Default Image
20, Nov 2023
ሱረቱ አል አንፋል አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran 8 Al-Anfaal

ሱረቱ አል አንፋል አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran 8 Al-Anfaal

يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَنفَالِ ۖ قُلِ الْأَنفَالُ لِلَّهِ وَالرَّسُولِ ۖ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَصْلِحُوا ذَاتَ بَيْنِكُمْ ۖ وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ  [1]

(1) ከጦር ዘረፋ ገንዘቦች ይጠይቁሃል። «የዘረፋ ገንዘቦች የአላህና የመልክተኛው ናቸው።» ስለዚህ አላህን ፍሩ። በመካከላችሁ ያለችውንም ኹኔታ አሳምሩ። አማኞችም እንደኾናችሁ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ በላቸው።

(1) They ask you [O Prophet] about the spoils of war. Say, “The spoils of war belong to Allah and the Messenger. So fear Allah, settle your affairs among yourselves, and obey Allah and His Messenger, if you are [true] believers.”

إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ  [2]

(2) ፍጹም ምእምናን እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ በነሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው።

(2) The true believers are those whose hearts are filled with awe when Allah is mentioned, and their faith increases when His verses are recited to them, and they put their trust only in their Lord;

الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ  [3]

(3) እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው።

(3) those who establish prayer and spend out of what We have provided for them.

أُولَٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَمَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ  [4]

(4) እነዚያ በእውነት አማኞች እነሱ ብቻ ናቸው። ለእነሱ በጌታቸው ዘንድ ደረጃዎች ምህረትና የከበረ ሲሳይም አላቸው።

(4) Such are the true believers; they will have high ranks with their Lord, and forgiveness and an honorable provision.

كَمَا أَخْرَجَكَ رَبُّكَ مِن بَيْتِكَ بِالْحَقِّ وَإِنَّ فَرِيقًا مِّنَ الْمُؤْمِنِينَ لَكَارِهُونَ  [5]

(5) (ይህ በዘረፋ ክፍያ የከፊሉ ሰው መጥላት) ከምእምናን ከፊሉ የጠሉ ሲኾኑ ጌታህ ከቤትህ በእውነት ላይ ኾነህ እንዳወጣህ ነው።

(5) Just as your Lord brought you [O Prophet] out of your home for a just cause, even though a group of the believers were averse to it.

يُجَادِلُونَكَ فِي الْحَقِّ بَعْدَمَا تَبَيَّنَ كَأَنَّمَا يُسَاقُونَ إِلَى الْمَوْتِ وَهُمْ يَنظُرُونَ  [6]

(6) እነርሱ እያዩ ወደሞት እንደሚነዱ ኾነው በእውነቱ ነገር (በመጋደል ግዴታነት) ከተገለጸላቸው በኋላ ይከራከሩሃል።

(6) They disputed with you concerning the truth after it had become clear to them, as if they were being driven towards death while they were looking on.

وَإِذْ يَعِدُكُمُ اللَّهُ إِحْدَى الطَّائِفَتَيْنِ أَنَّهَا لَكُمْ وَتَوَدُّونَ أَنَّ غَيْرَ ذَاتِ الشَّوْكَةِ تَكُونُ لَكُمْ وَيُرِيدُ اللَّهُ أَن يُحِقَّ الْحَقَّ بِكَلِمَاتِهِ وَيَقْطَعَ دَابِرَ الْكَافِرِينَ  [7]

(7) አላህም ከሁለቱ ጭፍሮች አንደኛዋን እርሷ ለናንተ ናት ሲል ተስፋ በሰጣችሁ ጊዜ፣ የሀይል ባለቤት ያልኾነችውም (ነጋዴይቱ) ለናንተ ልትኾን በወደዳችሁ ጊዜ፣ አላህም በተስፋ ቃላቱ እውነትን ማረጋገጡን ሊገልጽና የከሓዲዎችንም መጨረሻ ሊቆርጥ በሻ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)።

(7) And [remember, O believers], when Allah promised you one of the two parties, that it would fall to you, and you wished that the unarmed one would fall to you. But it was Allah’s Will to establish the truth by His Words and exterminate the disbelievers,

لِيُحِقَّ الْحَقَّ وَيُبْطِلَ الْبَاطِلَ وَلَوْ كَرِهَ الْمُجْرِمُونَ  [8]

(8) (ይህንንም ያደረገው) አጋሪዎቹ ቢጠሉም እውነቱን ሊያረጋግጥ ክህደትንም ሊያጠፋ ነው።

(8) so that He might establish the truth and nullify the falsehood, even though the wicked are averse to it.

إِذْ تَسْتَغِيثُونَ رَبَّكُمْ فَاسْتَجَابَ لَكُمْ أَنِّي مُمِدُّكُم بِأَلْفٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُرْدِفِينَ  [9]

(9) ከጌታችሁ ርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ «እኔ በሺህ መላእክት ተከታታዮች ሲኾኑ እረዳችኋለሁ» ሲል ለናንተ የተቀበላችሁን (አስታውሱ)።

(9) [Remember] when you were seeking help of your Lord [at Badr] and He responded to you, “I will reinforce you with a thousand angels, following one another in succession.”

وَمَا جَعَلَهُ اللَّهُ إِلَّا بُشْرَىٰ وَلِتَطْمَئِنَّ بِهِ قُلُوبُكُمْ ۚ وَمَا النَّصْرُ إِلَّا مِنْ عِندِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ  [10]

(10) አላህም (ይኽንን ርዳታ) ለብስራትና ልቦቻችሁ በርሱ ሊረኩበት እንጂ ለሌላ አላደረገውም። ድልም መንሳት ከአላህ ዘንድ እንጂ ከሌላ አይደለም። አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና።

(10) Allah granted this only as glad tidings and to reassure your hearts, for victory only comes from Allah. Indeed, Allah is All-Mighty, All-Wise.

إِذْ يُغَشِّيكُمُ النُّعَاسَ أَمَنَةً مِّنْهُ وَيُنَزِّلُ عَلَيْكُم مِّنَ السَّمَاءِ مَاءً لِّيُطَهِّرَكُم بِهِ وَيُذْهِبَ عَنكُمْ رِجْزَ الشَّيْطَانِ وَلِيَرْبِطَ عَلَىٰ قُلُوبِكُمْ وَيُثَبِّتَ بِهِ الْأَقْدَامَ  [11]

(11) ከእርሱ በኾነው ጸጥታ (በጦር ግንባር) በእንቅልፍ በሸፈናችሁና ውሃውንም በእርሱ ሊያጠራችሁ፣ የሰይጣንንም ጉትጎታ ከእናንተ ሊያስወግድላችሁ፣ ልቦቻችሁንም (በትዕግስት) ሊያጠነክርላችሁ፣ በእርሱም ጫማዎችን (በአሸዋው ላይ) ሊያደላድልላችሁ በእናንተ ላይ ከሰማይ ባወረደላችሁ ጊዜ (አስታውሱ)።

(11) [Remember] when He caused drowsiness to overcome you as an assurance from Him, and He sent down rain from the sky to purify you and to remove Satan’s whispers from you, and to strengthen your hearts and to steady your footsteps.

إِذْ يُوحِي رَبُّكَ إِلَى الْمَلَائِكَةِ أَنِّي مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا الَّذِينَ آمَنُوا ۚ سَأُلْقِي فِي قُلُوبِ الَّذِينَ كَفَرُوا الرُّعْبَ فَاضْرِبُوا فَوْقَ الْأَعْنَاقِ وَاضْرِبُوا مِنْهُمْ كُلَّ بَنَانٍ  [12]

(12) ጌታህ ወደ መላእክቱ «»እኔ (በእርዳታዬ) ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ። በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ። ከአንገቶችም በላይ (ራሶችን) ምቱ። ከእነሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ። ሲል ያወረደውን (አስታውስ)።

(12) [Remember] when your Lord inspired the angels, “I am with you, so make firm the feet of those who believe. I will cast terror into the hearts of those who disbelieve. So strike their necks and strike all their limbs.”

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ شَاقُّوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ وَمَن يُشَاقِقِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَإِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ  [13]

(13) ይህ እነርሱ አላህንና መልክተኛውን ስለተቃወሙ ነው። አላህንና መልክተኛውንም የሚቃወም ሁሉ አላህ ቅጣቱ ብርቱ ነው።

(13) That is because they opposed Allah and His Messenger. Whoever opposes Allah and His Messenger, Allah is indeed severe in punishment.

ذَٰلِكُمْ فَذُوقُوهُ وَأَنَّ لِلْكَافِرِينَ عَذَابَ النَّارِ  [14]

(14) ይህ (ቅጣታችሁ ነው) ቅመሱትም። ለከሓዲዎችም የእሳት ቅጣት በእርግጥ አለባቸው።

(14) That is for you, so taste it, and for the disbelievers there will be the punishment of the Fire.

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا لَقِيتُمُ الَّذِينَ كَفَرُوا زَحْفًا فَلَا تُوَلُّوهُمُ الْأَدْبَارَ  [15]

(15) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን የካዱትን ሰዎች (ለጦር) ሲጓዙ ባገኛችኋቸው ጊዜ ጀርባዎችን አታዙሩላቸው።

(15) O you who believe, when you confront the disbelievers in battle, do not turn your backs to them.

وَمَن يُوَلِّهِمْ يَوْمَئِذٍ دُبُرَهُ إِلَّا مُتَحَرِّفًا لِّقِتَالٍ أَوْ مُتَحَيِّزًا إِلَىٰ فِئَةٍ فَقَدْ بَاءَ بِغَضَبٍ مِّنَ اللَّهِ وَمَأْوَاهُ جَهَنَّمُ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ  [16]

(16) ያን ጊዜም ለግድያ ለመዘዋወር ወይም ወደ ሠራዊት ለመቀላቀል ሳይኾን ጀርባውን የሚያዞርላቸው ሰው ከአላህ በኾነ ቁጣ በእርግጥ ተመለሰ። መኖሪያውም ገሀነም ናት። መመለሻይቱም ከፋች።

(16) Whoever turns his back to them on such a day – unless it is for tactical reasons or joining another group – he will incur the wrath of Allah and his abode will be Hell. What a terrible destination!

فَلَمْ تَقْتُلُوهُمْ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ قَتَلَهُمْ ۚ وَمَا رَمَيْتَ إِذْ رَمَيْتَ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ رَمَىٰ ۚ وَلِيُبْلِيَ الْمُؤْمِنِينَ مِنْهُ بَلَاءً حَسَنًا ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ  [17]

(17) አልገደላችኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው። (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም። ግን አላህ ወረወረ (ወደ ዓይኖቻቸው አደረሰው)። ለአማኞችም ከርሱ የኾነን መልካም ጸጋ ለመስጠት (ይህን አደረገ)። አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነውና።

(17) It was not you who killed them, but it was Allah Who killed them; and it was not you [O Prophet] who threw when you threw [a handful of sand] but it was Allah Who threw, so that He might test the believers with a great test. Allah is All-Hearing, All-Knowing.

ذَٰلِكُمْ وَأَنَّ اللَّهَ مُوهِنُ كَيْدِ الْكَافِرِينَ  [18]

(18) ይህ (ዕውነት ነው)። አላህም የከሓዲዎችን ተንኮል አድካሚ ነው።

(18) As such, Allah undermines the plans of the disbelievers.

إِن تَسْتَفْتِحُوا فَقَدْ جَاءَكُمُ الْفَتْحُ ۖ وَإِن تَنتَهُوا فَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ وَإِن تَعُودُوا نَعُدْ وَلَن تُغْنِيَ عَنكُمْ فِئَتُكُمْ شَيْئًا وَلَوْ كَثُرَتْ وَأَنَّ اللَّهَ مَعَ الْمُؤْمِنِينَ  [19]

(19) ፍትሕን (ፍርድን) ብትጠይቁ ፍትሑ በእርግጥ መጥቶላችኋል። (ክህደትንና መዋጋትን) ብትከለከሉም እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው። (ወደ መጋደል) ብትመለሱም እንመለሳለን። ሰራዊታችሁም ብትበዛም እንኳ ከናንተ ምንም አትጠቅማችሁም። አላህም ከምእምናን ጋር ነው።

(19) If you [disbelievers] were seeking the decision, it has come to you. If you desist, it will be better for you, but if you return [to war], We too will return. And your forces – no matter how great in number they are – will not avail you anything, for Allah is with the believers.

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَا تَوَلَّوْا عَنْهُ وَأَنتُمْ تَسْمَعُونَ  [20]

(20) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ። እናንተም የምትሰሙ ስትኾኑ ከርሱ አትሽሹ።

(20) O you who believe, obey Allah and His Messenger, and do not turn away from him after hearing [his command].

وَلَا تَكُونُوا كَالَّذِينَ قَالُوا سَمِعْنَا وَهُمْ لَا يَسْمَعُونَ  [21]

(21) እንደነዚያም እነሱ የማይሰሙ ሲኾኑ ሰማን እንዳሉት አትሁኑ።

(21) And do not be like those who say, “We hear,” while they do not actually listen.

إِنَّ شَرَّ الدَّوَابِّ عِندَ اللَّهِ الصُّمُّ الْبُكْمُ الَّذِينَ لَا يَعْقِلُونَ  [22]

(22) ከተንቀሳቃሾች ሁሉ አላህ ዘንድ መጥፎ ተንኮለኞች እነዚያ የማያውቁት፣ ደንቆሮዎቹ፣ ዲዳዎቹ ናቸው።

(22) The worst of creatures before Allah are those that are deaf and dumb, who do not understand.

وَلَوْ عَلِمَ اللَّهُ فِيهِمْ خَيْرًا لَّأَسْمَعَهُمْ ۖ وَلَوْ أَسْمَعَهُمْ لَتَوَلَّوا وَّهُم مُّعْرِضُونَ  [23]

(23) በውስጣቸውም ደግ መኖሩን አላህ ባወቀ ኖሮ (የመረዳትን መስማት) ባሰማቸው ነበር። (ደግ የሌለባቸው መኾኑን ሲያውቅ) ባሰማቸውም ኖሮ እነሱ እውነትን የተው ኾነው በሸሹ ነበር።

(23) If Allah had known any good in them, He would have made them hear, but even if He had made them hear, they would have turned away in aversion.

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَجِيبُوا لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمْ لِمَا يُحْيِيكُمْ ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ يَحُولُ بَيْنَ الْمَرْءِ وَقَلْبِهِ وَأَنَّهُ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ  [24]

(24) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልክተኛው) ሕያው ወደሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልክተኛው ታዘዙ። አላህም በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መኾኑን ወደርሱም የምትሰበሰቡ መኾናችሁን እወቁ።

(24) O you who believe, respond to Allah and the Messenger when He calls you to what gives you life, and know that Allah comes between a person and his heart, and it is to Him that you will all be gathered.

وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ  [25]

(25) ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ። አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ።

(25) Beware of a trial that will not only befall the wrongdoers among you, and know that Allah is severe in punishment.

وَاذْكُرُوا إِذْ أَنتُمْ قَلِيلٌ مُّسْتَضْعَفُونَ فِي الْأَرْضِ تَخَافُونَ أَن يَتَخَطَّفَكُمُ النَّاسُ فَآوَاكُمْ وَأَيَّدَكُم بِنَصْرِهِ وَرَزَقَكُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ  [26]

(26) እናንተም በምድር ላይ የተናቃችሁ ጥቂቶች ኾናችሁ ሳላችሁ ሰዎች ሊነጥቁዋችሁ የምትፈሩ ስትኾኑ ያስጠጋችሁን በእርዳታውም ያበረታችሁን ከመልካሞች ሲሳዮችም ታመሰግኑ ዘንድ የሰጣችሁን አስታውሱ።

(26) And remember when you were few in number and oppressed in the land, fearing that the people would snatch you away. Then He sheltered you, and strengthened you with His help, and provided you with good things, so that you may give thanks.

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَخُونُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ وَتَخُونُوا أَمَانَاتِكُمْ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ  [27]

(27) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን አትክዱ። አደራዎቻችሁንም እናንተ እያወቃችሁ አትክዱ።

(27) O you who believe, do not betray Allah and the Messenger, nor betray your trusts knowingly.

وَاعْلَمُوا أَنَّمَا أَمْوَالُكُمْ وَأَوْلَادُكُمْ فِتْنَةٌ وَأَنَّ اللَّهَ عِندَهُ أَجْرٌ عَظِيمٌ  [28]

(28) ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ፈተና ብቻ መኾናቸውንና አላህም እሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለው መኾኑን እወቁ።

(28) Know that your wealth and your children are only a trial and that with Allah is an immense reward.

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن تَتَّقُوا اللَّهَ يَجْعَل لَّكُمْ فُرْقَانًا وَيُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ  [29]

(29) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያን ብርሃን ያደርግላችኋል። ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከእናንተ ላይ ያብስላችኋል። ለእናንተም ይምራችኋል። አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው።

(29) O you who believe, if you fear Allah, He will provide you with an insight to distinguish between right and wrong, absolve you of your sins and forgive you, for Allah is the Lord of great bounty.

وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ ۚ وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ اللَّهُ ۖ وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ  [30]

(30) እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም (ከመካ) ሊያወጡህ ባንተ ላይ በመከሩብህ ጊዜ (አስታውስ)። ይመክራሉም አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል። አላህም ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው።

(30) And [remember] when the disbelievers plotted against you, to take you as captive, kill you or expel you. They plan, and Allah also plans, but Allah is the Best of those who plan.

وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا قَالُوا قَدْ سَمِعْنَا لَوْ نَشَاءُ لَقُلْنَا مِثْلَ هَٰذَا ۙ إِنْ هَٰذَا إِلَّا أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ  [31]

(31) አንቀጾቻችንም በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «በእርግጥ ሰምተናል፤ በሻን ኖሮ የዚህን ብጤ ባልን ነበር፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ጽሑፍ ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» ይላሉ።

(31) When Our verses are recited to them, they say, “We have heard. If we wished, we could say something like this. This is nothing but ancient fables.”

وَإِذْ قَالُوا اللَّهُمَّ إِن كَانَ هَٰذَا هُوَ الْحَقَّ مِنْ عِندِكَ فَأَمْطِرْ عَلَيْنَا حِجَارَةً مِّنَ السَّمَاءِ أَوِ ائْتِنَا بِعَذَابٍ أَلِيمٍ  [32]

(32) «ጌታችን ሆይ! ይህ እርሱ ካንተ ዘንድ (የተወረደ) እውነት እንደ ኾነ በኛ ላይ ከሰማይ ድንጋዮችን አዝንብብን ወይም አሳማሚ ቅጣትን አምጣብን» ባሉም ጊዜ (አስታውስ)

(32) And [remember] when they said, “O Allah, if this is indeed the truth from You, then rain down upon us stones from the heaven or bring upon us a painful punishment.”

وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُعَذِّبَهُمْ وَأَنتَ فِيهِمْ ۚ وَمَا كَانَ اللَّهُ مُعَذِّبَهُمْ وَهُمْ يَسْتَغْفِرُونَ  [33]

(33) አላህም አንተ በውስጣቸው እያለህ (ድንጋይ በማዝነብና ባሳማሚ ቅጣት) የሚቀጣቸው አይደለም። አላህም እነሱ ምህረትን የሚለምኑ ሲኾኑ የሚቀጣቸው አይደለም።

(33) But Allah would not punish them while you [O Prophet] are among them, nor would Allah punish them as long as they seek forgiveness.

وَمَا لَهُمْ أَلَّا يُعَذِّبَهُمُ اللَّهُ وَهُمْ يَصُدُّونَ عَنِ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ وَمَا كَانُوا أَوْلِيَاءَهُ ۚ إِنْ أَوْلِيَاؤُهُ إِلَّا الْمُتَّقُونَ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ  [34]

(34) እነሱ ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሲኾኑም አላህ (በሰይፍ) የማይቀጣቸው ለነሱ ምን አልላቸው (የቤቱ) ጠባቂዎችም አልነበሩም። ጠባቂዎቹ (ክሕደትን) ተጠንቃቂዎቹ እንጂ ሌሎቹ አይደሉም። ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም።

(34) Why should Allah not punish them when they prevent [people] from the Sacred Mosque, although they are not its rightful guardians? Its rightful guardians are only those who fear Allah, but most of them do not know.

وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمْ عِندَ الْبَيْتِ إِلَّا مُكَاءً وَتَصْدِيَةً ۚ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ  [35]

(35) በቤቱ ዘንድም (በካዕባ) ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም። ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ (ይባላሉ)።

(35) Their prayer at the Sacred House was nothing but whistling and clapping. So taste the punishment for your disbelief.

إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ لِيَصُدُّوا عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ فَسَيُنفِقُونَهَا ثُمَّ تَكُونُ عَلَيْهِمْ حَسْرَةً ثُمَّ يُغْلَبُونَ ۗ وَالَّذِينَ كَفَرُوا إِلَىٰ جَهَنَّمَ يُحْشَرُونَ  [36]

(36) እነዚያ የካዱት ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘቦቻቸውን ያወጣሉ። በእርግጥም ያወጡዋታል። ከዚያም በእነሱ ላይ ጸጸት ትኾንባቸዋለች። ከዚያም ይሸነፋሉ። እነዚያም የካዱት ወደ ገሀነም ይሰበሰባሉ።

(36) The disbelievers spend their wealth to prevent [people] from the way of Allah. They will continue to spend it, then it will be a source of regret for them, then they will be defeated, and those who disbelieve will be gathered into Hell,

لِيَمِيزَ اللَّهُ الْخَبِيثَ مِنَ الطَّيِّبِ وَيَجْعَلَ الْخَبِيثَ بَعْضَهُ عَلَىٰ بَعْضٍ فَيَرْكُمَهُ جَمِيعًا فَيَجْعَلَهُ فِي جَهَنَّمَ ۚ أُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ  [37]

(37) አላህ መጥፎውን ከመልካሙ ሊለይ መጥፎውንም ከፊሉን በከፊሉ ላይ ሊያደርግና ባንድ ላይ ሊያነባብረው በገሀነም ውስጥም ሊያደርገው (ይሰበሰባሉ)። እነዚያ እነሱ ከሳሪዎቹ ናቸው።

(37) so that Allah may separate the wicked from the good, and pile up the wicked all together and then cast them into Hell. It is they who are the losers.

قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُوا إِن يَنتَهُوا يُغْفَرْ لَهُم مَّا قَدْ سَلَفَ وَإِن يَعُودُوا فَقَدْ مَضَتْ سُنَّتُ الْأَوَّلِينَ  [38]

(38) ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ ያለፈውን (ሥራ) ምሕረት ይደረግላቸዋል። (ወደ መጋደል) ቢመለሱም (እናጠፋቸዋለን)። የቀድሞዎቹ ሕዝቦች ልማድ በእርግጥ አልፋለችና።

(38) Say to those who disbelieve that if they desist, their past will be forgiven, but if they persist, then they have a precedent in those who have passed before them.

وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ كُلُّهُ لِلَّهِ ۚ فَإِنِ انتَهَوْا فَإِنَّ اللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ بَصِيرٌ  [39]

(39) ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሏቸው። ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው።

(39) Fight them until there is no more persecution and the religion is entirely for Allah; but if they desist, then Allah is All-Seeing of what they do.

وَإِن تَوَلَّوْا فَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ مَوْلَاكُمْ ۚ نِعْمَ الْمَوْلَىٰ وَنِعْمَ النَّصِيرُ  [40]

(40) (ከእምነት) ቢዞሩም አላህ ረዳታችሁ መኾኑን ዕወቁ። (እርሱ) ምን ያምር ጠባቂ! ምን ያምርም ረዳት!

(40) But if they turn away, then know that Allah is your Protector. What an excellent Protector and an excellent Helper!

وَاعْلَمُوا أَنَّمَا غَنِمْتُم مِّن شَيْءٍ فَأَنَّ لِلَّهِ خُمُسَهُ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَابْنِ السَّبِيلِ إِن كُنتُمْ آمَنتُم بِاللَّهِ وَمَا أَنزَلْنَا عَلَىٰ عَبْدِنَا يَوْمَ الْفُرْقَانِ يَوْمَ الْتَقَى الْجَمْعَانِ ۗ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ  [41]

(41) ከማንኛውም ነገር በጦር (ከከሓዲዎች) የዘረፋችሁትም አንድ አምስተኛው ለአላህና ለመልክተኛው፣ (ለነቢዩ) የዝምድና ባለቤቶችም፣ ለየቲሞችም፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኛም የተገባ መኾኑን ዕውቁ፣ በአላህና በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙበት (በበድር) ቀን በባሪያችን ላይ ባወረድነው የምታምኑ እንደኾናችሁ (ይህንን ዕወቁ)። አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

(41) Know that whatever spoils you obtain, one-fifth belongs to Allah and the Messenger, to his close relatives, the orphans, the needy and the [stranded] travelers – if you truly believe in Allah and in what We sent down to Our slave on the day of Criterion – the day when the two armies met [at Badr]. And Allah is Most Capable of all things.

إِذْ أَنتُم بِالْعُدْوَةِ الدُّنْيَا وَهُم بِالْعُدْوَةِ الْقُصْوَىٰ وَالرَّكْبُ أَسْفَلَ مِنكُمْ ۚ وَلَوْ تَوَاعَدتُّمْ لَاخْتَلَفْتُمْ فِي الْمِيعَادِ ۙ وَلَٰكِن لِّيَقْضِيَ اللَّهُ أَمْرًا كَانَ مَفْعُولًا لِّيَهْلِكَ مَنْ هَلَكَ عَن بَيِّنَةٍ وَيَحْيَىٰ مَنْ حَيَّ عَن بَيِّنَةٍ ۗ وَإِنَّ اللَّهَ لَسَمِيعٌ عَلِيمٌ  [42]

(42) እናንተ በቅርቢቱ ዳርቻ ኾናችሁ እነርሱም በሩቂቱ ዳርቻ ኾነው የነጋዴዎቹም ጭፍራ ከናንተ በታች ሲኾኑ በሰፈራችሁ ጊዜ (ያደረግንላችሁን አስታውሱ)። በተቃጠራችሁም ኖሮ በቀጠሮው በተለያያችሁ ነበር። ግን አላህ ሊሠራው የሚገባውን ነገር ሊፈጽም የሚጠፋ ሰው ከአስረጅ በኋላ እንዲጠፋ ሕያው የሚኾንም ሰው ከአስረጅ በኋላ ሕያው እንዲኾን (ያለቀጠሮ አጋጠማችሁ)። አላህም በእርግጥ ሰሚ ዐዋቂ ነው።

(42) [Remember] when you were on the near side of the valley [of Badr], and they were on the far side, and the caravan was on the lower ground beneath you. If you had made prior arrangements to encounter, you would have failed to keep that appointment. But [it happened] so that Allah might accomplish what had already been decreed, and so that those who chose to perish would perish after seeing clear evidence, and those who chose to survive would survive after seeing clear evidence. Indeed, Allah is All-Hearing, All-Knowing.

إِذْ يُرِيكَهُمُ اللَّهُ فِي مَنَامِكَ قَلِيلًا ۖ وَلَوْ أَرَاكَهُمْ كَثِيرًا لَّفَشِلْتُمْ وَلَتَنَازَعْتُمْ فِي الْأَمْرِ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ سَلَّمَ ۗ إِنَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ  [43]

(43) አላህ በሕልምህ እነሱን ጥቂት አድርጎ ባሳየህ ጊዜ (አስታውስ)። እነሱን ብዙ አድርጎ ባሳየህም ኖሮ በፈራችሁና በነገሩ በተጨቃጨቃችሁ ነበር። ግን አላህ አዳናችሁ። እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነውና።

(43) [Remember] when Allah showed them to you in your dream as few in number; if He had shown them to you as many, you [believers] would have lost courage and disputed in the matter. But Allah spared you [of that], for He is All-Knowing of what is in the hearts.

وَإِذْ يُرِيكُمُوهُمْ إِذِ الْتَقَيْتُمْ فِي أَعْيُنِكُمْ قَلِيلًا وَيُقَلِّلُكُمْ فِي أَعْيُنِهِمْ لِيَقْضِيَ اللَّهُ أَمْرًا كَانَ مَفْعُولًا ۗ وَإِلَى اللَّهِ تُرْجَعُ الْأُمُورُ  [44]

(44) አላህም ሊሠራው የሚገባን ነገር ይፈጽም ዘንድ በተጋጠማችሁ ጊዜ እነርሱን በዓይኖቻችሁ ጥቂት አድርጎ ያሳያችሁንና በዓይኖቻቸውም ላይ ያሳነሳችሁን (አስታውሱ)። ነገሮቹም ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ።

(44) And [remember] when you met, He made them appear as few in your eyes, and made you appear as few in their eyes, so that Allah may accomplish what was already decreed. And to Allah will return all matters.

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا لَقِيتُمْ فِئَةً فَاثْبُتُوا وَاذْكُرُوا اللَّهَ كَثِيرًا لَّعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ  [45]

(45) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሰራዊትን በገጠማችሁ ጊዜ እርጉ፤ (መክቱ)። አላህንም በብዙ አውሱ፤ በእርግጥ ትድናላችሁና።

(45) O you who believe, when you encounter a group [in battle], stand firm and remember Allah much, so that you may triumph.

وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَا تَنَازَعُوا فَتَفْشَلُوا وَتَذْهَبَ رِيحُكُمْ ۖ وَاصْبِرُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ  [46]

(46) አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ። አትጨቃጨቁም። ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትኼዳለችና። ታገሱም፤ አላህ ከትዕግስተኞች ጋር ነውና።

(46) Obey Allah and His Messenger, and do not dispute with one another, or else you will lose courage and your strength will weaken. And be steadfast, for Allah is with those who are steadfast.

وَلَا تَكُونُوا كَالَّذِينَ خَرَجُوا مِن دِيَارِهِم بَطَرًا وَرِئَاءَ النَّاسِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ وَاللَّهُ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطٌ  [47]

(47) እንደነዚያ ለትዕቢትና ለሰዎች ይዩልኝ ሲሉ ከአላህም መንገድ ለማገድ ከአገራቸው እንደወጡት አትኹኑ። አላህም በሚሠሩት ሁሉ (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው።

(47) Do not be like those who came out of their homes insolently, showing off to people, and preventing others from Allah’s way, for Allah is All-Encompassing of what they do.

وَإِذْ زَيَّنَ لَهُمُ الشَّيْطَانُ أَعْمَالَهُمْ وَقَالَ لَا غَالِبَ لَكُمُ الْيَوْمَ مِنَ النَّاسِ وَإِنِّي جَارٌ لَّكُمْ ۖ فَلَمَّا تَرَاءَتِ الْفِئَتَانِ نَكَصَ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ وَقَالَ إِنِّي بَرِيءٌ مِّنكُمْ إِنِّي أَرَىٰ مَا لَا تَرَوْنَ إِنِّي أَخَافُ اللَّهَ ۚ وَاللَّهُ شَدِيدُ الْعِقَابِ  [48]

(48) ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ባሳመረላቸውና «ዛሬ ለእናንተ ከሰዎች አሸናፊ የላችሁም እኔም ለእናንተ ረዳት ነኝ» ባለ ጊዜም (አስታውስ)። ሁለቱ ጭፍሮችም በተያዩ ጊዜ፤ ወደኋላው አፈገፈገ። «እኔ ከናንተ ንጹህ ነኝ። እኔ እናንተ የማታዩትን አያለሁ። እኔ አላህን እፈራለሁ። አላህም ቅጣተ ብርቱ ነው» አላቸውም።

(48) And [remember] when Satan made their misdeeds appealing to them, and said, “No one can overcome you today, and I am your protector.” But when the two armies faced each other, he turned on his heels and said, “I have nothing to do with you, for I see what you do not see. I surely fear Allah, for Allah is severe in punishment.”

إِذْ يَقُولُ الْمُنَافِقُونَ وَالَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ غَرَّ هَٰؤُلَاءِ دِينُهُمْ ۗ وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَإِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ  [49]

(49) መናፍቃንና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው «እነዚህን (ሙስሊሞች) ሃይማኖታቸው አታለላቸው» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)። በአላህም ላይ የሚጠጋ (ያሸንፋል)፤ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና።

(49) And [remember] when the hypocrites and those who have sickness in their hearts said, “These [believers] are deluded by their religion.” But whoever puts his trust in Allah, Allah is indeed All-Mighty, All-Wise.

وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ يَتَوَفَّى الَّذِينَ كَفَرُوا ۙ الْمَلَائِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَارَهُمْ وَذُوقُوا عَذَابَ الْحَرِيقِ  [50]

(50) እነዚያንም የካዱትን መላእክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ» (እያሉ) በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)።

(50) If only you could see when the angels take the souls of the disbelievers, beating their faces and their backs, “Taste the punishment of the scorching fire!

ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيكُمْ وَأَنَّ اللَّهَ لَيْسَ بِظَلَّامٍ لِّلْعَبِيدِ  [51]

(51) ይህ እጆቻችሁ ባስቀደሙት ምክንያት አላህም ለባሮቹ በዳይ ባለመኾኑ ነው (ይባላሉ)።

(51) This is because of what your hands have sent forth, for Allah is never unjust to [His] slaves.”

كَدَأْبِ آلِ فِرْعَوْنَ ۙ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ ۚ كَفَرُوا بِآيَاتِ اللَّهِ فَأَخَذَهُمُ اللَّهُ بِذُنُوبِهِمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ قَوِيٌّ شَدِيدُ الْعِقَابِ  [52]

(52) (የነዚያ ልማድ) እንደ ፈርዖን ቤተሰብና እንደነዚያም ከእነሱ በፊት እንደ ነበሩት ልማድ ነው። በአላህ አንቀጾች ካዱ፤ አላህም በኃጢኣቶቻቸው ያዛቸው፤ አላህ ኀይለኛ ቅጣተ ብርቱ ነውና።

(52) Their case is like the people of Pharaoh and those who came before them. They disbelieved in the signs of Allah, so Allah seized them for their sins. Indeed, Allah is All-Powerful, Severe in Punishment.

ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ لَمْ يَكُ مُغَيِّرًا نِّعْمَةً أَنْعَمَهَا عَلَىٰ قَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا مَا بِأَنفُسِهِمْ ۙ وَأَنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ  [53]

(53) ይህ (ቅጣት) አላህ በሕዝቦች ላይ የለገሰውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ነገር እስከሚለውጡ ድረስ የማይለውጥ በመኾኑ ምክንያት ነው። አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው።

(53) This is because Allah would never change the blessings He has bestowed upon a people until they change their own attitude and conduct. Indeed, Allah is All-Hearing, All-Knowing.

كَدَأْبِ آلِ فِرْعَوْنَ ۙ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ ۚ كَذَّبُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ فَأَهْلَكْنَاهُم بِذُنُوبِهِمْ وَأَغْرَقْنَا آلَ فِرْعَوْنَ ۚ وَكُلٌّ كَانُوا ظَالِمِينَ  [54]

(54) እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደእነዚያም ከእነሱ በፊት እንደ ነበሩት ልማድ (እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥባቸውም)። በጌታቸው ተአምራት አስተባበሉና በኃጢኣቶቻቸው አጠፋናቸው። የፈርዖንንም ቤተሰቦች አሰጠምናቸው። ሁሉም በዳዮች ነበሩም።

(54) Their case is like the people of Pharaoh and those who came before them. They rejected the signs of their Lord, so We destroyed them for their sins and drowned the people of Pharaoh; they were all wrongdoers.

إِنَّ شَرَّ الدَّوَابِّ عِندَ اللَّهِ الَّذِينَ كَفَرُوا فَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ  [55]

(55) ከሚንቀሳቀሱ እንስሳዎች ሁሉ አላህ ዘንድ ይበልጥ ክፉዎቹ እነዚያ ዘወትር የካዱት ናቸው። ስለዚህ እነሱ አያምኑም።

(55) The worst of moving creatures before Allah are those who persist in disbelief, so they do not believe,

الَّذِينَ عَاهَدتَّ مِنْهُمْ ثُمَّ يَنقُضُونَ عَهْدَهُمْ فِي كُلِّ مَرَّةٍ وَهُمْ لَا يَتَّقُونَ  [56]

(56) እነዚያ ከነሱ ቃል ኪዳን የያዝክባቸው ከዚያም በየጊዜው ቃል ኪዳናቸውን የሚያፈርሱ ናቸው። እነሱም አይጠነቀቁም።

(56) those with whom you [O Prophet] made a treaty, but they break their treaty every time, and they do not fear Allah.

فَإِمَّا تَثْقَفَنَّهُمْ فِي الْحَرْبِ فَشَرِّدْ بِهِم مَّنْ خَلْفَهُمْ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ  [57]

(57) በጦርም ላይ ብታገኛቸው በእነርሱ ቅጣት ምክንያት (ሌሎቹ ከሓዲዎች) ይገሰጹ ዘንድ ከኋላቸው ያሉትን በትንባቸው።

(57) If you encounter them in battle, make a fearsome example of them for those who are behind them, so that they may be deterred.

وَإِمَّا تَخَافَنَّ مِن قَوْمٍ خِيَانَةً فَانبِذْ إِلَيْهِمْ عَلَىٰ سَوَاءٍ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْخَائِنِينَ  [58]

(58) ከሕዝቦችም ክዳትን ብትፈራ (የኪዳኑን መፍረስ በማወቅ) በመተካከል ላይ ኾናችሁ ኪዳናቸውን ወደነሱ ጣልላቸው። አላህ ከዳተኞችን አይወድምና።

(58) If you fear betrayal from any people, throw their treaty back at them openly, for Allah does not like the treacherous.

وَلَا يَحْسَبَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا سَبَقُوا ۚ إِنَّهُمْ لَا يُعْجِزُونَ  [59]

(59) እነዚያም የካዱት ከአላህ ቅጣት ያመለጡ መኾናቸውን አያስቡ። እነሱ አያቅቱምና።

(59) The disbelievers should not think that they are unreachable; they cannot escape.

وَأَعِدُّوا لَهُم مَّا اسْتَطَعْتُم مِّن قُوَّةٍ وَمِن رِّبَاطِ الْخَيْلِ تُرْهِبُونَ بِهِ عَدُوَّ اللَّهِ وَعَدُوَّكُمْ وَآخَرِينَ مِن دُونِهِمْ لَا تَعْلَمُونَهُمُ اللَّهُ يَعْلَمُهُمْ ۚ وَمَا تُنفِقُوا مِن شَيْءٍ فِي سَبِيلِ اللَّهِ يُوَفَّ إِلَيْكُمْ وَأَنتُمْ لَا تُظْلَمُونَ  [60]

(60) ለእነሱም ከማንኛውም ኃይልና ከታጀቡ ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከእነርሱ በቀር ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ የሚያውቃቸውን (መናፍቃን) የምታሸብሩበት ስትኾኑ አዘጋጁላቸው። ከማንኛውም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱትም ምንዳው ወደናንተ በሙሉ ይሰጣል። እናንተም አትበደሉም።

(60) Prepare against them whatever force you can and cavalry, to deter Allah’s enemies and your enemies, and others besides them whom you do not know, but Allah knows them. Whatever you spend in the cause of Allah will be repaid to you in full, and you will not be wronged.

وَإِن جَنَحُوا لِلسَّلْمِ فَاجْنَحْ لَهَا وَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ  [61]

(61) ወደ ዕርቅም ቢያዘነብሉ ወደ እርሷ አዘንብል። በአላህም ላይ ተጠጋ። እነሆ እርሱ ሰሚ ዐዋቂ ነውና።

(61) If they incline to peace, then incline to it, and put your trust in Allah, for He is the All-Hearing, the All-Knowing.

وَإِن يُرِيدُوا أَن يَخْدَعُوكَ فَإِنَّ حَسْبَكَ اللَّهُ ۚ هُوَ الَّذِي أَيَّدَكَ بِنَصْرِهِ وَبِالْمُؤْمِنِينَ  [62]

(62) ሊያታልሉህም ቢፈልጉ አላህ በቂህ ነው። እርሱ ያ በእርዳታውና በምእምናን ያበረታህ ነው።

(62) But if they intend to deceive you, then Allah is sufficient for you; it is He Who supported you with His help and with that of the believers.

وَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ ۚ لَوْ أَنفَقْتَ مَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مَّا أَلَّفْتَ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ أَلَّفَ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ  [63]

(63) በልቦቻቸውም መካከል ያስማማ ነው። በምድር ያለውን ሁሉ (ሀብት) በለገስክ ኖሮ በልቦቻቸው መካከል ባላስማማህ ነበር። ግን አላህ በመካከላቸው አስማማ። እርሱ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና።

(63) He brought their hearts together, even if you had spent all that is on earth, you could not have brought their hearts together, but Allah has brought them together, for He is All-Mighty, All-Wise.

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ حَسْبُكَ اللَّهُ وَمَنِ اتَّبَعَكَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ  [64]

(64) አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ በቂህ ነው። ለተከተሉህም ምእምናን (አላህ በቂያቸው ነው)።

(64) O Prophet, Allah is sufficient for you and for the believers who follow you.

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ حَرِّضِ الْمُؤْمِنِينَ عَلَى الْقِتَالِ ۚ إِن يَكُن مِّنكُمْ عِشْرُونَ صَابِرُونَ يَغْلِبُوا مِائَتَيْنِ ۚ وَإِن يَكُن مِّنكُم مِّائَةٌ يَغْلِبُوا أَلْفًا مِّنَ الَّذِينَ كَفَرُوا بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَفْقَهُونَ  [65]

(65) አንተ ነቢዩ ሆይ! ምእምናንን በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው። ከእናንተ ውስጥ ሃያ ታጋሾች ኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ። ከእናንተም መቶ ቢኖሩ ከእነዚያ ከካዱት እነሱ የማያውቁ ሕዝቦች ስለኾኑ ሺህን ያሸንፋሉ፤

(65) O Prophet, urge the believers to fight. If there are twenty steadfast among you, they will overcome two hundred; and if there are a hundred of you, they will overcome a thousand of the disbelievers, for they are a people who do not understand.

الْآنَ خَفَّفَ اللَّهُ عَنكُمْ وَعَلِمَ أَنَّ فِيكُمْ ضَعْفًا ۚ فَإِن يَكُن مِّنكُم مِّائَةٌ صَابِرَةٌ يَغْلِبُوا مِائَتَيْنِ ۚ وَإِن يَكُن مِّنكُمْ أَلْفٌ يَغْلِبُوا أَلْفَيْنِ بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ مَعَ الصَّابِرِينَ  [66]

(66) አሁን አላህ ከእናንተ ላይ አቀለለላችሁ። በእናንተ ውስጥም ድክመት መኖሩን ዐወቀ። ስለዚህ ከእናንተ መቶ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ። ከእናንተም ሺህ ቢኖሩ በአላህ ፈቃድ ሁለት ሺህን ያሸንፋሉ። አላህም ከታጋሾቹ ጋር ነው።

(66) Now Allah has lightened your burden, for He knew that there is weakness in you. So if there are a hundred steadfast men among you, they will overcome two hundred; and if there are a thousand, they will overcome two thousand, by Allah’s permission. And Allah is with those who are steadfast.

مَا كَانَ لِنَبِيٍّ أَن يَكُونَ لَهُ أَسْرَىٰ حَتَّىٰ يُثْخِنَ فِي الْأَرْضِ ۚ تُرِيدُونَ عَرَضَ الدُّنْيَا وَاللَّهُ يُرِيدُ الْآخِرَةَ ۗ وَاللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ  [67]

(67) ለነቢይ በምድር ላይ እስቲያደክም ድረስ ለእርሱ ምርኮኞች ሊኖሩት አይገባም። የቅርቢቱን ዓለም ጠፊ ጥቅም ትፈልጋላችሁ። አላህም መጨረሻይቱን ይሻል። አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።

(67) It is not befitting for a prophet to take captives until he thoroughly subdues [the enemy] in the land. You desire the gains of this world, but Allah desires [for you] the Hereafter. And Allah is All-Mighty, All-Wise.

لَّوْلَا كِتَابٌ مِّنَ اللَّهِ سَبَقَ لَمَسَّكُمْ فِيمَا أَخَذْتُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ  [68]

(68) ከአላህ ያለፈ ፍርድ ባልነበረ ኖሮ በወሰዳችሁት (ቤዛ) ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር።

(68) Were it not for a prior decree from Allah, you would have surely been afflicted with a great punishment for what you have taken [of ransom].

فَكُلُوا مِمَّا غَنِمْتُمْ حَلَالًا طَيِّبًا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ  [69]

(69) (ከጠላት) ከዘረፋችሁትም (ሀብት) የተፈቀደ መልካም ሲኾን ብሉ። አላህንም ፍሩ። አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና።

(69) So enjoy what you have gained in war, for it is lawful and good, but fear Allah. Allah is indeed All-Forgiving, Most Merciful.

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّمَن فِي أَيْدِيكُم مِّنَ الْأَسْرَىٰ إِن يَعْلَمِ اللَّهُ فِي قُلُوبِكُمْ خَيْرًا يُؤْتِكُمْ خَيْرًا مِّمَّا أُخِذَ مِنكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ  [70]

(70) አንተ ነቢዩ ሆይ! ከምርኮኞች በእጆቻችሁ ላሉት በላቸው፡- «አላህ በልቦቻችሁ ውስጥ በጎን ነገር (እምነትን) ቢያውቅ ከእናንተ ከተወሰደባችሁ የተሻለን ይሰጣችኋል። ለእናንተም ይምራችኋል። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።»

(70) O Prophet, tell those captives who are in your custody, “If Allah knows of any good in your hearts, He will give you something better than what has been taken from you, and will forgive you, for Allah is All-Forgiving, Most Merciful.”

وَإِن يُرِيدُوا خِيَانَتَكَ فَقَدْ خَانُوا اللَّهَ مِن قَبْلُ فَأَمْكَنَ مِنْهُمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ  [71]

(71) ሊከዱህም ቢፈልጉ ከዚህ በፊት አላህን በእርግጥ ከድተዋል። ከነሱም አስመችቶሃል። አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።

(71) But if they intend to betray you, they have already betrayed Allah before, so He empowered you over them. And Allah is All-Knowing, All-Wise.

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَٰئِكَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يُهَاجِرُوا مَا لَكُم مِّن وَلَايَتِهِم مِّن شَيْءٍ حَتَّىٰ يُهَاجِرُوا ۚ وَإِنِ اسْتَنصَرُوكُمْ فِي الدِّينِ فَعَلَيْكُمُ النَّصْرُ إِلَّا عَلَىٰ قَوْمٍ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُم مِّيثَاقٌ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ  [72]

(72) እነዚያ ያመኑና የተሰደዱ። በአላህም መንገድ ላይ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የታገሉ። እነዚያም (ስደተኞቹን) ያስጠጉና የረዱ። እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው። እነዚያም ያመኑና ያልተሰደዱ እስከሚሰደዱ ድረስ ከነሱ ምንም ዝምድና የላችሁም። በሃይማኖትም እርዳታን ቢፈልጉባችሁ በእናንተና በነሱ መካከል ቃል ኪዳን ባላችሁ ሕዝቦች ላይ ካልኾነ በስተቀር በናንተ ላይ መርዳት አለባችሁ። አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው።

(72) Those who believed, migrated, and fought with their wealth and their lives in the cause of Allah, and those who provided [migrants] with shelter and help – they are allies of one another. As for those who believed but did not migrate, you have no obligation to protect them until they migrate. But if they seek your help in religion, it is your obligation to help, except against people with whom you have a treaty. And Allah is All-Seeing of what you do.

وَالَّذِينَ كَفَرُوا بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ إِلَّا تَفْعَلُوهُ تَكُن فِتْنَةٌ فِي الْأَرْضِ وَفَسَادٌ كَبِيرٌ  [73]

(73) እነዚያም የካዱት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው። (ከምእምናን መረዳዳትን ከከሓዲያን መቆራረጥን) ባትሠሩት በምድር ላይ ሁከትና ታላቅ ጥፋት ይኾናል።

(73) Those who disbelieve are protectors of one another. Unless you do likewise, there will be persecution in the land and a great corruption.

وَالَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ  [74]

(74) እነዚያም ያመኑና የተሰደዱ በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ፣ እነዚያም ያስጠጉና የረዱ እነዚያ እነሱ በእውነት አማኞች ናቸው። ለእነሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው።

(74) Those who believed, migrated and fought in the cause of Allah, as well as those who gave them refuge and help – it is they who are the true believers; they will have forgiveness and an honorable provision.

وَالَّذِينَ آمَنُوا مِن بَعْدُ وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا مَعَكُمْ فَأُولَٰئِكَ مِنكُمْ ۚ وَأُولُو الْأَرْحَامِ بَعْضُهُمْ أَوْلَىٰ بِبَعْضٍ فِي كِتَابِ اللَّهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ  [75]

(75) እነዚያም በኋላ ያመኑና የተሰደዱ፣ ከእናንተም ጋር ኾነው የታገሉ እነዚያ ከናንተው ናቸው። የዝምድናዎች ባለቤቶችም በአላህ መጽሐፍ ከፊሎቻቸው በከፊሉ (መውረስ) የተገቡ ናቸው። አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው።

(75) And those who believed afterwards, migrated and fought along with you – they belong to you. But blood relatives are more entitled to inherit from one another according to the Book of Allah. Indeed, Allah is All-Knowing of everything.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

ሱረቱል አል-በቀራህ አማርኛ ቅዱስ ቁርአን ምዕራፍ 2 Amharic Quran

ሱረቱል አል-በቀራህ አማርኛ ቅዱስ ቁርአን ምዕራፍ 2 Amharic Quran بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ Bismillah hir rahman nir raheem الم  [1] (1) አ.ለ.መ    (1)…

38 – Saad

38 – Saad (1) ጸ. (ሷድ) የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ (ብዙ አማልክት አሉ እንደሚሉት አይደለም)፡፡ (1) Sād. By the Qur’an, full of…

46 – Al-Ahqaf

46 – Al-Ahqaf (1) ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ (1) Hā Mīm. (2) የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ነው፡፡ (2) The revelation…