Default Image
19, Dec 2023
99 – Az-Zalzala

99 – Az-Zalzala

(1) ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤ (1) When the earth is shaken with a mighty quake,
(2) ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤ (2) and the earth throws out its burdens,
(3) ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤ (3) and man says, “What is the matter with it?”
(4) በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡ (4) On that Day it will recount all its news,
(5) ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡ (5) because your Lord has inspired it [to do so].
(6) በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡ (6) On that Day all people will come forward in separate groups to be shown their deeds.
(7) የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡ (7) So whoever does an atom’s weight of good will see it,
(8) የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡ (8) and whoever does an atom’s weight of evil will see it.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

62 – Al-Jumu’a

62 – Al-Jumu’a (1) በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ፣ ቅዱስ፣ አሸናፊ፣ ጥበበኛ ለኾነው ያሞግሳል፡፡ (1) All that is…

46 – Al-Ahqaf

46 – Al-Ahqaf (1) ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ (1) Hā Mīm. (2) የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ነው፡፡ (2) The revelation…

36 – Yaseen

36 – Yaseen (1) የ.ሰ.(ያ ሲን) (1) Yā Sīn (2) ጥበብ በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡ (2) By the Qur’an, full of…