Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል ሐቃህ፤ (የአረጋጋጪቱ ምዕራፍ)

69:1
እዉነትን አረጋጋጪቱ (ትንሣኤ)

The Inevitable Reality -

69:2
አረጋጋጪቱ (እርሷ) ምንድን ናት

What is the Inevitable Reality?

69:3
አረጋጋጪቱም ምን እንደ ሆነች ምን አሳወቀህ

And what can make you know what is the Inevitable Reality?

69:4
ሠሙድማ ዓድ በቆርቋሪይቱ (ትንሣኤ) አስተባበሉ።

Thamud and 'Aad denied the Striking Calamity.

69:5
ሠሙድማ ወሰን በሌላት ጩኸት ተጠፉ (ተወደሙ)።

So as for Thamud, they were destroyed by the overpowering [blast].

69:6
ዓድማ በኀይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ።

And as for 'Aad, they were destroyed by a screaming, violent wind

69:7
ተከታታይ በሆኑ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት መዓልቶች ዉስጥ በነሱ ላይ ለቀቃት ሕዝቹንም በዉስጧ () የተጣሉ ሆነዉ ልክ ክፍት የሆኑ የዘንባባ ግንዶች መስለው ታያቸዋለህ።

Which Allah imposed upon them for seven nights and eight days in succession, so you would see the people therein fallen as if they were hollow trunks of palm trees.

69:8
ለነሱም ቀሪን ታያለህን

Then do you see of them any remains?

69:9
ፈርዖን ከበፊቱ የነበሩትም ሰዎች ተገልባጮቹም (ከተሞች) በኀጢአት (ሥራዎች) መጡ።

And there came Pharaoh and those before him and the overturned cities with sin.

69:10
የጌታቸዉንም መልዕክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ የበረታችንም አያያዝ ያዛቸው።

And they disobeyed the messenger of their Lord, so He seized them with a seizure exceeding [in severity].

69:11
እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሻላይቱ ታንኳ ውስጥ ጫናቸው።

Indeed, when the water overflowed, We carried your ancestors in the sailing ship

69:12
ለናንተ መገሰጫ ልናደርጋት አጥኒ የሆነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ።

That We might make it for you a reminder and [that] a conscious ear would be conscious of it.

69:13
በቀንዱም አንዲት መነፋት በተነፋች ጊዜ።

Then when the Horn is blown with one blast

69:14
በምድርና ጋራዎችም (ከስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ።

And the earth and the mountains are lifted and leveled with one blow -

69:15
በዚያ ቀን ኋኝቱ (ትንሳኤ) ትሆናለች።

Then on that Day, the Resurrection will occur,

69:16
ሰማይም ትቀደዳለች ስለዚህ እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት።

And the heaven will split [open], for that Day it is infirm.

69:17
መልዕክትም በየጫፎችዋ ላይ ይሆናሉ የጌታህንም ዐርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላእክት ከበላያቸው ይሸከማሉ።

And the angels are at its edges. And there will bear the Throne of your Lord above them, that Day, eight [of them].

69:18
በዚያ ቀን ከናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲሆኑ ትቅቀረባላሁ።

That Day, you will be exhibited [for judgement]; not hidden among you is anything concealed.

69:19
መጽሐፉን በቀኙ የተሰተ ሰውማ (ለጓደኞቹ) እንኩ መጽሐፌን አንብቡ ይላል።

So as for he who is given his record in his right hand, he will say, "Here, read my record!

69:20
እኔ ምርምራየን የሚገናኝ መሆሆኔን አረጋገጥኩ (ተዘጋጀሁም ይላል)።

Indeed, I was certain that I would be meeting my account."

69:21
እርሱም በተወደደች ኑሮ ውስጥ ይሆናል።

So he will be in a pleasant life -

69:22
በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ።

In an elevated garden,

69:24
በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምንያት ብሉ ጠጡም (ይባላሉ)።

[They will be told], "Eat and drink in satisfaction for what you put forth in the days past."

69:25
መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ ዋ ጥፋቴ ምነው ምጽሐፌን ባልተሰጠሁ ይላል።

But as for he who is given his record in his left hand, he will say, "Oh, I wish I had not been given my record

69:26
ምርመራየንም ምን እንደ ሆነ ባላወቅሁ።

And had not known what is my account.

69:27
እርሷ (ሞት ሕይወቴን) ምነው ፈጻሚ በሆነች። (1)

I wish my death had been the decisive one.

69:28
ገንዘቤ ከኔ ምንንም አላብቃቃኝ (አልትጠቀመኝም)።

My wealth has not availed me.

69:29
ኅይሌ ከኔ ላይ ጠፋ (ይላል)።

Gone from me is my authority."

69:30
ያዙት አሰሩትም።

[ Allah will say], "Seize him and shackle him.

69:31
ከዚያም በእሳትም ውስጥ አግቡት።

Then into Hellfire drive him.

69:32
ከዚያም ርዝመቷ ሰባ ክንድ በሆነች ሰንሰለት ውስጥ አግቡት።

Then into a chain whose length is seventy cubits insert him."

69:33
እርሷ ታላቅ በሆነው አላህ አያምንም ነበርና።

Indeed, he did not used to believe in Allah , the Most Great,

69:34
ድሆችንም በማብላት ላይ አያግባባም ነበርና።

Nor did he encourage the feeding of the poor.

69:35
ለርሱም ዛሬ እዚህ ዘመድ የለውም።

So there is not for him here this Day any devoted friend

69:36
ምግብም በእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ (እዥ) በስተቀር የለውም።

Nor any food except from the discharge of wounds;

69:37
ኅጢአተኞች እንጅ ሌላ አይበላውም (ይባላል)።

None will eat it except the sinners.

69:38
በምታዩትም ነገር እምላለው።

So I swear by what you see

69:39
በማታዩትም ነገር።

And what you do not see

69:40
እርሱ (ቁርአን) የተከበረ መለክተኛ ቃል ነው። (1)

[That] indeed, the Qur'an is the word of a noble Messenger

69:41
እርሱም የባለቅኔ ቃል (ግጥም)አይደለም ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ።

And it is not the word of a poet; little do you believe.

69:42
የጠንቋይም ቃል አይደለም ጥቂቱን ብቻ ታስታዉሳላችሁ።

Nor the word of a soothsayer; little do you remember

69:43
ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው።

[It is] a revelation from the Lord of the worlds.

69:44
በኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤

And if Muhammad had made up about Us some [false] sayings,

69:45
በኅይል በያዝነው ነበር።

We would have seized him by the right hand;

69:46
ከዚያም ከርሱ የልቡን ስር (የተንጠለጠለበትን ጂማት) በቆረጥን ነበር።

Then We would have cut from him the aorta.

69:47
ከእናንተም ውስጥ ከርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም።

And there is no one of you who could prevent [Us] from him.

69:48
እርሱም (ቁርአን) ለጥንቁቆች መገሠጫ ነው።

And indeed, the Qur'an is a reminder for the righteous.

69:49
እኛም ከናንተ ውስጥ አስተባባዮች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን።

And indeed, We know that among you are deniers.

69:50
እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው።

And indeed, it will be [a cause of] regret upon the disbelievers

69:51
እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው።

And indeed, it is the truth of certainty.

69:52
የታላቁን ገታህንም ስም አወድስ።

So exalt the name of your Lord, the Most Great.

Copyright 2013, AmharicQuran.com