Amharic Quran
Chapters/Surah

አል-ነበእ፤ (የዜናው ምዕራፍ)

78:1
ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?

About what are they asking one another?

78:2
ከታላቁ ዜና (ከቁርአን ይጠያየቃሉ)።

About the great news -

78:3
ከዚያ እነሱ በርሱ የተለያዩበት ከሆነው።

That over which they are in disagreement.

78:4
ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስባቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ።

No! They are going to know.

78:5
ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ።

Then, no! They are going to know.

78:6
ምድርንም ምንጣፍ አላደረግንም?

Have We not made the earth a resting place?

78:7
ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን?

And the mountains as stakes?

78:8
ብዙ አይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ።

And We created you in pairs

78:9
እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን።

And made your sleep [a means for] rest.

78:10
ሌሊቱንም ልባስ አደረግን።

And made the night as clothing

78:11
ቀኑንም (ለኑሮ) መሥሪያ አደረግን።

And made the day for livelihood

78:12
ከበላያችሁ ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት)ገነባን።

And constructed above you seven strong [heavens]

78:13
አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን።

And made [therein] a burning lamp

78:14
ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ዉሃን አወረድን።

And sent down, from the rain clouds, pouring water

78:15
በርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)።

That We may bring forth thereby grain and vegetation

78:16
የተቆላለፉ አትክልቶችንም።

And gardens of entwined growth.

78:17
የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው።

Indeed, the Day of Judgement is an appointed time -

78:18
በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭድሮች ሆናችሁ በምትመጡ ቀን ነው።

The Day the Horn is blown and you will come forth in multitudes

78:19
ሰማይም በምትከፈተና (ባለ) ደጃፎችም በምትሆንበት።

And the heaven is opened and will become gateways

78:20
ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚሆኑበት (ቀን)፣ ነው።

And the mountains are removed and will be [but] a mirage.

78:21
ገሃነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት።

Indeed, Hell has been lying in wait

78:22
ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትሆን።

For the transgressors, a place of return,

78:23
በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲሆኑ፤

In which they will remain for ages [unending].

78:24
በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም።

They will not taste therein [any] coolness or drink

78:25
ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)።

Except scalding water and [foul] purulence -

78:26
ተስማሚን ምንዳ ይመነዳሉ።(1)

An appropriate recompense.

78:27
እነሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና።

Indeed, they were not expecting an account

78:28
በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባብሉና።

And denied Our verses with [emphatic] denial.

78:29
ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲሆን አጠቃለልነው።

But all things We have enumerated in writing.

78:30
ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)።

"So taste [the penalty], and never will We increase you except in torment."

78:31
ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አላቸው።

Indeed, for the righteous is attainment -

78:32
አትክልቶችና ወይኖችም።

Gardens and grapevines

78:33
እኩያዎች የሆኑ ጡተ ጉቻማዎችም።

And full-breasted [companions] of equal age

78:34
የተሞሉ ብርጭቆዎችም።

And a full cup.

78:35
በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም።

No ill speech will they hear therein or any falsehood -

78:36
ከጌታህ የሆነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)።

[As] reward from your Lord, [a generous] gift [made due by] account,

78:37
የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ጌታ በጣም አዛኝ ከሆነው (ተመነዱ)፤ ከርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም።

[From] the Lord of the heavens and the earth and whatever is between them, the Most Merciful. They possess not from Him [authority for] speech.

78:38
መንፈሱ (ጂብሪል) መላ እክቶቹም የተሰለፉ ሆነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢሆን እንጅ (ምነጋገርን አይችሉም)።

The Day that the Spirit and the angels will stand in rows, they will not speak except for one whom the Most Merciful permits, and he will say what is correct.

78:39
ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው። የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል።

That is the True Day; so he who wills may take to his Lord a [way of] return.

78:40
እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሐዲውም ዋ ምኞቴ ምንነው ዐፈር በሆንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የሆነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ።

Indeed, We have warned you of a near punishment on the Day when a man will observe what his hands have put forth and the disbeliever will say, "Oh, I wish that I were dust!"

Copyright 2013, AmharicQuran.com