Amharic Quran
Chapters/Surah


68:1
ነ. (ኑን)፤ (1) በብርዕ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት።

Nun. By the pen and what they inscribe,

68:2
አንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትሆን ዕብድ አይደለህም።

You are not, [O Muhammad], by the favor of your Lord, a madman.

68:3
ላንተ ከጌታህ የማይቋረጥ ዋጋ በእርግጥ አለህ።

And indeed, for you is a reward uninterrupted.

68:4
አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ።

And indeed, you are of a great moral character

68:5
ወደፊትም ታያለህ፤ ያያሉም፤

So you will see and they will see

68:6
ዕብደት በማንኛችሁ እንዳልለ።

Which of you is the afflicted [by a devil].

68:7
ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው።

Indeed, your Lord is most knowing of who has gone astray from His way, and He is most knowing of the [rightly] guided.

68:8
ለአስተባባዮችም አትታዘዝ።

Then do not obey the deniers.

68:9
ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ።

They wish that you would soften [in your position], so they would soften [toward you].

68:10
መሐለኛ ወራዳንም ሁሉ አትታዘዝ።

And do not obey every worthless habitual swearer

68:11
ሰውን አነዋሪንና በማሳበቅ ኼያጅን።

[And] scorner, going about with malicious gossip -

68:12
ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፤ወሰን አላፊን፤ ኃጢአተኛን፤

A preventer of good, transgressing and sinful,

68:13
ልበ ደረቅን፤ ከዚህ በኋላ ዲቃላን (ሁሉ አትታዘዝ)።

Cruel, moreover, and an illegitimate pretender.

68:14
የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመሆኑ (ያስተባብላል)።

Because he is a possessor of wealth and children,

68:15
በርሱ ላይ አንቀጾቻችን በሚነበቡ ጊዜ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው ይላል።

When Our verses are recited to him, he says, "Legends of the former peoples."

68:16
በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክት እናደርግበታለን።

We will brand him upon the snout

68:17
እኛ የአትክልቲቱን ባለቤቶች እንደ ሞከርን (የመካን ሰዎች) ሞከርናቸው፤ ማልደው (ፍሬዋን) ሊለቅሟት በማሉ ጊዜ።

Indeed, We have tried them as We tried the companions of the garden, when they swore to cut its fruit in the [early] morning

68:18
(በመሐላቸው) አያስቀሩምም።(1)

Without making exception.

68:19
እነርሱ የተኙ ሆነውም ሳሉ ከጌታህ የሆነ ዟሪ በርሷ ላይ ዞረባት።

So there came upon the garden an affliction from your Lord while they were asleep.

68:20
እንደ ሌሊት ጨለማም ሆና አነጋች፤ (ከሰለች)።

And it became as though reaped.

68:21
ያነጉም ሆነው ተጠራሩ።

And they called one another at morning,

68:22
ቆራጮች እንደ ሆናችሁ በእርሻችሁ ላይ ማልዱ በማለት።

[Saying], "Go early to your crop if you would cut the fruit."

68:23
እነሱ የሚንሾካሾኩ ሆነው ኼዱም።

So they set out, while lowering their voices,

68:24
ዛሬ በናንተ ላይ ደሃ እንዳይገባት በማለት።

[Saying], "There will surely not enter it today upon you [any] poor person."

68:25
(ድሆችን) በመከልከልም ላይ (በሐሳባቸው) ቻዮች ሆነው ማለዱ።

And they went early in determination, [assuming themselves] able.

68:26
ተቃጥላ ባዩዋትም ጊዜ እኛ በርግጥ ተሳሳቾች ነን አሉ።

But when they saw it, they said, "Indeed, we are lost;

68:27
ይልቁንም እኛ የተከለከልን ነን አሉ።

Rather, we have been deprived."

68:28
ትክክለኛቸው ለናንተ አላህን ለምን አታጠሩም አላልኳችሁምን? አላቸው።

The most moderate of them said, "Did I not say to you, 'Why do you not exalt [ Allah ]?' "

68:29
ጌታችን ጥራት ይገባው፤ እኛ በዳዮች ነበርን፤ አሉ።

They said, "Exalted is our Lord! Indeed, we were wrongdoers."

68:30
የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ።

Then they approached one another, blaming each other.

68:31
ዋ ጥፋታችን! እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን፤ አሉ።

They said, "O woe to us; indeed we were transgressors.

68:32
ጌታችን ከርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጅላል፤ እኛ ወደ ጌታችን ከጃዮች ነን፤ (አሉ)።

Perhaps our Lord will substitute for us [one] better than it. Indeed, we are toward our Lord desirous."

68:33
ቅጣቱ እንደዚሁ ነው። የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ታላቅ ነው፤ የሚያውቁ በሆኑ ኖሮ (በተጠነቀቁ ነበር)።

Such is the punishment [of this world]. And the punishment of the Hereafter is greater, if they only knew.

68:34
ለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው።

Indeed, for the righteous with their Lord are the Gardens of Pleasure.

68:35
ሙስሊሞቹን እንደ ከሐዲዎች እናደርጋለን?

Then will We treat the Muslims like the criminals?

68:36
ለናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ።

xWhat is [the matter] with you? How do you judge?

68:37
በውነቱ ለናንተ በርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን?

Or do you have a scripture in which you learn

68:38
በውስጡ ለናንተ የምትመርጡት አላችሁ (የሚል)

That indeed for you is whatever you choose?

68:39
ወይስ ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሣኤ ቀን ደራሽ የሆኑ መሐላዎች ለናንተ በኛ ላይ አሏችሁን?

Or do you have oaths [binding] upon Us, extending until the Day of Resurrection, that indeed for you is whatever you judge?

68:40
በዚህ ማናቸው ተያዥ እንደሆነ ጠይቃቸው።

Ask them which of them, for that [claim], is responsible.

68:41
ወይስ ለነሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) ተጋሪዎች አሏቸውን? እውነተኞችም እንደ ሆኑ ተናጋሪዎቻቸውን ያምጡ።

Or do they have partners? Then let them bring their partners, if they should be truthful.

68:42
ባት የሚገለጥበትን (ከሐዲዎች) ወደ መስገድም የሚጥጠሩበትንና የማይችሉበትን ቀን (አስታውስ)።

The Day the shin will be uncovered and they are invited to prostration but the disbelievers will not be able,

68:43
ዓይኖቻቸው የፈሩ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲሆኑ፤ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን)፤ እነሱም (በምድረ ዓለም) ደህና ሆነው ሳሉ ወደ ስግደት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ።

Their eyes humbled, humiliation will cover them. And they used to be invited to prostration while they were sound.

68:44
በዚህም ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተዎኝ፤ (እነሱን እኔ እበቃሃለሁ)። ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን።

So leave Me, [O Muhammad], with [the matter of] whoever denies the Qur'an. We will progressively lead them [to punishment] from where they do not know.

68:45
እነርሱንም አዘገያለሁ፤ ዘዴዬ ብርቱ ነውና።

And I will give them time. Indeed, My plan is firm.

68:46
በውነቱ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን?ስለዚህ እነሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን?

Or do you ask of them a payment, so they are by debt burdened down?

68:47
ወይስ እነሱ ዘንድ የሩቁ ሚስጢር ዕውቀት አለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን?

Or have they [knowledge of] the unseen, so they write [it] down?

68:48
ለጌታህም ፍርድ ታገሥ፤ (በመበሳጨትና ባለ መታገሥ) እንደ አሳው ባለቤት (እንደ ዮናስ) አትሁን፤እርሱ በጭንቀት የተሞላ ሆኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ።

Then be patient for the decision of your Lord, [O Muhammad], and be not like the companion of the fish when he called out while he was distressed.

68:49
ከጌታው የሆነ ሰጋ ባላገኘው ኖሮ፣ በምድረ በዳ ተወቃሽ ሆኖ በተጣለ ነበር።

If not that a favor from his Lord overtook him, he would have been thrown onto the naked shore while he was censured.

68:50
ጌታውም (በነቢይነት) መረጠው ከደጋጎቹም አደረገው።

And his Lord chose him and made him of the righteous.

68:51
እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁር አኑን በሰሙ ጊዜ በአይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ፤ እርሱም በእርግጥ እብድ ነው ይላሉ።

And indeed, those who disbelieve would almost make you slip with their eyes when they hear the message, and they say, "Indeed, he is mad."

68:52
ግን እርሱ (ቁርአን) ለአለማት መገሠጫ እንጂ ለሌላ አይደለም።

But it is not except a reminder to the worlds.

Copyright 2013, AmharicQuran.com