Default Image
20, Nov 2023
ሱረቱ አል ሁድ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran 11 Al-Hud

ሱረቱ አል ሁድ አማርኛ ቁርአን Free Amharic Quran 11 Al-Hud

الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ  [1]

(1) አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርኣን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው። ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው።

(1) Alif Lām Ra. This is a Book whose verses are perfected, then fully explained, from One Who is All-Wise, All-Aware.

أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ  [2]

(2) (እንዲህ በላቸው)፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ። እኔ ለእናንተ ከርሱ (የተላክሁ) አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ።»

(2) [Say O Prophet], “Worship none except Allah. Indeed, I am sent to you from Him, as a warner and bearer of glad tidings.

وَأَنِ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ يُمَتِّعْكُم مَّتَاعًا حَسَنًا إِلَىٰ أَجَلٍ مُّسَمًّى وَيُؤْتِ كُلَّ ذِي فَضْلٍ فَضْلَهُ ۖ وَإِن تَوَلَّوْا فَإِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ كَبِيرٍ  [3]

(3) ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት። ከዚያም ወደእርሱ ተመለሱ። እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋልና። የትሩፋትንም ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳውን) ይሰጠዋል። ብትሸሹም እኔ በእናንተ ላይ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።

(3) And seek your Lord’s forgiveness and turn to Him in repentance, He will grant you good enjoyment of life for an appointed term and graciously reward the doers of good. But if you turn away, I truly fear for you the punishment of a great Day.

إِلَى اللَّهِ مَرْجِعُكُمْ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ  [4]

(4) መመለሻችሁ ወደ አላህ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

(4) To Allah is your return, and He is Most Capable of all things.”

أَلَا إِنَّهُمْ يَثْنُونَ صُدُورَهُمْ لِيَسْتَخْفُوا مِنْهُ ۚ أَلَا حِينَ يَسْتَغْشُونَ ثِيَابَهُمْ يَعْلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعْلِنُونَ ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ  [5]

(5) ንቁ! እነሱ ከእርሱ (ከአላህ) ይደበቁ ዘንድ ደረቶቻቸውን ያጥፋሉ። ንቁ! ልብሶቻቸውን በሚከናነቡ ጊዜ የሚደብቁትን የሚገልጹትንም ሁሉ ያውቃል። እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነውና።

(5) Indeed, they lean forward to conceal their feelings from Him, but even when they cover themselves with their clothes, He knows what they conceal and what they reveal, for He is All-Knowing of what is in the hearts.

وَمَا مِن دَابَّةٍ فِي الْأَرْضِ إِلَّا عَلَى اللَّهِ رِزْقُهَا وَيَعْلَمُ مُسْتَقَرَّهَا وَمُسْتَوْدَعَهَا ۚ كُلٌّ فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ  [6]

(6) በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ። ማረፊያዋንም መርጊያዋንም ያውቃል። ሁሉም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው።

(6) There is no moving creature on earth but upon Allah is its provision. He knows its place of dwelling and its place of rest; everything is [written] in a clear Record.

وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۗ وَلَئِن قُلْتَ إِنَّكُم مَّبْعُوثُونَ مِن بَعْدِ الْمَوْتِ لَيَقُولَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا إِنْ هَٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ  [7]

(7) እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ነው። ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር። የትኛችሁ ሥራው ያማረ መሆኑን ይፈትናችሁ ዘንድ (ፈጠራቸው)። «እናንተ ከሞት በኋላ በእርግጥ ተቀስቃሾች ናችሁ» ብትልም እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም ይላሉ።

(7) It is He Who created the heavens and earth in six Days – and His Throne was upon the water – so that He may test you as to which of you is best in deed. But if you say to them, “You will certainly be raised after death,” the disbelievers will surely say, “This is nothing but clear magic!”

وَلَئِنْ أَخَّرْنَا عَنْهُمُ الْعَذَابَ إِلَىٰ أُمَّةٍ مَّعْدُودَةٍ لَّيَقُولُنَّ مَا يَحْبِسُهُ ۗ أَلَا يَوْمَ يَأْتِيهِمْ لَيْسَ مَصْرُوفًا عَنْهُمْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا بِهِ يَسْتَهْزِئُونَ  [8]

(8) ቅጣቱንም ወደ ተቆጠሩ (ጥቂት) ጊዜያቶች ከእነርሱ ብናቆይላቸው «(ከመውረድ) የሚከለክለው ምንድን ነው» ይላሉ። ንቁ! በሚመጣባቸው ቀን ከእነሱ ላይ ተመላሽ አይደለም። በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩትም (ቅጣት) በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል።

(8) If We delay their punishment for a limited time, they will surely say, “What is holding it back?” Indeed, the day when it comes upon them, it will not be averted from them, and they will be encompassed by what they used to ridicule.

وَلَئِنْ أَذَقْنَا الْإِنسَانَ مِنَّا رَحْمَةً ثُمَّ نَزَعْنَاهَا مِنْهُ إِنَّهُ لَيَئُوسٌ كَفُورٌ  [9]

(9) ሰውንም ከእኛ ችሮታን ብናቀምሰው ከዚያም ከርሱ ብንወስዳት እርሱ በእርግጥ ተስፋ ቆራጭ ክህደተ ብርቱ ነው።

(9) If We give man a taste of Our mercy, then take it away from him, he becomes utterly despaired and ungrateful.

وَلَئِنْ أَذَقْنَاهُ نَعْمَاءَ بَعْدَ ضَرَّاءَ مَسَّتْهُ لَيَقُولَنَّ ذَهَبَ السَّيِّئَاتُ عَنِّي ۚ إِنَّهُ لَفَرِحٌ فَخُورٌ  [10]

(10) ካገኘችውም ችግር በኋላ ጸጋዎችን ብናቀምሰው «ችግሮች ከኔ ላይ በእርግጥ ተወገዱ» ይላል (አያመሰግንም)። እርሱ ተደሳች ጉረኛ ነውና።

(10) But if We give him a taste of prosperity after being afflicted with hardship, he will surely say, “All my ills are gone,” and becomes exultant and boastful,

إِلَّا الَّذِينَ صَبَرُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُولَٰئِكَ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ كَبِيرٌ  [11]

(11) ግን እነዚያ የታገሱ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ እነዚያ ለእነሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አልላቸው።

(11) except those who are patient and do righteous deeds; it is they who will have forgiveness and a great reward.

فَلَعَلَّكَ تَارِكٌ بَعْضَ مَا يُوحَىٰ إِلَيْكَ وَضَائِقٌ بِهِ صَدْرُكَ أَن يَقُولُوا لَوْلَا أُنزِلَ عَلَيْهِ كَنزٌ أَوْ جَاءَ مَعَهُ مَلَكٌ ۚ إِنَّمَا أَنتَ نَذِيرٌ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ  [12]

(12) በእርሱ ላይ የገንዘብ ድልብ ለምን አልተወረደም ወይም ከርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም ማለታቸውንም በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በእርሱም ልብህ ጠባብ ሊኾን ይፈራልሃል። አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ። አላህም በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው።

(12) Perhaps you may disregard some of what is revealed to you [O Prophet], and may feel distressed because they say, “Why has not a treasure been sent down to him, or why has not an angel come with him?” You are only a warner, and Allah is in charge of all things.

أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ ۖ قُلْ فَأْتُوا بِعَشْرِ سُوَرٍ مِّثْلِهِ مُفْتَرَيَاتٍ وَادْعُوا مَنِ اسْتَطَعْتُم مِّن دُونِ اللَّهِ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ  [13]

(13) ይልቁንም «(ቁርኣንን) ቀጣጠፈው» ይላሉን፡- «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን ዐስር የተቀጣጠፉ ሱራዎች አምጡ። ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን (ረዳት) ጥሩ» በላቸው።

(13) Or do they say, “He has fabricated it”? Say, “Then produce ten fabricated Chapters like it and seek help from whoever you can besides Allah, if you are truthful!”

فَإِلَّمْ يَسْتَجِيبُوا لَكُمْ فَاعْلَمُوا أَنَّمَا أُنزِلَ بِعِلْمِ اللَّهِ وَأَن لَّا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ  [14]

(14) ለእናንተም (ጥሪውን) ባይቀበሏችሁ የተወረደው በአላህ እውቀት ብቻ መሆኑንና ከእርሱ ሌላ አምላክ አለመኖሩን ዕወቁ። ታዲያ እናንተ የምትሰልሙ ናችሁን (ስለሙ በላቸው)።

(14) But if they do not respond to you, then know that it has been revealed with the knowledge of Allah, and that none has the right to be worshiped except Him. Will you then submit to Him [as Muslims]?

مَن كَانَ يُرِيدُ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيْهِمْ أَعْمَالَهُمْ فِيهَا وَهُمْ فِيهَا لَا يُبْخَسُونَ  [15]

(15) ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) በእርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን። እነሱም በርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም፤

(15) Those who seek the life of this world and its splendor, We will repay them in full in this life for their deeds, and nothing will be diminished from them therein.

أُولَٰئِكَ الَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ إِلَّا النَّارُ ۖ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا فِيهَا وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ  [16]

(16) እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው። የሠሩትም ሥራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ። (በቅርቢቱ ዓለም) ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው።

(16) It is they who will have nothing in the Hereafter but the Fire. All their efforts will be worthless, and all their deeds will be futile.

أَفَمَن كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّهِ وَيَتْلُوهُ شَاهِدٌ مِّنْهُ وَمِن قَبْلِهِ كِتَابُ مُوسَىٰ إِمَامًا وَرَحْمَةً ۚ أُولَٰئِكَ يُؤْمِنُونَ بِهِ ۚ وَمَن يَكْفُرْ بِهِ مِنَ الْأَحْزَابِ فَالنَّارُ مَوْعِدُهُ ۚ فَلَا تَكُ فِي مِرْيَةٍ مِّنْهُ ۚ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ  [17]

(17) ከጌታው ከአስረጅ ጋር የኾነ ሰው፤ ከእርሱም (ከአላህ) የኾነ መስካሪ የሚከተለው፣ ከእርሱ በፊትም የሙሳ መጽሐፍ መሪና እዝነት ሲኾን (የመሰከረለት) የቅርቢቱን ሕይወት እንደሚሻው ሰው ነውን እነዚያ በእርሱ (በቁርኣን) ያምናሉ። ከአሕዛቦቹም በእርሱ የሚክድ ሰው እሳት መመለሻው ናት። ከእርሱም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን። እርሱ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም።

(17) Can they be like those who are upon clear proof from their Lord, backed by a witness [Gabriel] from Him, and before it was the Book of Moses a guide and mercy? Such people believe in it. But whoever of the factions disbelieves in it, the Fire will be their promised end. So have no doubt about it, for it is the truth from your Lord, but most people do not believe.

وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا ۚ أُولَٰئِكَ يُعْرَضُونَ عَلَىٰ رَبِّهِمْ وَيَقُولُ الْأَشْهَادُ هَٰؤُلَاءِ الَّذِينَ كَذَبُوا عَلَىٰ رَبِّهِمْ ۚ أَلَا لَعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ  [18]

(18) በአላህ ላይ እብለትን ከሚቀጣጥፍም ይበልጥ በዳይ ማነው እነዚያ በጌታቸው ላይ ይቀርባሉ። መስካሪዎቹም «እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹት ናቸው» ይላሉ። ንቁ! የአላህ ርግማን በበዳዮች ላይ ይሁን።

(18) Who does greater wrong than he who fabricates lies against Allah? Such people will be presented before their Lord, and the witnesses will say, “These are the ones who lied against their Lord.” Indeed, Allah’s curse is upon the wrongdoers,

الَّذِينَ يَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ وَيَبْغُونَهَا عِوَجًا وَهُم بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ  [19]

(19) (እነሱም) እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚከለክሉ መጥመሟንም የሚፈልጓት ናቸው። እነሱም መጨረሻይቱን ዓለም እነሱ ከሓዲዎች ናቸው፡፤

(19) those who hinder [people] from the way of Allah, seeking to make it crooked, and they disbelieve in the Hereafter.”

أُولَٰئِكَ لَمْ يَكُونُوا مُعْجِزِينَ فِي الْأَرْضِ وَمَا كَانَ لَهُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ۘ يُضَاعَفُ لَهُمُ الْعَذَابُ ۚ مَا كَانُوا يَسْتَطِيعُونَ السَّمْعَ وَمَا كَانُوا يُبْصِرُونَ  [20]

(20) እነዚያ በምድር ውስጥ (ከአላህ) የሚያመልጡ አልነበሩም። ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ረዳቶች አልነበሯቸውም። ለእነሱ ቅጣቱ ይደራረብላቸዋል። (እውነትን) መስማትን የሚችሉ አልነበሩም የሚያዩም አልነበሩም።

(20) They will have no escape on earth, nor will they have any protector besides Allah. Their punishment will be doubled, for they failed to hear or see [the truth].

أُولَٰئِكَ الَّذِينَ خَسِرُوا أَنفُسَهُمْ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ  [21]

(21) እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር የጠፋቸው ናቸው።

(21) It is they who destroyed themselves, and all what they fabricated will be lost from them.

لَا جَرَمَ أَنَّهُمْ فِي الْآخِرَةِ هُمُ الْأَخْسَرُونَ  [22]

(22) እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም በጣም ከሳሪዎቹ እነሱ መሆናቸው ጥርጥር የለውም።

(22) There is no doubt that they will be the worst losers in the Hereafter.

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَأَخْبَتُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ  [23]

(23) እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸውም የተዋረዱት እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው። እነሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው።

(23) Those who believe, do righteous deeds and humble themselves before their Lord, it is they who are the people of Paradise, they will abide therein forever.

مَثَلُ الْفَرِيقَيْنِ كَالْأَعْمَىٰ وَالْأَصَمِّ وَالْبَصِيرِ وَالسَّمِيعِ ۚ هَلْ يَسْتَوِيَانِ مَثَلًا ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ  [24]

(24) የሁለቱ ክፍሎች ምሳሌ እንደ ዕውርና እንደ ደንቆሮ እንደሚያይና እንደሚሰማም ብጤ ነው። በምሳሌ ይተካከላሉን አትገሰጹምን

(24) The similitude of the two parties is that of the blind and deaf, compared to the seeing and hearing. Are they equal? Will you not then take heed?

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ إِنِّي لَكُمْ نَذِيرٌ مُّبِينٌ  [25]

(25) ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክን። (አላቸውም)፡- «እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ (አስጠንቃቂ) ነኝ።»

(25) We sent Noah to his people [and he said], “I am indeed a clear warner to you,

أَن لَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۖ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ أَلِيمٍ  [26]

(26) «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ። እኔ በእናንተ ላይ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።»

(26) that you worship none except Allah. I truly fear for you the punishment of a painful Day.”

فَقَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن قَوْمِهِ مَا نَرَاكَ إِلَّا بَشَرًا مِّثْلَنَا وَمَا نَرَاكَ اتَّبَعَكَ إِلَّا الَّذِينَ هُمْ أَرَاذِلُنَا بَادِيَ الرَّأْيِ وَمَا نَرَىٰ لَكُمْ عَلَيْنَا مِن فَضْلٍ بَلْ نَظُنُّكُمْ كَاذِبِينَ  [27]

(27) ከሕዝቦቹም እነዚያ የካዱት መሪዎቹ ብጤያችን ሰው ሆነህ እንጂ አናይህም። እነዚያም እነሱ ሐሳበ ጥሬዎች የሆኑት ወራዶቻችን እንጂ ሌላ ተከትሎህ አናይህም። ለእናንተም በእኛ ላይ ምንም ብልጫን አናይም። ከቶውንም ውሸታሞች መሆናችሁን እንጠረጥራችኋለን አሉ።

(27) But the chiefs of his people who disbelieved said, “We only see you as a human being like ourselves, and we do not see those who follow you except the lowest among us apparently. We do not see you superior to us, rather, we think that you are liars.”

قَالَ يَا قَوْمِ أَرَأَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّي وَآتَانِي رَحْمَةً مِّنْ عِندِهِ فَعُمِّيَتْ عَلَيْكُمْ أَنُلْزِمُكُمُوهَا وَأَنتُمْ لَهَا كَارِهُونَ  [28]

(28) «ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ (ነብይነት) ቢሰጠኝና በእናንተ ላይ ብትደበቅባችሁ እናንተ ለርቯ ጠይዎች ስትሆኑ እርቯን (በመቀበል) እናስገድዳችኋለን» አላቸው።

(28) He said, “O my people, what do you think, if I should have a clear proof from my Lord, and He has bestowed mercy upon me from Himself, but you fail to see it, can we force you to accept it despite your aversion to it?

وَيَا قَوْمِ لَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ مَالًا ۖ إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَى اللَّهِ ۚ وَمَا أَنَا بِطَارِدِ الَّذِينَ آمَنُوا ۚ إِنَّهُم مُّلَاقُو رَبِّهِمْ وَلَٰكِنِّي أَرَاكُمْ قَوْمًا تَجْهَلُونَ  [29]

(29) «ሕዝቦቼም ሆይ! በርሱ (በተላክሁበት ማድረስ) ላይ ገንዘብን አልጠይቃችሁም። ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም። እኔም እነዚያን ያመኑትን አባራሪ አይደለሁም። እነርሱ ጌታቸውን የሚገናኙ ናቸውና። ግን እኔም የምትሳሳቱ ሕዝቦች ሆናችሁ አያችኋለሁ።»

(29) O my people, I do not ask you for any wealth in return for it; my reward is only with Allah. I will not dismiss those who believe; they will surely meet their Lord, but I see that you are ignorant people.

وَيَا قَوْمِ مَن يَنصُرُنِي مِنَ اللَّهِ إِن طَرَدتُّهُمْ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ  [30]

(30) «ሕዝቦቼም ሆይ ባባርራቸው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማን ነው አትገሰጹምን»

(30) O my people, who would protect me from Allah if I were to dismiss them? Will you not then take heed?

وَلَا أَقُولُ لَكُمْ عِندِي خَزَائِنُ اللَّهِ وَلَا أَعْلَمُ الْغَيْبَ وَلَا أَقُولُ إِنِّي مَلَكٌ وَلَا أَقُولُ لِلَّذِينَ تَزْدَرِي أَعْيُنُكُمْ لَن يُؤْتِيَهُمُ اللَّهُ خَيْرًا ۖ اللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا فِي أَنفُسِهِمْ ۖ إِنِّي إِذًا لَّمِنَ الظَّالِمِينَ  [31]

(31) «ለእናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አልሉ ሩቅንም ዐውቃለሁ አልላችሁም። እኔም መልአክ ነኝ አልላችሁም። ለእነዚያም ዓይኖቻችሁ ለሚያዋርዷቸው አላህ ደግ ነገርን (እምነትን) አይሰጣቸውም አልልም። አላህ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር አዋቂ ነው። እኔ ያን ጊዜ ከበደለኞች እሆናለሁና» (አላቸው)።

(31) I do not tell you that I have Allah’s treasures or that I know the unseen, nor do I say that I am an angel. Nor do I say about those whom you look down upon, that Allah will never grant them any good, for Allah knows best what is in their hearts. If I did so, I would surely be one of the wrongdoers.”

قَالُوا يَا نُوحُ قَدْ جَادَلْتَنَا فَأَكْثَرْتَ جِدَالَنَا فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَا إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ  [32]

(32) «ኑህ ሆይ! በእርግጥ ተከራከርከን። እኛን መከራከርህንም አበዛኸው። ከእውነተኞቹም እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው» አሉ፡

(32) They said, “O Noah, you have argued far too much with us, so bring what you are threatening us with, if you are one of the truthful.”

قَالَ إِنَّمَا يَأْتِيكُم بِهِ اللَّهُ إِن شَاءَ وَمَا أَنتُم بِمُعْجِزِينَ  [33]

(33) «እርሱን የሚያመጣባችሁ የሻ እንደ ሆነ አላህ ብቻ ነው። እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም» አላቸው።

(33) He said, “It is only Allah Who can bring it upon you if He wills, then you will have no escape.

وَلَا يَنفَعُكُمْ نُصْحِي إِنْ أَرَدتُّ أَنْ أَنصَحَ لَكُمْ إِن كَانَ اللَّهُ يُرِيدُ أَن يُغْوِيَكُمْ ۚ هُوَ رَبُّكُمْ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ  [34]

(34) «ለእናንተም ልመክራችሁ ብሻ አላህ ሊያጠማችሁ ሽቶ እንደ ኾነ ምክሬ አይጠቅማችሁም። እርሱ ጌታችሁ ነው። ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ» (አላቸው)።

(34) Nor will my advice benefit you – no matter how hard I try – if Allah wills to leave you astray. He is your Lord, and to Him you will be returned.”

أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ ۖ قُلْ إِنِ افْتَرَيْتُهُ فَعَلَيَّ إِجْرَامِي وَأَنَا بَرِيءٌ مِّمَّا تُجْرِمُونَ  [35]

(35) «ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን ብቀጥፈው ኃጢኣቴ (ቅጣቱ) በኔ ላይ ነው። እኔም ከምታጠፉት (ጥፋት) ንጹሕ ነኝ» በላቸው።

(35) Or do they say that he has fabricated it”? Say [O Prophet], “If I did fabricate it, then I am responsible for my sin, but I am innocent of the sins you commit.”

وَأُوحِيَ إِلَىٰ نُوحٍ أَنَّهُ لَن يُؤْمِنَ مِن قَوْمِكَ إِلَّا مَن قَدْ آمَنَ فَلَا تَبْتَئِسْ بِمَا كَانُوا يَفْعَلُونَ  [36]

(36) ወደ ኑሕም እነሆ «ከሕዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር (ወደፊት) አያምኑም። ይሠሩትም በነበሩት (ክህደት) አትዘን ማለት ተወረደ።»

(36) It was revealed to Noah, “None of your people will ever believe except those who have already believed. So do not grieve over what they do.

وَاصْنَعِ الْفُلْكَ بِأَعْيُنِنَا وَوَحْيِنَا وَلَا تُخَاطِبْنِي فِي الَّذِينَ ظَلَمُوا ۚ إِنَّهُم مُّغْرَقُونَ  [37]

(37) (አላህም) «በጥበቃችንና በትእዛዛችንም ሆነህ መርከቢቱን ሥራ። በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ እነሱ በእርግጥ ሰማጮች ናቸውና» (አለው)።

(37) Construct the Ark under Our [watchful] Eyes and Our direction, and do not plead with Me for those who did wrong, for they will surely be drowned.”

وَيَصْنَعُ الْفُلْكَ وَكُلَّمَا مَرَّ عَلَيْهِ مَلَأٌ مِّن قَوْمِهِ سَخِرُوا مِنْهُ ۚ قَالَ إِن تَسْخَرُوا مِنَّا فَإِنَّا نَسْخَرُ مِنكُمْ كَمَا تَسْخَرُونَ  [38]

(38) ከወገኖቹም መሪዎቹ በእርሱ አጠገብ ባለፉ ቁጥር ከእርሱ እየተሳለቁ መርከቢቱን ይሠራል። «ከእኛ ብትሳለቁ እኛም እንደተሳለቃችሁብን ከናንተ እንሳለቅባችኋለን» አላቸው።

(38) So he started constructing the Ark, and every time some chiefs of his people passed by him, they ridiculed him. He said, “If you ridicule us now, we will soon ridicule you as you are ridiculing us.

فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ مَن يَأْتِيهِ عَذَابٌ يُخْزِيهِ وَيَحِلُّ عَلَيْهِ عَذَابٌ مُّقِيمٌ  [39]

(39) «የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትን በእርሱም ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበት ሰው (ማን እንደ ሆነ) ወደፊት ታውቃላችሁ» (አላቸው)።

(39) You will come to know who will be afflicted with a disgracing punishment, and upon whom will descend an everlasting punishment.”

حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَمْرُنَا وَفَارَ التَّنُّورُ قُلْنَا احْمِلْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ الْقَوْلُ وَمَنْ آمَنَ ۚ وَمَا آمَنَ مَعَهُ إِلَّا قَلِيلٌ  [40]

(40) ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በእርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት (ወንድና ሴት) ፤ ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን» አልነው። ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም።

(40) When Our command came and the oven overflowed, We said, “Take on board a pair from every species and your family – except those who have already been decreed [to drown] – and those who believe.” But none believed with him except a few.

وَقَالَ ارْكَبُوا فِيهَا بِسْمِ اللَّهِ مَجْرَاهَا وَمُرْسَاهَا ۚ إِنَّ رَبِّي لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ  [41]

(41) «መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው እያላችሁም በውስጧ ተሳፈሩ። ጌታ መሓሪ አዛኝ ነውና» አላቸው።

(41) Noah said, “Board it; in the name of Allah it sails and anchors. My Lord is All-Forgiving, Most Merciful.”

وَهِيَ تَجْرِي بِهِمْ فِي مَوْجٍ كَالْجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ابْنَهُ وَكَانَ فِي مَعْزِلٍ يَا بُنَيَّ ارْكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ الْكَافِرِينَ  [42]

(42) እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ በእነርሱ (ይዛቸው) የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት)። ኑሕም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከኛ ጋር ተሳፈር ከከሓዲዎቹም አትሁን» ሲል ጠራው።

(42) As it sailed with them through waves like mountains, Noah called out to his son, who had kept himself apart, “O my son, come aboard with us, and do not be with the disbelievers.”

قَالَ سَآوِي إِلَىٰ جَبَلٍ يَعْصِمُنِي مِنَ الْمَاءِ ۚ قَالَ لَا عَاصِمَ الْيَوْمَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ إِلَّا مَن رَّحِمَ ۚ وَحَالَ بَيْنَهُمَا الْمَوْجُ فَكَانَ مِنَ الْمُغْرَقِينَ  [43]

(43) (ልጁም) «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ» አለ። (አባቱም)፡- «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም (እርሱ) ያዘነለት ካልሆነ በቀር» አለው። ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ። ከሰጣሚዎቹም ሆነ።

(43) He said, “I will take shelter on a mountain which will save me from the water.” Noah said, “Today no one will be saved from Allah’s punishment except those on whom He may have mercy.” Thereupon the waves came between them, and he was among those who were drowned.

وَقِيلَ يَا أَرْضُ ابْلَعِي مَاءَكِ وَيَا سَمَاءُ أَقْلِعِي وَغِيضَ الْمَاءُ وَقُضِيَ الْأَمْرُ وَاسْتَوَتْ عَلَى الْجُودِيِّ ۖ وَقِيلَ بُعْدًا لِّلْقَوْمِ الظَّالِمِينَ  [44]

(44) ተባለም፡- «ምድር ሆይ! ውሃሽን ዋጪ። ሰማይም ሆይ (ዝናብሽን) ያዢ። ውሃውም ሰረገ። ቅጣቱም ተፈጸም። ጁዲይ በሚባልም ተራራ ላይ (መርከቢቱ) ተደላደለች። ለከሓዲዎችም ሰዎች ጥፋት ተገባቸው (ጠፉ)» ተባለ።

(44) And it was said, “O earth, swallow up your water. O sky, withhold [your rain]!” The water subsided and the command was fulfilled, and the Ark settled on Mount Judi, and it was said, “Away with the wrongdoing people!”

وَنَادَىٰ نُوحٌ رَّبَّهُ فَقَالَ رَبِّ إِنَّ ابْنِي مِنْ أَهْلِي وَإِنَّ وَعْدَكَ الْحَقُّ وَأَنتَ أَحْكَمُ الْحَاكِمِينَ  [45]

(45) ኑሕም ጌታውን ጠራ። አለም «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ ነው። ኪዳንህም እውነት ነው። አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ዐዋቂ ነህ።»

(45) Noah called out to his Lord, saying, “My Lord, my son is one of my family, and Your promise is true and You are the Most Just of all judges!”

قَالَ يَا نُوحُ إِنَّهُ لَيْسَ مِنْ أَهْلِكَ ۖ إِنَّهُ عَمَلٌ غَيْرُ صَالِحٍ ۖ فَلَا تَسْأَلْنِ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۖ إِنِّي أَعِظُكَ أَن تَكُونَ مِنَ الْجَاهِلِينَ  [46]

(46) (አላህም) «ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ» አለ።

(46) Allah said, “O Noah, he is not of your family, for he was not righteous in his conduct. So do not ask Me of what you have no knowledge. I admonish you, so you do not be among the ignorant.”

قَالَ رَبِّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ أَنْ أَسْأَلَكَ مَا لَيْسَ لِي بِهِ عِلْمٌ ۖ وَإِلَّا تَغْفِرْ لِي وَتَرْحَمْنِي أَكُن مِّنَ الْخَاسِرِينَ  [47]

(47) «ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ። ለእኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎቹ እሆናለሁ» አለ።

(47) Noah said, “My Lord, I seek refuge with You from asking You that of which I have no knowledge. Unless You forgive me and have mercy upon me, I will be among the losers.”

قِيلَ يَا نُوحُ اهْبِطْ بِسَلَامٍ مِّنَّا وَبَرَكَاتٍ عَلَيْكَ وَعَلَىٰ أُمَمٍ مِّمَّن مَّعَكَ ۚ وَأُمَمٌ سَنُمَتِّعُهُمْ ثُمَّ يَمَسُّهُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٌ  [48]

(48) «ኑሕ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች (ትውልድ) ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ። (ከእነሱው ዘሮች የሆኑ) ሕዝቦችም በቅርቢቱ ዓለም በእርግጥ እናስመቻቸዋለን። ከዚያም ከኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይነካቸዋል» ተባለ።

(48) It was said, “O Noah, disembark with peace from Us, and with blessings upon you and upon some nations [descending] from those who are with you. As for other nations, We will grant them enjoyment for a while, then they will be afflicted with a painful punishment from Us.”

تِلْكَ مِنْ أَنبَاءِ الْغَيْبِ نُوحِيهَا إِلَيْكَ ۖ مَا كُنتَ تَعْلَمُهَا أَنتَ وَلَا قَوْمُكَ مِن قَبْلِ هَٰذَا ۖ فَاصْبِرْ ۖ إِنَّ الْعَاقِبَةَ لِلْمُتَّقِينَ  [49]

(49) ይህቺ ከሩቁ ወሬዎች ናት። ወደ አንተ እናወርዳታለን። አንተም ሕዝቦችህም ከዚህ በፊት የምታውቋት አልነበራችሁም። ታገስም፤ ምስጉን የሆነችው ፍጻሜ ለሚጠነቀቁት ናትና።

(49) This is one of the stories of the unseen that we reveal to you [O Prophet]; neither you nor your people knew it before this. So be patient; the outcome is for the righteous.

وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا مُفْتَرُونَ  [50]

(50) ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን (ላክን)። አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ። ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም። እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።

(50) To the people of ‘Ād We sent their brother Hūd. He said, “O my people, worship Allah; you have no god other than Him. You are but fabricators.

يَا قَوْمِ لَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ أَجْرًا ۖ إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَى الَّذِي فَطَرَنِي ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ  [51]

(51) «ሕዝቦቼ ሆይ! በእርሱ (በማድረሴ) ላይ ምንዳን አልጠይቃችሁም። ምንዳዬ በዚህ በፈጠረኝ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም። አታውቁምን

(51) O my people, I ask you no reward for it. My reward is only with the One Who created me. Do you not then understand?

وَيَا قَوْمِ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ يُرْسِلِ السَّمَاءَ عَلَيْكُم مِّدْرَارًا وَيَزِدْكُمْ قُوَّةً إِلَىٰ قُوَّتِكُمْ وَلَا تَتَوَلَّوْا مُجْرِمِينَ  [52]

(52) «ሕዝቦቼም ሆይ! ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት። ከዚያም ወደርሱ ተጸጸቱ። ዝናብን በእናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና። ወደ ኃይላችሁም ኃይልን ይጨምርላችኋል። አመጸኞችም ሆናችሁ አትሽሹ።»

(52) O my people, seek forgiveness of your Lord and turn to Him in repentance; He will send down upon you abundant rain from the sky, and will add strength to your strength. So do not turn away in wickedness.”

قَالُوا يَا هُودُ مَا جِئْتَنَا بِبَيِّنَةٍ وَمَا نَحْنُ بِتَارِكِي آلِهَتِنَا عَن قَوْلِكَ وَمَا نَحْنُ لَكَ بِمُؤْمِنِينَ  [53]

(53) አሉ፡- «ሁድ ሆይ! በአስረጅ አልመጣህልንም። እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም። እኛም ለአንተ አማኞች አይደለንም።

(53) They said, “O Hūd, you have not brought us any clear evidence, and we will not forsake our gods on account of what you say, nor will we believe in you.

إِن نَّقُولُ إِلَّا اعْتَرَاكَ بَعْضُ آلِهَتِنَا بِسُوءٍ ۗ قَالَ إِنِّي أُشْهِدُ اللَّهَ وَاشْهَدُوا أَنِّي بَرِيءٌ مِّمَّا تُشْرِكُونَ  [54]

(54) «ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፉ ነገር (በዕብደት) ለክፈውሃል እንጂ ሌላን አንልም» (አሉ)። «እኔ አላህን አስመሰክራለሁ። ከምታጋሩትም እኔ ንጹሕ መሆኔን መስክሩ» አላቸው።

(54) All we can say is that some of our gods have afflicted you with madness.” He said, “I take Allah as witness, and you too be witnesses, that I disown whatever you associate

مِن دُونِهِ ۖ فَكِيدُونِي جَمِيعًا ثُمَّ لَا تُنظِرُونِ  [55]

(55) ከእርሱ ሌላ (አማልክትን ከምታጋሩት ንጹህ ነኝ)። ሁላችሁም ሆናችሁ ተንኮልን ሥሩብኝ፤ ከዚያም አታቆዩኝ።

(55) with Him. So plot against me all together, then give me no respite.

إِنِّي تَوَكَّلْتُ عَلَى اللَّهِ رَبِّي وَرَبِّكُم ۚ مَّا مِن دَابَّةٍ إِلَّا هُوَ آخِذٌ بِنَاصِيَتِهَا ۚ إِنَّ رَبِّي عَلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ  [56]

(56) «እኔ በጌታዬና በጌታችሁ በአላህ ላይ ተጠጋሁ። በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም እርሱ አናትዋን የያዛት ብትሆን እንጂ። ጌታዬ (ቃሉም ሥራውም) በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነው» (አላቸው)።

(56) I put my trust in Allah, my Lord and your Lord. There is no moving creature but He holds it by its forelock. My Lord is on a straight path.

فَإِن تَوَلَّوْا فَقَدْ أَبْلَغْتُكُم مَّا أُرْسِلْتُ بِهِ إِلَيْكُمْ ۚ وَيَسْتَخْلِفُ رَبِّي قَوْمًا غَيْرَكُمْ وَلَا تَضُرُّونَهُ شَيْئًا ۚ إِنَّ رَبِّي عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَفِيظٌ  [57]

(57) «ብትዞሩም በእርሱ ወደእናንተ የተላክሁበትን ነገር በእርግጥ አድርሼላችኋለሁ። ጌታዬ ከእናንተ ሌላ ሕዝብም ይተካል ምንም አትጎዱትምም። ጌታዬ በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና» (አላቸው)።

(57) But if you turn away, I have conveyed to you what I have been sent with. My Lord will replace you with other people, and you cannot harm Him in the least. My Lord watches over all things.”

وَلَمَّا جَاءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا هُودًا وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَنَجَّيْنَاهُم مِّنْ عَذَابٍ غَلِيظٍ  [58]

(58) ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሁድንና እነዚያን ከእሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን። ከብርቱ ቅጣትም አዳናቸው።

(58) When Our command came, We saved Hūd and those who believed with him by Our mercy, and We saved them from a harsh punishment.

وَتِلْكَ عَادٌ ۖ جَحَدُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ وَعَصَوْا رُسُلَهُ وَاتَّبَعُوا أَمْرَ كُلِّ جَبَّارٍ عَنِيدٍ  [59]

(59) ይህች (ነገድ) ዓድ ናት። በጌታቸው ታምራት ካዱ። መልክተኞቹንም አመጹ፤ የኃያል ሞገደኛን ሁሉ ትዕዛዝም ተከተሉ።

(59) Such were the people of ‘Ād, who denied the signs of their Lord, disobeyed His Messengers and followed the command of every obstinate oppressor.

وَأُتْبِعُوا فِي هَٰذِهِ الدُّنْيَا لَعْنَةً وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ أَلَا إِنَّ عَادًا كَفَرُوا رَبَّهُمْ ۗ أَلَا بُعْدًا لِّعَادٍ قَوْمِ هُودٍ  [60]

(60) በዚህች በቅርቢቱ ዓለምም እርግማን እንዲከተላቸው ተደረጉ። በትንሣኤም ቀን (እንደዚሁ)። ንቁ! ዓዶች ጌታቸውን ካዱ። ንቁ! የሁድ ሕዝቦች ለሆኑት ዓዶች (ከእዝነት) መራቅ ይገባቸው።

(60) They were overtaken by a curse in this world and again on the Day of Resurrection. Indeed, ‘Ād denied their Lord; so away with ‘Ād, the people of Hūd!

وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيبٌ  [61]

(61) ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን (ላክን)። «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ። ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም። እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ። በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ። ምሕረቱንም ለምኑት። ከዚህም ወደእርሱ ተመለሱ። ጌታዬ ቅርብ (ለለመነው) ተቀባይ ነውና» አላቸው።

(61) To the people of Thamūd, We sent their brother Sālih. He said, “O my people, worship Allah; you have no god except Him. It is He Who brought you into being from the earth and settled you therein. So seek His forgiveness then turn to Him in repentance, for My Lord is Ever Near, All-Responsive.”

قَالُوا يَا صَالِحُ قَدْ كُنتَ فِينَا مَرْجُوًّا قَبْلَ هَٰذَا ۖ أَتَنْهَانَا أَن نَّعْبُدَ مَا يَعْبُدُ آبَاؤُنَا وَإِنَّنَا لَفِي شَكٍّ مِّمَّا تَدْعُونَا إِلَيْهِ مُرِيبٍ  [62]

(62) «ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ (መሪ ልትሆን) በእርግጥ የምትከጅል ነበርክ። አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን እኛም ወደርሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን» አሉ።

(62) They said, “O Sālih, we truly had hopes in you before this. Do you forbid us to worship what our fathers used to worship? We are in disturbing doubt about what you are calling us to.”

قَالَ يَا قَوْمِ أَرَأَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّي وَآتَانِي مِنْهُ رَحْمَةً فَمَن يَنصُرُنِي مِنَ اللَّهِ إِنْ عَصَيْتُهُ ۖ فَمَا تَزِيدُونَنِي غَيْرَ تَخْسِيرٍ  [63]

(63) «ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም የሆነን ችሮታ (ነቢይነት) ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማነው ከማሳሳትም በስተቀር ምንም አትጨምሩልኝም» አላቸው።

(63) He said, “O my people, what do you think, if I should have a clear proof from my Lord, and He has bestowed mercy upon me from Himself, who could protect me from Allah, if I were to disobey Him? You would only increase me in loss.

وَيَا قَوْمِ هَٰذِهِ نَاقَةُ اللَّهِ لَكُمْ آيَةً فَذَرُوهَا تَأْكُلْ فِي أَرْضِ اللَّهِ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابٌ قَرِيبٌ  [64]

(64) ሕዝቦቼም ሆይ! ይህቺ ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናት። ተውዋትም። በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ። በክፉም አትንኳት። ቅርብ የሆነ ቅጣት ይይዛችኋልና» (አላቸው)።

(64) O my people, this she-camel of Allah is a sign to you; so leave her to graze in Allah’s land, and do not touch her with harm, or else an imminent punishment will overtake you.”

فَعَقَرُوهَا فَقَالَ تَمَتَّعُوا فِي دَارِكُمْ ثَلَاثَةَ أَيَّامٍ ۖ ذَٰلِكَ وَعْدٌ غَيْرُ مَكْذُوبٍ  [65]

(65) ወግተው ገደሏትም። (ሷሊህ) «በአገራችሁም ሶስትን ቀናት (ብቻ) ተጠቀሙ። ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው» አላቸው።

(65) But they hamstrung her, so he said, “Enjoy yourselves in your homes for three days. That is an unfailing promise!”

فَلَمَّا جَاءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا صَالِحًا وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَمِنْ خِزْيِ يَوْمِئِذٍ ۗ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ الْقَوِيُّ الْعَزِيزُ  [66]

(66) ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳን። ከዚያም ቀን ውርደት (አዳንናቸው)። ጌታህ እርሱ ብርቱው አሸናፊው ነውና።

(66) So when Our command came, We saved Sālih and those who believed with him, by Our mercy, and from the disgrace of that day. Your Lord is the All-Powerful, the All-Mighty.

وَأَخَذَ الَّذِينَ ظَلَمُوا الصَّيْحَةُ فَأَصْبَحُوا فِي دِيَارِهِمْ جَاثِمِينَ  [67]

(67) እነዚያንም የበደሉትን ጩኸት ያዛቸው። በቤቶቻቸውም ውስጥ የተንበረከኩ ሆነው ሞተው አነጉ።

(67) The huge blast seized those who did wrong, and they fell dead in their homes,

كَأَن لَّمْ يَغْنَوْا فِيهَا ۗ أَلَا إِنَّ ثَمُودَ كَفَرُوا رَبَّهُمْ ۗ أَلَا بُعْدًا لِّثَمُودَ  [68]

(68) በእሷ ውስጥ እንዳልኖሩባት ሆኑ። ንቁ! ሰሙዶች ጌታቸውን በእርግጥ ካዱ። ንቁ! ለሰሙዶች (ከአላህ እዝነት) መራቅ ተገባቸው።

(68) as though they had never lived there. Indeed, Thamūd denied their Lord; so away with Thamūd!

وَلَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ ۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَاءَ بِعِجْلٍ حَنِيذٍ  [69]

(69) መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በ(ልጅ) ብስራት በእርግጥ መጡት። ሰላም አሉት። ሰላም አላቸው። ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ።

(69) Our angel-messengers came to Abraham with glad tidings. They said, “Peace.” He said, “Peace.” And in a short while he brought a roasted calf.

فَلَمَّا رَأَىٰ أَيْدِيَهُمْ لَا تَصِلُ إِلَيْهِ نَكِرَهُمْ وَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً ۚ قَالُوا لَا تَخَفْ إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَىٰ قَوْمِ لُوطٍ  [70]

(70) እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው። ከነሱም ፍርሃት ተሰማው። «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት።

(70) When he saw their hands not reaching the food, he became suspicious and felt scared of them. They said, “Do not be scared. We have been sent to the people of Lot.”

وَامْرَأَتُهُ قَائِمَةٌ فَضَحِكَتْ فَبَشَّرْنَاهَا بِإِسْحَاقَ وَمِن وَرَاءِ إِسْحَاقَ يَعْقُوبَ  [71]

(71) ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም። በኢስሐቅም አበሰርናት። ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)።

(71) His wife was standing by, and laughed after We gave her glad tidings of [the birth of] Isaac and Jacob after Isaac.

قَالَتْ يَا وَيْلَتَىٰ أَأَلِدُ وَأَنَا عَجُوزٌ وَهَٰذَا بَعْلِي شَيْخًا ۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيْءٌ عَجِيبٌ  [72]

(72) (እርሷም) ዋልኝ! እኔ አሮጊት ይህም ባሌ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው አለች።

(72) She said, “Alas for me! How can I bear a child while I am an old woman, and this is my husband, an old man? This is a strange thing indeed!”

قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ  [73]

(73) «ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና» አሉ።

(73) They said, “Are you amazed at the decree of Allah? May Allah’s mercy and blessings be upon you, O people of the house. He is Praiseworthy, All-Glorious.”

فَلَمَّا ذَهَبَ عَنْ إِبْرَاهِيمَ الرَّوْعُ وَجَاءَتْهُ الْبُشْرَىٰ يُجَادِلُنَا فِي قَوْمِ لُوطٍ  [74]

(74) ከኢብራሂም ፍራቻው በሌደለትና ብስራት በመጣችለትም ጊዜ በሉጥ ሕዝቦች (ነገር) ይከራከረን ጀመር።

(74) When the shock of fear left Abraham and the glad tidings [of Isaac’s birth] came to him, he started pleading with Us concerning the people of Lot.

إِنَّ إِبْرَاهِيمَ لَحَلِيمٌ أَوَّاهٌ مُّنِيبٌ  [75]

(75) ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ አልቃሻ መላሳ ነውና።

(75) Abraham was indeed forbearing, tenderhearted, and constantly returning in repentance.

يَا إِبْرَاهِيمُ أَعْرِضْ عَنْ هَٰذَا ۖ إِنَّهُ قَدْ جَاءَ أَمْرُ رَبِّكَ ۖ وَإِنَّهُمْ آتِيهِمْ عَذَابٌ غَيْرُ مَرْدُودٍ  [76]

(76) «ኢብራሂም ሆይ! ከዚህ (ክርክር) ተው። እነሆ የጌታህ ትዕዛዝ በእርግጥ መጥቷል። እነሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው» (አሉት)።

(76) [The angels said], “O Abraham, leave this, for indeed the command of your Lord has already come to pass, and there will come upon them a punishment that cannot be averted.”

وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا لُوطًا سِيءَ بِهِمْ وَضَاقَ بِهِمْ ذَرْعًا وَقَالَ هَٰذَا يَوْمٌ عَصِيبٌ  [77]

(77) መልክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በነሱ (ምክንያት) አዘነ። ልቡም በነሱ ተጨነቀ። «ይህ ብርቱ ቀን ነውም» አለ።

(77) When Our angel-messengers came to Lot, he was perturbed and felt troubled on their account, and said, “This is a distressing day.”

وَجَاءَهُ قَوْمُهُ يُهْرَعُونَ إِلَيْهِ وَمِن قَبْلُ كَانُوا يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ ۚ قَالَ يَا قَوْمِ هَٰؤُلَاءِ بَنَاتِي هُنَّ أَطْهَرُ لَكُمْ ۖ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَلَا تُخْزُونِ فِي ضَيْفِي ۖ أَلَيْسَ مِنكُمْ رَجُلٌ رَّشِيدٌ  [78]

(78) ሕዝቦቹም ወደርሱ እየተጣደፉ መጡት። ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር። «ሕዝቦቼ ሆይ! እኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው። እነሱ ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው፤ (አግቧቸው)። አላህንም ፍሩ። በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ። ከእናንተ ውስጥ ቅን ሰው የለምን» አላቸው።

(78) His people came rushing to him, and they were accustomed to committing evil deeds. He said, “O my people, here are my daughters [for marriage]; they are purer for you. So fear Allah and do not disgrace me concerning my guests. Is there not a right-minded man among you?”

قَالُوا لَقَدْ عَلِمْتَ مَا لَنَا فِي بَنَاتِكَ مِنْ حَقٍّ وَإِنَّكَ لَتَعْلَمُ مَا نُرِيدُ  [79]

(79) «ከሴቶች ልጆችህ ለእኛ ምንም ጉዳይ የለንም። አንተም የምንሻውን በእርግጥ ታውቃለህ» አሉት።

(79) They said, “You already know that we have no need for your daughters, and you surely know what we want!”

قَالَ لَوْ أَنَّ لِي بِكُمْ قُوَّةً أَوْ آوِي إِلَىٰ رُكْنٍ شَدِيدٍ  [80]

(80) «በእናንተ ላይ ለኔ ኀይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ብጠጋ ኖሮ (የምሠራውን በሠራሁ ነበር)» አላቸው።

(80) He said, “Would that I had some strength [to stop you] or could rely on a mighty support!”

قَالُوا يَا لُوطُ إِنَّا رُسُلُ رَبِّكَ لَن يَصِلُوا إِلَيْكَ ۖ فَأَسْرِ بِأَهْلِكَ بِقِطْعٍ مِّنَ اللَّيْلِ وَلَا يَلْتَفِتْ مِنكُمْ أَحَدٌ إِلَّا امْرَأَتَكَ ۖ إِنَّهُ مُصِيبُهَا مَا أَصَابَهُمْ ۚ إِنَّ مَوْعِدَهُمُ الصُّبْحُ ۚ أَلَيْسَ الصُّبْحُ بِقَرِيبٍ  [81]

(81) «ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልክተኞች ነን። (ሕዝቦችህ) ወደ አንተ (በክፉ) አይደርሱብህም። ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሊድ። ከእናንተም አንድም (ወደኋላው) አይገላመጥ። ሚስትህ ብቻ ስትቀር። እነሆ እርሷን (እነሱን) የሚያገኛቸው ስቃይ ያገኛታልና። ቀጠሯቸው እንጋቱ ላይ ነው። ንጋቱ ቅርብ አይደለምን» አሉት።

(81) [The angels said], “O Lot, we are messengers of your Lord; they can never reach you. So set out with your family in the dark part of night, and none of you should look back, except your wife; she will suffer the same fate as the others. Their appointed time is the morning; is not the morning near?”

فَلَمَّا جَاءَ أَمْرُنَا جَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهَا حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ مَّنضُودٍ  [82]

(82) |ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ (ከተማይቱን) ላይዋን ከታችዋ አደረግን (ገለበጥናት)። ተከታታይም የሆነን የሸክላ ድንጋይ በርሷ ላይ አዘነብን።

(82) When Our command came, We turned their cities upside down and rained down upon them clustered stones of baked clay,

مُّسَوَّمَةً عِندَ رَبِّكَ ۖ وَمَا هِيَ مِنَ الظَّالِمِينَ بِبَعِيدٍ  [83]

(83) ከጌታህ ዘንድ ምልክት የተደረገባት ስትሆን (አዘነብናት)። እርሷም ከበደለኞቹ ሩቅ አይደለችም።

(83) marked by your Lord; this is not far from the evildoers.

وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ وَلَا تَنقُصُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ ۚ إِنِّي أَرَاكُم بِخَيْرٍ وَإِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ مُّحِيطٍ  [84]

(84) ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን (ላክን)። አላቸው «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ። ከእርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም። ስፍርንና ሚዛንንም አታጉድሉ፤ እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ። እኔም በእናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።

(84) And to the people of Midian We sent their brother Shu‘ayb. He said, “O my people, worship Allah; you have no god besides Him. Do not give short measure or weight. I see that you are in prosperity, but I fear for you the punishment of an encompassing Day.

وَيَا قَوْمِ أَوْفُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ  [85]

(85) «ሕዝቦቼም ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ። ሰዎችንም ምንም ነገራቸውን አታጉድሉባቸው። በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ።

(85) O my people, give full measure and weight with justice, and do not defraud people of their dues, nor go about spreading corruption on earth.

بَقِيَّتُ اللَّهِ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ ۚ وَمَا أَنَا عَلَيْكُم بِحَفِيظٍ  [86]

(86) አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው። ምእመናን እንደሆናችሁ (አላህ በሰጣችሁ ውደዱ)። እኔም (መካሪ እንጅ) በናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም።»

(86) What remains from the provision of Allah is far better, if you are [true] believers; I am not a keeper over you.”

قَالُوا يَا شُعَيْبُ أَصَلَاتُكَ تَأْمُرُكَ أَن نَّتْرُكَ مَا يَعْبُدُ آبَاؤُنَا أَوْ أَن نَّفْعَلَ فِي أَمْوَالِنَا مَا نَشَاءُ ۖ إِنَّكَ لَأَنتَ الْحَلِيمُ الرَّشِيدُ  [87]

(87) «ሹዐይብ ሆይ! ስግደትህ አባቶቻችን የሚገዙትን ጣዖታት እንድንተው ወይም በገንዘቦቻችን የምንሻውን መሥራትን (እንድንተው) ታዝሃለችን አንተ በእርግጥ ታጋሹ ቅኑ አንተ ነህና» አሉት።

(87) They said, “O Shu‘ayb, does your prayer command you that we should forsake what our forefathers worshiped, or that we should give up dealing with our wealth as we please? Indeed, you are such a forbearing and right-minded man!”

قَالَ يَا قَوْمِ أَرَأَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّي وَرَزَقَنِي مِنْهُ رِزْقًا حَسَنًا ۚ وَمَا أُرِيدُ أَنْ أُخَالِفَكُمْ إِلَىٰ مَا أَنْهَاكُمْ عَنْهُ ۚ إِنْ أُرِيدُ إِلَّا الْإِصْلَاحَ مَا اسْتَطَعْتُ ۚ وَمَا تَوْفِيقِي إِلَّا بِاللَّهِ ۚ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ أُنِيبُ  [88]

(88) «ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ፤ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ብሆንና ከእርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ (በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን) ከእርሱ ወደ ከለከልኳችሁም ነገር ልለያችሁ አልሻም። በተቻለኝ ያክል ማበጀትን እንጂ አልሻም (ለደግ ሥራ) መገጠሜም በአላህ እንጂ በሌላ አይደለም። በእርሱ ላይ ተመካሁ። ወደእርሱም እመለሳለሁ፤» አላቸው።

(88) He said, “O my people, what do you think, if I should have a clear proof from my Lord, and He has given me good provision from Himself. I do not want to go against what I am forbidding you. I only want to put things right to the best of my ability. My success only comes through Allah; in Him I put my trust and to Him I turn.

وَيَا قَوْمِ لَا يَجْرِمَنَّكُمْ شِقَاقِي أَن يُصِيبَكُم مِّثْلُ مَا أَصَابَ قَوْمَ نُوحٍ أَوْ قَوْمَ هُودٍ أَوْ قَوْمَ صَالِحٍ ۚ وَمَا قَوْمُ لُوطٍ مِّنكُم بِبَعِيدٍ  [89]

(89) «ወገኖቼም ሆይ! እኔን መከራከራችሁ የኑሕን ሕዝቦች ወይም የሁድን ሕዝቦች ወይም የሷሊሕን ሕዝቦች ያገኛቸው (ቅጣት) ብጤ እንዲያገኛችሁ አይገፋፋችሁ። የሉጥም ሕዝቦች ከእናንተ ሩቅ አይደሉም።

(89) O my people, do not let your opposition to me cause you to suffer a punishment similar to that of the people of Noah, the people of Hūd or the people of Sālih. And the people of Lot are not far away from you.

وَاسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي رَحِيمٌ وَدُودٌ  [90]

(90) «ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት። ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ። ጌታዬ አዛኝ ወዳድ ነውና (አላቸው)።

(90) Seek forgiveness of your Lord and turn to Him in repentance. Indeed, My Lord is Most Merciful, Most Affectionate.”

قَالُوا يَا شُعَيْبُ مَا نَفْقَهُ كَثِيرًا مِّمَّا تَقُولُ وَإِنَّا لَنَرَاكَ فِينَا ضَعِيفًا ۖ وَلَوْلَا رَهْطُكَ لَرَجَمْنَاكَ ۖ وَمَا أَنتَ عَلَيْنَا بِعَزِيزٍ  [91]

(91) «ሹዐይብ ሆይ! ከምትለው ነገር ብዙውን አናውቀውም። እኛም አንተን በእኛ ውስጥ ደካማ ሆነህ እናይሃለን። ጎሳዎችህም ባልኖሩ ኖሮ በወገርንህ ነበር፤ አንተም በእኛ ላይ የተከበርክ አይደለህም» አሉት።

(91) They said, “O Shu‘ayb, we do not understand much of what you say, and we surely see you weak among us. Were it not for your clan, we would have surely stoned you, for you have no standing among us.”

قَالَ يَا قَوْمِ أَرَهْطِي أَعَزُّ عَلَيْكُم مِّنَ اللَّهِ وَاتَّخَذْتُمُوهُ وَرَاءَكُمْ ظِهْرِيًّا ۖ إِنَّ رَبِّي بِمَا تَعْمَلُونَ مُحِيطٌ  [92]

(92) «ሕዝቦቼ ሆይ! ጎሳዎቼ በእናንተ ላይ ከአላህ ይልቅ የከበሩ ናቸውን (አላህን) ከኋላችሁ ወደ ጀርባ አድርጋችሁም ያዛችሁት። ጌታዬ በምትሠሩት ሁሉ ከባቢ ነው» አላቸው።

(92) He said, “O my people, does my clan have a higher status to you than Allah? And you have abandoned Him behind your backs. Indeed, my Lord encompasses all what you do.

وَيَا قَوْمِ اعْمَلُوا عَلَىٰ مَكَانَتِكُمْ إِنِّي عَامِلٌ ۖ سَوْفَ تَعْلَمُونَ مَن يَأْتِيهِ عَذَابٌ يُخْزِيهِ وَمَنْ هُوَ كَاذِبٌ ۖ وَارْتَقِبُوا إِنِّي مَعَكُمْ رَقِيبٌ  [93]

(93) «ሕዝቦቼም ሆይ! በችሎታችሁ ልክ ሥሩ። እኔ ሠሪ ነኝና። የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትና እርሱ ውሸታም የሆነው ማን እንደኾነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ። ጠብቁም እኔ ከናንተ ጋር ተጠባባቂ ነኝና»(አላቸው)።

(93) O my people, do whatever you can; I will do mine. You will come to know who will receive a disgracing punishment, and who is a liar. Wait; I too am waiting with you.”

وَلَمَّا جَاءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا شُعَيْبًا وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَأَخَذَتِ الَّذِينَ ظَلَمُوا الصَّيْحَةُ فَأَصْبَحُوا فِي دِيَارِهِمْ جَاثِمِينَ  [94]

(94) ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሹዐይብንና እነዚያን ከርሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን። እነዚያን የበደሉትንም (የጂብሪል) ጩኸት ያዘቻቸው። በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አደሩ።

(94) When Our command came, We saved Shu‘ayb and those who believed with him by Our mercy. But the huge blast seized the wrongdoers, so they fell dead in their homes,

كَأَن لَّمْ يَغْنَوْا فِيهَا ۗ أَلَا بُعْدًا لِّمَدْيَنَ كَمَا بَعِدَتْ ثَمُودُ  [95]

(95) በእርሷ ውስጥ እንዳልነበሩ ሆኑ። ንቁ! ሰሙድ (ከአላህ እዝነት) እንደ ራቀች መድየንም ትራቅ።

(95) as if they had never dwelt there. Behold, away with Midian just as it was with Thamūd!

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِآيَاتِنَا وَسُلْطَانٍ مُّبِينٍ  [96]

(96) ሙሳንም በተዓምራታችንና በግልጽ ብርሃን በእርግጥ ላክነው።

(96) And We sent Moses with Our signs and compelling proof

إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِ فَاتَّبَعُوا أَمْرَ فِرْعَوْنَ ۖ وَمَا أَمْرُ فِرْعَوْنَ بِرَشِيدٍ  [97]

(97) ወደ ፈርዖንና ወደ ሰዎቹ (ላክነው)። የፈርዖንንም ነገር (ሕዝቦቹ) ተከተሉ። የፈርዖን ነገርም ቀጥተኛ አልነበረም።

(97) to Pharaoh and his courtiers, but they followed the command of Pharaoh, even though the command of Pharaoh was misguided.

يَقْدُمُ قَوْمَهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فَأَوْرَدَهُمُ النَّارَ ۖ وَبِئْسَ الْوِرْدُ الْمَوْرُودُ  [98]

(98) በትንሣኤ ቀን ሕዝቦቹን ይቀድማል። ወደ እሳትም ያወርዳቸዋል። የሚገቡትም አገባብ ምንኛ ከፋ!

(98) He will be at the forefront of his people on the Day of Resurrection, leading them into the Fire. What a terrible place to be led to!

وَأُتْبِعُوا فِي هَٰذِهِ لَعْنَةً وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ بِئْسَ الرِّفْدُ الْمَرْفُودُ  [99]

(99) በዚችም (በቅርቢቱ ዓለም) እርግማንን አስከተልናቸው። በትንሣኤም ቀን (እንደዚሁ)። የተሰጡት ስጦታ ምንኛ ከፋ!

(99) They were pursued by a curse in this world as well as on the Day of Resurrection. What a terrible gift to receive!

ذَٰلِكَ مِنْ أَنبَاءِ الْقُرَىٰ نَقُصُّهُ عَلَيْكَ ۖ مِنْهَا قَائِمٌ وَحَصِيدٌ  [100]

(100) ይህ (የተነገረው) ከከተሞቹ ወሬዎች ነው። ባንተ ላይ እንተርከዋለን። ከእርሷ ፋናው የቀረና ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ አለ።

(100) These are some of the stories of the towns that We relate to you; some are still standing, while others have been mowed down.

وَمَا ظَلَمْنَاهُمْ وَلَٰكِن ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ۖ فَمَا أَغْنَتْ عَنْهُمْ آلِهَتُهُمُ الَّتِي يَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مِن شَيْءٍ لَّمَّا جَاءَ أَمْرُ رَبِّكَ ۖ وَمَا زَادُوهُمْ غَيْرَ تَتْبِيبٍ  [101]

(101) እኛም አልበደልናቸውም። ግን ነፍሶቻቸውን በደሉ። የአላህም ትእዛዝ በመጣ ጊዜ እነዚያ ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸው አማልክቶቻቸው በምንም አላዳኗቸውም። ከማክሰርም በቀር ምንም አልጨመሩላቸውም።

(101) We did not wrong them, rather they wronged themselves. Their gods whom they invoked besides Allah were of no avail to them in the least when the command of your Lord came, and they only added to their destruction.

وَكَذَٰلِكَ أَخْذُ رَبِّكَ إِذَا أَخَذَ الْقُرَىٰ وَهِيَ ظَالِمَةٌ ۚ إِنَّ أَخْذَهُ أَلِيمٌ شَدِيدٌ  [102]

(102) የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው። ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው።

(102) Such is the seizing of your Lord when He seizes the towns that are given to wrongdoing; His seizing is surely painful and severe.

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّمَنْ خَافَ عَذَابَ الْآخِرَةِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّجْمُوعٌ لَّهُ النَّاسُ وَذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّشْهُودٌ  [103]

(103) በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ። ይህ (የትንሣኤ ቀን) ሰዎች በርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው። ይህም የሚጣዱት ቀን ነው።

(103) Indeed, there is a sign in this for those who fear the punishment of the Hereafter. That is a Day for which people will be gathered and a Day that will be witnessed.

وَمَا نُؤَخِّرُهُ إِلَّا لِأَجَلٍ مَّعْدُودٍ  [104]

(104) (ይህንን ቀን) ለተቆጠረም ጊዜ እንጂ አናቆየውም።

(104) We only delay it until a fixed term.

يَوْمَ يَأْتِ لَا تَكَلَّمُ نَفْسٌ إِلَّا بِإِذْنِهِ ۚ فَمِنْهُمْ شَقِيٌّ وَسَعِيدٌ  [105]

(105) በሚመጣ ቀን ማንኛዋም ነፍስ በእርሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትናገርም። ከነሱም መናጢና ዕድለኛም አልለ።

(105) When that Day comes, no one will speak except by His permission. Some among them will be wretched and others blissful.

فَأَمَّا الَّذِينَ شَقُوا فَفِي النَّارِ لَهُمْ فِيهَا زَفِيرٌ وَشَهِيقٌ  [106]

(106) እነዚያ መናጢ የሆኑትማ፡ በእሳት ውስጥ ናቸው። ለእነርሱ በእርሷ ውስጥ ማናፋትና መንሰቅሰቅ አላቸው።

(106) As for those who are wretched, they will be in the Fire, wherein they will be moaning and gasping,

خَالِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ إِلَّا مَا شَاءَ رَبُّكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ  [107]

(107) ጌታህ ከሻው (ጭማሬ) ሌላ ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውተሪዎች ሲኾኑ (በእሳት ይኖራሉ)። ጌታህ የሚሻውን ሠሪ ነውና።

(107) they will abide therein for as long as the heavens and earth exist, except what your Lord wills; your Lord does what He wills.

وَأَمَّا الَّذِينَ سُعِدُوا فَفِي الْجَنَّةِ خَالِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ إِلَّا مَا شَاءَ رَبُّكَ ۖ عَطَاءً غَيْرَ مَجْذُوذٍ  [108]

(108) እነዚያም ዕድለኞቹማ ጌታህ ከሻው (ጭማሬ) ሌላ ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ኾነው በገነት ውስጥ ይኖራሉ። የማይቋረጥ ስጦታን ተሰጡ።

(108) As for those who are destined for bliss, they will be in Paradise abiding therein as long as the heavens and earth exist, except what your Lord wills – an unceasing gift.

فَلَا تَكُ فِي مِرْيَةٍ مِّمَّا يَعْبُدُ هَٰؤُلَاءِ ۚ مَا يَعْبُدُونَ إِلَّا كَمَا يَعْبُدُ آبَاؤُهُم مِّن قَبْلُ ۚ وَإِنَّا لَمُوَفُّوهُمْ نَصِيبَهُمْ غَيْرَ مَنقُوصٍ  [109]

(109) እነዚህ (ከሓዲዎች) ከሚገዙት ጣዖት በመጠራጠር ውስጥ አትሁን፤ አባቶቻቸው ከዚህ በፊት እንደሚግገዙት እንጂ አይግገዙም። እኛም (እነዚህን) ፈንታቸውን የማይጓደል ሲሆን የምንሞላላቸው ነን።

(109) Have no doubt about what they worship; they only worship what their forefathers worshiped. We will surely give them their full share undiminished.

وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ فَاخْتُلِفَ فِيهِ ۚ وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيْنَهُمْ ۚ وَإِنَّهُمْ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ مُرِيبٍ  [110]

(110) ለሙሳም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው። በእርሱም ተለያዩበት። ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው (አሁን) ይፈረድ ነበር። እነሱም ከእርሱ (ከቁርኣን) አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ናቸው።

(110) We gave Moses the Scripture, but dispute arose about it. If it had not been for a prior decree from your Lord, the matter would have been decided between them. They are indeed in a disquieting doubt about it.

وَإِنَّ كُلًّا لَّمَّا لَيُوَفِّيَنَّهُمْ رَبُّكَ أَعْمَالَهُمْ ۚ إِنَّهُ بِمَا يَعْمَلُونَ خَبِيرٌ  [111]

(111) ሁሉንም ጌታህ ሥራዎቻቸውን (ምንዳቸውን) በእርግጥ ይሞላላቸዋል። እርሱ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነውና።

(111) Your Lord will surely pay everyone in full for their deeds, for He is All-Aware of what they do.

فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ  [112]

(112) እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል። ከአንተ ጋር ያመኑትም (ቀጥ ይበሉ)። ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና።

(112) So stay on a straight path as you have been commanded, along with those who repented with you, and do not cross the limits. Indeed, He is All-Seeing of what you do.

وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ  [113]

(113) ወደእነዚያም ወደ በደሉት አትጠጉ። እሳት ትነካችኋለችና። ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም። ከዚያም አትረድዱም።

(113) Do not incline to the wrongdoers, or else the Fire will seize you. Then you will have no protectors besides Allah, nor will you be helped.

وَأَقِمِ الصَّلَاةَ طَرَفَيِ النَّهَارِ وَزُلَفًا مِّنَ اللَّيْلِ ۚ إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ ۚ ذَٰلِكَ ذِكْرَىٰ لِلذَّاكِرِينَ  [114]

(114) ሶላትንም በቀን ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም። መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወገድዳሉና። ይህ ለተገሳጮች ግሳጼ ነው።

(114) Establish prayer at the two ends of the day and in some hours of the night. Indeed, good deeds wipe out evil deeds. This is a reminder for those who are mindful.

وَاصْبِرْ فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ الْمُحْسِنِينَ  [115]

(115) ታገስም፤ አላህ የበጎ ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና።

(115) And be patient, for indeed Allah does not let the reward of those who do good to go to waste.

فَلَوْلَا كَانَ مِنَ الْقُرُونِ مِن قَبْلِكُمْ أُولُو بَقِيَّةٍ يَنْهَوْنَ عَنِ الْفَسَادِ فِي الْأَرْضِ إِلَّا قَلِيلًا مِّمَّنْ أَنجَيْنَا مِنْهُمْ ۗ وَاتَّبَعَ الَّذِينَ ظَلَمُوا مَا أُتْرِفُوا فِيهِ وَكَانُوا مُجْرِمِينَ  [116]

(116) ከእናንተም በፊት ከነበሩት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ውስጥ በምድር ላይ ከማበላሸት የሚከለክሉ የመልካም ቀሪ ሥራዎች ባለቤቶች ለምን አልነበሩም ግን ከእነሱ ያዳንናቸው ጥቂቶቹ (ከለከሉና ዳኑ)። እነዚያም የበደሉት ሰዎች (አልከለከሉም)። በእርሱ የተቀማጠሉበትን ተድላ ተከተሉ። አመጸኞችም ነበሩ።

(116) If only there had been among the generations before you righteous people who would forbid others from spreading corruption in the land, except a few of them whom We saved. But the wrongdoers pursued their luxury which they were given therein, and they were wicked.

وَمَا كَانَ رَبُّكَ لِيُهْلِكَ الْقُرَىٰ بِظُلْمٍ وَأَهْلُهَا مُصْلِحُونَ  [117]

(117) ጌታህም ከተሞችን ባለቤቶቻቸው መልካም ሠሪዎች ሆነው ሳሉ በመበደል የሚያጠፋቸው አልነበረም።

(117) Your Lord would never destroy the towns unjustly while their people were acting righteously.

وَلَوْ شَاءَ رَبُّكَ لَجَعَلَ النَّاسَ أُمَّةً وَاحِدَةً ۖ وَلَا يَزَالُونَ مُخْتَلِفِينَ  [118]

(118) ጌታህም በሻ ኖሮ ሰዎችን ሁሉ አንድ ሕዝብ ባደረጋቸው ነበር። የተለያዩም ከመሆን አይወገዱም።

(118) If your Lord had willed, He could have made mankind a single community, but they will not cease to differ,

إِلَّا مَن رَّحِمَ رَبُّكَ ۚ وَلِذَٰلِكَ خَلَقَهُمْ ۗ وَتَمَّتْ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ  [119]

(119) ጌታህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር፤ (ከመለያየት አይወገዱም)። ለዚሁም ፈጠራቸው። የጌታህም ቃል ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ በማለት ተፈጸመች።

(119) except those whom Allah has given mercy, and for this He created them, and the word of your Lord will be fulfilled: “I will certainly fill Hell with jinn and humans all together.”

وَكُلًّا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ الرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِ فُؤَادَكَ ۚ وَجَاءَكَ فِي هَٰذِهِ الْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ  [120]

(120) ከመልክተኞቹም ዜናዎች (ተፈላጊውን) ሁሉንም ልብህን በርሱ የምናረካበትን እንተርክልሃለን። በዚህችም (ሱራ) እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሃል።

(120) We relate to you [O Prophet] the stories of the messengers to strengthen your heart. And there has come to you in this the truth, an admonition and a reminder to the believers.

وَقُل لِّلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ اعْمَلُوا عَلَىٰ مَكَانَتِكُمْ إِنَّا عَامِلُونَ  [121]

(121) ለእነዚያም ለማያምኑት ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሥሩ፤ እኛ ሠሪዎች ነንና በላቸው።

(121) Say to those who do not believe, “Carry on in your ways; so will we do.

وَانتَظِرُوا إِنَّا مُنتَظِرُونَ  [122]

(122) ተጠባበቁም እኛ ተጠባባቂዎች ነንና (በላቸው)።

(122) And wait; we too are waiting.”

وَلِلَّهِ غَيْبُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَإِلَيْهِ يُرْجَعُ الْأَمْرُ كُلُّهُ فَاعْبُدْهُ وَتَوَكَّلْ عَلَيْهِ ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ  [123]

(123) በሰማያትና በምድርም ያለው ምስጢር ሁሉ የአላህ ነው። ነገሩ ሁሉም ወደርሱ ይመለሳል። ስለዚህ ተገዛው። በእርሱም ላይ ተጠጋ። ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም።

(123) To Allah belongs the unseen of the heavens and earth, and to Him will return all matters. So worship Him and put your trust in Him, for your Lord is not unaware of what you do.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

45 – Al-Jaathiya

                                45 – Al-Jaathiya (1) ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ (1) Hā Mīm. (2) የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ነው፡፡ (2) The…

20 – Taa-Haa 

(1) ጠ.ሀ. (ጣ ሃ) (1) Tā Ha (2) ቁርኣንን ባንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም፡፡ (2) We have not sent down the Qur’an…

23 – Al-Muminoon

23 – Al-Muminoon (1) ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡ (1) The believers have attained true success: (2) እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው…