Default Image
11, Dec 2023
78 – An-Naba

78 – An-Naba

(1) ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?(1) About what are they asking one another?
(2) ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡(2) About the momentous news,
(3) ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡(3) about which they differ.
(4) ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡(4) No indeed; they will come to know.
(5) ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡(5) Again no; they will come to know.
(6) ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን?(6) Have We not made the earth a resting place?
(7) ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን?(7) And the mountains as stakes,
(8) ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡(8) and created you in pairs,
(9) እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡(9) and made your sleep for rest,
(10) ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡(10) and made the night a covering,
(11) ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡(11) and made the day for seeking livelihood,
(12) ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡(12) and built above you seven mighty heavens,
(13) አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡(13) and made therein a blazing lamp,
(14) ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡(14) and sent down from the rainclouds abundant water,
(15) በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡(15) so that We may produce thereby grains and vegetation,
(16) የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡(16) and gardens with dense foliage?
(17) የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡(17) Indeed, the Day of Judgment is a time appointed,
(18) በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡(18) the Day when the Trumpet will be blown, you will come forth in crowds,
(19) ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡(19) and the sky will be opened up and will become gateways,
(20) ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡(20) and the mountains will vanish, becoming like a mirage.
(21) ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡(21) Indeed, Hell is lying in wait,
(22) ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡(22) a resort for the transgressors,
(23) በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤(23) wherein they will abide for endless ages.
(24) በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡(24) They will neither taste therein any coolness nor any drink,
(25) ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡(25) except scalding water and discharge of wounds,
(26) ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡(26) a fitting recompense.
(27) እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡(27) Indeed, they did not expect a reckoning,
(28) በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡(28) and utterly rejected Our verses.
(29) ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡(29) But We have enumerated everything in a record.
(30) ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡(30) So taste [the punishment], for We will not increase you except in torment.”
(31) ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡(31) Indeed, the righteous will have salvation,
(32) አትክልቶችና ወይኖችም፡፡(32) gardens and vineyards,
(33) እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡(33) and full-bosomed maidens of equal age,
(34) የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡(34) and a full cup [of wine].
(35) በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡(35) They will not hear therein vain talk or lies –
(36) ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡(36) a reward and a generous gift from your Lord,
(37) የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡(37) [from] the Lord of the heavens and earth and all that is between them, the Most Compassionate; none will dare to speak to Him.
(38) መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡(38) On the Day when the Spirit and the angels will stand in rows; none will dare to speak, except those to whom the Most Compassionate granted permission, and they will only speak the truth.
(39) ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡(39) That Day is sure to come. So whoever wills may seek a path leading to his Lord.
(40) እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡(40) Indeed, We have warned you of an imminent punishment on the Day when everyone will see what his hands have sent forth, and the disbeliever will say, “Oh, I wish that I were dust!”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

55 – Ar-Rahmaan

55 – Ar-Rahmaan (1) አል-ረሕማን፤ (1) The Most Compassionate, (2) ቁርኣንን አስተማረ፡፡ (2) has taught the Qur’an, (3) ሰውን ፈጠረ፡፡…

67 – Al-Mulk

67 – Al-Mulk (1) ያ ንግሥና በእጁ የኾነው አምላክ ችሮታው በዛ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ (1) Blessed is…

37 – As-Saaffaat

37 – As-Saaffaat (1) መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡ (1) By those [angels] lined up in rows, (2) መገሠጽንም በሚገሥጹት፤ (2) and those who drive [the…