Skip to content

Amharic Quran

ከመሞትህ በፊት ቁርአንን አንብብ! (Read the holy Quran before you die!)

  • Home
    • ቁርአንን እንረዳው
    • Download
  • ሱራዎች / Surah List
    • አል-ፋቲሐ (Al-Fatiha)
    • አል-በቀራህ (Al-Beqerah)
    • አል-ዒምራን (Al-Imran)
    • አል-ኒሳዕ (An-Nisa)
    • አል-ማዒዳህ (Al-Maidah) 
    • አንዓም (Al-anam)
    • አል አዕራፍ (Al-Aeraf)
    • አል አንፋል (Al-Anfal)
    • አል ተውባ (At-Tawba)
    • አል ዩኑስ (Yunus)
    • አል ሁድ (Al-Hud)
    • ዩሱፍ (Yusuf)
    • 13 – Ar-Ra’d
    • 14 – Ibrahim
    • አል ሒጅር (Al-Hijr)
    • 16 – An-Nahl
    • 17 – Al-Israa
    • ከህፍ (Al-Kahf )
    • 19 Maryam
    • ጧሃ (Taa-Ha)
    • 21 – Al-Anbiyaa
    • አል ሐጅ (Al-Hajj)
    • 23 – Al-Muminoon
    • 24 – An-Noor
    • 25 – Al -Furqan
    • 26 – Ash-Shu’araa
    • 27 – An-Naml
    • 28 – Al-Qasas
    • 29 – Al-Ankaboot
    • 30 – Ar-Room
    • 31 – Luqman
    • 32 – As-Sajda
    • 33 – Al-Ahzaab
    • 34 – Saba
    • 35 – Faatir
    • 36 – Yaseen
    • 37 – As-Saaffaat
    • 38 – Saad
    • 39 – Az-Zumar
    • 40 – Al-Ghaafir
    • 41 – Fussilat
    • 42 – Ash-Shura
    • 43 – Az-Zukhruf
    • 44 – Ad-Dukhaan
    • 45 – Al-Jaathiya
    • 46 – Al-Ahqaf
    • 47 – Muhammad
    • 48 – Al-Fath
    • 49 – Al-Hujuraat
    • 50 – Qaaf
    • 51 – Adh-Dhaariyat
    • 52 – At-Tur
    • 53 – An-Najm
    • 54 – Al-Qamar
    • 55 – Ar-Rahmaan
    • 56 – Al-Waaqia
    • 57 – Al-Hadid
    • 58 – Al-Mujaadila
    • 59 – Al-Hashr
    • 60 – Al-Mumtahana
    • 61 – As-Saff
    • 62 – Al-Jumu’a
    • 63 – Al-Munaafiqoon
    • 64 – At-Taghaabun
    • 65 – At-Talaaq
    • 66 – At-Tahrim
    • 67 – Al-Mulk
    • 68 – Al-Qalam
    • 69 – Al-Haaqqa
    • 70 – Al-Ma’aarij
    • 71 – Nooh
    • 72 – Al-Jinn
    • 73 – Al-Muzzammil
    • 74 – Al-Muddaththir
    • 75 – Al-Qiyaama
    • 76 – Al-Insaan
    • 77 – Al-Mursalaat
    • 78 – An-Naba
    • 79 – An-Naazi’aat
    • 80 – Abasa
    • 81 – At-Takwir
    • 82 – Al-Infitaar
    • 83 – Al-Mutaffifin
    • 84 – Al-Inshiqaaq
    • 85 – Al-Burooj
    • 86 – At-Taariq
    • 87 – Al-A’laa
    • 88 – Al-Ghaashiya
    • 89 – Al-Fajr
    • 90 – Al-Balad
    • 91 – Ash-Shams
    • 92 – Al-Lail
    • 93 – Ad-Dhuhaa
    • 94 – Ash-Sharh
    • 95 – At-Tin
    • 96 – Al-Alaq
    • 97 – Al-Qadr
    • 98 – Al-Bayyina
    • 99 – Az-Zalzala
    • 100 – Al-Aadiyaat
    • 101 – Al-Qaari’a
    • 102 – At-Takaathur
    • 103 – Al-Asr
    • 104 – Al-Humaza
    • 105 – Al-Fil
    • 106 – Quraish
    • 107 – Al-Maa’un
    • 108 – Al-Kawthar
    • 109 – Al-Kaafiroon
    • 110 – An-Nasr
    • 111 – Al-Masad
    • 112 – Al-Ikhlaas
    • 113 – Al-Falaq
    • 114 – An-Naas

ግደሉ የሚለው ቁርአን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ?

Posted on February 3, 2024July 24, 2026 By Amharic Quran No Comments on ግደሉ የሚለው ቁርአን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ?
ቁርአንን እንረዳው, አማርኛ ቁርአን

ግደሉ የሚለው ቁርአን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ?

የግድያ መፅሀፍ የሚመስለው ቅዱስ ቁርአን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ? እስኪ ከመፅሀፍ ቅዱስ ጀምረን እንየው:-

  • ግደል የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ተደጋግሞ ተጠቅሷል?

ንፅፅሩን እዚህ ተጭነው በቪዲዮ ሊያዳምጡት ይችላሉ።

ግደል የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከ 400 ጊዜ በላይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ደግሞ ከ 90 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል። ግደል የሚለው ቃል በአጠቃላይ በባይብል ውስጥ በትንሹ ከ 450 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል።

በእርግጥ እንደ ቨርዥኑ ይለያያል። ይህ ቁጥር በ ERV ቨርዥን መሰረት ነው።

  • በኪንግ ጀምስ ቨርዥን ካየነው ደግሞ ግደል የሚለው ቃል በአጠቃላይ 119 ጊዜ ያህል ተጠቅሷል።
  • በ NASB ቨርዥን 118 ጊዜ፣
  • በ NetFree ቨርዥን መሰረት ደግሞ 222 ጊዜ ተጠቅሷል።
  • በነዚህ ቨርዥኖች ላይ የተጠቀሰው ቁጥር ያነሰው ግን “kill” የሚለውን ቃል እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው ወይም “Stone him to deat” በሚለው ስለተተካ ነው። የዚህም ትርጉም ያው ግደለው ነው የሚለው። አልሸሹም ዘወር ነው። ሆኖም በባይብል ውስጥ ግደል የሚለው ቃል ቢያንስ ከ 400 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል በትንሹ ማለት ነው።

ወደ ቅዱስ ቁርአን ስንመጣስ? ግደል የሚለው ቃል በቁርአን ውስጥስ ምን ያህል ጊዜ ተጠቅሷል?

የሚገርመው ነገር ግን “ግደሉ ወይም ግደሏቸው” የሚለው ቃል በቁርአን ውስጥ የተጠቀሰው 11 ጊዜ ብቻ መሆኑ ነው።

ስለዚህ የግድያ መፅሀፍ የሚመስለው ቁርአን ነው ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ? ሰላማዊውስ ሀይማኖት የትኛው ይመስላችኋል። መልሱን ላንባቢያን ልተው።

ለምን እውነታው አይገለጥልንም ግን? ለምን ማመን ከበደን?!

አሁን ደግሞ ከሁለቱም የተወሰኑ ምሳሌዎችን እንመልከት። በቅድሚያ ከመፅሀፍ ቅዱስ እንጀምር:-

ባይብል የማይታወቅ አምላክ እናምልክ ብለው ጥሪ የሚያቀርቡላችሁንና ሊያስቷችሁ የሚሞክሩ ሰዎችን በማስረጃ አጣርታችሁ በሙሉ ግደሏቸው ነው የሚለው።

ለምስላሌ ዘዳግም 13 እስከመጨረሻው ድረስ የሚያዘው ይሄንኑ ነው።

“ወደ ጣዖት አምልኮ የሚጠሯችሁን ሰዎች ለአምላክ ያላችሁን ቆራጥነት ያውቁ ዘንድ ግደሏቸው” ይላል። ከዚያ በኋላ ሌሎች ሰዎች ወደ ጣዖት አምልኮ አይጠሯችሁም ነው መልእክቱ።

እስኪ ከ ዘዳግም  ምዕራፍ 13 ከአንቀፅ 12 እስከ 18 እናንብበው:-
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹²-¹³ አምላክህ እግዚአብሔር ልትኖርባት በሚሰጥህ በአንዲቱ ከተማህ፦ ክፋተኞች ሰዎች ከእናንተ ዘንድ ወጥተው፦ ሄደን የማታውቋቸውን ሌሎችን አማልክት እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብትሰማ፥

¹⁴ ትፈልጋለህ፥ ትመረምራለህም፥ ትጠይቃለህም፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከልህ እንደ ተደረገ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥

¹⁵ የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋለህ፤ ከተማይቱን፥ በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፋቸዋለህ።

¹⁶ ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበሰባለህ፥ ከተማይቱንም ዕቃዋንም ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በእሳት ፈጽመህ ታቃጥላለህ፤ ለዘላለምም ወና ትሆናለች፥ ደግሞም አትሠራም።

¹⁷-¹⁸ ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኘውን ታደርግ ዘንድ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ስትሰማ፥ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ቍጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥ እርም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አይንጠልጠልብህ። ይላል፣ ከእንደነዚህ አይነት ሰዎች ራስህን አፅዳ ማለት ነው።

# ዘዳግም 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² አምላክህ እግዚአብሔር ከሰጠህ ከአገርህ ደጆች በማንኛይቱም ውስጥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ቃል ኪዳኑን በማፍረስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ክፋት የሠራ ቢገኝ፥
³ ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥
⁴ ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያንን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥
⁵ ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ።
⁶ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ሞት የሚገባው ይገደል፤ በአንድ ምስክር አፍ አይገደል።
⁷ እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት፤ እንዲሁም ክፋቱን ከመካከልህ አስወግድ።
⁸ በደምና በደም፥ በፍርድና በፍርድ፥ በመቍሰልና በመቍሰል መካከል በአገርህ ደጅ ውስጥ ሰዎች ስለሚከራከሩበት ክርክር የሚሳንህ የፍርድ ነገር ቢነሣ፥ አንተ ተነሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትወጣለህ፤
⁹ ወደ ሌዋውያን ካህናት በዚያም ዘመን ወደ ተሾመው ፈራጅ መጥተህ ትጠይቃለህ፤ እነርሱም የፍርዱን ነገር ይነግሩሃል።
¹⁰ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ የነገሩህን የፍርድ ነገር ታደርጋለህ፤ እንዳስተማሩህም ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።
¹¹ እንዳስተማሩህም ሕግ፥ እንደ ነገሩህም ፍርድ አድርግ፤ ከነገሩህ ፍርድ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።
¹² ማናቸውም ሰው ቢኰራ፥ በዚያም አምላክህን እግዚአብሔርን ለማገልገል የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ለመስማት ባይወድድ፥ ያ ሰው ይሙት፥ ከእስራኤልም ዘንድ ክፋትን አስወግድ፤
¹³ ሕዝቡም ሁሉ ሰምቶ ይፈራል፥ ከዚያም ወዲያ አይኰራም።

# ዘኍልቁ ምዕራፍ 31 ከአንቀፅ 7 እስከ 18 ያለውን እናንብብ ደግሞ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፥ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ።
⁸ ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ነገሥታት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት።
⁹ የእስራኤልም ልጆች የምድያምን ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና መንጎቻቸውንም ዕቃቸውንም ሁሉ በዘበዙ።
¹⁰ የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ።
¹¹ የሰውንና የእንስሳን ምርኮና ብዝበዛ ሁሉ ወሰዱ።
¹² የማረኩአቸውንም ሰዎች ምርኮውንና ብዝበዛውን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር፥ በዮርዳኖስም አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር አመጡ።
¹³ ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም የማኅበሩም አለቆች ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ሊገናኙአቸው ወጡ።
¹⁴ ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጭፍራ አለቆች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ።
¹⁵ ሙሴም አላቸው፦ በውኑ ሴቶችን ሁሉ አዳናችኋቸውን?
¹⁶ እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር እግዚአብሔርን ይበድሉ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ።
¹⁷ አሁን እንግዲህ ከልጆቹ ወንዱን ሁሉ ግደሉ፥ ወንድንም በመኝታ የሚያውቁትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ።
¹⁸ ወንድን የማያውቁትን ሴቶች ልጆችን ሁሉ ግን ለራሳችሁ አድኑአቸው። (ድንግል ያልሆኑትን ግደሉ፣ ደናግሎቹን ሴቶችን ደግሞ አትግደሉ ይልቅስ ለራሳችሁ ውሰዷቸው ማለት ነው። ጣኦት አምላኪ ከሆነች ድንግሏስ ለምን አትገደልም፣ ከዚያስ ሁሉ ሴት ድንግል ያላትንና የሌላትን በምን ይለዩአታል የሚለው ሌላ ጥያቄ ነው።)

እስካሁን ያየናቸው ምዕራፎች እንግድህ ስለግድያ የሚያወሩ ናቸው።

  — ዘኍልቁ 35፥ ከአንቀፅ 19-34 ብንመለከትም ያው ስለግድያ ነው የሚያወራው።

“ደም ተበቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳዩን ይግደል፤ ባገኘው ጊዜ ይግደለው።”

ዘኍልቁ 35 ከአንቀፅ 11

# ህዝቄል 9ን እንመልከት ደግሞ አሁን:-
ሕዝቅኤል 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄዶ ነበር፤ በፍታም የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ።
⁴ እግዚአብሔርም፦ በከተማይቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው።
⁵ እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ፦ እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም፤ ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም፤
⁶ ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
⁷ እርሱም፦ ቤቱን አርክሱ፥ በተገደሉትም ሰዎች አደባባዮችን ሙሉ፤ ውጡ አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማይቱ ገደሉ።
⁸ ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስ ራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን? ብዬ ጮኽሁ። 9 እርሱም፦ የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኃጢአት እጅግ በዝቶአል ምድሪቱም ደም፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፤ እነርሱም፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል እግዚአብሔርም አያይም ብለዋል።”

# 1ኛ ሳሙኤል 15-35
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን እበቀላለሁ።
³ አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል።
⁴ ሳኦልም ሕዝቡን ጠርቶ በጌልገላ ቈጠራቸው፤ ሁለት መቶ ሺህ እግረኞች፥ ከይሁዳም አሥር ሺህ ሰዎች ነበሩ።
⁵ ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ወጣ፥ በሸለቆውም ውስጥ ተደበቀ።
⁶ ሳኦል ቄናውያንን፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፤ ከግብጽ በወጡ ጊዜ ለእስራኤል ልጆች ቸርነት አድርጋችኋልና ከአማሌቅ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከመካከላቸው ውረዱ አላቸው፤ ቄናውያንም ከአማሌቃውያን መካከል ሄዱ።
⁷ ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብጽ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው።
⁸ የአማሌቅንም ንጉሥ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፥ ሕዝቡንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው።
⁹ ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ ለአጋግ፥ ለተመረጡትም በጎችና በሬዎች ለሰቡትም ጥጆችና ጠቦቶች፥ ለመልካሞቹም ሁሉ ራሩላቸው፥ ፈጽሞ ሊያጠፉአቸውም አልወደዱም፤ ነገር ግን ምናምንቴንና የተናቀውን ሁሉ ፈጽመው አጠፉት።
¹⁰-¹¹ የእግዚአብሔርም ቃል፦ ሳኦል እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና ስላነገሥሁት ተጸጸትሁ ብሎ ወደ ሳሙኤል መጣ። ሳሙኤልም ተቈጣ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
¹² ሳሙኤልም በነጋው ሳኦልን ለመገ ናኘት ማለደ፦ ሳኦልም ወደ ቀርሜሎስ መጣ፤ እነሆም፥ የመታሰቢያ ዓምድ ባቆመ ጊዜ ዞሮ አለፈ፥ ወደ ጌልገላም ወረደ የሚል ወሬ ለሳሙኤል ደረሰለት።
¹³ ሳሙኤልም ወደ ሳኦል መጣ፤ ሳኦልም፦ አንተ ለእግዚአብሔር የተባረክህ ሁን፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ አለው።
¹⁴ ሳሙኤልም፦ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ጩኸትና የበሬዎች ግሣት ምንድር ነው? አለ።
¹⁵ ሳኦልም፦ ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ መልካሞቹን በጎችና በሬዎች አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አምጥተዋቸዋል፤ የቀሩትንም ፈጽመን አጠፋን አለው።
¹⁶ ሳሙኤልም ሳኦልን፦ ቆይ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ አለው፤ እርሱም፦ ተናገር አለው።
¹⁷ ሳሙኤልም አለ፦ በዓይንህ ምንም ታናሽ ብትሆን ለእስራኤል ነገዶች አለቃ አልሆንህምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ።
¹⁸ እግዚአብሔርም፦ ሄደህ ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ውጋቸው ብሎ በመንገድ ላከህ።
¹⁹ ለምርኮ ሳስተህ ለምን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማህም? ለምንስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረግህ?
²⁰ ሳኦልም ሳሙኤልን፦ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቻለሁ፥ እግዚአብሔርም በላከኝ መንገድ ሄጃለሁ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጥቻለሁ፥ አማሌቃውያንንም ፈጽሜ አጥፍቻለሁ።
²¹ ሕዝቡ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በጌልገላ ይሠዉ ዘንድ ከእርሙ የተመረጡትን በጎችንና በሬዎችን ከምርኮው ወሰዱ አለው።
²² ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።
²³ ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።
²⁴ ሳኦልም ሳሙኤልን፦ ሕዝቡን ስለ ፈራሁ፥ ቃላቸውንም ስለ ሰማሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና የአንተን ቃል በመተላለፍ በድያለሁ።
²⁵ አሁንም፥ እባክህ፥ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፥ ለእግዚአብሔርም እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋ ር ተመለስ አለው።
²⁶ ሳሙኤልም ሳኦልን፦ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃልና ከአንተ ጋር አልመለስም አለው።
²⁷ ሳሙኤልም ሊሄድ ዘወር ባለ ጊዜ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፥ ተቀደደም።
²⁸ ሳሙኤልም፦ እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀደዳት፥ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጣት፤
²⁹ የእስራኤል ኃይል እንደ ሰው የሚጸጸት አይደለምና አይዋሽም አይጸጸትምም አለው።
³⁰ እርሱም፦ በድያለሁ፤ አሁን ግን በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊትና በእስራኤል ፊት፥ እባክህ፥ አክብረኝ፤ ለአምላክህም ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ አለው።
³¹ ሳሙኤልም ከሳኦል በኋላ ተመለሰ፤ ሳኦልም ለእግዚአብሔር ሰገደ።
³² ሳሙኤልም፦ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ አለ። አጋግም እየተንቀጠቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋግም፦ በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን? አለ።
³³ ሳሙኤልም፦ ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች አለ፤ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቈራረጠው።
³⁴ ሳሙኤልም ወደ አርማቴም ሄደ፤
³⁵ ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ጊብዓ ወጣ፦ ሳሙኤልም እስከ ሞተበት ቀን ድረስ ሳኦልን ለማየት ዳግመኛ አልሄደም፥ ሳሙኤልም ለሳኦል አለቀሰ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ሳኦልን ስላነገሠ ተጸጸተ።

# አስቴር 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ በአሥራ ሁለተኛው ወር በአዳር በአሥራ ሦስተኛው ቀን አይሁድን ሁሉ፥ ልጆችንና ሽማግሌዎችን፥ ሕፃናቶችንና ሴቶችን፥ በአንድ ቀን ያጠፉና ይገድሉ ዘንድ፥ ይደመስሱም ዘንድ፥ ምርኮአቸውንም ይዘርፉ ዘንድ ደብዳቤዎች በመልእክተኞች እጅ ወደ ንጉሡ አገሮች ሁሉ ተላኩ።
¹⁴ በዚያም ቀን ይዘጋጁ ዘንድ የደብዳቤው ቅጅ በየአገሩ ላሉ አሕዛብ ሁሉ ታወጀ።

¹⁵ መልእክተኞቹም በንጉሡ ትእዛዝ እየቸኰሉ ሄዱ፥ አዋጁም በሱሳ ግንብ ተነገረ። ንጉሡና ሐማ ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ከተማይቱ ሱሳ ግን ተደናገጠች።

አሁን ደግሞ ወደ ቁርአን እንመለስ። በቁርአን ግደሉ የሚሉት አንቀፆችና ተደጋግመው የሚነሱት ቀጥለው የቀረቡት ናቸው:-

ሱረት አል በቀራህ 2:191

ባገኛችኋቸውም ስፍራ ሁሉ ግደሉዋቸው፡፡ ከአወጧችሁም ስፍራ አውጧቸው፡፡ መከራም ከመግደል ይበልጥ የበረታች ናት፡፡ በተከበረው መስጊድም ዘንድ በርሱ ውስጥ እስከሚጋደሉዋችሁ ድረስ አትጋደሉዋቸው፡፡ ቢጋደሉዋችሁም ግደሉዋቸው፤ የከሓዲዎች ቅጣት እንደዚህ ነው፡፡

ማንን ነው ግን ግደሉ የሚለው? ይህን ለመረዳት እነዚያንም 190ኛውን አንቀፅ ማንበብ ያስፈልጋል። እንድህ ይነበባል:-

የሚጋደሉዋችሁን (ከሓዲዎች) በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና፡፡ 2:290

(የሚጋደሏችሁን፣ ክርስቲያንም ይሁኑ አይሁድ ወይም ጣዖት አምላኪ ከተዋጓችሁ ሁከት እስከሚጠፋ ድረስ ተዋጓቸው፣ ግደሏቸው ለከሀዲዎች ዋጋቸው ይሄ ነውና ግን ድንበር አትለፉ። ይላል)

ቀጥሎ ያለው አንቀፅ ደግሞ “ከመጥፎ ድርጊታቸው ቢታቀቡ ግን አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡” ይላል። ስለዚህ ቁርአ ንን ስናነብ አንዷን አንቀፅ ብቻ ይዘን መሄድ የለብንም። ሙሉውን ምዕራፍ ማንበብ ያስፈልጋል።

# ሰዎች ከእስልምና ሲወጡ ይገደላሉ የሚባለው እውነት ነው?

በመጀመሪያ እስልምናን አለመቀበል ይችላል የሚያስገድደው የለም። ወዶ ከተቀለ በኋላ ግን ለቅቆ ቢወጣ ሰዎችን እንዲያወናብድ ስለማይፈቀድለት ይገደላል።

እነርሱ እንደ ካዱ ብትክዱና እኩል ብትኾኑ ተመኙ! በአላህም ሃይማኖት እስከሚሰደዱ ድረስ ከነሱ ወዳጆችን አትያዙ፡፡ (ከእምነት) ቢያፈገፍጉም ያዙዋቸው፤ (ማርኩዋቸው)፡፡ ባገኛችሁበትም ስፍራ ግደሉዋቸው፡፡ ከእነሱም ወዳጅንና ረዳትን አትያዙ፡፡

ሱረቱ ኒሳዕ (4: 89)

አወ እውነት ነው፣ ሙርተዲን መግደል በኢስላም ይፈቀዳል። ከመጀመሪያው እስልምናን አልቀበልም ማለት ትችላለህ ማንም አስገድዶ ተቀበል የሚልህ የለም።

ነገር ግን ሰልሚያለሁ ካልክ በኋላ መልሰህ “እስልምና በዚህ በዚህ ምክንያት ስህተት ነው፣ ሰልሜ አይቸው ነበር ግን አይረባም” እያልክ እውቀት የሌላቸው ሰዎችን እንዲታሳስትና ሸር እንዲትሰራ አይፈቀድልህም።

ስለዚህ ኢስላማዊ መንግስት ባለበት ሀገር አዎ ትገደላለህ።

ሌሎች ከእናንተ ለመዳን ከወገኖቻቸውም ለመዳን የሚፈልጉን ታገኛላችሁ፡፡ ወደ እውከት እንዲመለሱ በተጠሩ ቁጥር በርሷ ውስጥ ይመለሳሉ፡፡ ባይተውዋችሁና እርቅንም ባያቀርቡላችሁ፣ እጆቻቸውንም ባይሰበስቡ፣ ባገኛችኋቸው ስፍራ ማርኩዋቸው፡፡ ግደሉዋቸውም፡፡ እነዚያንም ለእናንተ በነሱ ላይ ግልጽ ማስረጃን አድርገናል፡፡

ሱረቱ ኒሳዕ (4:91)

ይህም “ባይተውዋችሁና እርቅንም ባያቀርቡላችሁ፣ እጆቻቸውንም ባይሰበስቡ፣ ነው ግደሏቸው የሚለው። ምክንያቱም ሰላምን የማይፈልግ ሰው ምንጊዜም በጦርነት ነው ልክ የሚገባው።

የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው፡፡ ያዙዋቸውም፣ ክበቡዋቸውም፣ ለእነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ፡፡ ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

ሱረቱ አት-ተውባህ (9:5)

ይሄ አንቀፅ ብዙ ጊዜ ያለ አገባቡ ሲጠቀስ ይስተዋላል። አሁንም ይሄን አንቀፅ ለመረዳት የመጀመሪያዎቹን 4 አንቀፆች መረዳት ያስፈልጋል።

የመጀመሪያው አንቀፅ ውላቸውን ላፈረሱ የተላለፈ አዋጅ ነው። እሱም “ውላችንን አፍርሳችኋል ከዚህ በኋላ ምንም ነገር ብናደርጋችሁ ተጠያቂነት የለብንም” የሚል አንድምታ ነው ያለው።

ሁለተኛው አንቀፅ ደግሞ፣ “ነገር ግን ለአራት ወራት በነፃነት እንዲትንቀሳቀሱ እንፈቅድላችኋለን፣ ከአላህ ቅጣት የማታመልጡ መኾናችሁንና አላህም ከሓዲዎችን አዋራጅ መኾኑን ግን ከወድሁ ዕወቁት ብላችሁ ንገሯቸው።” ይላል።

ሶስተኛው አንቀፅ ደግሞ:- ይህ ከአላህና ከመልክተኛው በታላቁ ሐጅ ቀን የተሰጠ፣ አላህና መልክተኛው በአጋሪዎቹ ዙሪያ ምንም አይነት አስገዳጅ የውል ስምምነት እንደሌለባቸው የሚያሳውቅ፣ እንድሁም ጣኦታውያኑ ቢፀፀቱና ወደ ትክክለኛው መስመር ቢገቡ ለነሱ የተሻለ እንደሆነ፣ እንቢ ካሉ ደግሞ አላህን እንደማያቅቱትና በዚህም አለም በዛኛውም አለም ውርደትን እንደሚያከናንባቸው ሊያውቁ እንደሚገባ የሚናገር መግለጫ ነው።

አራተኛው አንቀፅ ደግሞ:- “ጣኦት አምላኪ ሆነው ሳለ ቃል ኪዳናቸውን የጠበቁና እናንተን የሚወጉ ቡድኖችን ያልደገፉ ሰዎችን ግን እንዳትነኩ፣ እነሱ ቃላቸውን እንዳከበሩ እናንተም ቃላችሁን አክብሩላቸው። አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡” የሚል ሙስሊሞችን የሚያስጠነቅቅ መግለጫ ነው የያዘው።

አምስተኛው አንቀፅ ደግሞ:- “የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ፣ ለአጋሪያን የተሰጣቸው ጊዜ ካለቀ በኋላ፣ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው፡፡ ያዙዋቸውም፣ ክበቡዋቸውም፣ ለእነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ፡፡ አሁንም ቢሆን ግን ከተጸጸቱ፣ ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

ስለዚህ ይህ አንቀፅ በሀይማኖት ስለማስገደድ አይደለም የሚናገረው፣ ግን ስምምነትንና ቃል ኪዳንን ስለመጠበቅ ነው።

ቁርአኑ ገና ሲጀምር “ከአሁን በኋላ ውል የለንም፣ ውላችን ፈርሷል” በማለት ይጀምራል። ቁርአን ይህን ያለው ውሉን ያፈረሱት የመካ ጣኦት አምላኪዎች በመሆናቸው ነው። ውሉን አፍርሳችሁታል፣ ጊዜም ሰጥተናችኋል ከአሁን በኋላ ተዋግተን ብንገድላችሁ ተጠያቂነት የለብንም የሚል መልርክት የያዘ ነው። ስለክርስቲያኖች ወይም ስለ አይሁዶች አይደለም ደግሞ አንቀፁ የሚያወራውም። ውሉን ስላፈረሱት አረብ ጣዖታውያኖች ነው።

በኢስላም ማስገደድ ቢኖር ኖሮ ክርስቲያኖች፣ ጣዖት አምላኪያን፣ እምነት የለሾች እና አይሁዶች ገና ከስምንት መቶ አመታት በፊት ጠፍተው ነበር።

እንድሁም የሚዋጉንን ነው መዋጋት የተፈቀደልን እንጂ ሴቶችን፣ ህፃናትን፣ ሽማግሌዎችንና መነኩሴዎችን እንድሁም ስምምነቱን የጠበቁ ሰዎችን እንድንዋጋ አልተፈቀደልንም። እንኳን ሙሉ ከተማውን ማጥፋት ይቅርና ዛፍ መቁረጥ እንኳን ክልክል ነው በኢስላም። እንደክርስትናና እንደ አይሁድ እምነት አይደለም ኢስላም።

“የአላህን ብርሀን ለሰዎች እንዳታደርሱ የሚያግዷችሁን ሰዎች ተዋጓቸው” ነው የሚለው ኢስላም።

ከተቀደሰው መስጅደል ሀራም ውጪ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው፡፡ መስጅደል ሀራም ላይ ግን ካልተጋደሏችሁ በስተቀር አትጋደሉ።

ስለዚህ ይሄንን እውነት ማወቅ አለብን። እባካችሁ ክርስቲያኖች እስልምና ገዳይ ሀይማኖት ነው፣ ቁርአን ሰዎችን ግደሉ ይላሉ፣ ወዘተ እያላችሁ ከማውራታችሁ በፊት እነዚህን እውነታዎች እወቁ መጀመሪያ። ይጠቅማችኋል እንጂ አይጎዳችሁም። እውነት አርነት ያወጣችኋል።

አሁን የትኛው ሀማኖት ሰላም እንደሚሰብክና የትኛው ጦርነት እንደሚሰብክ በማስረጃ አይተናል። ከአሁን በኋላ እስልምናን መውቀስ እና ማንቋሸሽ ማቆም አለባችሁ ማለት ነው ክርስቲያን ወገኖች። ውሸት አያዋጣችሁምና።

ምን ጊዜም ሸር ማድረግ አይረሳ። ይሄን ሊንክ ጫንን ብላችሁ ያዙትና ሊንኩን ኮፒ አድርጋችሁ፣ ፌስቡክ ላይ፣ ቴሌግራም ቻነል ላይ፣ ዋትስአፕ ላይ ዩቱብ ላይ ወዘተ ጫኑት። በመልካም ንያ ከሰራችሁት የአጅሩ ተከፋይ ትሆናላችሁ። ኢንሻ አላህ።

Tags: Amharic Quran quran amharic quran in amharic ሱረቱል በቀራህ ሱረቱል ከህፍ ቁረአን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ቁራን በአማርኛ ትርጉም ቁርአን በአማርኛ የቁራን ትርጉም

Post navigation

❮ Previous Post: 114 – An-Naas
Next Post: Arabic Quran ❯

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ሁሉም ሱራዎች / All Chapters

  1. ሱረቱ አል-ፋቲሃ – Al-Fātihah
  2. ሱረቱ አል-በቀራህ – Al-Baqarah
  3. ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን – Āl-‘Imrān
  4. ሱረቱ አን-ኒሳዕ – An-Nisā’
  5. ሱረቱ አል-ማኢዳህ – Al-Mā’idah
  6. ሱረቱ አል-አንዓም – Al-An‘ām
  7. ሱረቱ አል-አዕራፍ – Al-A‘rāf
  8. ሱረቱ አል-አንፋል – Al-Anfāl
  9. ሱረቱ አት-ተውባህ – At-Tawbah
  10. ሱረቱ ዩኑስ – Yūnus
  11. ሱረቱ ሁድ – Hūd
  12. ሱረቱ ዩኑስ – Yūsuf
  13. ሱረቱ አር-ረዕድ – Ar-Ra‘d
  14. ሱረቱ ኢብራሂም – Ibrāhīm
  15. ሱረቱ አል ሒጅር – Al-Hijr
  16. ሱረቱ አን–ነሕል – An-Nahl
  17. ሱረቱ አል ኢስራዕ – Al-Isrā’
  18. ሱረቱ አል ከህፍ – Al-Kahf
  19. ሱረቱ መርየም – Maryam
  20. ሱረቱ ጣሃ – Tā-ha
  21. ሱረቱ አል አንቢያ – Al-Anbiyā’
  22. ሱረቱ አል ሐጅ – Al-Hajj
  23. ሱረቱ አል–ሙዕሚኑን – Al-Mu’minūn
  24. ሱረቱ አልን ኑር – An-Noor
  25. ሱረቱ አል ፉርቃን – Al-Furqān
  26. ሱረቱ አሽ ሹዐራእ – Ash-Shu‘arā’
  27. ሱረቱ አን ነምል – An-Naml
  28. ሱረቱ አል ቀሰስ – Al-Qasas
  29. ሱረቱ አል ዐንከቡት – Al-‘Ankabūt
  30. ሱረቱ አር ሩም – Ar-Rūm
  31. ሱረቱ አል ሉቅማን – Luqmān
  32. ሱረቱ አስ ሰጅደህ – As-Sajdah
  33. ሱረቱ አል አሕዛብ – Al-Ahzāb
  34. ሱረቱ ሰበእ – Saba’
  35. ሱረቱ ፋጢር – Fātir
  36. ሱረቱ ያሲን – Yā-Sīn
  37. ሱረቱ አስ ሷፋት – As-Sāffāt
  38. ሱረቱ ሷድ – Sād
  39. ሱረቱ አዝ ዙመር – Az-Zumar
  40. ሱረቱ ጋፊር – Ghāfir
  41. ሱረቱ ፉሲለት – Fussilat
  42. ሱረቱ አሽ ሹራ – Ash-Shūra
  43. ሱረቱ አዝ ዙኽሩፍ – Az-Zukhruf
  44. ሱረቱ አድ ዱኻን – Ad-Dukhān
  45. ሱረቱ አል ጃሲያህ – Al-Jāthiyah
  46. ሱረቱ አል አህቃፍ – Al-Ahqāf
  47. ሱረቱ ሙሐመድ – Muhammad
  48. ሱረቱ አል ፈትህ – Al-Fat’h
  49. ሱረቱ አል ሑጅራት – Al-Hujurāt
  50. ሱረቱ ቃፍ – Qāf
  51. ሱረቱ አዝ ዛሪያት – Adh-Dhāriyāt
  52. ሱረቱ አጥ ጡር – At-Toor
  53. ሱረቱ አን ነጅም – An-Najm
  54. ሱረቱ አል ቀመር – Al-Qamar
  55. ሱረቱ አር ረሕማን – Ar-Rahmān
  56. ሱረቱ አል ዋቂዓህ – Al-Wāqi‘ah
  57. ሱረቱ አል ሐዲድ – Al-Hadīd
  58. ሱረቱ አል ሙጃደላ – Al-Mujādalah
  59. ሱረቱ አል ሐሽር – Al-Hashr
  60. ሱረቱ አል ሙምተሂና – Al-Mumtahanah
  61. ሱረቱ አስ ሶፍ – As-Saff
  62. ሱረቱ አል ጁሙዓህ – Al-Jumu‘ah
  63. ሱረቱ አል ሙናፊቁን – Al-Munāfiqūn
  64. ሱረቱ አት ተጋቡን – At-Taghābun
  65. ሱረቱ አጥ ጠላቅ – At-Talāq
  66. ሱረቱ አት ተህሪም – At-Tahrīm
  67. ሱረቱ አል ሙልክ – Al-Mulk
  68. ሱረቱ አል ቀለም – Al-Qalam
  69. ሱረቱ አል ሓቃህ – Al-Hāqqah
  70. ሱረቱ አል መዓሪጅ – Al-Ma‘ārij
  71. ሱረቱ ኑህ – Nūh
  72. ሱረቱ አል ጂን – Al-Jinn
  73. ሱረቱ አል ሙዘሚል – Al-Muzzammil
  74. ሱረቱ አል ሙደሲር – Al-Muddaththir
  75. ሱረቱ አል ቂያማህ – Al-Qiyāmah
  76. ሱረቱ አል ኢንሳን – Al-Insān
  77. ሱረቱ አል ሙርሰላት – Al-Mursalāt
  78. ሱረቱ አን ነበእ – An-Naba’
  79. ሱረቱ አን ናዚዓት – An-Nāzi‘āt
  80. ሱረቱ ዐበሰ – ‘Abasa
  81. ሱረቱ አት ተክዊር – At-Takwīr
  82. ሱረቱ አል ኢንፊጣር – Al-Infitār
  83. ሱረቱ አል ሙጠፊፊን – Al-Mutaffifīn
  84. ሱረቱ አል ኢንሺቃቅ – Al-Inshiqāq
  85. ሱረቱ አል ቡሩጅ – Al-Burūj
  86. ሱረቱ አጥ ጣሪቅ – At-Tāriq
  87. ሱረቱ አል አዕላ – Al-A‘lā
  88. ሱረቱ አል ጋሺያህ – Al-Ghāshiyah
  89. ሱረቱ አል ፈጅር – Al-Fajr
  90. ሱረቱ አል በለድ – Al-Balad
  91. ሱረቱ አሽ ሸምስ – Ash-Shams
  92. ሱረቱ አል ለይል – Al-Layl
  93. ሱረቱ አድ ዱሓ – Ad-Duhā
  94. ሱረቱ አሽ ሸርህ – Ash-Sharh
  95. ሱረቱ አት ቲን – At-Teen
  96. ሱረቱ አል ዐለቅ – Al-‘Alaq
  97. ሱረቱ አል ቀድር – Al-Qadr
  98. ሱረቱ አል–በይናህ – Al-Bayyinah
  99. ሱረቱ አል ዘልዘላህ – Az-Zalzalah
  100. ሱረቱ አል ዓዲያት – Al-‘Ādiyāt
  101. ሱረቱ አል ቃሪዓሕ – Al-Qāri‘ah
  102. ሱረቱ አት ተካሱር – At-Takāthur
  103. ሱረቱ አል ዓስር – Al-‘Asr
  104. ሱረቱ አል ሁመዛህ – Al-Humazah
  105. ሱረቱ አል ፊል – Al-Feel
  106. ሱረቱ ቁረይሽ – Quraysh
  107. ሱረቱ አል ማዑን – Al-Mā‘ūn
  108. ሱረቱ አል ከውሰር – Al-Kawthar
  109. ሱረቱ አል ካፊሩን – Al-Kāfirūn
  110. ሱረቱ አን ነስር – An-Nasr
  111. ሱረቱ አል መሰድ – Al-Masad
  112. ሱረቱ አል ኢኽላስ – Al-Ikhlās
  113. ሱረቱ አል ፈለቅ – Al-Falaq
  114. ሱረቱ አን ናስ – An-Nās

Copyright © 2026 Amharic Quran.

Theme: Oceanly by ScriptsTown