Default Image
19, Dec 2023
91 – Ash-Shams

91 – Ash-Shams

(1) በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡ (1) By the sun and its brightness,
(2) በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤ (2) and by the moon as it follows it,
(3) በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤ (3) and by the day as it displays it,
(4) በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤ (4) and by the night as it covers it,
(5) በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤ (5) and by the sky and how He made it,
(6) በምድሪቱም በዘረጋትም፤ (6) and by the earth and how He spread it,
(7) በነፍስም ባስተካከላትም፤ (7) and by the soul and how He fashioned it,
(8) አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡ (8) then inspired it [to know] its wickedness and righteousness,
(9) (ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡ (9) Indeed, he who purifies his soul will attain success,
(10) (በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡ (10) and he who corrupts it will be doomed.
(11) ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡ (11) Thamūd rejected [the messenger] because of their transgression,
(12) ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡ (12) when the most wretched among them rose [to kill the camel].
(13) ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡ (13) Although the messenger of Allah warned them, “Hands off the she-camel of Allah and her drink!”
(14) አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡ (14) Yet they rejected him and hamstrung her. So their Lord destroyed them for their sin and leveled them to the ground.
(15) ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡ (15) And He has no fear of the consequences thereof.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

67 – Al-Mulk

67 – Al-Mulk (1) ያ ንግሥና በእጁ የኾነው አምላክ ችሮታው በዛ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ (1) Blessed is…

14 – Ibrahim

14 – Ibrahim (1) አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርአን) ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አሸናፊ ምስጉን ወደ ኾነው፡፡…

ሱረቱ አል ሁድ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran 11 Al-Hud

ሱረቱ አል ሁድ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran 11 Al-Hud الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ…