Amharic Quran
Chapters/Surah

አል-ቂያማህ፤ (የትንሣኤ ምዕራፍ)

75:1
(ነገሩ ከሐዲዎች እንደሚሉት)፤ አይደለም፤ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ።

I swear by the Day of Resurrection

75:2
(ራሷን ወቃሽ በሆነች ነፍስም እምላለሁ፤ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)።

And I swear by the reproaching soul [to the certainty of resurrection].

75:3
ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን?

Does man think that We will not assemble his bones?

75:4
አይደለም፣ ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላዮ ቻዮች ስንሆን (እንሰበስባቸዋለን)።

Yes. [We are] Able [even] to proportion his fingertips.

75:5
ይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል።

But man desires to continue in sin.

75:6
የትንሣኤው ቀን መቼ ነው? ሲል ይጠይቃል።

He asks, "When is the Day of Resurrection?"

75:7
ዓይንም በዋለለ ጊዜ፤

So when vision is dazzled

75:8
ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፤

And the moon darkens

75:9
ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፤

And the sun and the moon are joined,

75:10
ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው? ይላል።

Man will say on that Day, "Where is the [place of] escape?"

75:11
ይከልከል ምንም መጠጊያ የለም።

No! There is no refuge.

75:12
በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው።

To your Lord, that Day, is the [place of] permanence.

75:13
ሰው፣ በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል።

Man will be informed that Day of what he sent ahead and kept back.

75:14
በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው። (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)።

Rather, man, against himself, will be a witness,

75:15
ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ፣ (አይሰማም)

Even if he presents his excuses.

75:16
በርሱ (በቁርአን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በርሱ አታላውስ።

Move not your tongue with it, [O Muhammad], to hasten with recitation of the Qur'an.

75:17
(በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ (1) በኛ ላይ፣ ነውና።

Indeed, upon Us is its collection [in your heart] and [to make possible] its recitation.

75:18
ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል።

So when We have recited it [through Gabriel], then follow its recitation

75:19
ከዚያም ማብራራቱ በኛ ላይ ነው።

Then upon Us is its clarification [to you].

75:20
(ከመጣደፍ) ተከልከል፤ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ።

No! But you love the immediate

75:21
መጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ። (አትዘጋጁላትም)።

And leave the Hereafter.

75:22
ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው።

[Some] faces, that Day, will be radiant,

75:23
ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው።

Looking at their Lord.

75:24
ፊቶችም፣ በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው።

And [some] faces, that Day, will be contorted,

75:25
በርሳቸውም አደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ።

Expecting that there will be done to them [something] backbreaking.

75:26
ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን (2) በደረሰች ጊዜ፤

No! When the soul has reached the collar bones

75:27
አሻሪው ማነው? በተባለም ጊዜ፤

And it is said, "Who will cure [him]?"

75:28
(ሕመምተኛው) እርሱ (የሠፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መለየት መሆኑን ባረጋገጠም ጊዜ፤

And the dying one is certain that it is the [time of] separation

75:29
ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፤

And the leg is wound about the leg,

75:30
በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው።

To your Lord, that Day, will be the procession.

75:31
አላመነምም፤ አልሰገደምም።

And the disbeliever had not believed, nor had he prayed.

75:32
ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም።

But [instead], he denied and turned away.

75:33
ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ።

And then he went to his people, swaggering [in pride].

75:34
የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፤ ላንተም ተገቢህም ነው።

Woe to you, and woe!

75:35
ከዚያም ጥፋት፣ ይጠጋህ፣ ለአንተ የተገባህም ነው።

Then woe to you, and woe!

75:36
ሰው ስድ ሆኖ መትተውን ይጠረጥራልን?

Does man think that he will be left neglected?

75:37
የሚፈስስ ከሆነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?

Had he not been a sperm from semen emitted?

75:38
ከዚያም የረጋ ደም ሆነ፤ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፤ አስተካከለውም።

Then he was a clinging clot, and [ Allah ] created [his form] and proportioned [him]

75:39
ከርሱም ሁለት ዓይነቶችን፣ ወንድና ሴትን አደረገ።

And made of him two mates, the male and the female.

75:40
ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?

Is not that [Creator] Able to give life to the dead?

Copyright 2013, AmharicQuran.com