Default Image
11, Dec 2023
71 – Nooh

71 – Nooh

(1) እኛ ኑሕን «ሕዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ሕዝቦቹ ላክነው፡፡»(1) Indeed, We sent Noah to his people, “Warn your people before there comes to them a painful punishment.”
(2) (እርሱም) አለ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ ገላጭ የኾንኩ አስጠንቃቂ ነኝ፡፡(2) He said: “O my people, indeed I am a clear warner to you,
(3) «አላህን ተገዙት፣ ፍሩትም፣ ታዘዙኝም በማለት፤ (አስጠንቃቂ ነኝ)፡፡(3) that you worship Allah and fear Him, and obey me;
(4) «ለእናንተ ከኀጢኣቶቻችሁ ይምራልና፡፡ ወደተወሰነው ጊዜም ያቆያችኋል፡፡ የአላህ (የወሰነው) ጊዜ በመጣ ወቅት አይቆይም፡፡ የምታውቁት ብትኾኑ ኖሮ (በታዘዛችሁ ነበር)፡፡»(4) He will forgive you some of your sins and grant you respite until an appointed term. Indeed, when Allah’s appointed term comes, it cannot be delayed, if you only knew!”
(5) (ስለ ተቃወሙትም) «አለ ጌታዬ ሆይ! እኔ ሌሊትም ቀንም ሕዝቦቼን ጠራሁ፡፡(5) He said, “My Lord, I have surely called my people night and day,
(6) «ጥሪየም መሸሽን እንጅ ሌላ አልጨመረላቸውም፡፡(6) but my call only drove them further away.
(7) «እኔም ለእነርሱ ትምር ዘንድ (ወደ እምነት) በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ፡፡ ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ፡፡ (በመጥፎ ሥራቸው ላይ) ዘወተሩም፡፡ (ያለ ልክ) መኩራትንም ኮሩ፡፡(7) Every time I call them so that You may forgive them, they thrust their fingers into their ears and cover their faces with their garments, and persist in obstinacy and grow extremely arrogant.
(8) «ከዚያም እኔ በጩኸት ጠራኋቸው፡፡(8) Then I called them openly,
(9) «ከዚያም እኔ ለእነርሱ ገለጽኩ፡፡ ለእነርሱም መመስጠርን መሰጠርኩ(9) then I addressed them in public and in private,
(10) «አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡(10) I said, ‘Seek forgiveness from your Lord. Indeed, He is Most Forgiving.
(11) «በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል፡፡(11) He will shower you with abundant rain from the sky,
(12) «በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል፡፡»(12) and He will give you wealth and children, and bestow upon you gardens and rivers.
(13) ለአላህ ልቅናን የማትሹት ለእናንተ ምን አላችሁ?(13) What is the matter with you that you do not fear the Majesty of Allah,
(14) በልዩ ልዩ ኹኔታዎች በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲኾን፡፡(14) when He has created you in stages?
(15) አላህ ሰባትን ሰማያት አንዱ ካንዱ በላይ ሲኾን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን?(15) Do you not see how Allah has created seven heavens, one above another,
(16) በውስጣቸውም ጨረቃን አብሪ አደረገ፡፡ ፀሐይንም ብርሃን አደረገ፡፡(16) and has placed the moon therein as a light and the sun as a burning lamp?
(17) አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ፡፡(17) Allah has produced you from the earth like a plant,
(18) ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል፡፡ ማውጣትንም ያወጣችኋል፡፡(18) then He will return you into it, and then will bring you out again.
(19) አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት፡፡(19) Allah has made the earth wide spread for you
(20) ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ፡፡(20) so that you may tread its spacious paths.’”
(21) ኑሕ አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! እነሱ አምመጹብኝ፡፡ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ፡፡(21) Noah said, “My Lord, they have disobeyed me and followed those whose wealth and children did not increase them except in loss.
(22) «ታላቅንም ተንኮል የመከሩትን ሰዎች» (ተከተሉ)፡፡(22) They have contrived a mighty plot,
(23) አሉም «አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው፡፡(23) They said, ‘Do not abandon your gods; and do not abandon Wadd, Suwā‘, Yaghūth, Ya‘ūq, and Nasr.’
(24) «በእርግጥም ብዙዎችን አሳሳቱ፡፡ ከሓዲዎችንም ጥመትን እንጅ ሌላን አትጨምርላቸው» (አለ)፡፡(24) They have led many astray. So [O Lord], do not increase the wrongdoers except in error.”
(25) በኀጢኣቶቻቸው ምክንያት ተሰጠሙ፡፡ እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የኾኑ ረዳቶችን አላገኙም፡፡(25) Because of their sins, they were drowned and then were cast into the Fire, and they did not find any helpers against Allah.
(26) ኑሕም አለ «ጌታዬ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው፡፡(26) Noah said, “My Lord, do not leave on earth a single disbeliever.
(27) «አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና፡፡ ኀጢኣተኛ ከሓዲንም እንጅ ሌላን አይወልዱም፡፡(27) For if You leave them, they will surely lead Your slaves astray and beget none but wicked disbelievers.
(28) «ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ምእመን ኾኖ በቤቴ ለገባም ሰው ሁሉ ለምእመናንና ለምእምናትም ምሕረት አድርግ፡፡ ከሓዲዎችንም ከጥፋት በቀር አትጨምርላቸው፤» (አለ)፡፡(28) My Lord, forgive me and my parents, and whoever enters my house as a believer, and all the believing men and women, and do not increase the wrongdoers except in ruin.”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

95 – At-Tin

95 – At-Tin (1) በበለስና በዘይት ወይራ እምላለሁ፡፡ (1) By the fig and the olive [of Jerusalem], (2) በሲኒን ተራራም፤ (2)…

52 – At-Tur

52 – At-Tur (1) በጡር (ጋራ) እምላለሁ፡፡ (1) By the mount of Tūr, (2) በተጻፈው መጽሐፍም፡፡ (2) and by the Book inscribed…

38 – Saad

38 – Saad (1) ጸ. (ሷድ) የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ (ብዙ አማልክት አሉ እንደሚሉት አይደለም)፡፡ (1) Sād. By the Qur’an, full of…