Amharic Quran
Chapters/Surah

አል-ሙዘሚል፤ (የተከናናቢው ምዕራፍ)

73:1
አንተ ተከናናቢው ሆይ።

O you who wraps himself [in clothing],

73:2
ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም፤ (ስገድ)።

Arise [to pray] the night, except for a little

73:3
ግማሹን፣ (ቁም)፤ ወይም ከርሱ ጥቂት ቀንስ።

Half of it - or subtract from it a little

73:4
ወይም በርሱ ላይ ጨምር፤ ቁርአንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ።

Or add to it, and recite the Qur'an with measured recitation

73:5
እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እንጥላለንና።

Indeed, We will cast upon you a heavy word.

73:6
የሌሊት መነሳት፣ እርሷ (ሕዋሳትንና ልብን) ለማስማማት በጣም ብርቱ ናት፤ ለማንበብም ትክክለኛ ናት።

Indeed, the hours of the night are more effective for concurrence [of heart and tongue] and more suitable for words.

73:7
ላንተ በቀን ውስጥ ረዢም መዘዋወር አልለህ።

Indeed, for you by day is prolonged occupation.

73:8
የጌታህንም ስም አውሳ፤ ወደርሱም (መግገዛት)፣ መቋረጥን ተቋረጥ)። (1)

And remember the name of your Lord and devote yourself to Him with [complete] devotion.

73:9
(እርሱም) የምስራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ መጠጊያ አድርገህም ያዘው።

[He is] the Lord of the East and the West; there is no deity except Him, so take Him as Disposer of [your] affairs.

73:10
(ከሐዲዎች) በሚሉትም ላይ ታገሥ፤ መልካምንም መተው ተዋቸው።

And be patient over what they say and avoid them with gracious avoidance.

73:11
የድሎት ባለቤቶችም ከሆኑት አስተባባዮች ጋር ተዎኝ፤ ጥቂትንም ጊዜ አቆያቸው።

And leave Me with [the matter of] the deniers, those of ease [in life], and allow them respite a little.

73:12
እኛ ዘንድ ከባድ ማሠሪያዎች፣ እሳትም አለና።

Indeed, with Us [for them] are shackles and burning fire

73:13
የሚያንቅ ምግብም፤ አሳማሚ ቅጣትም፣ (አልለ)።

And food that chokes and a painful punishment -

73:14
ምድርና ጋራዎች በሚርገፈገፉበት፣ ጋራዎችም ፈሳሽ የአሸዋ ክምር በሚሆኑበት ቀን።

On the Day the earth and the mountains will convulse and the mountains will become a heap of sand pouring down.

73:15
እኛ በናንተ ላይ መስካሪ መልክተኛን እንደላክን።

Indeed, We have sent to you a Messenger as a witness upon you just as We sent to Pharaoh a messenger.

73:16
ፈርዖንም መልክተኛውን አመጠ፤ ብርቱ መያዝንም ያዝነው።

But Pharaoh disobeyed the messenger, so We seized him with a ruinous seizure.

73:17
ብትክዱ፣ ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን፣ (ቅጣት) እንዴት ትጠበቃላችሁ!

Then how can you fear, if you disbelieve, a Day that will make the children white- haired?

73:18
ሰማዩ በርሱ (በዚያ ቀን) ተሰንጣቂ ነው። ቀጠሮው ተፈጻሚ ነው።

The heaven will break apart therefrom; ever is His promise fulfilled.

73:19
ይህቺ መገሠጫ ናት፤ (መዳንን) የሻም ሰው፣ ወደ ጌታው መንገድን ይይዛል።

Indeed, this is a reminder, so whoever wills may take to his Lord a way.

73:20
አንተ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ያነሰን፣ ግማሹንም፣ ሢሶውንም፣ የምትቆም መሆንህን ጌታህ በርግጥ ያውቃል። ከነዚያም አብረውህ ካሉት ከፊሎች፣ (የሚቆሙ መሆናቸውን ያውቃል)፤ አላህም ሌሊትንና ቀንን ይለክካል፣ (ሌሊቱን) የማታዳርሱት መኾናችሁን ዐወቀ፤ በናንተ ላይም (ወደ ማቃለል)፣ ተመለሰላችሁ፤ ስለዚህ ከቁርአን (በስግደት) የተቻላችሁን አንብቡ፤ ከናንተ ውስጥ በሺተኞች፣ ሌሎችም ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ፣ ሌሎችም በአላህ መንገድ (ሃይማኖት) የሚጋደሉ እንደሚኖሩ ዐወቀ፤ (አቃለላቸውም)። ከርሱም የተቻላችሁን አንብቡ ሶላትንም ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፤ ለአላህም መልካም ብድርን አበድሩ፤ ከመልካም ሥራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ፣ እርሱ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ሆኖ አላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ፤ አላህንም ምሕረትን ለምኑት፤ አላህ በጣም መሐሪ አዛኝ ነውና።

Indeed, your Lord knows, [O Muhammad], that you stand [in prayer] almost two thirds of the night or half of it or a third of it, and [so do] a group of those with you. And Allah determines [the extent of] the night and the day. He has known that you [Muslims] will not be able to do it and has turned to you in forgiveness, so recite what is easy [for you] of the Qur'an. He has known that there will be among you those who are ill and others traveling throughout the land seeking [something] of the bounty of Allah and others fighting for the cause of Allah . So recite what is easy from it and establish prayer and give zakah and loan Allah a goodly loan. And whatever good you put forward for yourselves - you will find it with Allah . It is better and greater in reward. And seek forgiveness of Allah . Indeed, Allah is Forgiving and Merciful.

Copyright 2013, AmharicQuran.com