47 – Muhammad
47 – Muhammad
| (1) እነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድም የከለከሉ (አላህ) ሥራዎቻቸውን አጠፋባቸው፡፡ | (1) Those who disbelieve and prevent others from Allah’s way, He will render their deeds void. |
| (2) እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡ | (2) As for those who believe, do righteous deeds, and believe in what has been sent down to Muhammad – which is the truth from their Lord – He will absolve them of their sins and set their condition right. |
| (3) ይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመኾናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው የኾነን እውነት ስለተከተሉ ነው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል፡፡ | (3) That is because the disbelievers follow falsehood, whereas the believers follow the truth from their Lord. This is how Allah explains for people their comparisons. |
| (4) እነዚያንም የካዱትን (በጦር ላይ) ባገኛችሁ ጊዜ ጫንቃዎችን በኀይል ምቱ፡፡ ባደካማችኋቸውም ጊዜ (አትግደሏቸው ማርኳቸው)፡፡ ማሰሪያውንም አጥብቁ፡፡ በኋላም ወይም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ፤ ወይም ትበዧቸዋላችሁ፡፡ (ይህም) ጦሪቱ መሳሪያዋን እስከምትጥል ድረስ ነው፡፡ (ነገሩ) ይህ ነው፡፡ አላህም ቢሻ ከእነርሱ (ያለጦር) በተበቀለ ነበር፡፡ ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)፡፡ እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉትን ሥራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸውም፡፡ | (4) When you encounter the disbelievers [in battle], strike [their] necks until you have thoroughly subdued them, then bind the captives firmly. Later [you may free them] as a favor or for ransom until the war comes to an end. That [is Our command], if Allah had willed, He could have subjected them to punishment, but [He ordered you to fight] to test some of you by means of others. Those who are killed in the way of Allah, He will never render their deeds void. |
| (5) በእርግጥ ይመራቸዋል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡ | (5) He will guide them, and will set their condition right, |
| (6) ገነትንም ያገባቸዋል፡፡ ለእነርሱ አስታውቋታል፡፡ | (6) and He will admit them to Paradise, which He has already made known to them. |
| (7) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ሃይማኖቱን) ብትረዱ፤ ይረዳችኋል፡፡ ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል፡፡ | (7) O you who believe, if you stand up for Allah, He will help you and make your steps firm. |
| (8) እነዚያም የካዱት ለእነርሱ ጥፋት ተገባቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም አጠፋባቸው፡፡ | (8) As for those who disbelieve, how wretched will be their state! And He will render their deeds void. |
| (9) ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው፡፡ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው፡፡ | (9) That is because they detest what Allah has sent down, so He rendered their deeds worthless. |
| (10) የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት (ከሓዲዎች) መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ያዩ ዘንድ በምድር ለይ አልኼዱምን? አላህ በእነርሱ ላይ (ያላቸውን ሁሉ) አጠፋባቸው፡፡ ለከሐዲዎችም ሁሉ ብጤዎችዋ አልሏቸው፡፡ | (10) Have they not traveled through the land to see what was the end of those before them? Allah destroyed them utterly, and a similar end awaits the disbelievers. |
| (11) ይህ አላህ የእነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ስለኾነና ከሓዲዎችም ለእነርሱ ረዳት ስለሌላቸው ነው፡፡ | (11) That is because Allah is the Protector of the believers whereas the disbelievers have no protector. |
| (12) አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያገባቸዋል፡፡ እነዚያም የካዱት (በቅርቢቱ ዓለም) ይጣቀማሉ፡፡ እንስሳዎችም እንደሚበሉ ይበላሉ፡፡ እሳትም ለእነርሱ መኖሪያቸው ናት፡፡ | (12) Allah will surely admit those who believe and do righteous deeds to gardens under which rivers flow. As for those who disbelieve, they enjoy themselves [in this world] and they eat as cattle eat; their final abode is the Fire. |
| (13) ከከተማም እርሷ ከዚያች ካወጣችህ ከተማህ ይበልጥ በኀይል ጠንካራ የኾነች (ባለቤቶችዋን) ያጠፋናቸው ብዙ ናት፡፡ ለእነርሱም ረዳት አልነበራቸውም፡፡ | (13) How many towns We destroyed that were more powerful than your town that expelled you, and there was none to help them. |
| (14) ከጌታው በኾነች አስረጅ ላይ የኾነ ምእመን ክፉ ሥራቸው ለእነርሱ እንደ ተሸለመላቸውና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉት ነውን? | (14) Are those who possess clear proof from their Lord like those whose evil deeds are made appealing to them and who follow their own desires? |
| (15) የዚያች ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት ገነት ምስል በውስጧ ሺታው ከማይለውጥ ውሃ ወንዞች፣ ጣዕሙ ከማይለወጥ ወተትም ወንዞች፣ ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከኾነች የወይን ጠጅም ወንዞች ከተነጠረ ማርም ወንዞች አልሉባት፡፡ ለእነርሱም በውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ (በያይነቱ) ከጌታቸው ምሕረትም አልላቸው፡፡ (በዚች ገነት ውስጥ ዘውታሪ የኾነ ሰው) እርሱ በእሳት ውስጥ ዘውታሪ እንደኾነ ሰው፣ ሞቃትንም ውሃ እንደተጋቱ፣ አንጀቶቻቸውንም ወዲያውኑ እንደቆራረጠው ነውን? (አይደለም)፡፡ | (15) The likeness of Paradise promised to the righteous is that of a [garden which has] rivers of fresh water; rivers of milk the taste of which never changes; rivers of wine delicious to drink; and rivers of pure honey. They will have therein all kinds of fruit and forgiveness from their Lord. Can they be like those who will abide in the Fire forever, and will be given boiling water to drink that tears apart their intestines? |
| (16) ከእነርሱም ወዳንተ የሚያዳምጡ አልሉ፡፡ ከአንተም ዘንድ በወጡ ጊዜ ለእነዚያ ዕውቀት ለተሰጡት «አሁን ምን አለ?» ይላሉ፡፡ እነዚህ እነዚያ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተመባቸው ዝንባሌዎቻቸውንም የተከተሉ ናቸው፡፡ | (16) Among these [hypocrites] are some who listen to you [O Prophet], but when they leave your presence, they say to those who were given knowledge, “What did he just say?” It is they whose hearts Allah has sealed up and who follow their desires. |
| (17) እነዚያም የተመሩት (አላህ) መመራትን ጨመረላቸው፡፡ (ከእሳት) መጥጠበቂያቸውንም ሰጣቸው፡፡ | (17) As for those who follow guidance, He increases them in guidance and blesses them with righteousness. |
| (18) ሰዓቲቱንም ድንገት የምትመጣባቸው መኾንዋን እንጅ ይጠባበቃሉን? ምልክቶችዋም በእርግጥ መጥተወል፡፡ በመጣቻቸውም ጊዜ ማስታወሳቸው ለእነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል? | (18) Are they but waiting for the Hour to come upon them by surprise? Already [some of] its signs have appeared. What good will it do them to take heed when it actually befalls them? |
| (19) እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን፡፡ አላህም መዘዋወሪያችሁን፣ መርጊያችሁንም ያውቃል፡፡ | (19) Then know [O Prophet] that none has the right to be worshiped except Allah, and seek forgiveness for your sins and for the [the sins of] the believing men and women, for Allah knows your movements and your places of rest. |
| (20) እነዚያም ያመኑት ሰዎች (መታገል ያለባት) «ሱራ አትወርድም ኖሮአልን?» ይላሉ፡፡ የጠነከረችም ሱራ በተወረደችና በውስጧም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሺታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የኾነ መከራ በርሱ ላይ እንደ ወደቀበት ሰው አስተያየት ወዳንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ ለእነሱም ወዮላቸው፡፡ | (20) Those who believe say, “If only a Chapter were sent down [about fighting]? But when a precise Chapter is sent down and fighting is mentioned therein, you see those in whose hearts is sickness looking at you like someone who is about to die. It would have been better for them |
| (21) ታዛዥነትና መልካም ንግግር (ይሻላቸዋል) ትዕዛዙም ቁርጥ በኾነ ጊዜ ለአላህ (ትዕዛዝ) እውነተኞች በኾኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር፡፡ | (21) to obey and say good words. Once the fighting was ordained, it would be better for them to be truthful to Allah. |
| (22) ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን? | (22) Then if you turn away, what else can be expected but that you will spread corruption in the land and sever your ties of kinship? |
| (23) እነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው፣ ያደነቆራቸውም፣ ዓይኖቻቸውንም ያወራቸው ናቸው፡፡ | (23) These are the ones whom Allah has cursed, and has made them deaf and has blinded their sight. |
| (24) ቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አልሉባትን? | (24) Do they not reflect upon the Qur’an, or are there locks upon their hearts? |
| (25) እነዚያ ለእነርሱ ቅኑ መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት ሰይጣን ለእነርሱ መመለሳቸውን ሸለመላቸው፡፡ ለእነርሱም አዝዘናጋቸው፡፡ | (25) Indeed, those who turn back [to disbelief] after guidance had become clear to them, it is Satan who has tempted them and has deceived them with false hopes of a long life. |
| (26) ይህ እነርሱ ለእነዚያ አላህ ያወረደውን ለጠሉት «በነገሩ ከፊል እንታዘዛችኋለን» ያሉ በመኾናቸው ነው፡፡ አላህም መደበቃቸውን ያውቃል፡፡ | (26) That is because they say to those who hate what Allah has sent down, “We will obey you in some matters.” But Allah knows their secret schemes. |
| (27) መላእክትም ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን የሚመቱ ሲኾኑ በገደሉዋቸው ጊዜ (ኹኔታቸው) እንዴት ይኾናል? | (27) How will they feel when the angels take their souls, striking their faces and their backs? |
| (28) ይህ እነርሱ አላህን ያስቆጣውን ነገር ስለ ተከተሉ ውዴታውንም ስለ ጠሉ ነው፡፡ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው፡፡ | (28) That is because they follow what incurs Allah’s wrath and they hate what pleases Him, so He will render their deeds worthless. |
| (29) እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አላህ ቂሞቻቸውን አለማውጣቱን ጠረጠሩን? | (29) Do those in whose hearts is sickness think that Allah will never expose their malice? |
| (30) በሻንም ኖሮ እነርሱን ባሳየንህና በምልክታቸውም በእርግጥ ባወቅሃቸው ነበር፡፡ ንግግርንም በማሸሞራቸው በእርግጥ ታውቃቸዋለህ፡፡ አላህም ሥራዎቻችሁን ያውቃል፡፡ | (30) If We willed, We could show them to you [O Prophet], so you would recognize them by their faces, but you will surely recognize them by the manner of their speech. And Allah knows all what you do. |
| (31) ከእናንተም ታጋዮቹንና ታጋሾቹን እስከምናውቅ፣ ወሬዎቻችሁንም እስከምንገልጽ ድረስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ | (31) We will certainly test you so as to reveal those of you who struggle [in Allah’s way] and remain patient, and We will test the sincerity of your assertions. |
| (32) እነዚያ የካዱና ከአላህም መንገድ ያገዱ ለእነርሱም ቅኑ መንገድ ከተገለጸላቸው በኋላ መልክተኛውን የተከራከሩ አላህን በምንም አይጎዱትም፡፡ ሥራዎቻቸውንም በእርግጥ ያበላሻል፡፡ | (32) Those who disbelieve and prevent others from Allah’s way, and oppose the Messenger after guidance had become clear to them, they will never harm Allah in the least, and He will render their deeds worthless. |
| (33) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ ሥራዎቻችሁንም አታበላሹ፡፡ | (33) O you who believe, obey Allah and obey the Messenger, and do not cause your deeds to be nullified. |
| (34) እነዚያ የካዱ፣ ከአላህም መንገድ ያገዱ፣ ከዚያም እነርሱ ከሓዲዎች ኾነው የሞቱ አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም፡፡ | (34) Those who disbelieve and prevent others from Allah’s way, and then die as disbelievers, Allah will never forgive them. |
| (35) እናንተም አሸናፊዎቹ ስትኾኑ አላህ ከእናንተ ጋር ሲሆን አትድከሙ፡፡ ወደ ዕርቅም አትጥሩ፡፡ ሥራዎቻችሁንም ፈጽሞ አያጎድልባችሁም፡፡ | (35) Do not lose heart or call for peace, for you will have the upper hand and Allah is with you. And He will never detract [the reward of] your deeds. |
| (36) ቅርቢቱ ሕይወት ጫወታና ዛዛታ ብቻ ናት፡፡ ብታምኑም ብትጠነቀቁም ምንዳዎቻችሁን ይሰጣችኋል፡፡ ገንዘቦቻችሁንም (ሁሉ) አይጠይቃችሁም፡፡ | (36) The life of this world is only play and amusement. But if you believe and fear Allah, He will give you your rewards, and He does not ask you for all your wealth. |
| (37) እርሷን ቢጠይቃችሁና ችክ ቢልባችሁ ትሰስታላችሁ፡፡ ቂሞቻችሁንም ያወጣል፡፡ | (37) If He were to ask you for it and insist that you give it, you would greedily withhold, and He would expose your resentment [for spending]. |
| (38) ንቁ! እናንተ እነዚያ በአላህ መንገድ ትለግሱ ዘንድ የምትጥጠሩ ናችሁ፡፡ ከእናንተም ውስጥ የሚሰስት ሰው አልለ፡፡ የሚሰስትም ሰው የሚሰስተው በራሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ አላህም ከበርቴ ነው፡፡ እናንተም ድኾች ናችሁ፡፡ ብትሸሹም ሌሎችን ሕዝቦች ይለውጣል፡፡ ከዚያም (ባለመታዘዝ) ብጤዎቻችሁ አይኾኑም፡፡ | (38) O you who are being called to spend in Allah’s way; among you are some who greedily withhold, but whoever withholds, he in fact withholds against himself, for Allah is the Self-Sufficient, whereas you are in need [of Him]. If you turn away, He will replace you with another people, then they will not be like you. |
