Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አልጦላቅ (የፍች ምዕራፍ)

65:1
አንተ ነቢዩ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው(1) ፍቱዋቸው፤ ዒዳንም ቁጠሩ፤ አላህንም ጌታችሁን ፍሩ፤ ግልጽ የሆነችን ጠያፍ ካልሰሩ በስተቀር ከቤታችሁ አታስውጧቸው፤ አይውጡም ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት፤ የአላህንም ሕግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ፤ ከዚህ (ፍች) በኋላ አላህ (የመማለስ) ነገርን ምናልባት ያመጣ እንደሆነ አታውቅም።

O Prophet, when you [Muslims] divorce women, divorce them for [the commencement of] their waiting period and keep count of the waiting period, and fear Allah , your Lord. Do not turn them out of their [husbands'] houses, nor should they [themselves] leave [during that period] unless they are committing a clear immorality. And those are the limits [set by] Allah . And whoever transgresses the limits of Allah has certainly wronged himself. You know not; perhaps Allah will bring about after that a [different] matter.

65:2
ጊዜአቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፤ ወይንም በመልካም ተለያዩዋቸው ከናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፤ ምስክርነትም ለአላህ አስተካክሉ፤ ይሃችሁ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በርሱ ይገሠጽበታል፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ለርሱ መውጫን ያደርግለታል።

And when they have [nearly] fulfilled their term, either retain them according to acceptable terms or part with them according to acceptable terms. And bring to witness two just men from among you and establish the testimony for [the acceptance of] Allah . That is instructed to whoever should believe in Allah and the Last day. And whoever fears Allah - He will make for him a way out

65:3
ከማያስበው በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል፤ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፤ አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው፤ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አርጓል።

And will provide for him from where he does not expect. And whoever relies upon Allah - then He is sufficient for him. Indeed, Allah will accomplish His purpose. Allah has already set for everything a [decreed] extent.

65:4
አሊያም ከአደፍ ያቋረቱት (በዒዳቸው ሕግ) ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሶስት ወር ነው፤ እሊያም ገና እድፍን ያላዩት (ዒዳቸው እንደዚሁ ነው) የ እርግዝና ባለቤቶችምጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ መግራትን ያደርግለታል።

And those who no longer expect menstruation among your women - if you doubt, then their period is three months, and [also for] those who have not menstruated. And for those who are pregnant, their term is until they give birth. And whoever fears Allah - He will make for him of his matter ease.

65:5
ይህ የአላህ ፍርድ ነው። ወደናንተም አወረደው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ኅጢአቶቹን ከርሱ ያሰርይለታል፣ ምንዳንም ለሱ ያተልቅለታል።

That is the command of Allah , which He has sent down to you; and whoever fears Allah - He will remove for him his misdeeds and make great for him his reward.

65:6
ከችሎታችሁ ከተቀመታችሁበት ስፍራ አስቀምጧቸው፤ በነሱም ላይ ልታጣብቡ አትጉዷቸው፤ የ እርግዝና ባለቤቶችም ቢሆኑእርጉዛቸውን እስኪወልዱ ድረስ በነሱ ላይ ቀልቡ፤ ለናንተም (ልጆቻችሁን) ቢያጠቡላችሁ ምንዳዎቻቸውን ስጧቸው፤ በመካከላችሁም በመልካም ነገር ተመካከሩ፤ ብትቸጋገሩም ለርሱ ሌላ (ሴት) ታጠባለታለች።

Lodge them [in a section] of where you dwell out of your means and do not harm them in order to oppress them. And if they should be pregnant, then spend on them until they give birth. And if they breastfeed for you, then give them their payment and confer among yourselves in the acceptable way; but if you are in discord, then there may breastfeed for the father another woman

65:7
የችሎታ ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ፤ በርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድድም፤ አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል።

Let a man of wealth spend from his wealth, and he whose provision is restricted - let him spend from what Allah has given him. Allah does not charge a soul except [according to] what He has given it. Allah will bring about, after hardship, ease

65:8
ከከተማም ከጌታዋ ትእዛዝ ከመልክተኞቹም ያመጠች ብርቱንም ቁጥጥር የተቆጣጠርናት መጥፎንም ቅጣት የቀጣናት ብዙ ናት።

And how many a city was insolent toward the command of its Lord and His messengers, so We took it to severe account and punished it with a terrible punishment.

65:9
የነገርዋን ቅጣት ቀመሰች የነገርዋም መጨረሻ ከሳራ ሆነ።

And it tasted the bad consequence of its affair, and the outcome of its affair was loss.

65:10
አላህ ለነርሱ ብርቱ ቅጣት አዘጋጀ፤ እናንተም የአእምሮ ባለ ቤቶች ሆይ አላህን ፍሩ፤ እነዚያን ያመኑ (ሆይ)! አላህ ወደናንተ ግሣጼን በእርግጥ አወረደመልክተኛን ላከ።

Allah has prepared for them a severe punishment; so fear Allah , O you of understanding who have believed. Allah has sent down to you the Qur'an.

65:11
እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣ ዘንድ የአላህን አንቀጾች ገላጮች ሲሆኑ በናንተ ላይ የሚያነብላችሁን (ላከ)፤ በአላህም አንቀጾች የሚያምን መልካምን ሥራ የሚሠራም ከሥሮቻቸውወንዙች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ለዘላለም ዘውታሪውች ሲሆኑ ያገባዋል፤ አላህ ለርሱ ሲሳይን በርግጥ አሳመረ።

[He sent] a Messenger [Muhammad] reciting to you the distinct verses of Allah that He may bring out those who believe and do righteous deeds from darknesses into the light. And whoever believes in Allah and does righteousness - He will admit him into gardens beneath which rivers flow to abide therein forever. Allah will have perfected for him a provision

65:11
አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፤ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸው ትእዛዙ ይወርዳል፤ አላህ በነገር ሁሉ ቻይ መሆኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)።

It is Allah who has created seven heavens and of the earth, the like of them. [His] command descends among them so you may know that Allah is over all things competent and that Allah has encompassed all things in knowledge.

Copyright 2013, AmharicQuran.com