| (1) እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡ |
(1) By the galloping, panting horses, |
| (2) (በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤ |
(2) striking sparks of fire [with their hooves], |
| (3) በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤ |
(3) launching raids at dawn, |
| (4) በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤ |
(4) stirring up thereby clouds of dust, |
| (5) በ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡ |
(5) plunging thereby into the midst of the enemy, |
| (6) ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡ |
(6) indeed, man is very ungrateful to his Lord – |
| (7) እርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡ |
(7) and he himself is a witness to that – |
| (8) እርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡ |
(8) and he is truly extreme in his love of wealth. |
| (9) (ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤ |
(9) Does he not know that the contents of graves will be overturned, |
| (10) በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡ |
(10) and the secrets of the hearts will be brought to light? |
| (11) ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡ |
(11) Indeed, their Lord is All-Aware of them on that Day. |