Default Image
10, Dec 2023
42 – Ash-Shura

42 – Ash-Shura

(1) ሐ.መ (ሐ፡ ሚም)፡፡(1) Hā Mīm.
(2) ዐ.ሰ.ቀ (ዓይን ሲን ቃፍ)፤(2) ‘Ain Sīn Qāf.
(3) እንደዚሁ (በዚህች ሱራ ውስጥ እንዳለው) አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ወዳንተ ያወርዳል፡፡ ወደእነዚያም ከአንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች (አውርዷል)፡፡(3) This is how Allah, the Al-Mighty, All-Wise, sends revelation to you [O Prophet] and to those before you.
(4) በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው፡፡(4) To him belongs all that is in the heavens and all that is on earth, and He is the Most High, the Most Great.
(5) (ከአላህ ፍራቻ) ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፡፡ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያወድሳሉ፡፡ በምድርም ላለው ፍጡር ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ ንቁ! አላህ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነው፡፡(5) The heavens almost burst apart above them [in awe of Him], and the angels glorify the praises of their Lord, and seek forgiveness for those on earth. Indeed, Allah is the All-Forgiving, Most Merciful.
(6) እነዚያም ከእርሱ ሌላ (የጣዖታት) ረዳቶችን የያዙ፤ አላህ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ አንተም በእነርሱ ላይ ኀላፊ አይደለህም፡፡(6) As for those who take others as protectors besides Him, Allah is Watchful over them, and you are not a keeper over them.
(7) እንደዚሁም የከተሞች እናት የኾነችውን (የመካን ሰዎች) በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስፈራራ የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲኾን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የኾነን ቁርኣን ወደ አንተ አወረድን፡፡ (ከእነርሱም) ከፊሉ በገነት ውሰጥ ከፊሉም በእሳት ውስጥ ነው፡፡(7) Thus We have revealed to you an Arabic Qur’an, so that you may warn the Mother Town [of Makkah] and all those around it, and warn them of the Day of Gathering, about which there is no doubt; one party will be in Paradise and the other in the Blaze.
(8) አላህም በሻ ኖሮ (ባንድ ሃይማኖት ላይ) አንድ ሕዝብ ባደረጋቸው ነበር፡፡ ግን የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባል፡፡ በዳዮችም ለእነርሱ ወዳጅና ረዳት ምንም የላቸውም፡፡(8) If Allah had willed, He would have made all of them a single community, but He admits to His mercy whom He wills, and the wrongdoers will have no protector or helper.
(9) ከእርሱ ሌላ ረዳቶችን ያዙን? (ረዳቶች አይደሉም)፡፡ አላህም ረዳት እርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ሙታንን ሕያው ያደርጋል፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡(9) How do they take protectors besides Him? While Allah alone is the Protector, for He gives life to the dead, and He is Most Capable of all things.
(10) ከምንም ነገር ያ በእርሱ የተለያዩበት ፍርዱ ወደ አላህ ነው፡፡ «እርሱ አላህ ጌታዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ፣ ወደርሱም እመለሳለሁ» (በላቸው)፡፡(10) Whatever is the subject of your differences, it is for Allah to judge. Such is Allah, my Lord; in Whom I put my trust, and to Whom I turn,
(11) ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፡፡ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንስሳዎችም ዓይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ በእርሱ ያበዛችኋል፡፡ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡(11) the Originator of the heavens and earth. He has given you spouses of your own kind, and pairs of livestock; by which He causes you to multiply. There is nothing like unto Him, and He is the All-Hearing, the All-Seeing.
(12) የሰማያትና የምድር (ድልቦች) መከፈቻዎች የእርሱ ናቸው፡፡ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ እርሱ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡(12) To Him belong the keys of the heavens and earth; He extends provision to whom He wills or restricts it. Indeed, He is All-Knowing of all things.
(13) ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፡፡ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ወደእርሱ (እምነት) ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል፡፡(13) He has prescribed for you [believers] the same religion which He enjoined upon Noah, and that which We have revealed to you [O Prophet] and that which We enjoined upon Abraham, Moses, and Jesus: “You should uphold the religion and make no divisions therein.” What you are calling the polytheists to is very hard for them. Allah chooses for Himself whom He wills, and guides to Himself who turns to Him.
(14) (የሃይማኖት ሰዎች) ዕውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም፡፡ እስከ ተወሰነም ጊዜ (በማቆየት) ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፉን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው፡፡(14) They did not become divided except after the knowledge had come to them, out of envious rivalry between them. Were it not for a prior decree from your Lord until an appointed term, a decisive judgment would already have been passed between them. Indeed, those who inherited the Scripture after them are in disquieting doubt about it.
(15) ለዚህም (ድንጋጌ ሰዎችን) ጥራ፡፡ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል፡፡ «በላቸውም ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ፡፡ በመካከላችሁም ላስተካክል ታዘዝኩ፡፡ አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው፡፡ ለእኛ ሥራዎቻችን አልሉን፡፡ ለእናንተም ሥራዎቻችሁ አልሏችሁ፡፡ በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም፡፡ አላህ በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ መመለሻም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡»(15) Therefore call to that [religion, O Prophet] and keep to the straight path as you are commanded, and do not follow their desires, and say, “I believe in every Scripture that Allah has sent down, and I have been commanded to judge fairly among you. Allah is our Lord and your Lord. We have our deeds and you have your deeds. Let there be no [further] argument between us and you; Allah will bring us together, and to Him is the final return.”
(16) እነዚያም በአላህ (ሃይማኖት) ለእርሱ ተቀባይ ካገኘ በኋላ የሚከራከሩት ማስረጃቸው በጌታቸው ዘንድ ብልሹ ናት፡፡ በእነርሱም ላይ ቁጣ አልለባቸው፡፡ ለእነርሱም ብርቱ ቅጣት አልላቸው፡፡(16) As for those who argue about [the religion of] Allah after it has been accepted [by many], their argument carries no weight with their Lord; they have incurred [His] wrath, and for them there will be a severe punishment.
(17) አላህ ያ መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው፡፡ ሚዛንንም (እንደዚሁ)፡፡ ሰዓቲቱ ምንአልባት ቅርብ መኾንዋን ምን ያሳውቅሃል?(17) It is Allah Who has sent down the Book with the truth and justice. How could you know that perhaps the Hour is near?
(18) እነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ፡፡ እነዚያም ያመኑት ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው፡፡ እርሷም እውነት መኾንዋን ያውቃሉ፡፡ ንቁ! እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩት በእርግጥ (ከእውነት) በራቀ ስሕተት ውስጥ ናቸው፡፡(18) Those who disbelieve in it seek to hasten it, but those who believe are apprehensive about it and know that it is the truth. Indeed, those who dispute concerning the Hour have gone far astray.
(19) አላህ በባሮቹ ሩህሩህ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው (በሰፊው) ሲሳይን ይሰጣል፡፡ እርሱም ብርቱው አሸናፊው ነው፡፡(19) Allah is Kind to His slaves; He gives provision to whom He wills, and He is the All-Powerful, the All-Mighty.
(20) (በሥራው) የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የኾነ ሰው ለእርሱ በአዝመራው ላይ እንጨምርለታለን፡፡ የቅርቢቱንም ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የኾነ ሰው ከእርሷ (የተወሰነለትን ብቻ) እንሰጠዋለን፡፡ ለእርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ፋንታ የለውም፡፡(20) Whoever seeks the harvest of the Hereafter, We will increase for him his harvest; and whoever seeks the harvest of this world, We will give him thereof, but in the Hereafter he will have no share.
(21) ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አልሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ በደለኞችም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አልላቸው፡፡(21) Or do they have partners who have prescribed for them a religion that is not sanctioned by Allah? If it had not been for a prior decisive decree, the matter would have been judged between them. And for the wrongdoers there will surely be a painful punishment.
(22) በደለኞችን ከሠሩት ሥራ (ዋጋ በትንሣኤ ቀን) ፈሪዎች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ እርሱም በእነርሱ ላይ ወዳቂ ነው፡፡ እነዚያም ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት በገነቶች ጨፌዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው፡፡(22) You will see the wrongdoers apprehensive about what they have earned, which will inevitably befall them. But those who believe and do righteous deeds will be in meadows of the Gardens. They will have whatever they wish with their Lord; that is the great bounty.
(23) ይህ (ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ባሮቹን የሚያበስርበት ነው፡፡ «በእርሱ (መልክቴን በማድረሴ) ላይ በዝምድና ውዴታን እንጅ ዋጋን አልጠይቃችሁም» በላቸው፡፡ መልካሚቱንም ሥራ የሚሠራ ሰው ለእርሱ በእርሷ መልካምን ነገር እንጨምርለታለን፡፡ አላህ መሓሪ አመስጋኝ ነውና፡፡(23) That is the glad tidings that Allah gives to His slaves who believe and do righteous deeds. Say, “I do not ask you any reward for it, except kindness because of our kinship.” Whoever does a good deed, We will increase its merit for him. Indeed, Allah is All-Forgiving, Most Appreciative.
(24) ይልቁንም «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈ» ይላሉን? አላህም ቢሻ በልብህ ላይ ያትማል፡፡ አላህም ውሸቱን ያብብሳል፡፡ እውነቱንም በቃላቱ ያረጋግጣል፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡(24) Or do they say, “He has fabricated lies about Allah!”? But if Allah willed, He could seal up your heart. Allah wipes out falsehood and establishes the truth by His Words. Indeed, He is All-Knowing of what is in the hearts.
(25) እርሱም ያ ከባሮቹ ንስሓን የሚቀበል፣ ከኃጢአቶችም ይቅር የሚል፣ የምትሠሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ነው፡፡(25) It is He Who accepts repentance from His slaves and pardons sins, and He knows all what you do.
(26) እነዚያንም ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ልመናቸውን ይቀበላል፡፡ ከችሮታውም ይጨምርላቸዋል፡፡ ከሓዲዎቹም ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አልላቸው፡፡(26) He responds to [the supplication of] those who believe and do righteous deeds, and increases their reward out of His bounty. But for the disbelievers, there will be a severe punishment.
(27) አላህም ለባሮቹ (ሁሉ) ሲሳይን በዘረጋ ኖሮ በምድር ውስጥ (ሁሉም) ወሰን ባለፉ ነበር፡፡ ግን የሚሻውን በልክ ያወርዳል፡፡ እርሱ በባሮቹ ውስጥ ዐዋቂ ተመልካች ነውና፡፡(27) If Allah were to give abundant provision to [all] His slaves, they would transgress on earth; but He sends down what He wills in due measure. Indeed, He is All-Aware and All-Seeing of His slaves.
(28) እርሱም ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናምን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው፡፡ እርሱም ረዳቱ ምስጉኑ ነው፡፡(28) It is He Who sends down rain after they have lost hope, and spreads His mercy. He is the Guardian, the Praiseworthy.
(29) ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ ከተንቀሳቃሽም በሁለቱ ውስጥ የበተነውን (መፍጠሩ) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ እርሱም በሚሻ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው፡፡(29) Among His signs is the creation of the heavens and earth, and what He spread between them of all living creatures. And He is Most Capable of bringing them together whenever He wills.
(30) ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት (ኃጢኣት) ምክንያት ነው፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡(30) Whatever calamity befalls you is because of what your own hands have earned, and He overlooks much.
(31) እናንተም በምድር ውስጥ የምታቅቱ አይደላችሁም፡፡ ለእናንተም ከአላህ ሌላ ከዘመድም ከረዳትም ምንም የላችሁም፡፡(31) You cannot escape [Him] on earth, and you do not have besides Allah any protector or helper.
(32) በባሕር ላይ እንደ ጋራዎች ኾነው ተንሻላዮቹም (መርከቦች) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው፡፡(32) And among His signs are the ships, sailing in the sea like mountains.
(33) ቢሻ ነፋሱን የረጋ ያደርገዋል፡፡ በባሕሩም ጀርባ ላይ ረጊዎች ይኾናሉ፡፡ በዚህ ውሰጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለኾነ ሁሉ በእርግጥ ምልክቶች አልሉ፡፡(33) If He wills, He can still the wind, leaving the ships motionless on its surface. Indeed, there are signs in this for everyone who is steadfast and grateful.
(34) ወይም በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት (በማስጠም) ያጠፋቸዋል፡፡ ከብዙም ይቅርታ ያደርጋል፡፡(34) Or He can capsize them for what they committed, but He pardons much,
(35) (ከእነርሱ ለመበቀል)፤ እነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚከራከሩትን ለማወቅ (ያጠፋቸዋል)፡፡ ለእነርሱ ምንም መሸሻ የላቸውም፡፡(35) then those who dispute concerning Our signs will know that they have no escape.
(36) ከምንም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ አላህ ዘንድ ያለውም ምንዳ ለእነዚያ ለአመኑትና በጌታቸው ላይ ለሚጠጉት በላጭና ሁል ጊዜ ነዋሪ ነው፡፡(36) Whatever you have been given is but a short enjoyment of the life of this world, but what is with Allah is better and more lasting for those who believe and put their trust in their Lord;
(37) ለእነዚያም የኀጢኣትን ታላላቆችና ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነሱ የሚምሩት ለኾኑት፡፡(37) and those who avoid major sins and shameful deeds, and when they are angered, they forgive;
(38) ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፣ ሶላትንም ላዘወተሩት፣ ነገራቸውም በመካከላቸው መመካከር ለኾነው ከሰጠናቸውም ሲሳይ ለሚለግሱት፡፡(38) and those who respond to their Lord and establish prayer, and conduct their affairs by mutual consultation, and spend out of what We have provided for them;
(39) ለእነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ እነርሱ (በመሰሉ) የሚመልሱ ለኾኑት (በላጭና ኗሪ ነው)፡፡(39) and those who retaliate fairly when oppressed.
(40) የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም፡፡(40) The retribution of harm is its equivalent harm, but whoever pardons and seeks reconciliation, his reward is with Allah. Indeed, He does not like the wrongdoers.
(41) ከተበደሉም በኋላ (በመሰሉ) የተበቀሉ እነዚያ በነርሱ ላይ ምንም (የወቀሳ) መንገድ የለባቸውም፡፡(41) But whoever retaliates after being wronged, there is no blame on them.
(42) (የወቀሳ) መንገዱ በእነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት፣ በምድርም ውስጥ ያለ ሕግ ወሰን በሚያልፉት፣ ላይ ብቻ ነው፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አልላቸው፡፡(42) Blame is only on those who wrong people and transgress in the land without right. For such there will be a painful punishment.
(43) የታገስና ምሕረት ያደረገም ሰው ይህ ከምርሮቹ (ከተፈላጊዎቹ) ነገሮች ነው፡፡(43) But whoever observes patience and forgives, it is indeed a matter of great resolve.
(44) አላህ የሚያጠመውም ሰው ከእርሱ በኋለ ለእርሱ ምንም ረዳት የለውም፡፡ በደለኞችንም ቅጣቱን ባዩ ጊዜ ወደ መመለስ መንገድ አልለን? የሚሉ ሲኾኑ ታያቸዋለህ፡፡(44) Whoever Allah causes to stray, he will have no protector thereafter. You will see the wrongdoers, when they see the punishment, saying, “Is there any way to go back?”
(45) ከውርደት የተነሳ ፈሪዎች ኾነው በዓይን ስርቆት ወደእርሷ (ወደ እሳት) እያስተዋሉ በእርሷ ላይ የሚቀረቡ ሲኾኑ ታያቸዋለህ፡፡ እነዚያም ያመኑት፡- «በእርግጥ ከሳሪዎቹ እነዚያ ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በትንሣኤ ቀን ያከሰሩት ናቸው» ይላሉ፡፡(45) You will see them exposed to the Fire in a state of abject humiliation, looking with a stealthy glance. Those who believed will say, “The real losers are those who have lost themselves and their families on the Day of Resurrection.” Indeed, the wrongdoers will suffer an everlasting punishment.
(46) ንቁ! በደለኞች በእርግጥ በዘውታሪ ስቃይ ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዷቸው ዘመዶች ምንም አልነበሩዋቸውም፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ (ወደ እውነት) ምንም መንገድ የለውም፡፡(46) They will have no protectors to help them against Allah; whoever Allah causes to stray, there is no way [to guidance] for him.
(47) ለእርሱ መመለስ የሌለው ቀን ከአላህ ከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ፡፡ በዚያ ቀን ለእናንተ ምንም መጠጊያ የላችሁም፡፡ ለእናንተም ምንም መካድ የላችሁም፡፡(47) Respond to your Lord before there comes from Allah a Day that cannot be averted. On that Day you will have no refuge, nor will you be able to deny [your sins].
(48) ቢዞሩም (ወቀሳ የለብህም)፡፡ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡ ባንተ ላይ ማድረስ እንጅ ሌላ የለብህም፡፡ እኛም ሰውን ከእኛ የኾነን ጸጋ ባቀመስነው ጊዜ በርሷ ይደሰታል፡፡ እጆቻቸው ባስቀደሙትም ኀጢአት ምክንያት መከራ ብትደርስባቸው (ተስፋ ይቆርጣሉ)፡፡ ሰው (ውለታን) በጣም ከሐዲ ነውና፡፡(48) But if they turn away, We have not sent you as their keeper; your duty is only to convey the message. If We give man a taste of Our mercy, he exults in it; but when a calamity befalls them because of what their hands have sent forth, then man becomes totally ungrateful.
(49) የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡(49) To Allah belongs the dominion of the heavens and earth. He creates what He wills; He grants females to whom He wills and grants males to whom He wills,
(50) ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና፡፡(50) or grants them males and females; and He leaves whom He wills barren. Indeed, He is All-Knowing, Most Capable.
(51) ለሰውም አላህ በራእይ፣ ወይም ከግርዶ ወዲያ፣ ወይም መልክተኛን (መልአክን) የሚልክና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ (በገሃድ) ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡(51) It is not for a human being that Allah should speak to him except through revelation or from behind a veil, or by sending an angel-messenger to reveal what He wills by His permission. Indeed, He is Most High, All-Wise.
(52) እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡(52) Likewise We have revealed to you a revelation by Our command. You knew nothing of the Scripture or matters of faith, but We have made it [the Qur’an] a light by which We guide whom We will of Our slaves. And you are truly leading people to a straight path,
(53) ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ኾነው አላህ መንገድ (ትመራለህ)፡፡ ንቁ! ነገሮቹ ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡(53) the path of Allah, to Whom belongs all that is in the heavens and all that is on earth. Indeed, to Allah return all matters.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

102 – At-Takaathur

102 – At-Takaathur (1) በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡ (1) Competition for worldly gains distracts you [from Allah], (2) መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡…

35 – Faatir

35 – Faatir (1) ምስጋና ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ባለ ሶስት ሶስትም፣ ባለ አራት አራትም ክንፎች የኾኑ…

38 – Saad

38 – Saad (1) ጸ. (ሷድ) የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ (ብዙ አማልክት አሉ እንደሚሉት አይደለም)፡፡ (1) Sād. By the Qur’an, full of…