Default Image
17, Dec 2023
84 – Al-Inshiqaaq

84 – Al-Inshiqaaq

(1) ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤(1) When the sky is rent asunder,
(2) ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤(2) and hearkens to its Lord, as it must,
(3) ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤(3) and when the earth is leveled out,
(4) በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤(4) and casts out all what it contains, and becomes empty,
(5) ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡(5) and hearkens to its Lord, as it must,
(6) አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡(6) O humans, you are toiling towards your Lord, and you will surely meet Him.
(7) መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤(7) Whoever is given his Record in his right hand,
(8) በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡(8) he will have an easy reckoning,
(9) ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡(9) and he will return to his people joyfully.
(10) መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤(10) But whoever is given his Record from behind his back,
(11) (ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡(11) he will call out for destruction,
(12) የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡(12) and he will enter the Blazing Fire.
(13) እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡(13) Indeed, he used to live among his people joyfully.
(14) እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡(14) and he thought that he would never return [to Allah].
(15) አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡(15) Indeed he will! His Lord was always watching him.
(16) አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡(16) Indeed, I swear by the twilight,
(17) በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤(17) and by the night and what it covers,
(18) በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡(18) and by the moon when it becomes full,
(19) ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡(19) You will surely pass from one stage to another.
(20) የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው?(20) Then what is the matter with them that they do not believe,
(21) በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?)(21) and when the Qur’an is recited to them, they do not prostrate?
(22) በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡(22) Rather, the disbelievers persist in denying it,
(23) አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡(23) but Allah knows best whatever they harbor in their hearts.
(24) በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡(24) So give them the tidings of a painful punishment.
(25) ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡(25) But those who believe and do righteous deeds will have a never-ending reward.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

24 – An-Noor

24 – An – Noor سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ [1] (1) (ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ምዕራፍ…

31 – Luqman

31 – Luqman (1) አ.ለ.መ. (አሊፍ ላም ሚም)፡፡ (1) Alif Lām Mīm. (2) ይህች ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡ (2) These…

ግደሉ የሚለው ቁርአን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ?

ግደሉ የሚለው ቁርአን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ? የግድያ መፅሀፍ የሚመስለው ቅዱስ ቁርአን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ? እስኪ ከመፅሀፍ ቅዱስ ጀምረን እንየው:- ግደል…