Skip to content

Amharic Quran

ከመሞትህ በፊት ቁርአንን አንብብ! (Read the holy Quran before you die!)

  • Home
    • ቁርአንን እንረዳው
    • Download
  • ሱራዎች / Surah List
    • አል-ፋቲሐ (Al-Fatiha)
    • አል-በቀራህ (Al-Beqerah)
    • አል-ዒምራን (Al-Imran)
    • አል-ኒሳዕ (An-Nisa)
    • አል-ማዒዳህ (Al-Maidah) 
    • አንዓም (Al-anam)
    • አል አዕራፍ (Al-Aeraf)
    • አል አንፋል (Al-Anfal)
    • አል ተውባ (At-Tawba)
    • አል ዩኑስ (Yunus)
    • አል ሁድ (Al-Hud)
    • ዩሱፍ (Yusuf)
    • 13 – Ar-Ra’d
    • 14 – Ibrahim
    • አል ሒጅር (Al-Hijr)
    • 16 – An-Nahl
    • 17 – Al-Israa
    • ከህፍ (Al-Kahf )
    • 19 Maryam
    • ጧሃ (Taa-Ha)
    • 21 – Al-Anbiyaa
    • አል ሐጅ (Al-Hajj)
    • 23 – Al-Muminoon
    • 24 – An-Noor
    • 25 – Al -Furqan
    • 26 – Ash-Shu’araa
    • 27 – An-Naml
    • 28 – Al-Qasas
    • 29 – Al-Ankaboot
    • 30 – Ar-Room
    • 31 – Luqman
    • 32 – As-Sajda
    • 33 – Al-Ahzaab
    • 34 – Saba
    • 35 – Faatir
    • 36 – Yaseen
    • 37 – As-Saaffaat
    • 38 – Saad
    • 39 – Az-Zumar
    • 40 – Al-Ghaafir
    • 41 – Fussilat
    • 42 – Ash-Shura
    • 43 – Az-Zukhruf
    • 44 – Ad-Dukhaan
    • 45 – Al-Jaathiya
    • 46 – Al-Ahqaf
    • 47 – Muhammad
    • 48 – Al-Fath
    • 49 – Al-Hujuraat
    • 50 – Qaaf
    • 51 – Adh-Dhaariyat
    • 52 – At-Tur
    • 53 – An-Najm
    • 54 – Al-Qamar
    • 55 – Ar-Rahmaan
    • 56 – Al-Waaqia
    • 57 – Al-Hadid
    • 58 – Al-Mujaadila
    • 59 – Al-Hashr
    • 60 – Al-Mumtahana
    • 61 – As-Saff
    • 62 – Al-Jumu’a
    • 63 – Al-Munaafiqoon
    • 64 – At-Taghaabun
    • 65 – At-Talaaq
    • 66 – At-Tahrim
    • 67 – Al-Mulk
    • 68 – Al-Qalam
    • 69 – Al-Haaqqa
    • 70 – Al-Ma’aarij
    • 71 – Nooh
    • 72 – Al-Jinn
    • 73 – Al-Muzzammil
    • 74 – Al-Muddaththir
    • 75 – Al-Qiyaama
    • 76 – Al-Insaan
    • 77 – Al-Mursalaat
    • 78 – An-Naba
    • 79 – An-Naazi’aat
    • 80 – Abasa
    • 81 – At-Takwir
    • 82 – Al-Infitaar
    • 83 – Al-Mutaffifin
    • 84 – Al-Inshiqaaq
    • 85 – Al-Burooj
    • 86 – At-Taariq
    • 87 – Al-A’laa
    • 88 – Al-Ghaashiya
    • 89 – Al-Fajr
    • 90 – Al-Balad
    • 91 – Ash-Shams
    • 92 – Al-Lail
    • 93 – Ad-Dhuhaa
    • 94 – Ash-Sharh
    • 95 – At-Tin
    • 96 – Al-Alaq
    • 97 – Al-Qadr
    • 98 – Al-Bayyina
    • 99 – Az-Zalzala
    • 100 – Al-Aadiyaat
    • 101 – Al-Qaari’a
    • 102 – At-Takaathur
    • 103 – Al-Asr
    • 104 – Al-Humaza
    • 105 – Al-Fil
    • 106 – Quraish
    • 107 – Al-Maa’un
    • 108 – Al-Kawthar
    • 109 – Al-Kaafiroon
    • 110 – An-Nasr
    • 111 – Al-Masad
    • 112 – Al-Ikhlaas
    • 113 – Al-Falaq
    • 114 – An-Naas

55 – Ar-Rahmaan

Posted on December 10, 2023August 5, 2026 By Muhammed No Comments on 55 – Ar-Rahmaan
Amharic Quran, ቁርአንን እንረዳው

55 – Ar-Rahmaan

(1) አል-ረሕማን፤(1) The Most Compassionate,
(2) ቁርኣንን አስተማረ፡፡(2) has taught the Qur’an,
(3) ሰውን ፈጠረ፡፡(3) He created man,
(4) መናገርን አስተማረው፡፡(4) and taught him speech.
(5) ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡(5) The sun and the moon follow their precise courses,
(6) ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡(6) and the stars and trees prostrate [to Allah].
(7) ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡(7) He raised the heaven and enjoined justice
(8) በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡(8) so that you may not transgress the limits of justice.
(9) መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡(9) Therefore establish weights in justice, and do not give short measure.
(10) ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡(10) He has spread out the earth for all creatures,
(11) በውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡(11) in which there are fruits and palm trees with date stalks,
(12) የገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡(12) and grain having chaff, and fragrant plants.
(13) (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(13) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(14) ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡(14) He created man from dry clay like pottery,
(15) ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡(15) and He created the jinn from a smokeless flame of fire.
(16) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(16) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(17) የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡(17) [He is] Lord of the two sunrises and Lord of the two sunsets.
(18) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(18) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(19) ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡(19) He merges the two seas [of fresh and salty water] meeting together,
(20) (እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡(20) yet between them is a barrier so that they do not cross.
(21) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›(21) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(22) ሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡(22) Out of both of them emerge pearls and coral.
(23) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(23) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(24) እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡(24) To Him belong the sailing ships raised up in the sea like mountains.
(25) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(25) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(26) በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡(26) Everyone on earth will perish,
(27) የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡(27) but there will remain the Face of your Lord, full of Majesty and Honor.
(28) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(28) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(29) በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡(29) All those in the heavens and earth ask of Him; every day He is engaged in some matters.
(30) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›(30) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(31) እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡(31) We will attend to you, O two multitudes [men and jinn].
(32) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(32) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(33) የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም)(33) O assembly of jinn and mankind, if you are able to pass beyond the realms of the heavens and earth, then pass; you cannot pass without [Our] authority.
(34) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(34) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(35) በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡(35) There will be sent against you flames of fire and smoke, and you will not be able to defend yourselves.
(36) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(36) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(37) ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡(37) When the heaven is split asunder and becomes crimson, like red hide.
(38) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(38) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(39) በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡(39) On that Day no human or jinn will be asked about his sin.
(40) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(40) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(41) ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡(41) The wicked will be known by their marks, and will be seized by their forelocks and their feet.
(42) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡(42) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(43) ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡(43) [They will be told] “This is the Hell that the wicked used to deny.”
(44) በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡(44) They will go round between it and scalding water.
(45) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(45) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(46) በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡(46) For those who fear of standing before their Lord will be two Gardens.
(47) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(47) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(48) የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡(48) Shaded by spreading branches.
(49) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(49) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(50) በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡(50) In each there are two flowing springs.
(51) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(51) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(52) በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡(52) In each there are two kinds of every fruit.
(53) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(53) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(54) የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡(54) They will recline on couches lined with rich brocade, with the fruits of both gardens within reach.
(55) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(55) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(56) በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡(56) In them there will be maidens of restrained gaze, untouched before them by any man or jinn.
(57) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(57) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(58) ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡(58) As if they were rubies and pearls.
(59) ከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(59) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(60) የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?(60) Is the reward for goodness anything but goodness?
(61) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(61) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(62) ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡(62) And besides these two there will be two other gardens.
(63) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?›(63) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(64) ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡(64) Both of deepest green.
(65) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(65) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(66) በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡(66) In each there are two gushing springs.
(67) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(67) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(68) በውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡(68) In each there are fruits, palm trees, and pomegranates.
(69) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(69) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(70) በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡(70) In them there are beautiful noble women.
(71) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(71) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(72) በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡(72) Maidens with gorgeous eyes, secluded in pavilions.
(73) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(73) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(74) ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡(74) No human or jinn has ever touched them before.
(75) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ?(75) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(76) በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡(76) [They will be] reclining on green cushions and splendid carpets.
(77) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?(77) Then which of the favors of your Lord will you [men and jinn] deny?
(78) የግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡(78) Blessed is the Name of your Lord, the Lord of Majesty and Honor.
Tags: Amharic Quran Free Amharic Quran quran amharic quran in amharic ምዕራፍ 2 ሱረቱ ተባረክ ሱረቱ አል ሐጅ ሱረቱ አል ከህፍ ሱረቱ አትተውባ ሱረቱ ጡር ሱረቱል ሙልክ ሱረቱል በቀራህ ሱረቱል አል ማዒዳህ ሱረቱል አል-በቀራህ ሱረቱል ከህፍ ቁረአን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ትርጉም ቁርአን በአማርኛ ቅዱስ ቁርአን አልበቀራህ አማርኛ ቁርአን አማርኛ ቅዱስ ቁርአን የቁራን ትርጉም

Post navigation

❮ Previous Post: 54 – Al-Qamar
Next Post: 56 – Al-Waaqia ❯

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ሁሉም ሱራዎች / All Chapters

  1. ሱረቱ አል-ፋቲሃ – Al-Fātihah
  2. ሱረቱ አል-በቀራህ – Al-Baqarah
  3. ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን – Āl-‘Imrān
  4. ሱረቱ አን-ኒሳዕ – An-Nisā’
  5. ሱረቱ አል-ማኢዳህ – Al-Mā’idah
  6. ሱረቱ አል-አንዓም – Al-An‘ām
  7. ሱረቱ አል-አዕራፍ – Al-A‘rāf
  8. ሱረቱ አል-አንፋል – Al-Anfāl
  9. ሱረቱ አት-ተውባህ – At-Tawbah
  10. ሱረቱ ዩኑስ – Yūnus
  11. ሱረቱ ሁድ – Hūd
  12. ሱረቱ ዩኑስ – Yūsuf
  13. ሱረቱ አር-ረዕድ – Ar-Ra‘d
  14. ሱረቱ ኢብራሂም – Ibrāhīm
  15. ሱረቱ አል ሒጅር – Al-Hijr
  16. ሱረቱ አን–ነሕል – An-Nahl
  17. ሱረቱ አል ኢስራዕ – Al-Isrā’
  18. ሱረቱ አል ከህፍ – Al-Kahf
  19. ሱረቱ መርየም – Maryam
  20. ሱረቱ ጣሃ – Tā-ha
  21. ሱረቱ አል አንቢያ – Al-Anbiyā’
  22. ሱረቱ አል ሐጅ – Al-Hajj
  23. ሱረቱ አል–ሙዕሚኑን – Al-Mu’minūn
  24. ሱረቱ አልን ኑር – An-Noor
  25. ሱረቱ አል ፉርቃን – Al-Furqān
  26. ሱረቱ አሽ ሹዐራእ – Ash-Shu‘arā’
  27. ሱረቱ አን ነምል – An-Naml
  28. ሱረቱ አል ቀሰስ – Al-Qasas
  29. ሱረቱ አል ዐንከቡት – Al-‘Ankabūt
  30. ሱረቱ አር ሩም – Ar-Rūm
  31. ሱረቱ አል ሉቅማን – Luqmān
  32. ሱረቱ አስ ሰጅደህ – As-Sajdah
  33. ሱረቱ አል አሕዛብ – Al-Ahzāb
  34. ሱረቱ ሰበእ – Saba’
  35. ሱረቱ ፋጢር – Fātir
  36. ሱረቱ ያሲን – Yā-Sīn
  37. ሱረቱ አስ ሷፋት – As-Sāffāt
  38. ሱረቱ ሷድ – Sād
  39. ሱረቱ አዝ ዙመር – Az-Zumar
  40. ሱረቱ ጋፊር – Ghāfir
  41. ሱረቱ ፉሲለት – Fussilat
  42. ሱረቱ አሽ ሹራ – Ash-Shūra
  43. ሱረቱ አዝ ዙኽሩፍ – Az-Zukhruf
  44. ሱረቱ አድ ዱኻን – Ad-Dukhān
  45. ሱረቱ አል ጃሲያህ – Al-Jāthiyah
  46. ሱረቱ አል አህቃፍ – Al-Ahqāf
  47. ሱረቱ ሙሐመድ – Muhammad
  48. ሱረቱ አል ፈትህ – Al-Fat’h
  49. ሱረቱ አል ሑጅራት – Al-Hujurāt
  50. ሱረቱ ቃፍ – Qāf
  51. ሱረቱ አዝ ዛሪያት – Adh-Dhāriyāt
  52. ሱረቱ አጥ ጡር – At-Toor
  53. ሱረቱ አን ነጅም – An-Najm
  54. ሱረቱ አል ቀመር – Al-Qamar
  55. ሱረቱ አር ረሕማን – Ar-Rahmān
  56. ሱረቱ አል ዋቂዓህ – Al-Wāqi‘ah
  57. ሱረቱ አል ሐዲድ – Al-Hadīd
  58. ሱረቱ አል ሙጃደላ – Al-Mujādalah
  59. ሱረቱ አል ሐሽር – Al-Hashr
  60. ሱረቱ አል ሙምተሂና – Al-Mumtahanah
  61. ሱረቱ አስ ሶፍ – As-Saff
  62. ሱረቱ አል ጁሙዓህ – Al-Jumu‘ah
  63. ሱረቱ አል ሙናፊቁን – Al-Munāfiqūn
  64. ሱረቱ አት ተጋቡን – At-Taghābun
  65. ሱረቱ አጥ ጠላቅ – At-Talāq
  66. ሱረቱ አት ተህሪም – At-Tahrīm
  67. ሱረቱ አል ሙልክ – Al-Mulk
  68. ሱረቱ አል ቀለም – Al-Qalam
  69. ሱረቱ አል ሓቃህ – Al-Hāqqah
  70. ሱረቱ አል መዓሪጅ – Al-Ma‘ārij
  71. ሱረቱ ኑህ – Nūh
  72. ሱረቱ አል ጂን – Al-Jinn
  73. ሱረቱ አል ሙዘሚል – Al-Muzzammil
  74. ሱረቱ አል ሙደሲር – Al-Muddaththir
  75. ሱረቱ አል ቂያማህ – Al-Qiyāmah
  76. ሱረቱ አል ኢንሳን – Al-Insān
  77. ሱረቱ አል ሙርሰላት – Al-Mursalāt
  78. ሱረቱ አን ነበእ – An-Naba’
  79. ሱረቱ አን ናዚዓት – An-Nāzi‘āt
  80. ሱረቱ ዐበሰ – ‘Abasa
  81. ሱረቱ አት ተክዊር – At-Takwīr
  82. ሱረቱ አል ኢንፊጣር – Al-Infitār
  83. ሱረቱ አል ሙጠፊፊን – Al-Mutaffifīn
  84. ሱረቱ አል ኢንሺቃቅ – Al-Inshiqāq
  85. ሱረቱ አል ቡሩጅ – Al-Burūj
  86. ሱረቱ አጥ ጣሪቅ – At-Tāriq
  87. ሱረቱ አል አዕላ – Al-A‘lā
  88. ሱረቱ አል ጋሺያህ – Al-Ghāshiyah
  89. ሱረቱ አል ፈጅር – Al-Fajr
  90. ሱረቱ አል በለድ – Al-Balad
  91. ሱረቱ አሽ ሸምስ – Ash-Shams
  92. ሱረቱ አል ለይል – Al-Layl
  93. ሱረቱ አድ ዱሓ – Ad-Duhā
  94. ሱረቱ አሽ ሸርህ – Ash-Sharh
  95. ሱረቱ አት ቲን – At-Teen
  96. ሱረቱ አል ዐለቅ – Al-‘Alaq
  97. ሱረቱ አል ቀድር – Al-Qadr
  98. ሱረቱ አል–በይናህ – Al-Bayyinah
  99. ሱረቱ አል ዘልዘላህ – Az-Zalzalah
  100. ሱረቱ አል ዓዲያት – Al-‘Ādiyāt
  101. ሱረቱ አል ቃሪዓሕ – Al-Qāri‘ah
  102. ሱረቱ አት ተካሱር – At-Takāthur
  103. ሱረቱ አል ዓስር – Al-‘Asr
  104. ሱረቱ አል ሁመዛህ – Al-Humazah
  105. ሱረቱ አል ፊል – Al-Feel
  106. ሱረቱ ቁረይሽ – Quraysh
  107. ሱረቱ አል ማዑን – Al-Mā‘ūn
  108. ሱረቱ አል ከውሰር – Al-Kawthar
  109. ሱረቱ አል ካፊሩን – Al-Kāfirūn
  110. ሱረቱ አን ነስር – An-Nasr
  111. ሱረቱ አል መሰድ – Al-Masad
  112. ሱረቱ አል ኢኽላስ – Al-Ikhlās
  113. ሱረቱ አል ፈለቅ – Al-Falaq
  114. ሱረቱ አን ናስ – An-Nās

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ!
ይህ ዌየብሳይት ገና በመበልጸግ ላይ ያለ ስለሆነ ብዙ ስህተቶችን ልታገኙበት ትችላላችሁ። ስለዚህ እባካችሁ የምታገኟቸውን ስህተቶች በኮመንት ላይ እንዲታሳውቁን ስንል በአላህ ስም እንጠይቃለን።

Copyright © 2026 Amharic Quran.

Theme: Oceanly by ScriptsTown