Default Image
10, Dec 2023
37 – As-Saaffaat

37 – As-Saaffaat

(1) መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡(1) By those [angels] lined up in rows,
(2) መገሠጽንም በሚገሥጹት፤(2) and those who drive [the clouds],
(3) ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡(3) and those who recite Allah’s words,
(4) አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡(4) indeed, your God is One,
(5) የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡(5) Lord of the heavens and earth and all that is between them, and Lord of the points of sunrise.
(6) እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡(6) We have adorned the sky with the beauty of the stars,
(7) አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡(7) and for safeguarding it against every rebellious devil,
(8) ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡(8) so that they cannot eavesdrop on the highest assembly [of angels] and are pelted from every side
(9) የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡(9) to repel them; and for them there will be a perpetual punishment,
(10) ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡(10) except who stealthily snatches away some words, he will be pursued by a piercing flame.
(11) ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡(11) So ask them, “Are they more difficult to create or other things We created? We created them from sticky clay.
(12) ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡(12) Rather you are astonished, while they ridicule it,
(13) በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡(13) and when they are reminded, they pay no heed,
(14) ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡(14) and when they see a sign, they ridicule it,
(15) ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡(15) and they say, “This is nothing but clear magic.
(16) «በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?(16) Is it that when we are dead and become dust and bones, will we really be raised up again,
(17) «የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡(17) and our forefathers too?”
(18) «አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡(18) Say, “Yes, and you will be disgraced.”
(19) እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡(19) It will only be a single Blast, and at once they will be looking around.
(20) «ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡(20) They will say, “Woe to us! This is the Day of Judgment!”
(21) «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡(21) [They will be told], “This is the Day of Decision that you used to deny.”
(22) (ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡(22) [The angels will be told], “Gather all those who did wrong and their fellows, and whatever they used to worship
(23) «ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡(23) besides Allah, and lead them to the way of Hell,
(24) «አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡(24) and stop them, for they are to be questioned.”
(25) (ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡(25) [They will be asked], “What is the matter with you, that you no longer help one another?”
(26) በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡(26) Rather on that Day they will surrender completely.
(27) የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡(27) They will turn to one another, reproaching one another.
(28) (ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡(28) [The followers] will say, “It was you who used to delude us from the right way.”
(29) (አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡(29) [The misleaders] will say, “Rather, you yourselves were not believers,
(30) «ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡(30) and We had no power over you, rather you yourselves were a transgressing people.
(31) «በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡(31) Now the punishment of our Lord has come true against us; we will surely taste it.
(32) «ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡(32) We did misguide you, for we ourselves were misguided”.
(33) ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡(33) On that Day they will all share in the punishment.
(34) እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡(34) This is how We deal with the wicked,
(35) እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡(35) for whenever it was said to them, “None has the right to be worshiped except Allah,” they became arrogant,
(36) እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡(36) and said, “Are we going to abandon our gods for a mad poet?”
(37) አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡(37) Rather, he came with the truth and confirmed the messengers.
(38) እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡(38) You will surely taste the painful punishment,
(39) ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡(39) and you will only be recompensed for what you used to do,
(40) ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡(40) except the chosen slaves of Allah.
(41) እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡(41) They will have a known provision,
(42) ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤(42) fruits; and they will be honored
(43) በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡(43) in Gardens of Bliss,
(44) ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡(44) facing one another on couches.
(45) ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡(45) They will be served with a cup of wine from a flowing stream,
(46) ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡(46) white and delicious for those who drink.
(47) በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡(47) It will cause no harm, nor will they be intoxicated by it,
(48) እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡(48) and with them will be maidens of modest gaze and beautiful eyes,
(49) እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡(49) as if they were well-protected eggs.
(50) የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡(50) Then they will turn to one another asking.
(51) ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡(51) One of them will say, “I had a close friend [in the world]
(52) «በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡(52) who used to say, ‘Are you one of those who believe
(53) «በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡(53) that when we die and become dust and bones, shall we be brought for judgment?’”
(54) እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡(54) He will say, “Do you wish to see [his fate]?”
(55) ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡(55) So he will look down and see him in the midst of the Blazing Fire.
(56) ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡(56) He will say, “By Allah, you were about to ruin me.
(57) «የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡»(57) Were it not for the grace of my Lord, I would have been among those who are brought [to Hell].”
(58) (የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን?(58) [He will say to his fellow believers], “Are we not going to die anymore,
(59) «የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡(59) except our first death, nor are we going to be punished ?”
(60) ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡(60) This is indeed the supreme triumph!
(61) ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡(61) For such [reward] let the workers work.
(62) በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?(62) Is this a better accommodation or the tree of Zaqqūm?
(63) እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡(63) We have made it a trial for the wrongdoers.
(64) እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡(64) It is a tree that grows in the bottom of the Blazing Fire;
(65) እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡(65) its fruits are like heads of devils.
(66) እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡(66) They will certainly eat from it, filling their bellies.
(67) ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡(67) Then on top of that they will be given a mixture of scalding water,
(68) ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡(68) then their final return will be to the Blazing Fire.
(69) እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡(69) For they found their forefathers astray,
(70) እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡(70) so they rushed to follow in their footsteps.
(71) ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡(71) Indeed, most of the earlier people went astray before them,
(72) በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡(72) even though We sent among them warners.
(73) የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡(73) Then see how was the end of those who were warned,
(74) ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡(74) except the chosen slaves of Allah.
(75) ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን!(75) Indeed, Noah called upon Us; how excellent are We at responding!
(76) እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡(76) And We saved him and his household from the great distress,
(77) ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤(77) and made his offspring the only survivors,
(78) በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡(78) and We left for him [a favorable mention] among later generations:
(79) «በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡»(79) “Peace be upon Noah among all the nations.”
(80) እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡(80) This is how We reward those who do good.
(81) እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡(81) He was one of Our believing slaves.
(82) ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡(82) Then we drowned the others.
(83) ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡(83) Indeed, Abraham was one of those who followed his way.
(84) ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡(84) When he came to his Lord with a sound heart,
(85) «ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡(85) and said to his father and his people, “What are you worshiping?
(86) «ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?(86) Is it false gods that you seek other than Allah?
(87) «በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡(87) Then what do you think of the Lord of the worlds?”
(88) በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡(88) He then cast a glance at the stars,
(89) «እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡(89) and said, “I am sick.”
(90) ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡(90) So they went away from him and left.
(91) ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?»(91) Then he turned to their gods and said, “Will you not eat?
(92) «የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?»(92) What is wrong with you that you do not speak?”
(93) በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡(93) Then he turned upon them, striking them with his right hand.
(94) ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡(94) Then his people came rushing towards him.
(95) አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?»(95) He said, “Do you worship what you yourselves carve,
(96) «አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡»(96) when it is Allah Who created you and all what you do?”
(97) «ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡(97) They said, “Build a pyre for him and throw him into the blazing fire.”
(98) በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡(98) They contrived a plan against him, but We made them the lowest.
(99) አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡»(99) He said, “I am going to my Lord; He will guide me.
(100) ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡(100) My Lord, grant me righteous offspring.”
(101) ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡(101) So We gave him glad tidings of a forbearing boy.
(102) ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡(102) Then when he reached the age where he could work with him, Abraham said, “O my dear son, I have seen in a dream that I must sacrifice you. What you think?” He said, “O my dear father, do as you are commanded. You will find me, if Allah wills, one of the steadfast.”
(103) ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡(103) When they both submitted [to Allah’s command] and Abraham laid him on his forehead,
(104) ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ!(104) and We called out to him, “O Abraham,
(105) ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡(105) You have fulfilled the dream.” This is how We reward those who do good.
(106) ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡(106) This was indeed a revealing test.
(107) በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡(107) And We ransomed him with a great sacrifice,
(108) በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡(108) and We left for him [a favorable mention] among later generations:
(109) ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡(109) “Peace be upon Abraham.”
(110) እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡(110) This is how We reward those who do good.
(111) እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡(111) He was one of Our believing slaves.
(112) በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡(112) And We gave him the glad tidings of Isaac, a prophet, and one of the righteous.
(113) በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡(113) We blessed him and Isaac, but among their offspring were some who did good and some who clearly wronged themselves.
(114) በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡(114) Indeed, We bestowed Our favor upon Moses and Aaron,
(115) እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡(115) and We saved them and their people from the great distress,
(116) ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡(116) and We helped them, so they were the victorious,
(117) በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡(117) and We gave them both the clear Scripture,
(118) ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡(118) and guided them to the straight path;
(119) በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡(119) and We left for them [a favorable mention] among later generations:
(120) ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡(120) “Peace be upon Moses and Aaron.”
(121) እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡(121) This is how We reward those who do good.
(122) ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡(122) Indeed, they were among Our believing slaves.
(123) ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡(123) Indeed, Elijah was one of the messengers.
(124) ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን?(124) When he said to his people: “Do you not fear Allah?
(125) በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን?(125) Do you call upon Ba‘l and ignore the Best of the Creators,
(126) አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)?(126) Allah, your Lord and the Lord of your forefathers?”
(127) አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡(127) But they rejected him, so they will surely be brought [for punishment],
(128) ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡(128) except the chosen slaves of Allah.
(129) በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡(129) And We left for him [a favorable mention] among later generations:
(130) ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡(130) “Peace be upon Elias.”
(131) እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡(131) This is how We reward those who do good.
(132) እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡(132) He was one of Our believing slaves.
(133) ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡(133) Indeed, Lot was one of the messengers.
(134) እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡(134) When We saved him and all of his household,
(135) (በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡(135) except an old woman who was among those who stayed behind.
(136) ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡(136) Then We destroyed the rest.
(137) እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡(137) You [Makkans] pass by their ruins by day
(138) በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን?(138) and by night. Do you still not understand?
(139) ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡(139) Indeed, Jonah was one of the messengers.
(140) ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡(140) When he fled to the fully-laden ship,
(141) ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡(141) then he cast lots with them, but was among those who lost.
(142) እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡(142) The whale then swallowed him while he was blameworthy.
(143) እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤(143) Were it not for the fact that he was one of those who glorify Allah,
(144) እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡(144) he would have stayed in its belly until the Day of Resurrection.
(145) እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡(145) But We cast him ashore on a barren land while he was ill,
(146) በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡(146) and caused a gourd vine to grow over him.
(147) ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡(147) We sent him to one hundred thousand people or more,
(148) አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡(148) and they believed, so We let them enjoy for a while.
(149) (የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?»(149) So ask them, “Does your Lord have daughters while they have sons?”
(150) ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?(150) Or did We create the angels as females while they were watching?
(151) ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡-(151) No indeed, it is one of their fabrications when they say,
(152) «አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡(152) “Allah has children,” and they are truly liars.
(153) በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን?(153) Did He choose daughters over sons?
(154) ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!(154) What is the matter with you? How do you judge?
(155) አትገነዘቡምን?(155) Will you not then take heed?
(156) ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን?(156) Do you have any compelling proof?
(157) «እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡(157) Then bring your scripture, if you are truthful.
(158) በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡(158) They claim that there is kinship between Him and the jinn, when the jinn themselves know that such people will surely be brought [for punishment].
(159) አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡(159) Glorified is Allah far above what they ascribe [to Him].
(160) ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡(160) But not the chosen slaves of Allah.
(161) እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤(161) Indeed, you and whatever you worship
(162) በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡(162) none of you can lure anyone away from Him,
(163) ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡(163) except those who are destined to burn in the Blazing Fire.
(164) (ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡(164) [The angels say], “There is none among us but has a known station:
(165) እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡(165) We are indeed those who stand lined up in rows,
(166) እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡(166) and we are indeed those who glorify Allah.”
(167) እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡-(167) And [the pagans] used to say,
(168) «ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤(168) “If only we had a scripture like the previous people,
(169) «የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡»(169) we would have surely been true slaves of Allah.”
(170) ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡(170) But they rejected it; soon they will come to know.
(171) (የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡(171) Our Word has already been given to Our slaves, the messengers,
(172) እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡(172) that it is surely they who will be given victory,
(173) ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡(173) and that Our soldiers will surely be the victors.
(174) ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡(174) So turn away from them for a while.
(175) እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡(175) Wait and see; soon they will see [their end].
(176) በቅጣታችንም ያቻኩላሉን?(176) Do they really seek to hasten Our punishment?
(177) በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!(177) When it descends on their courtyard, how terrible will be the morning of those who were warned!
(178) እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡(178) And turn away from them for a while.
(179) ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡(179) Wait and see; soon they will see [their end].
(180) የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡(180) Glory be to your Lord, the Lord of Might, far above what they ascribe [to Him],
(181) በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤(181) and peace be upon the messengers,
(182) ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡(182) and all praise be to Allah, the Lord of the worlds.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

14 – Ibrahim

14 – Ibrahim (1) አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርአን) ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አሸናፊ ምስጉን ወደ ኾነው፡፡…

112 – Al-Ikhlaas

112 – Al-Ikhlaas (1) በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ (1) Say: He is Allah, the One; (2) «አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ (2)…

99 – Az-Zalzala

99 – Az-Zalzala (1) ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤ (1) When the earth is shaken with a mighty quake, (2) ምድር ሸክሞችዋን…