምናንን (ከጭንቅ ሁሉ) እናድናለን። (ይህ) በእኛ ላይ ተረጋገጠ።

(103) Then We will save Our messengers and those who believe. For We took it upon Us to save the believers.

قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِن كُنتُمْ فِي شَكٍّ مِّن دِينِي فَلَا أَعْبُدُ الَّذِينَ تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَٰكِنْ أَعْبُدُ اللَّهَ الَّذِي يَتَوَفَّاكُمْ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ  [104]

(104) «እናንተ ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም። ግን ያንን የሚገድላችሁን አላህን እገዛለሁ። ከምእምናን እንድሆንም ታዝዣለሁ» በላቸው።

(104) Say [O Prophet], “O people, if you are in doubt about my religion, then I do not worship those whom you worship besides Allah. But I worship Allah, Who causes you to die, and I have been commanded to be one of the believers.

وَأَنْ أَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ  [105]

(105) ፊትህንም (ወደ ቀጥታ) ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ። ከአጋሪዎቹም አትሁን።

(105) And be steadfast and exclusively devoted to true faith, and never be of those who associate partners with Allah.

وَلَا تَدْعُ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكَ وَلَا يَضُرُّكَ ۖ فَإِن فَعَلْتَ فَإِنَّكَ إِذًا مِّنَ الظَّالِمِينَ  [106]

(106) «ከአላህም በቀር የማይጠቅምንና የማይጎዳን አትገዛ። ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» (ተብያለሁ በላቸው)።

(106) Do not supplicate besides Allah that which can neither benefit nor harm you, for if you do so, you will be one of the wrongdoers.

وَإِن يَمْسَسْكَ اللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُ إِلَّا هُوَ ۖ وَإِن يُرِدْكَ بِخَيْرٍ فَلَا رَادَّ لِفَضْلِهِ ۚ يُصِيبُ بِهِ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ ۚ وَهُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ  [107]

(107) አላህም ጉዳትን ቢያደርስብህ ከእርሱ ሌላ ለእርሱ ገላጭ የለውም። በጎንም ነገር ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ የለም። ከባሮቹ የሚሻውን በእርሱ ይለይበታል። እርሱም መሓሪ አዛኝ ነው።

(107) If Allah afflicts you with harm, none can remove it except Him; if He wants good for you, none can withhold His bounty. He grants it to whom He wills of His slaves, and He is the All-Forgiving, the Most Merciful.”

قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۖ وَمَا أَنَا عَلَيْكُم بِوَكِيلٍ  [108]

(108) «እናንተ ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ። (በእርሱ) የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ነው። የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው (ጉዳቱ) በራሱ ላይ ነው። እኔም በእናንተ ላይ ተጠባበቂ አይደለሁም» በላቸው።

(108) Say, “O people, the truth has come to you from your Lord. So whoever accepts guidance, it is only for his own good; and whoever goes astray, it is only for his own loss. I am not a keeper over you.”

وَاتَّبِعْ مَا يُوحَىٰ إِلَيْكَ وَاصْبِرْ حَتَّىٰ يَحْكُمَ اللَّهُ ۚ وَهُوَ خَيْرُ الْحَاكِمِينَ  [109]

(109) ወዳንተም የሚወረደውን ነገር ተከተል። አላህም (በነሱ ላይ) እስከሚፈርድ ድረስ ታገስ። እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነው።

(109) Follow what is revealed to you, and be patient until Allah passes His judgment, for He is the Best of Judges.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

ሱረቱ አል ሐጅ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran Suretu Al-Hajj 22

ሱረቱ አል ሐጅ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran Suretu Al-Hajj 22 يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمْ ۚ إِنَّ زَلْزَلَةَ السَّاعَةِ…