89 – Al-Fajr
| (1) በጎህ እምላለሁ፡፡ | (1) By the dawn, |
| (2) በዐሥር ሌሊቶችም፡፡ | (2) and the ten nights, |
| (3) በጥንዱም በነጠላውም፡፡ | (3) and the even and the odd, |
| (4) በሌሊቱም በሚኼድ ጊዜ፡፡ | (4) and by the night when it comes, |
| (5) በዚህ (መሓላ) ለባለ አእምሮ ታላቅ መሓላ አለበትን? | (5) are these oaths not sufficient for those who have sense? |
| (6) ጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታውቅምን? | (6) Have you not considered how your Lord dealt with ‘Ād |
| (7) በኢረም በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፡፡ | (7) of Iram, who were people of great stature, |
| (8) በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በኾነችው፡፡ | (8) the like of whom had never been created in the land; |
| (9) በሰሙድም በእነዚያ በሸለቆው ቋጥኝን የቆረጡ በኾኑት፡፡ | (9) and Thamūd, who carved out the rocks in the Valley; |
| (10) በፈርዖንም ባለ ችካሎች በኾነው፡፡ | (10) and the mighty and powerful Pharaoh? |
| (11) በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፡፡ | (11) All of them transgressed in the land, |
| (12) በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በኾኑት (እንዴት እንደሠራ አታውቅምን?) | (12) and spread therein much corruption, |
| (13) በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው፡፡ | (13) so your Lord poured upon them a scourge of punishment. |
| (14) ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና፡፡ | (14) Indeed, your Lord is ever vigilant. |
| (15) ሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) «ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)» ይላል፡፡ | (15) As for man, when he is tested by his Lord by honoring him and bestowing blessings upon him, he says, “My Lord has [deservedly] honored me!” |
| (16) በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ «ጌታዬ አሳነሰኝ» ይላል፡፡ | (16) But when he is tested by restricting his provision, he says, “My Lord has [undeservedly] humiliated me!” |
| (17) ይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፡፡ | (17) No indeed! You are not kind to the orphan, |
| (18) ድኻንም በማብላት ላይ አትታዘዙም፡፡ | (18) nor do you urge one another to feed the needy, |
| (19) የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል ትበላላችሁ፡፡ | (19) and you greedily consume the entire inheritance, |
| (20) ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡ | (20) and love wealth immensely. |
| (21) ተዉ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ፤ | (21) No indeed! When the earth is crushed over and over, |
| (22) መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ (ለሱ ክብር በምስማማ መልኩ) በመጣ ጊዜ፤ | (22) and your Lord comes with the angels, rank after rank, |
| (23) ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው (ጥፋቱን) ይገነዘባል፡፡ መገንዘብም ለእርሱ ከየቱ? | (23) and Hell is brought near on that Day – this is when man will understand, but what is the use of that understanding? |
| (24) «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል፡፡ | (24) He will say, “Would that I had sent forth something for my [eternal] life!” |
| (25) በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡ | (25) None can punish as He punishes on that Day, |
| (26) የእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም፡፡ | (26) and none can bind as He binds. |
| (27) (ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ! | (27) [It will be said to the believer,] “O the tranquil soul! |
| (28) «ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡ | (28) Return to your Lord, well pleased and pleasing [to Him]. |
| (29) «በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡ | (29) Join My [righteous] slaves, |
| (30) ገነቴንም ግቢ፤» (ትባላለች)፡፡ | (30) and enter My Paradise.” |