አል-ፋቲሐ (ቅዱስ ቁርአን ፣ ምዕራፍ 1) ቁርአን በአማርኛ ቋንቋ
አል-ፋቲሐህ (ቅዱስ ቁርአን ፣ ምዕራፍ 1)
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ [1] «ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒሂም»
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
In the name of Allah, the Most Compassionate, the Most Merciful.
ኢብኑ ዐባስ እንደዘገቡት፦ ነብዩ የአንድን ምዕራፍ
ማብቃት ያውቁት የነበረው «ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒሂም» ሲወርድ ነበር» ብለዋል።
አቡዳውድ እንደዘገቡትም፣ ዐብዱላህ ብን መስዑድ፦ «በሁለት ምዕራፎች መካከል መለያ ማወቅ
የጀመርነው «ቢስሚላ አር-ረሕማኒ አር-ረሂሒም» ከወረደ ወዲህ ነው» ብለዋል። ዐብዱላህ ብን
ዑመር፦ «ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒሂም» ከሁሉም ምዕራፍ ጋር አብሮ ወርዷል» ብለዋል።
(ዋሒዲ እና ሱዩጢ)
الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ [2]
ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤ (All praise be to Allah, the Lord of the worlds,)
الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ [3]
እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ (the Most Compassionate, the Most Merciful,)
مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ [4]
የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡ (Master of the Day of Judgment.)
إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ [5]
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡ (You alone we worship, and You alone we ask for help.)
اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ [6]
ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡ (Guide us to the straight path,)
صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ [7]
የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡ (the path of those whom You have blessed; not of those who incurred Your Wrath, or of those who went astray.)
በዚህ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ ኣሚን (ዱዓችንን ተቀበለን) የሚለዉን ቃል ማንበብ ተገቢ ነው። አህመድና ኢብኑ ማጃህ በዘገቡት ሐዲስ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم(፦ «አይሁዶች በሰላታችሁና ኣሚን በማለታችሁ የተመቀኟችሁን ያህል በምንም ነገር አልተመቀኟችሁም» ብለዋል። ትርጉሙም ዱዓችንን ተቀበለን ማለት ነው። ኢማምም የሆነ ሰው ቢሆን በትክከለኛው አባባል ፋቲሃን አንብቦ ሲያበቃ ድምፁን ከፍ አድርጎ ማንበብ ተገቢ መሆኑን ዋኢል ብን ሁጅር የተባሉት ሱሃቢ ነቢዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ወለዷሊን) የሚለዉን ካነበቡ በኋላ ድምፃቸዉን ከፍ አድርገው ኣሚን የሚለዉን ሳብ በማድረግ ያነቡት ነበር ብለዋል። ብቻዉን ሰጋጅና ተከታይ የሆነ ሰው በሁሉም ዘንድ ማለቱ ተገቢ ነው።
ከመክፈቻው ምዕራፍ ከምናገኛቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል በጥቂቱ:-
- ምስጋና በሙሉ የሚገባው የሁለንተናዊው ዓለም ፈጣሪና ተንከባካቢ ለሆነው ለአላህ ብቻ
እንደሆነ፤ - አላህ የሰው ልጆች በምድራዊ ቆይታቸው በሰሩት ስራ ምንዳ በሚያገኙበት የትንሳኤ ቀን ብቸኛ
ፍርድ ሰጪ ጌታ መሆኑን፤ - ከዱዓ ስርዓቶች መካከል ቅድሚያ አላህን ማሞገስ አስፈላጊ መሆኑን፤
- ለምድራዊም ሆነ አኼራዊ ጉዳዩች ብቸኛው ተለማኝ አንድ አላህ ብቻና ብቻ እንደሆነ፤ ከርሱም
በስተቀር ሊመለክና እርዳታ ሊጠየቅ የሚችል ሌላ አካል እንደሌለና በፍፁምነት ለእሱ
መተናነስና እርሱን ብቻ መጠየቅ እንደሚገባ፤ - አላህ መልካም ስሞችና ንፁህ ባህሪያት እንዳሉት እና ከባህሪያቶቹም እጅግ በጣም አዛኝና
ሩህሩህ የሚሉት ስሞች ግንባር ቀደም መሆናቸውን፤ - ቀጥተኛው መንገድ የሚባለው የነብያትን ፈለግ የተከተሉ ሁሉ የተጓዙበት በመሆኑንና የእነርሱን አርአያነት
መከተል ከምንም በላይ አስፈላጊ መሆኑን፤ - የአላህ ቁጣ ያደረባቸውን ሰዎች መንገድ ከመከተል መታቀብ ግዴታ መሆኑንና ለዚህም የአላህ
እገዛ አስፈላጊ እንደሆነና ሁሌም ቀጥተኛውን መንገድ ይመራን ዘንድ የእሱን እገዛ መጠየቅ እንዳለብን፤ - ወደ ቅኑዉም ሆነ መጥፎው መምራት የአላህ ስልጣን በመሆኑ ወደ ቅኑዉ እንዲመራን እሱን
ብቻ መማፀን እንዳለብን፤ - ከአላህ ሌላ ያለን አካል ነብያትንም ሆነ ወሊዮችን እርዳታ መጠየቅ ተገቢ አለመሆኑን
እንማራለን።
ሰዎች የእለት ጉርሳቸውን ይለምናሉ። እኛ ግን ዘላለማዊ ምሪትን እንለምናለን። ሰውየው ሙስሊምም ቢሆን በየጊዜው ሊሳሳት፣ የተሳሳተ ውሳኔ ሊወስን፣ ሰዎችን ሊበድል፣ ብሎም ከኢስላም ሊወጣ ይችላል፣ ስለዚህ የአላህን ምሪት አጥብቆ መለመን እጅግ በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።

አሰላም ዓለይኩም ቁርአን በአማርኛ እፈልጋለሁ።
ሙሉውን የአማርኛቁርአን ከነማብራሪያው እዚህ ያገኙታል። https://amharicquran.com/download/complete-quran-in-amharic-pdf-read-the-holy-quran-tafsir-in-the-amharic-language/
ሁሉንም 30 ጁዝ ቁረዐን በአማርኛ ማግኘት ፈልጌ ነበር።
ሙሉውን የአማርኛቁርአን ከነማብራሪያው እዚህ ያገኙታል። https://amharicquran.com/download/complete-quran-in-amharic-pdf-read-the-holy-quran-tafsir-in-the-amharic-language/