Skip to content

Amharic Quran

ከመሞትህ በፊት ቁርአንን አንብብ! (Read the holy Quran before you die!)

  • Home
    • ቁርአንን እንረዳው
    • Download
  • ሱራዎች / Surah List
    • አል-ፋቲሐ (Al-Fatiha)
    • አል-በቀራህ (Al-Beqerah)
    • አል-ዒምራን (Al-Imran)
    • አል-ኒሳዕ (An-Nisa)
    • አል-ማዒዳህ (Al-Maidah) 
    • አንዓም (Al-anam)
    • አል አዕራፍ (Al-Aeraf)
    • አል አንፋል (Al-Anfal)
    • አል ተውባ (At-Tawba)
    • አል ዩኑስ (Yunus)
    • አል ሁድ (Al-Hud)
    • ዩሱፍ (Yusuf)
    • 13 – Ar-Ra’d
    • 14 – Ibrahim
    • አል ሒጅር (Al-Hijr)
    • 16 – An-Nahl
    • 17 – Al-Israa
    • ከህፍ (Al-Kahf )
    • 19 Maryam
    • ጧሃ (Taa-Ha)
    • 21 – Al-Anbiyaa
    • አል ሐጅ (Al-Hajj)
    • 23 – Al-Muminoon
    • 24 – An-Noor
    • 25 – Al -Furqan
    • 26 – Ash-Shu’araa
    • 27 – An-Naml
    • 28 – Al-Qasas
    • 29 – Al-Ankaboot
    • 30 – Ar-Room
    • 31 – Luqman
    • 32 – As-Sajda
    • 33 – Al-Ahzaab
    • 34 – Saba
    • 35 – Faatir
    • 36 – Yaseen
    • 37 – As-Saaffaat
    • 38 – Saad
    • 39 – Az-Zumar
    • 40 – Al-Ghaafir
    • 41 – Fussilat
    • 42 – Ash-Shura
    • 43 – Az-Zukhruf
    • 44 – Ad-Dukhaan
    • 45 – Al-Jaathiya
    • 46 – Al-Ahqaf
    • 47 – Muhammad
    • 48 – Al-Fath
    • 49 – Al-Hujuraat
    • 50 – Qaaf
    • 51 – Adh-Dhaariyat
    • 52 – At-Tur
    • 53 – An-Najm
    • 54 – Al-Qamar
    • 55 – Ar-Rahmaan
    • 56 – Al-Waaqia
    • 57 – Al-Hadid
    • 58 – Al-Mujaadila
    • 59 – Al-Hashr
    • 60 – Al-Mumtahana
    • 61 – As-Saff
    • 62 – Al-Jumu’a
    • 63 – Al-Munaafiqoon
    • 64 – At-Taghaabun
    • 65 – At-Talaaq
    • 66 – At-Tahrim
    • 67 – Al-Mulk
    • 68 – Al-Qalam
    • 69 – Al-Haaqqa
    • 70 – Al-Ma’aarij
    • 71 – Nooh
    • 72 – Al-Jinn
    • 73 – Al-Muzzammil
    • 74 – Al-Muddaththir
    • 75 – Al-Qiyaama
    • 76 – Al-Insaan
    • 77 – Al-Mursalaat
    • 78 – An-Naba
    • 79 – An-Naazi’aat
    • 80 – Abasa
    • 81 – At-Takwir
    • 82 – Al-Infitaar
    • 83 – Al-Mutaffifin
    • 84 – Al-Inshiqaaq
    • 85 – Al-Burooj
    • 86 – At-Taariq
    • 87 – Al-A’laa
    • 88 – Al-Ghaashiya
    • 89 – Al-Fajr
    • 90 – Al-Balad
    • 91 – Ash-Shams
    • 92 – Al-Lail
    • 93 – Ad-Dhuhaa
    • 94 – Ash-Sharh
    • 95 – At-Tin
    • 96 – Al-Alaq
    • 97 – Al-Qadr
    • 98 – Al-Bayyina
    • 99 – Az-Zalzala
    • 100 – Al-Aadiyaat
    • 101 – Al-Qaari’a
    • 102 – At-Takaathur
    • 103 – Al-Asr
    • 104 – Al-Humaza
    • 105 – Al-Fil
    • 106 – Quraish
    • 107 – Al-Maa’un
    • 108 – Al-Kawthar
    • 109 – Al-Kaafiroon
    • 110 – An-Nasr
    • 111 – Al-Masad
    • 112 – Al-Ikhlaas
    • 113 – Al-Falaq
    • 114 – An-Naas

74 – Al-Muddaththir

Posted on December 11, 2023August 5, 2026 By Muhammed No Comments on 74 – Al-Muddaththir
Amharic Quran, ቁርአንን እንረዳው

74 – Al-Muddaththir

(1) አንተ (ልብስህን) ደራቢው ሆይ!(1) O you covered [in your cloak],
(2) ተነሳ አስጠንቅቅም፡፡(2) arise and warn,
(3) ጌታህንም አክብር፡፡(3) and proclaim the greatness of your Lord,
(4) ልብስህንም አጥራ፡፡(4) and purify your garments,
(5) ጣዖትንም ራቅ፡፡(5) and shun idol worshiping,
(6) ማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ፤ (በረከትን) አትለግስለለ(6) and do not do a favor for a greater return,
(7) ለጌታህም (ትዕዛዝ) ታገሥ፡፡(7) and be patient for the sake of your Lord.
(8) በቀንዱም በተነፋ ጊዜ (ነገሩ ይበረታል)፡፡(8) When the Trumpet is sounded,
(9) ይህም (ጊዜ) ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡(9) that Day will be a difficult day,
(10) በከሓዲዎች ላይ ገር ያልኾነ ነው፡፡(10) not easy for the disbelievers.
(11) አንድ ኾኖ ከፈጠርኩት ሰው ጋር ተዎኝ (እኔ እበቃሃለሁ)፡፡(11) Leave me to deal with the one whom I created lonely [having no wealth or children etc],
(12) ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በያይነቱ) ያደረግሁለት፡፡(12) and gave him abundant wealth,
(13) (በያደባባዩ) ተገኝዎች የኾኑ ወንዶች ልጆችንም፡፡(13) and sons by his side,
(14) ለእርሱም (ኑሮውን) መዘርጋትን የዘረጋሁለት (ከኾነ ሰው ገር ተዎኝ)፡፡(14) and gave him a life of comfort and power,
(15) ከዚያም ልጨምርለት ይከጅላል፡፡(15) yet he aspires that I should give him more.
(16) ይከልከል፤ እርሱ ለአንቀጾቻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበር፡፡(16) By no means! For he has been stubborn against Our verses.
(17) በእርግጥ ችግርን አስገድደዋለሁ፡፡(17) I will subject him to an unbearable punishment.
(18) እርሱ (በቁርኣን ነገር) ሐሰበ፤ ገመተም፡፡(18) For he reflected and plotted [against the Qur’an].
(19) ተረገመም፤ እንዴት ገመተ!(19) May he perish, how he plotted!
(20) ከዚያም (ከሞት በኋላ) ተረገመ፡፡ እንዴት ገመተ!(20) Again, may he perish, how he plotted!
(21) ከዚያም እንደ ገና (በቁርኣኑ ነገር) ተመለከተ፡፡(21) Then he looked around,
(22) ከዚያም ፊቱን አጨፈገገ፤ አኮማተረም፡፡(22) then he frowned and scowled,
(23) ከዚያም (ከማመን) ዞረ፤ ኮራም፡፡(23) then turned away with arrogance,
(24) አለም «ይህ (ከሌላ) የሚቀዳ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም፡፡(24) then said, “This is nothing but magic from the past.
(25) «ይህ የሰው ቃል እንጅ ሌላ አይደለም፡፡»(25) This is nothing but the words of a man.”
(26) በሰቀር ውስጥ በእርግጥ አገባዋለሁ፡፡(26) Soon I will make him burn in the Scorching Fire.
(27) ሰቀር ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?(27) How do you know what Scorching Fire is?
(28) (ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም አትተውምም፡፡(28) It leaves nothing and spares no one,
(29) ቆዳን በጣም አክሳይ ናት፡፡(29) scorching the skin.
(30) በእርሷም ላይ አሥራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት፡፡(30) It is overseen by nineteen [angels].
(31) የእሳትንም ዘበኞች መላእክት እንጅ ሌላ አላደረግንም፡፡ ቁጥራቸውንም ለእነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም፡፡ እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት እንዲያረጋግጡ፣ እነዚያም ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፣ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምእምናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፣ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው (መናፍቃን)፣ ከሓዲዎችም አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል? እንዲሉ (እንጅ አላደረግንም)፡፡ እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ የጌታህንም ሰራዊት (ልክ) ከርሱ በቀር ማንም አያውቅም፡፡ እርሷም (የሰቀር እሳት) ለሰዎች መገሰጫ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡(31) We have only appointed angels as keepers of the Fire, and We have only made their number as a test for the disbelievers, so that those who were given the Scripture may have certainty and the believers may increase in faith; and neither those who were given the Scripture nor the believers may have any doubts; and so that those [hypocrites] in whose hearts is sickness and the disbelievers may say, “What does Allah mean by this number?” Thus Allah causes to stray whom He wills and guides whom He wills, and none knows the soldiers of your Lord but He. This is but a reminder to mankind.
(32) (ከክህደት) ይከልከሉ፡፡ በጨረቃ እምላለሁ፡፡(32) No indeed! By the moon,
(33) በሌሊቱም በኼደ ጊዜ፡፡(33) and by the night when it departs,
(34) በንጋቱም ባበራ ጊዜ፡፡(34) and by the dawn when it brightens,
(35) እርሷ (ሰቀር) ከታላላቆቹ (አደጋዎች) አንዷ ናት፡፡(35) Hellfire is indeed one of the greatest matters,
(36) ለሰዎች አስፈራሪ ስትኾን፡፡(36) a warning to mankind,
(37) ከእናንተ (ወደ በጎ ነገር) መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለሻ ሰው (አስፈራሪ ስትኾኑ)፡፡(37) to whoever among you chooses to advance or regress.
(38) ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡(38) Every soul is held in pledge for its deeds,
(39) የቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ፡፡(39) except the People of the Right,
(40) (እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡(40) who will be in gardens, asking one another
(41) ከአመጸኞቹ ኹነታ፡፡(41) about the wicked:
(42) (ይሏቸዋልም) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?»(42) “What brought you to Hell?”
(43) (እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡(43) They will say, “We were not among those who prayed,
(44) «ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡(44) nor did we feed the poor,
(45) «ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡(45) and we indulged in falsehood along with those who indulged in it,
(46) «በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡(46) and we denied the Day of Judgment,
(47) «እርግጠኛው (ሞት) እስከ መጣን ድረስ፡፡»(47) until the certainty [of death] came to us.”
(48) የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡(48) So the intercession of intercessors will not benefit them.
(49) ከግሣጼዬም (ከቁርኣን) የሚያፈገፍጉት ለእነርሱ ምን አልላቸው?(49) Then what is the matter with them that they turn away from the Reminder,
(50) እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዮች ይመስላሉ፡፡(50) as if they were terrified wild asses,
(51) ከዐንበሳ የሸሹ፡፡(51) fleeing from a lion?
(52) ይልቁንም ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ የተዘረጉ ጽሑፎችን እንዲስሰጥ ይፈልጋል፡፡(52) In fact, each one of them desires that open [divine] letters be sent to each of them.
(53) ይከልከሉ፡፡ ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) አይፈሩም፡፡(53) By no means! They rather do not fear the Hereafter.
(54) ይከልከሉ፡፡ እርሱ (ቁርኣን) መገሠጫ ነው፡፡(54) No indeed! This [Qur’an] is a reminder.
(55) ስለዚህ የሻ ሰው ይገሰጽበታል፡፡(55) So whoever wills may take heed.
(56) አላህም ካልሻ በስተቀር አይገሠጹም፡፡ እርሱ (አላህ) የመፈራት ባለቤት የምሕረትም ባለቤት ነው፡፡(56) But they will not take heed unless Allah so wills. He is most worthy to be feared and most worthy to forgive.
Tags: Amharic Quran Free Amharic Quran quran amharic quran in amharic ምዕራፍ 2 ሱረቱ ተባረክ ሱረቱ አል ሐጅ ሱረቱ አል ከህፍ ሱረቱ አትተውባ ሱረቱ ጡር ሱረቱል ሙልክ ሱረቱል በቀራህ ሱረቱል አል ማዒዳህ ሱረቱል አል-በቀራህ ሱረቱል ከህፍ ቁረአን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ትርጉም ቁርአን በአማርኛ ቅዱስ ቁርአን አልበቀራህ አማርኛ ቁርአን አማርኛ ቅዱስ ቁርአን የቁራን ትርጉም

Post navigation

❮ Previous Post: 73 – Al-Muzzammil
Next Post: 75 – Al-Qiyaama ❯

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ሁሉም ሱራዎች / All Chapters

  1. ሱረቱ አል-ፋቲሃ – Al-Fātihah
  2. ሱረቱ አል-በቀራህ – Al-Baqarah
  3. ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን – Āl-‘Imrān
  4. ሱረቱ አን-ኒሳዕ – An-Nisā’
  5. ሱረቱ አል-ማኢዳህ – Al-Mā’idah
  6. ሱረቱ አል-አንዓም – Al-An‘ām
  7. ሱረቱ አል-አዕራፍ – Al-A‘rāf
  8. ሱረቱ አል-አንፋል – Al-Anfāl
  9. ሱረቱ አት-ተውባህ – At-Tawbah
  10. ሱረቱ ዩኑስ – Yūnus
  11. ሱረቱ ሁድ – Hūd
  12. ሱረቱ ዩኑስ – Yūsuf
  13. ሱረቱ አር-ረዕድ – Ar-Ra‘d
  14. ሱረቱ ኢብራሂም – Ibrāhīm
  15. ሱረቱ አል ሒጅር – Al-Hijr
  16. ሱረቱ አን–ነሕል – An-Nahl
  17. ሱረቱ አል ኢስራዕ – Al-Isrā’
  18. ሱረቱ አል ከህፍ – Al-Kahf
  19. ሱረቱ መርየም – Maryam
  20. ሱረቱ ጣሃ – Tā-ha
  21. ሱረቱ አል አንቢያ – Al-Anbiyā’
  22. ሱረቱ አል ሐጅ – Al-Hajj
  23. ሱረቱ አል–ሙዕሚኑን – Al-Mu’minūn
  24. ሱረቱ አልን ኑር – An-Noor
  25. ሱረቱ አል ፉርቃን – Al-Furqān
  26. ሱረቱ አሽ ሹዐራእ – Ash-Shu‘arā’
  27. ሱረቱ አን ነምል – An-Naml
  28. ሱረቱ አል ቀሰስ – Al-Qasas
  29. ሱረቱ አል ዐንከቡት – Al-‘Ankabūt
  30. ሱረቱ አር ሩም – Ar-Rūm
  31. ሱረቱ አል ሉቅማን – Luqmān
  32. ሱረቱ አስ ሰጅደህ – As-Sajdah
  33. ሱረቱ አል አሕዛብ – Al-Ahzāb
  34. ሱረቱ ሰበእ – Saba’
  35. ሱረቱ ፋጢር – Fātir
  36. ሱረቱ ያሲን – Yā-Sīn
  37. ሱረቱ አስ ሷፋት – As-Sāffāt
  38. ሱረቱ ሷድ – Sād
  39. ሱረቱ አዝ ዙመር – Az-Zumar
  40. ሱረቱ ጋፊር – Ghāfir
  41. ሱረቱ ፉሲለት – Fussilat
  42. ሱረቱ አሽ ሹራ – Ash-Shūra
  43. ሱረቱ አዝ ዙኽሩፍ – Az-Zukhruf
  44. ሱረቱ አድ ዱኻን – Ad-Dukhān
  45. ሱረቱ አል ጃሲያህ – Al-Jāthiyah
  46. ሱረቱ አል አህቃፍ – Al-Ahqāf
  47. ሱረቱ ሙሐመድ – Muhammad
  48. ሱረቱ አል ፈትህ – Al-Fat’h
  49. ሱረቱ አል ሑጅራት – Al-Hujurāt
  50. ሱረቱ ቃፍ – Qāf
  51. ሱረቱ አዝ ዛሪያት – Adh-Dhāriyāt
  52. ሱረቱ አጥ ጡር – At-Toor
  53. ሱረቱ አን ነጅም – An-Najm
  54. ሱረቱ አል ቀመር – Al-Qamar
  55. ሱረቱ አር ረሕማን – Ar-Rahmān
  56. ሱረቱ አል ዋቂዓህ – Al-Wāqi‘ah
  57. ሱረቱ አል ሐዲድ – Al-Hadīd
  58. ሱረቱ አል ሙጃደላ – Al-Mujādalah
  59. ሱረቱ አል ሐሽር – Al-Hashr
  60. ሱረቱ አል ሙምተሂና – Al-Mumtahanah
  61. ሱረቱ አስ ሶፍ – As-Saff
  62. ሱረቱ አል ጁሙዓህ – Al-Jumu‘ah
  63. ሱረቱ አል ሙናፊቁን – Al-Munāfiqūn
  64. ሱረቱ አት ተጋቡን – At-Taghābun
  65. ሱረቱ አጥ ጠላቅ – At-Talāq
  66. ሱረቱ አት ተህሪም – At-Tahrīm
  67. ሱረቱ አል ሙልክ – Al-Mulk
  68. ሱረቱ አል ቀለም – Al-Qalam
  69. ሱረቱ አል ሓቃህ – Al-Hāqqah
  70. ሱረቱ አል መዓሪጅ – Al-Ma‘ārij
  71. ሱረቱ ኑህ – Nūh
  72. ሱረቱ አል ጂን – Al-Jinn
  73. ሱረቱ አል ሙዘሚል – Al-Muzzammil
  74. ሱረቱ አል ሙደሲር – Al-Muddaththir
  75. ሱረቱ አል ቂያማህ – Al-Qiyāmah
  76. ሱረቱ አል ኢንሳን – Al-Insān
  77. ሱረቱ አል ሙርሰላት – Al-Mursalāt
  78. ሱረቱ አን ነበእ – An-Naba’
  79. ሱረቱ አን ናዚዓት – An-Nāzi‘āt
  80. ሱረቱ ዐበሰ – ‘Abasa
  81. ሱረቱ አት ተክዊር – At-Takwīr
  82. ሱረቱ አል ኢንፊጣር – Al-Infitār
  83. ሱረቱ አል ሙጠፊፊን – Al-Mutaffifīn
  84. ሱረቱ አል ኢንሺቃቅ – Al-Inshiqāq
  85. ሱረቱ አል ቡሩጅ – Al-Burūj
  86. ሱረቱ አጥ ጣሪቅ – At-Tāriq
  87. ሱረቱ አል አዕላ – Al-A‘lā
  88. ሱረቱ አል ጋሺያህ – Al-Ghāshiyah
  89. ሱረቱ አል ፈጅር – Al-Fajr
  90. ሱረቱ አል በለድ – Al-Balad
  91. ሱረቱ አሽ ሸምስ – Ash-Shams
  92. ሱረቱ አል ለይል – Al-Layl
  93. ሱረቱ አድ ዱሓ – Ad-Duhā
  94. ሱረቱ አሽ ሸርህ – Ash-Sharh
  95. ሱረቱ አት ቲን – At-Teen
  96. ሱረቱ አል ዐለቅ – Al-‘Alaq
  97. ሱረቱ አል ቀድር – Al-Qadr
  98. ሱረቱ አል–በይናህ – Al-Bayyinah
  99. ሱረቱ አል ዘልዘላህ – Az-Zalzalah
  100. ሱረቱ አል ዓዲያት – Al-‘Ādiyāt
  101. ሱረቱ አል ቃሪዓሕ – Al-Qāri‘ah
  102. ሱረቱ አት ተካሱር – At-Takāthur
  103. ሱረቱ አል ዓስር – Al-‘Asr
  104. ሱረቱ አል ሁመዛህ – Al-Humazah
  105. ሱረቱ አል ፊል – Al-Feel
  106. ሱረቱ ቁረይሽ – Quraysh
  107. ሱረቱ አል ማዑን – Al-Mā‘ūn
  108. ሱረቱ አል ከውሰር – Al-Kawthar
  109. ሱረቱ አል ካፊሩን – Al-Kāfirūn
  110. ሱረቱ አን ነስር – An-Nasr
  111. ሱረቱ አል መሰድ – Al-Masad
  112. ሱረቱ አል ኢኽላስ – Al-Ikhlās
  113. ሱረቱ አል ፈለቅ – Al-Falaq
  114. ሱረቱ አን ናስ – An-Nās

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ!
ይህ ዌየብሳይት ገና በመበልጸግ ላይ ያለ ስለሆነ ብዙ ስህተቶችን ልታገኙበት ትችላላችሁ። ስለዚህ እባካችሁ የምታገኟቸውን ስህተቶች በኮመንት ላይ እንዲታሳውቁን ስንል በአላህ ስም እንጠይቃለን።

Copyright © 2026 Amharic Quran.

Theme: Oceanly by ScriptsTown