Amharic Quran
Chapters/Surah

አል-ናዚዓት፤ (የአውጪዎች ምዕራፍ)

79:1
በኃይል አውጪዎች በሆኑት፤

By those [angels] who extract with violence

79:2
በቀስታ መምዘዝንም መዛዦች በሆኑት፤

And [by] those who remove with ease

79:3
መዋኘትንም ዋኚዎች በሆኑት፤

And [by] those who glide [as if] swimming

79:4
መቅደምንም ቀዳሚዎች በሆኑት፤

And those who race each other in a race

79:5
ነገርንም አስተናባሪዎች በሆኑት መላእክት እምላለሁ፤ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)።

And those who arrange [each] matter,

79:6
ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤

On the Day the blast [of the Horn] will convulse [creation],

79:7
ለጣቂይቱ የምትከተላት ስትሆን(ትቀሰቀሳላችሁ)።

There will follow it the subsequent [one].

79:8
በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው።

Hearts, that Day, will tremble,

79:9
አይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው።

Their eyes humbled.

79:10
እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ሁነታ ተመላሾች ነን? ይላሉ።

They are [presently] saying, "Will we indeed be returned to [our] former state [of life]?

79:11
የበሰበሱ አጥንቶች በሆን ጊዜ (እንቀሰቀሳለን?)

Even if we should be decayed bones?

79:12
ይህች ያን ጊዜ ባለ ኪሳራ መመለስ ናት ይላሉ።

They say, "That, then, would be a losing return."

79:13
እርሷም አንዲት ጩኸት ናት፤

Indeed, it will be but one shout,

79:14
ወዲያውኑ እነሱ እንቅልፍ በሌለባት (ምድር) ላይ ይሆናሉ።

And suddenly they will be [alert] upon the earth's surface.

79:15
የሙሳ ወሬ መጣልህን?

Has there reached you the story of Moses? -

79:16
ጌታው በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ በጠራው ጊዜ፤

When his Lord called to him in the sacred valley of Tuwa

79:17
ወደ ፈርዖን ኺድ፤ እርሱ ወሰን አልፏልና።

"Go to Pharaoh. Indeed, he has transgressed.

79:18
በለውም፦ ወደ መጥራራትህ ላንተ (መንገድ) አለህን?

And say to him, 'Would you [be willing to] purify yourself

79:19
ወደ ጌታህም ልመራህ ትፈራውም ዘንድ፤ (መንገድ አለህን?) አለው።

And let me guide you to your Lord so you would fear [Him]?'"

79:20
ታላቂቱንም ታምር አሳየው።

And he showed him the greatest sign,

79:21
አስተባበለም፤ አመጠም።

But Pharaoh denied and disobeyed.

79:22
ከዚያም (ለማጥፋት) የሚተጋ ሆኖ ዞረ።

Then he turned his back, striving.

79:23
(ሰራዊቶቹን) ሰበሰበም፤ ተጣራም።

And he gathered [his people] and called out

79:24
አለም፦እኔ ታላቁ ጌታችሁ (1) ነኝ።

And said, "I am your most exalted lord."

79:25
አላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ (ቃል) ቅጣት ያዘው።

So Allah seized him in exemplary punishment for the last and the first [transgression].

79:26
በዚህ ውስጥ ለሚፈራ ሰው በርግጥ መገምገሚያ አለበት።

Indeed in that is a warning for whoever would fear [ Allah ].

79:27
ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት።

Are you a more difficult creation or is the heaven? Allah constructed it

79:28
ከፍታዋን አጓነ፤ አስተካከላትም።

He raised its ceiling and proportioned it.

79:29
ሌሊቷንም አጨለመ፤ ቀንዋንም ገለጸ።

And He darkened its night and extracted its brightness.

79:30
ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት።

And after that He spread the earth.

79:31
ውሃዋንና ግጦሿን ከርሷ አወጣ።

He extracted from it its water and its pasture,

79:32
ጋራዎችንም አደላደላቸው።

And the mountains He set firmly

79:33
ለናንተና ለእንሰሶቻችሁ መጣቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይህን አደረገ)።

As provision for you and your grazing livestock

79:34
ታላቂቱም መዐት በመጣች ጊዜ፤

But when there comes the greatest Overwhelming Calamity -

79:35
ሰው ሁሉ የሠራውን በሚያስታውስበት ቀን

The Day when man will remember that for which he strove,

79:36
ገሃነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፤

And Hellfire will be exposed for [all] those who see -

79:37
የካደ ሰውማ፣

So as for he who transgressed

79:38
ቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ

And preferred the life of the world,

79:39
ገሃነም እርሷ በርግጥ መኖሪያው ናት።

Then indeed, Hellfire will be [his] refuge

79:40
በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱን ከዝንባሌዋ የከለከለ፣

But as for he who feared the position of his Lord and prevented the soul from [unlawful] inclination,

79:41
ከሰዓቲቱ መቼ ነው መሆኛዋ? ሲሉ ይጠይቁሃል።

Then indeed, Paradise will be [his] refuge.

79:42
አንተ እርሷን ከማስታወስ በምን ውስጥ ነህ?

They ask you, [O Muhammad], about the Hour: when is its arrival?

79:43
(የዕውቀት) መጨረሻዋ ወደ ጌታህ ብቻ ነው።

In what [position] are you that you should mention it?

79:44
አንተ የሚፈራትን ሰው አስፈራሪ ብቻ ነህ።

To your Lord is its finality.

79:45
እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ያንዲት ቀን ምሽትን ወይም ረፋዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ።

You are only a warner for those who fear it.

79:46
እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ያንዲት ቀን ምሽትን ወይም ረፋዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ።

It will be, on the Day they see it, as though they had not remained [in the world] except for an afternoon or a morning thereof.

Copyright 2013, AmharicQuran.com