34 – Saba
34 – Saba
| (1) ምስጋና ለዚያ በሰማያትም ያለ በምድርም ያለ ሁሉ የርሱ ለኾነው ለአላህ ይገባው፡፡ በመጨረሻይቱም ዓለም ምስጋና ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ብልሃተኛው ውስጠ ዐዋቂው ነው፡፡ | (1) All praise is for Allah to Whom belongs all that is in the heavens and all that is on earth, and to Him is the praise in the Hereafter; He is the All-Wise, All-Aware. |
| (2) በምድር ውስጥ የሚገባውን ሁሉ ከእርሷም የሚወጣውን ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ሁሉ ያውቃል፡፡ እርሱም አዛኙ መሓሪው ነው፡፡ | (2) He knows whatever goes into the earth and whatever comes out of it, and whatever descends from the heaven and whatever ascends to it, and He is the Most Merciful, All-Forgiving. |
| (3) እነዚያ የካዱትም «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡፡ በላቸው «አይደለም፤ ሩቁን ሁሉ ዐዋቂ በኾነው ጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትመጣባችኋለች፡፡ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእርሱ አይርቅም፡፡ ከዚህ ያነሰም ኾነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢኾን እንጅ፡፡» | (3) Those who disbelieve say, “The Hour will not come to us.” Say, “Yes, by my Lord, it will surely come to you.” [He is] the Knower of the unseen; not even an atom’s weight is hidden from Him in the heavens or on earth, nor is there anything smaller or bigger than that, except that it is in a clear Record, |
| (4) እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ሊመነዳ (ሰዓቲቱ ትመጣባችኋለች)፤ እነዚያ ለእነርሱ ምህረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው፡፡ | (4) so that He may reward those who believe and do righteous deeds; it is they who will have forgiveness and a generous provision. |
| (5) እነዚያም የሚያመልጡ መስሏቸው አንቀጾቻችንን ለማፍረስ የጣሩ እነዚያ ለእነርሱ ከመጥፎ ቅጣት የኾነ አሳማሚ ስቃይ አላቸው፡፡ | (5) But those who strive against Our verses, seeking to discredit them, for such there will be a punishment of agonizing pain. |
| (6) እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት ያንን ከጌታህ ወዳንተ የተወረደውን እርሱ እውነትና አሸናፊ ምስጉን ወደ ኾነው አላህ መንገድ የሚመራ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ | (6) Those who are blessed with knowledge can see that whatever has been sent down to you from your Lord is the truth, and that it guides to the path of the All-Mighty, the Praiseworthy. |
| (7) እነዚያም የካዱት «(ሙታችሁ) መበጣጠስን ሁሉ በተበጣጠሳችሁ ጊዜ እናንተ በአዲስ መፈጠር ውስጥ ትኾናላችሁ ብሎ የሚነግራችሁን ሰው እናሳያችሁን?» አሉ፡፡ | (7) The disbelievers [mockingly] say, “Shall we show you a man who will tell you that when you are completely disintegrated into dust, you will be created anew?” |
| (8) በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈን? ወይስ በእርሱ ዕብደት አለበትን? (አሉ)፡፡ እንዳሉት አይደለም፡፡ እነዚያ በመጨረሻይቱ (ዓለም) የሚያምኑት (በእርሷ) በቅጣት ውስጥ (አሁን) በራቀ ስህተትም ውስጥ ናቸው፡፡ | (8) Has he fabricated a lie against Allah, or is he mad?” No, but those who do not believe in the Hereafter will be in the punishment, and they are extremely misguided. |
| (9) ከሰማይና ከምድር በፊታቸውና በኋላቸው ወዳለው ሁሉ አይመለከቱምን? ብንሻ በእነርሱ ምድርን እንደረባባቸዋለን፡፡ ወይም በእነርሱ ላይ ከሰማይ ቁራጭን እንጥልባቸዋለን፤ በዚህ ውስጥ (ወደ ጌታው) ተመላሽ ለኾነ ባሪያ ሁሉ ምልክት አለበት፡፡ | (9) Do they not see all that is before them and all that is behind them of the heavens and earth? If We willed, We could cause the earth to swallow them up, or cause fragments of the sky to fall upon them. Indeed, there is a sign in this for every slave who turns to Allah in repentance. |
| (10) ለዳውድም ከእኛ የኾነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው፡፡ (አልንም)፡-«ተራራዎች ሆይ! ከእርሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ፡፡ በራሪዎችንም (ገራንለት)፡፡ ብረትንም ለእርሱ አለዘብንለት፡፡» | (10) Indeed, We bestowed favors upon David: “O mountains, echo Allah’s praise with him, and the birds too!” And We made iron malleable for him: |
| (11) ሰፋፊዎችን ጥሩሮች ሥራ፡፡ በአሠራርዋም መጥን፡፡ መልካምንም ሥራ ሥሩ፡፡ እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና (አልነው)፡፡ | (11) “Make coats of mail, and maintain balance in the linking rings, and do [all of you] righteous deeds, for I am All-Seeing of what you do.” |
| (12) ለሱለይማንም ነፋስን የቀትር በፊት ጉዞዋ የወር መንገድ የቀትር በኋላ ጉዞዋም የወር መንገድ ሲኾን ገራንለት፡፡ የነሐስንም ምንጭ ለእርሱ አፈሰስንለት፡፡ ከጋኔኖችም በጌታው ፈቃድ በፊቱ የሚሠሩን (አደረግንለት)፡፡ ከነርሱም ውስጥ ከትእዛዛችን ዝንፍ የሚል ከነዲድ እሳት ቅጣት እናቀምሰዋለን፡፡ | (12) And to Solomon [We subdued] the wind: its morning course was a month’s journey and its evening course was a month’s journey. And We caused a stream of molten brass to flow for him, and there were some jinn who worked for him by his Lord’s permission; whoever among them deviated from Our command, We made him taste the punishment of the Blazing Fire. |
| (13) ከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል፡፡ (አልናቸውም) «የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ! አመስጋኞች ኾናችሁ (ለጌታችሁ) ሥሩ፡፡» ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡ | (13) They made for him whatever he wished of sanctuaries, images, basins as large as reservoirs, and huge fixed cooking pots. “Do [good deeds] in gratitude, O household of David!” But few of My slaves are grateful.” |
| (14) በእርሱም ላይ ሞትን በፈጸምንበት ጊዜ መሞቱን በትሩን የምትበላ ተንቀሳቃሽ ምስጥ እንጂ ሌላ አላመለከታቸውም፡፡ በወደቀ ጊዜም ጋኔኖች ሩቅን ምስጢር የሚያወቁ በኾኑ ኖሮ በአዋራጅ ስቃይ ውስጥ የማይቆይ እንደነበሩ ተረዱ፡፡ | (14) Then when We decreed Solomon’s death, nothing showed them that he was dead except a creature of the earth eating away his staff. When he fell down, the jinn realized that if they had truly known the unseen, they would not have remained in the debasing servitude. |
| (15) ለሰበእ በመኖሪያቸው በእውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው፡፡ ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች (ነበሯቸው)፡፡ «ከጌታችሁ ሲሳይ ብሉ፡፡ ለእርሱም አመስግኑ፡፡ (አገራችሁ) ውብ አገር ናት፡፡ (ጌታችሁ) መሓሪ ጌታም ነው» (ተባሉ)፡፡ | (15) There was a sign for [the people of] Sheba in their dwelling place: two gardens – one on the right and one on the left. “Eat of your Lord’s provision, and be grateful to Him; a pleasant land and a Forgiving Lord.” |
| (16) (ከማመስገን) ዞሩም፡፡ በእነርሱም ላይ የግድቡን ጎርፍ ለቀቅንባቸው፡፡ በአትክልቶቻቸውም ሁለት አትክልቶች፣ ባለመርጋጋ ፍሬዎችን፣ ባለጠደቻና ከቁርቁራም ባለጥቂት ዛፎችን ለወጥናቸው፡፡ | (16) But they turned away, so We sent against them a devastating flood, and replaced their two gardens with two others of bitter fruit, and tamarisk bushes, and a few lote trees. |
| (17) በመካዳቸው ይህንን መነዳናቸው፤ (እንዲህ ያለውን ቅጣት) በጣም ከሓዲን እንጂ ሌላውን እንቀጣለን? | (17) This is how We punished them for their ingratitude; would We punish anyone except those who are utterly ungrateful? |
| (18) በእነርሱና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር (በሻም) መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አደረግን፡፡ በእርሷም ጉዞን ወሰንን፡፡ «ጸጥተኞች ኾናችሁ በሌሊቶችም በቀኖችም ተጓዙ፤» (አልን)፡፡ | (18) We placed [a chain of] towns between them and the towns We had blessed, and We made between them well-measured distances: “Travel through them by night and day safely.” |
| (19) «ጌታችን ሆይ! በጉዞዎቻችን መካከል አራርቅልን» አሉም፡፡ ነፍሶቻቸውንም በደሉ፡፡ (መገረሚያ) ወሬዎችም አደረግናቸው፡፡ መበታተንንም ሁሉ በታተንናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ መገሰጫዎች አሉበት፡፡ | (19) But they said, “Our Lord, make [the distance between] our journeys longer,” and they wronged themselves. So We made them tales [of the past], and dispersed them in all directions. Indeed, there are signs in this for everyone who is patient and grateful. |
| (20) ኢብሊስም በእነርሱ ላይ ምኞቱን በእርግጥ ፈጸመ፤ ከአመኑትም የሆኑት ጭፍሮች በስተቀር ተከተሉት፡፡ | (20) Satan found his assumption about them to be true, for they followed him, except for a group of the believers, |
| (21) በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያምነውን ከዚያ እርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ከሆነው ሰው ለይተን እንድናውቅ እንጅ በእነርሱ ላይ ለእርሱ ምንም ስልጣን አልነበረውም፡፡ ጌታህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ | (21) even though he had no authority over them, except that We might distinguish those who believe in the Hereafter from those who are in doubt about it. Your Lord is Watchful over all things.” |
| (22) «እነዚያን ከአላህ ሌላ (አማልክት ብላችሁ) የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም፤» በላቸው፡፡ | (22) Say, “Call upon those whom you claim [to be gods] besides Allah. They do not have even an atom’s weight of authority in the heavens or on earth, nor do they have any share in either of them, nor is any of them a helper to Allah.” |
| (23) ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፡፡ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጸም ጊዜ (ተማላጆቹ) «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ፡፡ (አማላጆቹ) «እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው» ይላሉ፡፡ | (23) No intercession will be of any benefit before Him, except for those whom He gave permission. Until when their hearts are relieved of dread, they will say [to the angels], “What did your Lord just say?” They will say, “The Truth, and He is the Most High, Most Great.” |
| (24) «ከሰማያትና ከምድር (ዝናብንና በቃይን) የሚሰጣችሁ ማነው?» በላቸው፡፡ «አላህ ነው፡፡ እኛ ወይም እናንተ በትክክለኛው መንገድ ላይ ወይም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነን» በላቸው፡፡ | (24) Say, “Who provides for you from the heavens and earth?” Say, “Allah! And surely either We or you are rightly guided or clearly misguided.” |
| (25) «ከአጠፋነው ጥፋት አትጠየቁም፡፡ ከምትሠሩትም ሥራ አንጠየቅም» በላቸው፡፡ | (25) Say, “You will not be questioned about our misdeeds, nor will we be questioned about your deeds.” |
| (26) «ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው» በላቸው፡፡ | (26) Say, “Our Lord will gather us together, then He will rightly judge between us, for He is the All-Knowing Judge.” |
| (27) «እነዚያን ተጋሪዎች አድርጋችሁ በእርሱ ያስጠጋችኋቸውን (ጣዖታት) አሳዩኝ፡፡ ተዉ (አታጋሩ)፤ በእውነቱ እርሱ አሸናፊው ብልሃተኛው አላህ ነው» በላቸው፡፡ | (27) Say, “Show me those whom you have associated with Him as partners. No indeed! Rather, He is Allah, the All-Mighty, All-Wise.” |
| (28) አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ | (28) We have not sent you [O Prophet] except as a bearer of glad tidings and a warner to all mankind, but most people do not know. |
| (29) «እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ፡፡ | (29) They say, “When will this promise come to pass, if you are truthful?” |
| (30) «ለእናንተ ከእርሱ አንዲትንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም የቀጠሮ ቀን አላችሁ» በላቸው፡፡ | (30) Say, “There is an appointed Day for you that you can neither delay for a while, nor can you bring it forward.” |
| (31) እነዚያ የካዱትም በዚህ ቁርኣን በዚያ ከበፊቱ ባለውም (መጽሐፍ) በጭራሽ አናምንም አሉ፡፡ | (31) Those who disbelieve say, “We will never believe in this Qur’an or in any [Scripture] before it.” If only you could see when the wrongdoers will be made to stand before their Lord, throwing blame at one another! Those who were oppressed will say to those who were arrogant, “Had it not been for you, we would have been believers.” |
| (32) እነዚያ የኮሩት ለእነዚያ ለተዋረዱት «ከትክክለኛው እምነት ከመጣላችሁ በኋላ እኛ ከለከልናችሁን? አይደለም (እናንተው) ከሓዲዎች ነበራችሁ» ይሏቸዋል፡፡ | (32) Those who were arrogant will say to those who were oppressed, “Was it we who prevented you from guidance after it came to you? Rather, you yourselves were wicked.” |
| (33) እነዚያም የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «አይደለም፤ በአላህ እንድንክድና ለእርሱ ባላንጣዎችን እንድናደርግ ስታዙን (የከለከለን) የሌሊትና የቀን ዱለታችሁ ነው» ይላሉ፡፡ ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይገልጻሉ፡፡ በእነዚያም በካዱት አንገቶች ላይ እንዛዝሎችን እናደርጋለን፡፡ ይሠሩት የነበሩትን እንጂ ሌላን ይመነዳሉን? | (33) Those who were oppressed will say to those who were arrogant, “Rather, [it was your] conspiracy of night and day when you were ordering us to disbelieve in Allah and to set up rivals to Him.” They will hide their remorse when they see the punishment, and We will put shackles around the necks of those who disbelieved. Will they be recompensed except for what they used to do? |
| (34) በከተማም አስፈራሪን አልላክንም፡፡ ነዋሪዎችዋ «እኛ በዚያ በርሱ በተላካችሁበት ከሓዲዎች ነን» ያሉ ቢኾኑ እንጂ፡፡ | (34) We never sent a warner to a town except that its affluent ones said, “We disbelieve in what you have been sent with.” |
| (35) «እኛም በገንዘቦችና በልጆች ይበልጥ የበዛን ነን፡፡ እኛም የምንቀጣ አይደለንም» አሉ፡፡ | (35) They said, “We have greater wealth and more children, and we will not be punished”. |
| (36) በላቸው «ጌታዬ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡» | (36) Say, “My Lord extends provision to whom He wills or restricts it, but most people do not know”. |
| (37) ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ያች እኛ ዘንድ መቅረብን የምታቀርባችሁ አይደለችም፡፡ ያመነና መልካምን የሠራ ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በሠሩት መልካም ሥራ እጥፍ ምንዳ አልላቸው፡፡ እነርሱም በገነት ሰገነቶች ውስጥ ጸጥተኞች ናቸው፡፡ | (37) It is not your wealth or your children that bring you closer to Us; but those who believe and do righteous deeds, it is they who will have a multiple reward for what they did, and they will be safe in the lofty mansions. |
| (38) እነዚያም የሚያቅቱ መስሏቸው አንቀጾቻችንን ለማበላሸት የሚጥሩት እነዚያ በቅጣቱ ውስጥ የሚጣዱ ናቸው፡፡ | (38) But those who strive against Our verses, seeking to discredit them, it is they who will be summoned to the punishment. |
| (39) «ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል፡፡ ለእርሱም ያጠብባል፡፡ ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል፡፡ እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው» በላቸው፡፡ | (39) Say, “My Lord extends provision to whom He wills of His slaves or restricts it. Whatever you spend in charity, He will compensate for it, for He is the Best of Providers.” |
| (40) ሁሉንም በሚሰበስባቸውና ከዚያም ለመላእክቶቹ «እነዚህ እናንተን ይግገዙ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን (የሚኾነውን አስታውስ)፡፡ | (40) On the Day when He gathers them all together, then He will say to the angels, “Was it you that they used to worship?” |
| (41) (መላእክቶቹም) «ጥራት ይገባህ ከእነርሱ ሌላ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፡፡ (እንደሚሉት) አይደለም ይልቁንም ጋኔንን ይግገዙ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ፡፡ | (41) They will say, “Glory be to You! You are our Protector, not they. Rather they used to worship the jinn; most of them believed in them.” |
| (42) ዛሬም ከፊላችሁ ለከፊሉ መጥቀምንም ኾነ መጉዳትን አይችሉም፡፡ ለእነዚያም ለበደሉት «ያችን በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» እንላቸዋለን፡፡ | (42) So Today none of you has the power to benefit or harm one another. And We will say to the wrongdoers, “Taste the punishment of the Fire which you used to deny!” |
| (43) በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጽ ኾነው በተነበቡላቸው ጊዜ «ይህ አባቶቻችሁ ይግገዙት ከነበሩት ነገር ሊከለክላችሁ የሚፈልግ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም» አሉ፡፡ «ይህም (ቁርኣን) የተቀጣጠፈ ውሸት ነው እንጂ ሌላ አይደለም» አሉ፡፡ እነዚያም የካዱት እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው እንጂ ሌላ አይደለም» አሉ፡፡ | (43) When Our clear verses are recited to them, they say, “This is nothing but a man who wishes to turn you away from what your forefathers used to worship.” And they say, “This is nothing but a fabricated lie.” And the disbelievers say about the Truth when it comes to them, “This is nothing but clear magic,” |
| (44) የሚያጠኑዋቸው የኾኑ መጽሐፍቶችንም ምንም አልሰጠናቸውም፡፡ ከአንተ በፊትም አስፈራሪ ነቢይን ወደእነርሱ አልላክንም፡፡ | (44) even though We did not give them any scriptures to study, nor did We send them any warner before you. |
| (45) እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ የሰጠናቸውንም ከዐስር አንዱን (እነዚህ) አልደረሱም፡፡ መልክተኞቼንም አስተባበሉ፤ (ነቀፍኳቸውም)፡፡ መንቀፌም እንዴት ነበር! | (45) Those who came before them also rejected [the truth], while these [Makkans] have not been given even one-tenth of what We had given those [earlier nations], yet they rejected My messengers; how severe was My response! |
| (46) «የምገስጻችሁ ባንዲት ነገር ብቻ ነው፡፡ (እርሷም) ሁለት ሁለት አንድ አንድም ኾናችሁ ለአላህ እንድትነሱ ከዚያም በጓደኛችሁ (በሙሐመድ) ምንም ዕብደት የሌለበት መኾኑን መርምራችሁ እንድትርረዱ ነው፡፡ እርሱ ለእናንተ ከብርቱ ቅጣት በስተፊት አስጠንቃቂ ነው እንጂ ሌላ አይደለም» በላቸው፡፡ | (46) Say [O Prophet], “I only advise you to do one thing: stand up for Allah, in pairs and individually, then reflect. There is no madness in your companion; he is but a warner to you ahead of a severe punishment.” |
| (47) «ከዋጋ ማንኛውም የጠየቅኋችሁ ቢኖር እርሱ ለእናንተው ነው፤ ዋጋዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ | (47) Say, “If I had ever asked you for a reward, it is yours. My reward is only with Allah, and He is Witness over all things.” |
| (48) «ጌታዬ እውነትን ያወርዳል፡፡ ሩቅ የኾኑትን ምስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ | (48) Say, “My Lord hurls the Truth [against falsehood], and He is the All-Knower of the unseen.” |
| (49) «እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡ | (49) Say, “The Truth has come, and falsehood can neither initiate nor restore anything.” |
| (50) «ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው፡፡ ብመራም ጌታዬ ወደኔ በሚያወርደው ነው፡፡ እርሱ ሰሚ ቅርብ ነውና» በላቸው፡፡ | (50) Say, “If I go astray, the detriment of my straying is only upon myself; but if I am guided, it is because of what my Lord reveals to me. He is indeed All-Hearing, Ever Near.” |
| (51) በደነገጡና ማምለጫ በሌላቸው ጊዜ ከቅርብ ስፍራም በተያዙ ጊዜ (ኹኔታቸውን) ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)፡፡ | (51) If only you could see when they are stricken with terror, but there will be no escape, and they will be seized from a nearby place. |
| (52) «በእርሱም (አሁን) አመንን» ይላሉ፡፡ ለእነርሱም ከሩቅ ስፍራ (እምነትን) በቀላል ማግኘት ከየታቸው? | (52) They will say, “Now we believe in it,” but how could they attain faith from such a distant place, |
| (53) በፊትም በእርሱ በእርግጥ ክደዋል፡፡ ከሩቅ ስፍራም በግምት ንግግርን ይጥላሉ፡፡ | (53) while they disbelieved in it before, making far-fetched conjectures about the unseen? |
| (54) ከዚህ ቀደም በመሰሎቻቸው እንደ ተሠራውም ብጤ በእነርሱና በሚፈልጉት መካከል ተጋረደ፡፡ እነርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ነበሩና፡፡ | (54) A barrier will be placed between them and what they desire, as was done with the likes of them before, for they were indeed in a disquieting doubt. |
