Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ተውባህ (የንስሐ ምዕራፍ)
9:1
(ይህች) ከአላህና ከመልክተኛው ወደነዚያ ቃል ኪዳን ወደ ተጋባችኋቸዉ አጋሪዎች የምትደርስ ንጽሕና ናት።

[This is a declaration of] disassociation, from Allah and His Messenger, to those with whom you had made a treaty among the polytheists.

9:2
በምድር ላይም አራት ወሮችን (ጸጥተኞች ስትሆኑ)ኺዱ፤ እናንተም ከአላህ (ቅጣት) የማታመልጡ መሆናችሁንና አላህም ከሐዲዎችን አዋራጅ መሆኑን ዕወቁ፤ (በሏቸዉ)።

So travel freely, [O disbelievers], throughout the land [during] four months but know that you cannot cause failure to Allah and that Allah will disgrace the disbelievers.

9:3
(ይህ) ከአላህና ከመልክተኛዉ በታላቁ ሐጅ ቀን የወጣ አላህ ከአጋሪዎቹ ንጹሕ ነው፣ መልክተኛዉም (እንደዚሁ)፤ (ከክሕደት) ብትጸጸቱም እርሱ ለናንተ በላጭ ነዉ (ከእምነት) ብትሸሹም እናንተ አላህን የማታቅቱት መሆናችሁን ዕወቁ፤ በማለት ወደ ሰዎች የሚያደርስ ማስታወቂያ ነው፤ (*) እነዚያን የካዱትንም በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው።
* ከዚህ ዓመት በኋላ ከሐዲ ከዕባን አይጎበኝም ራቁቱንም አይዞርም


And [it is] an announcement from Allah and His Messenger to the people on the day of the greater pilgrimage that Allah is disassociated from the disbelievers, and [so is] His Messenger. So if you repent, that is best for you; but if you turn away - then know that you will not cause failure to Allah . And give tidings to those who disbelieve of a painful punishment.

9:4
ከአጋሪዎቹ እነዚያ ቃል ኪዳን የተጋባችኋቸዉና ከዚያም ምንም ያላጎደሉባችሁ በናንተ ላይም አንድንም ያልረዱባችሁ ሲቀሩ፤ (እነዚህን) ቃል ኪዳናቸዉን እስከ ጊዚያታቸዉ (መጨረሻ) ሙሉላቸዉ፤ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና።

Excepted are those with whom you made a treaty among the polytheists and then they have not been deficient toward you in anything or supported anyone against you; so complete for them their treaty until their term [has ended]. Indeed, Allah loves the righteous [who fear Him].

9:5
የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ሰፍራ ግደሉዋቸዉ፤ ያዙዋቸዉም፤ ክበቡዋቸውም፤ ለነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ፤ ቢጸጸቱም፤ ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ፣ መንገዳቸውን ልቀቁላቸዉ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።

And when the sacred months have passed, then kill the polytheists wherever you find them and capture them and besiege them and sit in wait for them at every place of ambush. But if they should repent, establish prayer, and give zakah, let them [go] on their way. Indeed, Allah is Forgiving and Merciful.

9:6
ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፤ ከዚያም ወደ መጠበቂያዉ ስፍራ አድርሰው፤ ይህ እነሱ የማያዉቁ ሕዝቦች በመሆናቸው ነው።

And if any one of the polytheists seeks your protection, then grant him protection so that he may hear the words of Allah . Then deliver him to his place of safety. That is because they are a people who do not know.

9:7
ለአጋሪዎቹ አላህ ዘንድና እመልክተኛው ዘንድ ቃል ኪዳን እንዴት ይኖራቸዋል? እነዚያ በተከበረዉ መስጊድ ዘንድ ኪዳን የተገባችኋቸዉ ብቻ (*) ሲቀሩ (እነዚህ) በኪዳናቸዉ ለናንተ ቀጥ እስካሉላቸሁ ድረስ ለነርሱም ቀጥ በሉላቸዉ፤ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና።
* በኒ ዶምራ


How can there be for the polytheists a treaty in the sight of Allah and with His Messenger, except for those with whom you made a treaty at al-Masjid al-Haram? So as long as they are upright toward you, be upright toward them. Indeed, Allah loves the righteous [who fear Him].

9:8
በናንተ ላይ ቢያይሉም በናንተ ዉስጥ ዝምድናንና ቃል ኪዳንን የማይጠብቁ ሲሆኑ እንዴት? (ቃል ኪዳን ይኖራቸዋል)፣ በአፎቻቸው ያስወድዷችኋል፤ እንቢ ይላሉ፤ አብዛኞቻቸውም አመጠኞች ናቸው።

How [can there be a treaty] while, if they gain dominance over you, they do not observe concerning you any pact of kinship or covenant of protection? They satisfy you with their mouths, but their hearts refuse [compliance], and most of them are defiantly disobedient.

9:9
በአላህ አንቀጾች ጥቂትን ዋጋ ገዙ፤ ከመንገዱም አገዱ፤ እነርሱ ይሠሩት የነበሩት ሥራ ከፋ!

They have exchanged the signs of Allah for a small price and averted [people] from His way. Indeed, it was evil that they were doing.

9:10
በምእምን ነገር ዝምድናንም ኪዳንንም አይጠብቁም፤ እነዚያም እነሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው።

They do not observe toward a believer any pact of kinship or covenant of protection. And it is they who are the transgressors.

9:11
ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ ዘካንም ቢሰጡ፣ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው፤ ለሚያዉቁ ሕዝቦችም አንቀጾችን እናብራራለን።

But if they repent, establish prayer, and give zakah, then they are your brothers in religion; and We detail the verses for a people who know.

9:12
ከቃል ኪዳናቸው በኋላ መሐላዎቻቸውን ቢያፈርሱ ሃይማኖታቸሁንም ቢያነውሩ፣ የክሕደት መሪዎችን (ከክሕደት) ይከለከሉ ዘንድ ተዋጉዋቸው፤ እነርሱ ቃል ኪዳን የላቸውምና።

And if they break their oaths after their treaty and defame your religion, then fight the leaders of disbelief, for indeed, there are no oaths [sacred] to them; [fight them that] they might cease.

9:13
መሐላዎቻቸዉን ያፈረሱትን መልክተኛዉንም ለማዉጣት ያሰቡትን ሕዝቦች እነሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመሩዋችሁ ሲሆኑ ለምን አትዋጉዋቸውም፤ ትፈሩዋቸዋላችሁን? ምእምናን እንደ ሆናችሁም አላህ ይበልጥ ልትፈሩት የተገባዉ ነው።

Would you not fight a people who broke their oaths and determined to expel the Messenger, and they had begun [the attack upon] you the first time? Do you fear them? But Allah has more right that you should fear Him, if you are [truly] believers.

9:14
ተጋደሉዋቸዉ፤ አላህ በእጆቻችሁ ያሰቃያቸዋል፤ ያዋርዳቸዋልም፤ በነሱም ላይ ይረዳችኋል፤ የምእምናን ሕዝቦችንም ልቦች ያሽራል።

Fight them; Allah will punish them by your hands and will disgrace them and give you victory over them and satisfy the breasts of a believing people

9:15
የልቦቻችሁንም ቁጭት ያስወግዳል፤ አላህም ከሚሻው ሰዉ ላይ ጸጸትን ይቀበላል፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።

And remove the fury in the believers' hearts. And Allah turns in forgiveness to whom He wills; and Allah is Knowing and Wise.

9:16
እነዚያን ከናንተ ውስጥ የታገሉትንና ከአላህም ከመልክተኛውም ከምእምናንም ሌላ ምስጢረኛ ወደጅ ያልያዙትን አላህ ሳይገልጽ፣ ልትተዉ ታስባላችሁን? አላህን በምትሠሩት ሁሉ ዉስጠ ዐዋቂ ነው።

Do you think that you will be left [as you are] while Allah has not yet made evident those among you who strive [for His cause] and do not take other than Allah , His Messenger and the believers as intimates? And Allah is Acquainted with what you do.

9:17
ለከሐዲዎች፣ በነፍሶቻቸዉ ላይ በክሕደት የሚመሰክሩ ሲሆኑ፣ የአላህን መስጊዶች ሊሠሩ አይገባቸውም፤ እነዚያ ሥራዎቻቸዉ ተበላሹ እነሱም በእሳት ዉስጥ ዘውታሪዎች ናቸዉ።

It is not for the polytheists to maintain the mosques of Allah [while] witnessing against themselves with disbelief. [For] those, their deeds have become worthless, and in the Fire they will abide eternally.

9:18
የአላህን መስጊዶች የሚሠራዉ፤ በአላህና በመጨረሻዉ ቀን ያመነ፣ ሶላትንም በደንቡ የሰገደ፣ ግዴታ ምጽዋትንም የሰጠ፣ ከአላህም ሌላ (ማንንም) ያልፈራ ሰው ብቻ ነዉ፤ እነዚያም ከተመሩት ጭምር መሆናቸዉ ተረጋገጠ።

The mosques of Allah are only to be maintained by those who believe in Allah and the Last Day and establish prayer and give zakah and do not fear except Allah , for it is expected that those will be of the [rightly] guided.

9:19
ካዕባን ጎብኝዎችን ማጠጣትንና የተከበረዉን መስጊድ መሥራትን፣ በአላህና በመጨረሻዉ ቀን እንዳመነና በአላህ መንገድ እንደታገለ ሰው (እምነትና ትግል) አደረጋችሁን? አላህ ዘንድ አይተካከሉም፤ አላህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም።

Have you made the providing of water for the pilgrim and the maintenance of al-Masjid al-Haram equal to [the deeds of] one who believes in Allah and the Last Day and strives in the cause of Allah ? They are not equal in the sight of Allah . And Allah does not guide the wrongdoing people.

9:20
እነዚያ ያመኑት ከአገራቸዉም የተሰደዱት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸዉም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው፤ እነዚያም እነሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው።

The ones who have believed, emigrated and striven in the cause of Allah with their wealth and their lives are greater in rank in the sight of Allah . And it is those who are the attainers [of success].

9:21
ጌታቸዉ ከርሱ በሆነው እዝነትና ዉዴታ በገነቶችም ለነሱ በዉስጥዋ የማያቋርጥ መጠቀሚያ ያለባት ስትሆን ያበስራቸዋል።

Their Lord gives them good tidings of mercy from Him and approval and of gardens for them wherein is enduring pleasure.

9:22
በዉስጧ ዘላለም ዘዉታሪዎች ሲሆኑ፣ (ያበስራቸዋል)፤ አላህ እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለና።

[They will be] abiding therein forever. Indeed, Allah has with Him a great reward.

9:23
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክሕደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ፣ ወዳጆች አድርጋቸሁ አትያዙዋቸው፤ ከናንተም ዉስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው፣ እነዚያ እርሱ በዳዮች ናቸው፤

O you who have believed, do not take your fathers or your brothers as allies if they have preferred disbelief over belief. And whoever does so among you - then it is those who are the wrongdoers.

9:24
፦ አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣ የሰበሰባችኋቸዉ ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛዉ በርሱ መንገድም ከመታገል፣ ይበልጥ የተወደዱ እንደሆኑ፣ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ፣ በላቸው፤ አላህም አመጠኞች ሕዝቦችን አይመራም።

Say, [O Muhammad], "If your fathers, your sons, your brothers, your wives, your relatives, wealth which you have obtained, commerce wherein you fear decline, and dwellings with which you are pleased are more beloved to you than Allah and His Messenger and jihad in His cause, then wait until Allah executes His command. And Allah does not guide the defiantly disobedient people."

9:25
አላህም በብዙ ስፍራዎች በእርግጥ ረዳችሁ፤ የሑነይንም ቀን ብዛታችሁ በአስደነቀቻችሁና ከናንተም ምንም ባልጠቀመቻችሁ ጊዜ ምድርም ከስፋቷ ጋር በጠበበቻችሁና ከዚያም ተሸናፊዎች ሆናችሁ በዞራችሁ ጊዜ፣ (ረዳችሁ)።

Allah has already given you victory in many regions and [even] on the day of Hunayn, when your great number pleased you, but it did not avail you at all, and the earth was confining for you with its vastness; then you turned back, fleeing.

9:26
ከዚያም አላህ እርጋታውን በመልክተኛውና በምእምናኖቹ ላይ አወረደ፤ ያላያችኋቸዉንም ሰራዊት አወረደ፤ እነዚያን የካዱትንም በመግደልና በመማረክ አሰቃየ፤ ይህም የከሐዲያን ፍዳ ነው።

Then Allah sent down His tranquillity upon His Messenger and upon the believers and sent down soldiers angels whom you did not see and punished those who disbelieved. And that is the recompense of the disbelievers.

9:27
ከዚያም ከዚህ በኋላ አላህ በሚሻዉ ሰው ላይ ጸጸትን ይቀበላል፣ አላህም እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው።

Then Allah will accept repentance after that for whom He wills; and Allah is Forgiving and Merciful.

9:28
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች፣ እርኩሶች ብቻ ናቸዉ፤ ከዚህም ዓመታቸዉ (*) በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ፤ ድኽነትንም ብትፈሩ አላህ ቢሻ ከችሮታዉ በእርግጥ ያከብራችኋል አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነዉና።
* ዘጠነኛ ዓመተ ስደት


O you who have believed, indeed the polytheists are unclean, so let them not approach al-Masjid al-Haram after this, their [final] year. And if you fear privation, Allah will enrich you from His bounty if He wills. Indeed, Allah is Knowing and Wise.

9:29
ከነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ሰዎች፣ እነዚያን በአላህ በመጨረሻዉ ቀን የማያምኑትን፣ አላህና መልክተኛዉ እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትንና እዉነተኛዉንም ሃይማኖት የማይቀበሉትን እነርሱ የተዋረዱ ሆነዉ ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጉዋቸው።

Fight those who do not believe in Allah or in the Last Day and who do not consider unlawful what Allah and His Messenger have made unlawful and who do not adopt the religion of truth from those who were given the Scripture - [fight] until they give the jizyah willingly while they are humbled.

9:30
አይሁድ ዑዘይር የአላህ ልጅ ነዉ፣ አላችሁ፤ ክርስቲያኖችም አልመሲሕ የአላህ ልጅ ነዉ አሉ፤ ይህ በአፎቻቸዉ (የሚናገሩት) ቃላቸው ነው፤ የነዚያን ከነሱ በፊት የካዱትን ሰዎች ቃል ያመሳስላሉ፤ አላህ ያጥፋቸዉ (ከእዉነት) እንዴት ይመለሳሉ!

The Jews say, "Ezra is the son of Allah "; and the Christians say, "The Messiah is the son of Allah ." That is their statement from their mouths; they imitate the saying of those who disbelieved [before them]. May Allah destroy them; how are they deluded?

9:31
ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለዉን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፤ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው።

They have taken their scholars and monks as lords besides Allah , and [also] the Messiah, the son of Mary. And they were not commanded except to worship one God; there is no deity except Him. Exalted is He above whatever they associate with Him.

9:32
የአላህን ብርሃን በአፎቻቸዉ ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህም ከሐዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መምላትን እንጂ ሌላን አይሻም።

They want to extinguish the light of Allah with their mouths, but Allah refuses except to perfect His light, although the disbelievers dislike it.

9:33
እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛዉን (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነዉ።

It is He who has sent His Messenger with guidance and the religion of truth to manifest it over all religion, although they who associate others with Allah dislike it.

9:34
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሊቃዉንትና ከመነኮሳት ብዙዎቹ የሰዎችን ገንዘቦች በዉሸት በእርግጥ ይበላሉ፤ ከአላህም መንገድ ያግዳሉ፤ እነዚያንም ወርቅንና ብርን የሚያደልቡትን በአላህም መንገድ ላይ የማያወጧትን በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው።

O you who have believed, indeed many of the scholars and the monks devour the wealth of people unjustly and avert [them] from the way of Allah . And those who hoard gold and silver and spend it not in the way of Allah - give them tidings of a painful punishment.

9:35
በርሷ ላይ በገሀነም እሳት ዉስጥ በሚጋልባትና ግንባሮቻቸውም ጎኖቻቸውም፣ ጀርባዎቻቸዉም፣ በርሷ በሚተኮሱ ቀን፣ (አሳማሚ በሆነ ቅጣት አብስራቸው)፤ ይህ ለነፍሶቻችሁ ያደለባችሁት ነው ታደልቡት የነበራችሁትንም ቅመሱ (ይባላሉ)።

The Day when it will be heated in the fire of Hell and seared therewith will be their foreheads, their flanks, and their backs, [it will be said], "This is what you hoarded for yourselves, so taste what you used to hoard."

9:36
የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ዉስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፤ ከነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፤ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፤ በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፤ አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ሆነው እንደሚዋጉዋቸሁ በአንድ ላይ ሆናችሁ ተጋደሉዋቸው፤ አላህም ከሚፈሩት ጋር መሆኑን ዕወቁ።

Indeed, the number of months with Allah is twelve [lunar] months in the register of Allah [from] the day He created the heavens and the earth; of these, four are sacred. That is the correct religion, so do not wrong yourselves during them. And fight against the disbelievers collectively as they fight against you collectively. And know that Allah is with the righteous [who fear Him].

9:37
የአንዱን ወር ክብር ወደ ሌላው ማዘግየት በክሕደት ላይ (ክሕደትን)መጨመር ብቻ ነው፤ በርሱ እነዚያ የካዱት ሰዎች ይሳሳቱበታል፤ በአንድ ዓመት የተፈቀደ ያደርጉታል፤ በሌላው ዓመትም ያወግዙታል፤ (ይህ) አላህ ያከበራቸውን ወሮች ቁጥር ሊያስተካክሉ አላህም እርም ያደረገውን የተፈቀደ ሊያደርጉ ነዉ፤ የሥራዎቻቸዉ መጥፎዉ ለነርሱ ተዋበላቸው፤ አላህም ከሐዲያን ሕዝቦችን አይመራም።

Indeed, the postponing [of restriction within sacred months] is an increase in disbelief by which those who have disbelieved are led [further] astray. They make it lawful one year and unlawful another year to correspond to the number made unlawful by Allah and [thus] make lawful what Allah has made unlawful. Made pleasing to them is the evil of their deeds; and Allah does not guide the disbelieving people.

9:38
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ (ለመታገል) ዉጡ በተባለችሁ ጊዜ ወደ ምድር የምትወዘፉት፣ ለእናንተ ምን አላችሁ? የቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ ይበልጥ ወደዳችሁን? የቅርቢቱም ሕይወት ጥቅም በመጨረሻይቱ (አንጻር) ጥቂት እንጂ አይደለም።

O you who have believed, what is [the matter] with you that, when you are told to go forth in the cause of Allah , you adhere heavily to the earth? Are you satisfied with the life of this world rather than the Hereafter? But what is the enjoyment of worldly life compared to the Hereafter except a [very] little.

9:39
ለዘመቻ ባትወጡ (አላህ) አሳማሚን ቅጣት ይቀጣችኋል፤ ከናንተ ሌላ የሆኑንም ሕዝቦች ይለዉጣል በምንም አትጎዱትምም፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነዉ።

If you do not go forth, He will punish you with a painful punishment and will replace you with another people, and you will not harm Him at all. And Allah is over all things competent.

9:40
(ነቢዩን) ባትረዱት እነዚያ የካዱት ሕዝቦች የሁለት (ሰዎች) ሁለተኛ ሆኖ (ከመካ) ባወጡት ጊዜ አላህ በእርግጥ ረድቶታል ሁለቱም በዋሻዉ ሳሉ ለጓደኛዉ ነዉና ባለ ጊዜ አላህ እርካታዉን በርሱ ላይ አወረደ፤ ባላያችኋቸዉም ሰራዊት አበረታው፤ የነዚያንም የካዱትን ሰዎች ቃል ዝቅተኛ አደረገ፤ የአላህም ቃል እርሷ ከፍተኛ ናት፤ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።

If you do not aid the Prophet - Allah has already aided him when those who disbelieved had driven him out [of Makkah] as one of two, when they were in the cave and he said to his companion, "Do not grieve; indeed Allah is with us." And Allah sent down his tranquillity upon him and supported him with angels you did not see and made the word of those who disbelieved the lowest, while the word of Allah - that is the highest. And Allah is Exalted in Might and Wise.

9:41
ቀላሎችም ከባዶችም ሆናችሁ ዝመቱ፤ በአላህም መንገድ በገንዘቦቻችሁ በነፍሶቻችሁም ታገሉ፤ ይሃችሁ የምታዉቁ ብትሆኑ ለናንተ በጣም የተሻለ ነው።

Go forth, whether light or heavy, and strive with your wealth and your lives in the cause of Allah . That is better for you, if you only knew.

9:42
(የጠራህባቸዉ ነገር) ቅርብ ጥቅምና መካከለኛ ጉዞ በሆነ ኖሮ፣ በተከተሉህ ነበር ግን በነሱ ላይ መንገዲቱ ራቀችባቸዉ፤ በቻልንም ኖሮ ከናንተ ጋር በወጣን ነበር ሲሉ በአላህ ይምላሉ፤ ነፍሶቻቸዉን ያጠፋሉ፤ አላህም እነሱ ዉሸታሞች መሆናቸዉን በእርግጥ ያዉቃል።

Had it been an easy gain and a moderate trip, the hypocrites would have followed you, but distant to them was the journey. And they will swear by Allah , "If we were able, we would have gone forth with you," destroying themselves [through false oaths], and Allah knows that indeed they are liars.

9:43
አላህ ከአንተ ይቅር አለ፤ እነዚያ እዉነተኛዎች ላንተ እስከሚገለጹልህና ዉሸታሞቹንም እስከምታዉቅ ድረስ ለነርሱ (እንዲቀሩ) ለምን ፈቀድክላቸዉ?

May Allah pardon you, [O Muhammad]; why did you give them permission [to remain behind]? [You should not have] until it was evident to you who were truthful and you knew [who were] the liars.

9:44
እነዚያ በአላህና በመጨረሻዉ ቀን የሚያምኑት በገንዘቦቻቸዉና በነፍሶቻቸው ከመታገላቸው (ለመቅረት) ፈቃድን አይጠይቁህም፤ አላህም የሚፈሩትን ዐዋቂ ነው።

Those who believe in Allah and the Last Day would not ask permission of you to be excused from striving with their wealth and their lives. And Allah is Knowing of those who fear Him.

9:45
ፈቃድን የሚጠይቁህ እነዚያ በአላህና በመጨረሻዉ ቀን የማያምኑት ልቦቻቸዉም የተጠራጠሩት ብቻ ናቸው፤ እነሱም በጥረጣሬያቸው ዉስጥ ይዋልላሉ።

Only those would ask permission of you who do not believe in Allah and the Last Day and whose hearts have doubted, and they, in their doubt, are hesitating.

9:46
መዉጣትንም ባሰቡ ኖሮ ለርሱ ዝግጅትን ባሰናዱ ነበር፤ ግን አላህ (ለመዉጣት) እንቅስቃሴያቸዉ ጠላ፤ (አልሻውም)፤ አሰነፋቸውም፤ ከተቀማጮቹም ጋር (*)ተቀመጡ ተባሉ።
* ከሕፃናትና ከሴቶች ጋር።


And if they had intended to go forth, they would have prepared for it [some] preparation. But Allah disliked their being sent, so He kept them back, and they were told, "Remain [behind] with those who remain."

9:47
ከናንተ ጋር በወጡ ኖሮ ጥፋትን እንጂ አይጨምሩላችሁም ነበር፤ እውከትንም የሚፈልጉላችሁ ሲሆን በመካከላችሁ (በማሳበቅ) ይቻኮሉ ነበር በናንተም ዉስጥ ለነሱ አዳማጮች አሏቸው አላህም በዳዮችን ዐዋቂ ነው።

Had they gone forth with you, they would not have increased you except in confusion, and they would have been active among you, seeking [to cause] you fitnah. And among you are avid listeners to them. And Allah is Knowing of the wrongdoers.

9:48
እነርሱ ጠይዎች ሲሆኑ እውነቱ እስከመጣና የአላህም ትእዛዝ እስከ ተገለጸ ድረስ ከዚህ በፊት እዉከትን በእርግጥ ፈለጉ ነገሮችንም ሁሉ አገላበጡልህ።(*)
* መከሩብህ


They had already desired dissension before and had upset matters for you until the truth came and the ordinance of Allah appeared, while they were averse.

9:49
ከነሱም ዉስጥ ለኔ ፍቀድልኝ አትሞክረኝም የሚል ሰው አለ ንቁ በመከራ ዉስጥ ወደቁ፤ ገሀነምም ከሐዲዎችን በእርግጥ ከባቢ ናት።

And among them is he who says, "Permit me [to remain at home] and do not put me to trial." Unquestionably, into trial they have fallen. And indeed, Hell will encompass the disbelievers.

9:50
መልካም ነገር ብታገኝህ ታስከፋቸዋለች፤ መከራም ብታገኝህ ከዚህ በፊት በእርግጥ ጥንቃቄያችንን ይዘናል ይላሉ እነርሱም ተደሳቾች ሆነው ይሸሻሉ።

If good befalls you, it distresses them; but if disaster strikes you, they say, "We took our matter [in hand] before," and turn away while they are rejoicing.

9:51
አላህ ለኛ የጻፈልን (ጥቅም) እንጂ ሌላ አይነካንም እርሱ ረዳታችን ነው በአላህ ላይም ምእምናን ይመኩ በላቸዉ።

Say, "Never will we be struck except by what Allah has decreed for us; He is our protector." And upon Allah let the believers rely.

9:52
በኛ ላይ ከሁለቱ መልካሞች (*) አንደኛዋን እንጂ ሌላን ትጠባበቃላችሁን? እኛም አላህ ከርሱ በሆነው ቅጣት ወይም በእጆቻችን የሚያጠፋችሁ መሆኑን በናንተ ላይ እንጠባበቃለ፤ ተተባበቁም፤ እኛ ከናንተ ጋር ተጠባባቂዎች ነንና በላቸዉ።
* ድል ከመንሳትና ከሰማዕትነት


Say, "Do you await for us except one of the two best things while we await for you that Allah will afflict you with punishment from Himself or at our hands? So wait; indeed we, along with you, are waiting."

9:53
ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ለግሱ ከናንተ ተቀባይ የላችሁም እናንተ አመጠኞች ሕዝቦች ናችሁና በላቸዉ።

Say, "Spend willingly or unwillingly; never will it be accepted from you. Indeed, you have been a defiantly disobedient people."

9:54
ልግስናዎቻቸውን ከነሱ ተቀባይ የሚያገኙ ከመሆን እነሱ በአላህና በመልክተኛዉ የካዱ ሶላትንም እነሱ ታካቾች ሆነው በስተቀር የማይሰግዱ እነሱም ጠይዎች ሆነው በስተቀር የማይሰጡ መሆናቸዉ እንጂ ሌላ አልከለከላቸውም።

And what prevents their expenditures from being accepted from them but that they have disbelieved in Allah and in His Messenger and that they come not to prayer except while they are lazy and that they do not spend except while they are unwilling.

9:55
ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸውም አይድነቁህ፤ አላህ የሚሻው በቅርቢቱ ሕይወት በነርሱ (በገንዘቦቻቸዉና በልጆቻቸው) ሊቀጣቸው ነፍሶቻቸዉም እነሱ ከሐዲዎች ሆነዉ ሊወጡ ብቻ ነው።

So let not their wealth or their children impress you. Allah only intends to punish them through them in worldly life and that their souls should depart [at death] while they are disbelievers.

9:56
እነሱም በእርግጥ ከናንተ ለመሆናቸው በአላህ ይምላሉ፤ እነርሱም ከናንተ አይደሉም፤ ግን እነሱ (አጋሪዎችን ያገኘ እንዳያገኛቸዉ) የሚፈሩ ሕዝቦች ናቸው።

And they swear by Allah that they are from among you while they are not from among you; but they are a people who are afraid.

9:57
መጠጊያን ወይም ዋሻዎችን ወይም መግቢያን (ቀዳዳ) ባገኙ ኖሮ እነርሱ እየገሠገሡ ወደርሱ በሸሹ ነበር።

If they could find a refuge or some caves or any place to enter [and hide], they would turn to it while they run heedlessly.

9:58
ከነሱም ዉስጥ በምጽዋቶች የሚዘልፉህ ሰዎች አሉ። ከርሷም (የሚሹትን) ቢስሰጡ ይደሰታሉ፤ ከርሷም ባይስሰጡ እነሱ ያን ጊዜ ይጠላሉ።

And among them are some who criticize you concerning the [distribution of] charities. If they are given from them, they approve; but if they are not given from them, at once they become angry.

9:59
እነሱም አላህና መልክተኛዉ የሰጣቸዉን በወደዱ አላህም በቂያችን ነው አላህ ከችሮታው በእርግጥ ይሰጠናል መልክተኛውም (ይሰጠናል) እኛ ወደ አላህ ከጃዮች ነን ባሉ ኖሮ (ለነሱ በተሻላቸው ነበር)።

If only they had been satisfied with what Allah and His Messenger gave them and said, "Sufficient for us is Allah ; Allah will give us of His bounty, and [so will] His Messenger; indeed, we are desirous toward Allah ," [it would have been better for them].

9:60
ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድሆች ለምስኪኖችም በርሷም ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱት ጫንቃዎችንም ነጻ በማዉጣት በባለ ዕዳዎችም በአላህ መንገድም በሚሠሩ በመንገደኛም ብቻ ነዉ፤ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።

Zakah expenditures are only for the poor and for the needy and for those employed to collect [zakah] and for bringing hearts together [for Islam] and for freeing captives [or slaves] and for those in debt and for the cause of Allah and for the [stranded] traveler - an obligation [imposed] by Allah . And Allah is Knowing and Wise.

9:61
ከነሱም (ከመናፍቃን) እነዚያ ነቢዩን የሚያሰቃዩ እርሱም ጆሮ ነዉ (ወሬ ሰሚ ነዉ) የሚሉ አልሉ፤ በላቸው ፦ ለናንተ የበጎ (ወሬ) ሰሚ ነው፤ በአላህ ያምናል ምእምናንንም ያምናቸዋል ከናንተም ዉስጥ ለነዚያ ላመኑት እዝነት ነዉ፤ እነዚያም የአላህን መልክተኛ የሚያሰቃዩ ለነሱ አሳሚሚ ቅጣት አላቸው።

And among them are those who abuse the Prophet and say, "He is an ear." Say, "[It is] an ear of goodness for you that believes in Allah and believes the believers and [is] a mercy to those who believe among you." And those who abuse the Messenger of Allah - for them is a painful punishment.

9:62
አላህንና መልክተኛውን ሊያስወድዱ ተገቢያቸው ሲሆን እናንተን ያስወድዷችሁ ዘንድ በአላህ ይምሉላችኋል፤ ምእምናኖች ቢሆኑ (አላህንና መልክተኛውን ያስወድዱ)።

They swear by Allah to you [Muslims] to satisfy you. But Allah and His Messenger are more worthy for them to satisfy, if they should be believers.

9:63
አላህንና መልክተኛዉን የሚከራከር ሰው ለርሱ የገሀነም እሳት በዉስጧ ዘውታሪ ሲሆን የተገባቺው መሆኑን አያዉቁምን? ይህ ታላቅ ዉርደት ነው።

Do they not know that whoever opposes Allah and His Messenger - that for him is the fire of Hell, wherein he will abide eternally? That is the great disgrace.

9:64
መናፍቃን በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር የምትነግራቸው ሱራ በነርሱ ላይ መውረዷን ይፈራሉ፤ አልላግጡ አላህ የምትፈሩትን ሁሉ ገላጭ ነዉ በላቸዉ።

They hypocrites are apprehensive lest a surah be revealed about them, informing them of what is in their hearts. Say, "Mock [as you wish]; indeed, Allah will expose that which you fear."

9:65
በእርግጥ ብትጠይቃቸዉ እኛ የምንዘባርቅና የምንጫዎት ብቻ ነበርን ይላሉ፤ በአላህና በአንቀጾቹ በመልክተኛዉም ታላግጡ ነበራችሁን? በላቸው።

And if you ask them, they will surely say, "We were only conversing and playing." Say, "Is it Allah and His verses and His Messenger that you were mocking?"

9:66
አታመካኙ ከእምነታችሁ በኋላ በእርግጥ ካዳችሁ፤ ከናንተ አንዷን ጭፍራ ብንምር (ሌላዋን) ጭፍራ እነሱ ኃጢአተኞች በመሆናቸው እንቀጣለን።

Make no excuse; you have disbelieved after your belief. If We pardon one faction of you - We will punish another faction because they were criminals.

9:67
መናፍቃንና መናፍቃት ከፊሎቻቸው ከከፊሉ ናቸው፤ በመጥፎ ነገር ያዛሉ፤ ከደግም ነገር ይከለከላሉ፤ እጆቻቸዉንም (ከልግስና) ይሰበስባሉ፤ አላህን ረሱ ስለዚህ (እርሱ) ተዋቸዉ፤ መናፍቃን አመጠኖቹ እነሱ ናቸዉ።

The hypocrite men and hypocrite women are of one another. They enjoin what is wrong and forbid what is right and close their hands. They have forgotten Allah , so He has forgotten them [accordingly]. Indeed, the hypocrites - it is they who are the defiantly disobedient.

9:68
መናፍቃንንና መናፍቃትን ከሐዲዎችንም አላህ የገሀነም እሳት በዉስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ ቃል ገብቶላቸዋል እርሷ በቂያቸው ናት አላህም ረግሟቸዋል ለነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው።

Allah has promised the hypocrite men and hypocrite women and the disbelievers the fire of Hell, wherein they will abide eternally. It is sufficient for them. And Allah has cursed them, and for them is an enduring punishment.

9:69
እንደነዚያ ከናንተ በፊት እንደ ነበሩት ናችሁ፤ ከናንተ ይበልጥ በኀይል የበረቱ በገንዘቦችም በልጆችም ይበልጥ የበዙ ነበሩ በዕድላቸውም ተጠቀሙ፤ እነዚያም ከናንተ በፊት የነበሩት በዕድላቸው እንደ ተጠቀሙ በዕድላችሁ ተጠቀማችሁ እንደነዚያም እንደ ዘባረቁት ዘባረቃችሁ እነዚያ ሥራዎቻቸው በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም ተበላሹ፤ እነዚያም ከሳሪዎቹ እነሱ ናቸው።

[You disbelievers are] like those before you; they were stronger than you in power and more abundant in wealth and children. They enjoyed their portion [of worldly enjoyment], and you have enjoyed your portion as those before you enjoyed their portion, and you have engaged [in vanities] like that in which they engaged. [It is] those whose deeds have become worthless in this world and in the Hereafter, and it is they who are the losers.

9:70
የነዚያ ከናንተ በፊት የነበሩት የኑሕ ሕዝቦች የዓድና የሠሙድም የኢብራሂምም ሕዝቦች የመድየን ባለቤቶችና የተገልባጮቹም ከተሞች ወሬ አልመጣላቸውምን? መልክተኞቻቸዉ በታምራት መጧቸው፤ አላህም የሚበድላቸዉ አልነበረም፤ ግን ነፍሶቻቸዉን የሚበድሉ ነበሩ።

Has there not reached them the news of those before them - the people of Noah and [the tribes of] 'Aad and Thamud and the people of Abraham and the companions of Madyan and the towns overturned? Their messengers came to them with clear proofs. And Allah would never have wronged them, but they were wronging themselves.

9:71
ምእምናንና ምእምናትም ከፊሎቻቸዉ ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፤ ሶላትንም ይሰግዳሉ፤ ዘካንም ይሰጣሉ፤ አላህንና መልክተኛዉንም ይታዘዛሉ፤ እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል፤ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና።

The believing men and believing women are allies of one another. They enjoin what is right and forbid what is wrong and establish prayer and give zakah and obey Allah and His Messenger. Those - Allah will have mercy upon them. Indeed, Allah is Exalted in Might and Wise.

9:72
አላህ ምእምናንንና ምእምናትን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችም ዉስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል፤ ከአላህም የሆነዉ ዉዴታ ከሁሉ የበለጠ ነው፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው።

Allah has promised the believing men and believing women gardens beneath which rivers flow, wherein they abide eternally, and pleasant dwellings in gardens of perpetual residence; but approval from Allah is greater. It is that which is the great attainment.

9:73
አንተ ነቢዩ ሆይ ከሐዲዎችንና መናፍቃንን ታገል፤ በነሱም ላይ ጨክን፤ መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት፤ መመለሻይቱም ከፋች።

O Prophet, fight against the disbelievers and the hypocrites and be harsh upon them. And their refuge is Hell, and wretched is the destination.


9:74
ምንም ያላሉ ለመሆናቸው በአላህ ይምላሉ የክሕደትንም ቃል በእርግጥ አሉ፤ ከእስልምናቸውም በኋላ ካዱ ያላገኙትንም ነገር (*)አሰቡ አላህም ከችሮታው መልክተኛውም (እንደዚሁ) ያከበራቸዉ መሆኑን እንጂ ሌላን አልጠሉም፤ ቢጸጸቱም ለነሱ የተሻለ ይሆናል፤ ቢሸሹም አላህ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም አሳማሚን ቅጣት ይቀጣቸዋል፤ ለነሱም በምድር ውስጥ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸዉም።
* ነቢዩን መግደልን


They swear by Allah that they did not say [anything against the Prophet] while they had said the word of disbelief and disbelieved after their [pretense of] Islam and planned that which they were not to attain. And they were not resentful except [for the fact] that Allah and His Messenger had enriched them of His bounty. So if they repent, it is better for them; but if they turn away, Allah will punish them with a painful punishment in this world and the Hereafter. And there will not be for them on earth any protector or helper.

9:75
ከነሱም አላህን ከችሮታው ቢሰጠን በእርግጥ እንመጸውታለን ከመልካሞቹም በእርግጥ እንሆናለን ሲል ቃል የተገባ አለ፤

And among them are those who made a covenant with Allah , [saying], "If He should give us from His bounty, we will surely spend in charity, and we will surely be among the righteous."

9:76
ከችሮታውም በሰጣቸው ጊዜ በርሱ ሰሰቱ፣ እነሱ (ኪዳናቸውን) የተዉ ሆነዉም ዞሩ።

But when he gave them from His bounty, they were stingy with it and turned away while they refused.

9:77
አላህንም ቃል የገቡለትን በማፍረሳቸውና ይዋሹትም በነበሩት ምክንያት እስከሚገናኙት ቀን ድረስ ንፍቅናን አስከተላቸው።

So He penalized them with hypocrisy in their hearts until the Day they will meet Him - because they failed Allah in what they promised Him and because they [habitually] used to lie.

9:78
አላህ ምስጢራቸውንና ውይይታቸውን የሚያውቅ መሆኑን አላህም ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ መሆኑን አያዉቁምን

Did they not know that Allah knows their secrets and their private conversations and that Allah is the Knower of the unseen?

9:79
እነዚያ ከምእምናን በምጽዋቶች ፈቃደኛ የሆኑትን እነዚያንም የችሎታቸውን ያክል እንጂ የማያገኙትን ሰዎች የሚያነዉሩ፣ ከነሱም የሚሳለቁ፣ አላህ ከነሱ ይሳለቅባቸዋል፤ (ይቀጣቸዋል) ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው።

Those who criticize the contributors among the believers concerning [their] charities and [criticize] the ones who find nothing [to spend] except their effort, so they ridicule them - Allah will ridicule them, and they will have a painful punishment.

9:80
ለነርሱ ምሕረትን ለምንላቸው፤ ወይም ለነሱ ምሕረትን አትለምንላቸዉ፤ (እኩል ነው)። ለነሱ ሰባ ጊዜ ምሕረትን ብትለምንላቸዉ አላህ ለነሱ በፍጹም አይምርም ይኽ እነርሱ በአላህና በመልክተኛው በመካዳቸው ነዉ አላህም አመጠኞች ሕዝቦችን አያቀናም።

Ask forgiveness for them, [O Muhammad], or do not ask forgiveness for them. If you should ask forgiveness for them seventy times - never will Allah forgive them. That is because they disbelieved in Allah and His Messenger, and Allah does not guide the defiantly disobedient people.

9:81
እነዚያ ከዘመቻ የቀሩት ከአላህ መልክተኛ በኋላ በመቀመጣቸዉ ተደሰቱ፤ በአላህም መንገድ በገንዘቦቻቸዉና በነፍሶቻቸዉ መታገልን ጠሉ፤ በሐሩር አትኺዱ አሉም፤ የገሀነም እሳት ተኳሳነቱ በጣም የበረታ ነው በላቸው። የሚያዉቁ ቢሆኑ ኖሮ (አይቀሩም ነበር)።

If Allah should return you to a faction of them [after the expedition] and then they ask your permission to go out [to battle], say, "You will not go out with me, ever, and you will never fight with me an enemy. Indeed, you were satisfied with sitting [at home] the first time, so sit [now] with those who stay behind."

9:82
ጥቂትንም ይሳቁ፤ ይሠሩት በነበሩትም ዋጋ ብዙን ያለቅሳሉ፤

So let them laugh a little and [then] weep much as recompense for what they used to earn.

9:83
ከነሱም ወደ ሆነችው ጭፍራ አላህ ቢመልስህ፣ (ከአንተ ጋር) ለመዉጣትም ቢያስፈቅዱህ ፦ ከኔ ጋር ጠላትን አትዋጉም እናንተ በመጀመሪያ ጊዜ መቀመጥን ወዳችኋልና ከተቀማጮቹ፣ ጋርም ተቀመጡ በላቸዉ።

If Allah should return you to a faction of them [after the expedition] and then they ask your permission to go out [to battle], say, "You will not go out with me, ever, and you will never fight with me an enemy. Indeed, you were satisfied with sitting [at home] the first time, so sit [now] with those who stay behind."

9:84
ከነሱም በአንድም በሞተ ሰው ላይ ፈጽሞ አትሥገድ፤ በመቃብሩም ላይ አትቁም፤ እነሱ በአላህና በመልክተኛው ክደዋልና፤ እነሱም አመጠኞች ሆነው ሞተዋልና።

And do not pray [the funeral prayer, O Muhammad], over any of them who has died - ever - or stand at his grave. Indeed, they disbelieved in Allah and His Messenger and died while they were defiantly disobedient.

9:85
ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸውም አይድነቁህ አላህ የሚሻዉ በቅርቢቱ ዓለም በነሱ ሊቀጣቸውና፣ ከሐዲዎችም ሆነዉ ነፍሶቻቸው እንዲወጡ ብቻ ነው።

And let not their wealth and their children impress you. Allah only intends to punish them through them in this world and that their souls should depart [at death] while they are disbelievers.

9:86
በአላህ እመኑ፤ ከመልክተኛውም ጋር ሆናችሁ ታገሉ፤ በማለት ምዕራፍ በተወረደች ጊዜ፣ ከነሱ የሰፊ ሀብት ባለቤቶች የሆኑት፣ (ለመቅረት) ፈቃድ ይጠይቁሃል፤ ከተቀማጮቹ ጋርም እንሁን፤ ተዎን ይሉሃል።

And when a surah was revealed [enjoining them] to believe in Allah and to fight with His Messenger, those of wealth among them asked your permission [to stay back] and said, "Leave us to be with them who sit [at home]."

9:87
በቤት ከሚቀሩት ጋር መሆናቸዉን ወደዱ፤ በልቦቻቸዉም ላይ (ዝገት) ታተመባቸው፤ ስለዚህ እነሱ አያውቁም።

They were satisfied to be with those who stay behind, and their hearts were sealed over, so they do not understand.

9:88
ግን መልክተኛው እነዚያም ከርሱ ጋር ያመኑት፣ በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸዉም ታገሉ፤ እነዚያም መልካሞች ሁሉ ለነሱ ናቸው፤ እነዚያም እነሱ ምኞታቸዉን ያገኙ ናቸው።

But the Messenger and those who believed with him fought with their wealth and their lives. Those will have [all that is] good, and it is those who are the successful.

9:89
ለነሱም ገነቶችን በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸዉን በዉስጣቸዉ ዘዉታሪዎች ሲሆኑ አላህ አዘጋጅቶላቸዋል፤ ይህ ታላቅ ማግኘት ነዉ።

Allah has prepared for them gardens beneath which rivers flow, wherein they will abide eternally. That is the great attainment.

9:90
ከአዕርራቦቸም (*) ይቅርታ ፈላጊዎቹ፣ ለነሱ እንዲፈቀድላቸው መጡ፤ እነዚያ አላህንና መልክተኛዉን የዋሹትም ተቀመጡ፤ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል።
* ከዓረብ ዘላኖች።


And those with excuses among the bedouins came to be permitted [to remain], and they who had lied to Allah and His Messenger sat [at home]. There will strike those who disbelieved among them a painful punishment.

9:91
በደካሞች ላይ በበሽተኞችም ላይ በነዚያም የሚያወጡት ገንዘብ በማያገኙት ላይ ለአላህና ለመልክተኛዉ ፍጹም ታዛዦች ከሆኑ (ባይወጡም) ኃጢአት የለባቸዉም በበጎ አድራጊዎች ላይ (የወቀሳ) መንገድ ምንም የለባቸውም አላህም መሐሪ አዛኝ ነው።

There is not upon the weak or upon the ill or upon those who do not find anything to spend any discomfort when they are sincere to Allah and His Messenger. There is not upon the doers of good any cause [for blame]. And Allah is Forgiving and Merciful.

9:92
በነዚያም ልትጪናቸዉ (*) በመጡህ ጊዜ በርሱ ላይ የምጭናችሁ (አጋሰስ) አላገኝም፤ ያልካቸው ስትኾን የሚያወጡት ገንዘብ ባለማግኘታቸው ለማዘናቸው ዓይኖቻቸው እንባን እያፈሰሱ በዞሩት ላይ (የወቀሳ መንገድ) የለባቸውም።)
* የሚጭኑበት አጋሠሥ ልትሠጣቸው


Nor [is there blame] upon those who, when they came to you that you might give them mounts, you said, "I can find nothing for you to ride upon." They turned back while their eyes overflowed with tears out of grief that they could not find something to spend [for the cause of Allah ].

9:93
(የወቀሳ) መንገዱ በነዚያ እነሱ ባለጸጋዎች ሆነዉ ሳሉ ለመቅረት ፈቃድ በሚጠይቁህ ሰዎች ላይ ብቻ ነዉ፣ ከቀሪዎቹ ጋር መኾናቸውን ወደዱ፤ አላህም በልቦቻቸው ላይ አተመባቸው፣ ስለዚህ እነሱ አያውቁም።

The cause [for blame] is only upon those who ask permission of you while they are rich. They are satisfied to be with those who stay behind, and Allah has sealed over their hearts, so they do not know.

9:94
ወደነሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ምክንያታቸውን ያቀርቡላችኋል፣ አታመካኙ፤ እናንተን ፈጽሞ አናምንም፤ አላህ ከወሬዎቻችሁ በእርግጥ ነግሮናልናአላህም ሥራችሁን በእርግጥ ያያል፤ መልክተኛውም (እንደዚሁ)፤ ከዚያም ሩቅንና ቅርብን ሁሉ ዐዋቂ ወደ ሆነው (አላህ) ትመለሳላችሁ ወዲያዉም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል በላቸው።

They will make excuses to you when you have returned to them. Say, "Make no excuse - never will we believe you. Allah has already informed us of your news. And Allah will observe your deeds, and [so will] His Messenger; then you will be taken back to the Knower of the unseen and the witnessed, and He will inform you of what you used to do."

9:95
ወደነሱ በተመለሳችሁ ጊዜ እንድትተውዋቸው ለናንተ በእርግጥ በአላህ ይምላሉ፤ እነሱንም ተውዋቸው፤ እነሱ እርኩሶች ናቸዉና፤ ይሠሩትም በነበሩት ዋጋ መኖሪያቸዉ ገሀነም ነው።

They will swear by Allah to you when you return to them that you would leave them alone. So leave them alone; indeed they are evil; and their refuge is Hell as recompense for what they had been earning.

9:96
ከነሱ ትወዱላቸው ዘንድ ለናንተ ይምሉላችኋል፤ ከነሱ ብትወዱም አላህ ከአመጠኞች ሕዝቦች አይወድም።

They swear to you so that you might be satisfied with them. But if you should be satisfied with them - indeed, Allah is not satisfied with a defiantly disobedient people.

9:97
አዕራቦች በክሕደትና በንፍቅና በጣም የበረቱ፤ አላህም በመልክተኛው ላይ ያወረደውን ሕግጋት ባለማወቅ የተገቡ ናቸው፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።

The bedouins are stronger in disbelief and hypocrisy and more likely not to know the limits of what [laws] Allah has revealed to His Messenger. And Allah is Knowing and Wise.

9:98
ከአዕራቦችም (በአላህ መንገድ) የሚያወጣዉን (ገንዘብ) ዕዳ አድርጎ የሚይዝ፣ በናንተም ላይ የጊዜን መገለባበጥ የሚጠባበቅ ሰው አልለ፤ በነሱ ላይ ጥፋቱ ይዙርባቸው፤ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው።

And among the bedouins are some who consider what they spend as a loss and await for you turns of misfortune. Upon them will be a misfortune of evil. And Allah is Hearing and Knowing.

9:99
ከአዕራቦችም፣ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚሰጣቸውንም (ምጽዋቶች) አላህ ዘንድ መቃረቢያዎችና ወደ መልክተኛው ጸሎቶችን መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ሰዉ አልለ፤ ንቁ፤ እርሷ ለነሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት፤ አላህ በችሮታው ውስጥ (በገነቱ) በእርግጥ ያስገባቸዋል፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።

But among the bedouins are some who believe in Allah and the Last Day and consider what they spend as means of nearness to Allah and of [obtaining] invocations of the Messenger. Unquestionably, it is a means of nearness for them. Allah will admit them to His mercy. Indeed, Allah is Forgiving and Merciful.

9:100
ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች፣ እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸዉ አላህ ከነሱ ወዷል፤ (*) ከርሱም ወደዋል፤ (**) በሥሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች፣ በዉስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲሆኑ ለነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፣ ይህ ታላቅ ዕድል ነው።
* ሥራቸውን ተቀብሏል ** በተሠጣቸው ምንዳ ተደስተዋል


And the first forerunners [in the faith] among the Muhajireen and the Ansar and those who followed them with good conduct - Allah is pleased with them and they are pleased with Him, and He has prepared for them gardens beneath which rivers flow, wherein they will abide forever. That is the great attainment.

9:101
በዙሪያችሁም ካሉት ከዐረብ ዘላኖች መናፍቃን አልሉ፤ ከመዲና ሰዎችም በንፍቅና ላይ በማመጽ የዘውተሩ አልሉ፤ አታዉቃቸውም፤ እኛ እናዉቃቸዋለን፤ ሁለት ጊዜ (*) እንቀጣቸዋለን ከዚያም ወደ ታላቅ ቅጣት ይመለሳሉ።
* በወቅሳና በመቃብር ስቃይ


And among those around you of the bedouins are hypocrites, and [also] from the people of Madinah. They have become accustomed to hypocrisy. You, [O Muhammad], do not know them, [but] We know them. We will punish them twice [in this world]; then they will be returned to a great punishment.

9:102
ሌሎቸም በኃጢአቶቻቸው የተናዘዙ፤ (፬) መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አልሉ፤ አላህ ከነሱ ጸጸታቸውን ሊቀበል ይከጅላል፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነዉና።

And [there are] others who have acknowledged their sins. They had mixed a righteous deed with another that was bad. Perhaps Allah will turn to them in forgiveness. Indeed, Allah is Forgiving and Merciful.

9:103
ከገንዘቦቻቸው ስትሆን በርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የሆነችን፣ ምጽዋት ያዝ፤ ለነሱም ጸልይላቸዉ፤ ጸሎትህ ለነሱ እርካታ ነዉና አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው።

Take, [O, Muhammad], from their wealth a charity by which you purify them and cause them increase, and invoke [ Allah 's blessings] upon them. Indeed, your invocations are reassurance for them. And Allah is Hearing and Knowing.

9:104
አላህ እርሱ ከባሮቹ ንስሐን የሚቀበል፣ ምጽዋቶችንም የሚወስድ መሆኑን አላህም እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ መሆኑን አያዉቁምን?

Do they not know that it is Allah who accepts repentance from His servants and receives charities and that it is Allah who is the Accepting of repentance, the Merciful?

9:105
በላቸዉም፦ ሥሩ፤ አላህ ሥራችሁን በእርግጥ ያያልና መልክተኛውና ምእምናንም፤ (እንደዚሁ ያያሉ)። ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ ዐዋቂ ወደ ሆነዉም (አላህ) በእርግጥ ትመለሳላችሁ፤ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል።

And say, "Do [as you will], for Allah will see your deeds, and [so, will] His Messenger and the believers. And you will be returned to the Knower of the unseen and the witnessed, and He will inform you of what you used to do."

9:106
ሌሎችም ለአላህ ትእዛዝ የተቆዩ ሕዝቦች አልሉ ወይ ይቀጣቸዋል፤ ወይም ከነሱ ላይ ጸጸትን ይቀበላል፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።

And [there are] others deferred until the command of Allah - whether He will punish them or whether He will forgive them. And Allah is Knowing and Wise.

9:107
እነዚያም (ምእምናንን) ለመጉዳት፣ ክሕደትንም ለማበርታት፣ በምእምናንም መካከል ለመለያየት ከአሁን በፊት አላህንና መልክተኛዉን የተዋጋዉንም ሰው ለመጠባበቅ መስጊድን የሠሩት (ከነሱ ናቸው)፤ መልካምን ሥራ እንጂ ሌላ አልሻንም ሲሉም በእርግጥ ይምላሉ፤ አላህም እነሱ በእርግጥ ዉሸታሞች መሆናቸዉን ይመሰክራል።

And [there are] those [hypocrites] who took for themselves a mosque for causing harm and disbelief and division among the believers and as a station for whoever had warred against Allah and His Messenger before. And they will surely swear, "We intended only the best." And Allah testifies that indeed they are liars.

9:108
በርሱ ዉስጥ በፍጹም አትስገድ፤ ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው (የቁባ) መስጊድ በዉስጡ ልትሰግድበት ይልቅ የተገባው ነው በሱ ዉስጥ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አልሉ፤ አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል።

Do not stand [for prayer] within it - ever. A mosque founded on righteousness from the first day is more worthy for you to stand in. Within it are men who love to purify themselves; and Allah loves those who purify themselves.

9:109
አላህን በመፍራትና ዉዴታዉን በመፈለግ ላይ ግንቡን የመሠረተው ሰው ይበልጣን ወይስ ጎርፍ በሸረሸረው ለመናድ በተቃረበ ገደል አፋፍ ላይ ግንቡን የመሠረተውና በርሱ (ይዞት) በገሃነም እሳት ዉስጥ የወደቀ (ይበልጣል?) አላህም በደለኞች ሕዘቦችን አይመራም።

Then is one who laid the foundation of his building on righteousness [with fear] from Allah and [seeking] His approval better or one who laid the foundation of his building on the edge of a bank about to collapse, so it collapsed with him into the fire of Hell? And Allah does not guide the wrongdoing people.

9:110
ያ የካቡት ግንባቸው ልቦቻቸው (በሞት) ካልተቆራረጡ በቀር፣ በልቦቻቸው ዉስጥ የመጠራጠር ምክንያት ከመሆን አይወገድም፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።

Their building which they built will not cease to be a [cause of] skepticism in their hearts until their hearts are stopped. And Allah is Knowing and Wise.

9:111
አላህ ከምእምናን፣ ነፍሶቻቸዉንና ገንዘቦቻቸዉን፣ ገነት ለነሱ ብቻ ያላቸው በመሆን ገዛቸው፤ በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ፤ ይገድላሉም፤ ይገደላሉም፤ በተዉራት፣ በኢንጅልና በቁርአንም፣ (የተነገረውን) ተስፋ በርሱ ላይ አረጋገጠ፤ ከአላህም የበለጠ በኪዳኑ የሚሞላ ማነዉ? በዚያም በርሱ በተሻሻጣችሁበት ሽያጫችሁ ተደሰቱ፤ ይህም እርሱ ታላቅ ዕድል ነው።

Indeed, Allah has purchased from the believers their lives and their properties [in exchange] for that they will have Paradise. They fight in the cause of Allah , so they kill and are killed. [It is] a true promise [binding] upon Him in the Torah and the Gospel and the Qur'an. And who is truer to his covenant than Allah ? So rejoice in your transaction which you have contracted. And it is that which is the great attainment.

9:112
(እነርሱ) ተጸጻቺዎች፣ ተገዢዎች፣ አመስጋኞች ጿሚዎች፣ አጎንባሾች፣ በግንባር ተደፊዎች፣ በበጎ ሥራ አዛዦች፣ ከክፉም ከልካዮች የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው፤ ምእምናንንም አብስር።

[Such believers are] the repentant, the worshippers, the praisers [of Allah ], the travelers [for His cause], those who bow and prostrate [in prayer], those who enjoin what is right and forbid what is wrong, and those who observe the limits [set by] Allah . And give good tidings to the believers.

9:113
ለነቢዩና ለነዚያ ላመኑት፣ ለአጋሪዎቹ የዝምድና፣ ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ፣ እነሱ (ከሐዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ምሕረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም።

It is not for the Prophet and those who have believed to ask forgiveness for the polytheists, even if they were relatives, after it has become clear to them that they are companions of Hellfire.

9:114
የኢብራሂም ለአባቱ ምሕረትን መለመን፣ ለርሱ ገብቶለት ለነበረችዉ ቃል (ለመምላት) እንጂ ለሌላ አልነበረም። እርሱም የአላህ ጠላት መሆኑ ለርሱ በተገለጸለት ጊዜ፣ ከርሱ ራቀ፤ (ተወዉ)፤ ኢብራሂም በእርግጥ በጣም ርኅሩህ ታጋሽ ነውና።

And the request of forgiveness of Abraham for his father was only because of a promise he had made to him. But when it became apparent to Abraham that his father was an enemy to Allah , he disassociated himself from him. Indeed was Abraham compassionate and patient.

9:115
አላህም ሕዝቦችን ከአቀናቸው በኋላ፣ የሚጠነቀቁትን (ሥራ) ለርሱ እስከሚገልጽላቸዉ፣ (እስከሚተዉትም) ድረስ ጥፋተኛ የሚያደርግ አይደለም፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነውና።

And Allah would not let a people stray after He has guided them until He makes clear to them what they should avoid. Indeed, Allah is Knowing of all things.

9:116
አላህ የሰማያትና የምድር ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፤ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፤ ለናንተም ከርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም።

Indeed, to Allah belongs the dominion of the heavens and the earth; He gives life and causes death. And you have not besides Allah any protector or any helper.

9:117
በነቢዩ በነዚያም በችግሪቱ ጊዜያት (በተቡክ ዘመቻ) ከነሱ የከፊሎች ልቦች (ለመቅረት) ሊዘነበሉ ከተቃረቡ በኋላ፣ በተከተሉት ስደተኞችና ረዳቶች ላይ፣ አላህ በእርግጥ ጸጸታቸዉን ተቀበለ፤ ከዚያም ከነሱ ንስሐ መግባታቸውን ተቀበለ፤ እርሱ ለነሱ ርኅሩህ አዛኝ ነውና።

Allah has already forgiven the Prophet and the Muhajireen and the Ansar who followed him in the hour of difficulty after the hearts of a party of them had almost inclined [to doubt], and then He forgave them. Indeed, He was to them Kind and Merciful.

9:118
በነዚያም በሦስቱ ሰዎች ላይ ምድር ከስፋትዋ ጋር በነሱ ላይ እስከ ጠበበች፣ ነፍሶቻቸውም በርሳቸዉ ላይ እስከ ተጠበቡ፣ ከአላህም ወደርሱ ቢሆን እንጂ ሌላ መጠጊያ አለመኖሩን እስከ አረጋገጡ ድረስ በተቆዩት ላይ፣ (አላህ ጸጸትን ተቀበለ)። ከዚያም ይጸጸቱ ዘንድ ወደ ጸጸት መራቸው፤ አላህ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነዉና።

And [He also forgave] the three who were left behind [and regretted their error] to the point that the earth closed in on them in spite of its vastness and their souls confined them and they were certain that there is no refuge from Allah except in Him. Then He turned to them so they could repent. Indeed, Allah is the Accepting of repentance, the Merciful.

9:119
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከዉነተኞቹም ጋር ሁኑ።

O you who have believed, fear Allah and be with those who are true.

9:120
ለመዲና ሰዎችና ከአዕራብም በዙሪያቸው ላሉት ሰዎች፣ ከአላህ መልክተኛ ወደኋላ ሊቀሩ፣ ነፍሶቻቸውንም ከነፍሱ አብልጠው ሊወዱ አይገባቸውም ነበር፤ ይህ (ከመቅረት መከልከል) ለነርሱ መልካም ሥራ የሚጻፍላቸዉ ቢሆን እንጅ፣ በአላህ መንገድ ላይ ጥምም ድካምም፣ ረኃብም፣ የማይነካቸው፣ ከሐዲዎችንም የሚያስቆጭን ሰፍራ የማይረግጡ ከጠላትም የሚጎዳን ነገር (መግደልን መማረክን መዝረፍን) የማያገኙ፣ በመሆናቸው ነው። አላህ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና።

It was not [proper] for the people of Madinah and those surrounding them of the bedouins that they remain behind after [the departure of] the Messenger of Allah or that they prefer themselves over his self. That is because they are not afflicted by thirst or fatigue or hunger in the cause of Allah , nor do they tread on any ground that enrages the disbelievers, nor do they inflict upon an enemy any infliction but that is registered for them as a righteous deed. Indeed, Allah does not allow to be lost the reward of the doers of good.

9:121
ትንሽንም ትልቅንም ልግስና አይለግሱም፣ ወንዝንም አያቋርጡም፣ አላህ ይሠሩት ከነበረው የበለጠን ምንዳ ይመነዳቸው ዘንድ ለነሱ የሚጻፍላቸው ቢሆን እንጂ።

Nor do they spend an expenditure, small or large, or cross a valley but that it is registered for them that Allah may reward them for the best of what they were doing.

9:122
ምእምናንም (ነቢዩ ጋር ካልሆነ) በሙሉ ሊወጡ አይገባም፤ ከነሱ ዉስጥ ከየክፍሉ አንዲት ጭፍራ ለምን አትወጣም፤ (ሌሎቹ) ሃይማኖትን እንዲማሩና ወገኖቻቸውን ወደነርሱ በተመለሱ ጊዜ እንዲጠነቀቁ ይገሥጹዋቸው ዘንድ (ለምን አይቀሩም)።

And it is not for the believers to go forth [to battle] all at once. For there should separate from every division of them a group [remaining] to obtain understanding in the religion and warn their people when they return to them that they might be cautious.

9:123
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአቅራቢያችሁ ያሉትን ከሐዲዎች ተዋጉ፤ ከናንተም ብርታትን ያግኙ፤ አላህም ከሚጠነቀቁት ጋር መሆኑን ዕወቁ።

O you who have believed, fight those adjacent to you of the disbelievers and let them find in you harshness. And know that Allah is with the righteous.

9:124
ሱራም (ምዕራፍ) በተወረደች ጊዜ፣ ከነሱ (ከመናፍቃን) ዉስጥ ማንኛችሁ ነው? ይህቺ (ምዕራፍ) እምነትን የጨመረችለት የሚል ሰው አልለ፤ እነዚያ ያመኑትማ፣ የሚደሰቱ ሲሆኑ እምነትን ጨመረችላቸው።

And whenever a surah is revealed, there are among the hypocrites those who say, "Which of you has this increased faith?" As for those who believed, it has increased them in faith, while they are rejoicing.

9:125
እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸውማ፣ በርክሰታቸዉ ላይ ርክሰትን ጨመረችላቸው፤ እነሱም ከሐዲዎች ሆነው ሞቱ።

But as for those in whose hearts is disease, it has [only] increased them in evil [in addition] to their evil. And they will have died while they are disbelievers.

9:126
በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መሆናቸውን አያዩምን ? ከዚያም አይጸጸቱምን? እነሱም አይገሠጹምን?

Do they not see that they are tried every year once or twice but then they do not repent nor do they remember?

9:127
(እነሱን የምታነሳ) ምዕራፍም) በተወረደች ጊዜ አንድ ሰው ያያችኋልን? እያሉ፣ ከፊሎቻቸው ወደ ከፊሉ ይመለከታሉ፤ ከዚያም (ተደበቀው) ይኼዳሉ፤ እነርሱ የማያዉቁ ሕዝቦች በመሆናቸው አላህ ልቦቻቸውን አዞረ።

And whenever a surah is revealed, they look at each other, [saying], "Does anyone see you?" and then they dismiss themselves. Allah has dismissed their hearts because they are a people who do not understand.

9:128
ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በርሱ ላይ ጥኑ የሆነ፣ በናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን ርኅሩህ አዛኝ የሆነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ።

There has certainly come to you a Messenger from among yourselves. Grievous to him is what you suffer; [he is] concerned over you and to the believers is kind and merciful.

9:129
ቢያፈገፍጉም አላህ በቂዬ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ በርሱ ላይ ተጠጋሁ፤ እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው በላቸው።

But if they turn away, [O Muhammad], say, "Sufficient for me is Allah ; there is no deity except Him. On Him I have relied, and He is the Lord of the Great Throne."

Copyright 2013, AmharicQuran.com