Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አልተጋቡን፤ (የመጎዳዳት ምዕራፍ)

64:1
በሰማያት ውስጥ ያለው በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ ያሞግሳል፤ ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፤ ምስጋናም ለርሱ ነው፤ እርሱም በነገሩ ቻይ ነው።

Whatever is in the heavens and whatever is on the earth is exalting Allah . To Him belongs dominion, and to Him belongs [all] praise, and He is over all things competent.

64:2
እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው፤ ከናንተም ከሐዲ አለ፤ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ተመልካች ነው።

It is He who created you, and among you is the disbeliever, and among you is the believer. And Allah , of what you do, is Seeing.

64:3
ሰማያትንና ምድርን በውነት ፈጠረ፤ ቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም አሳመረ፤ መመለሻችሁም ወደርሱ ነው።

He created the heavens and earth in truth and formed you and perfected your forms; and to Him is the [final] destination.

64:4
በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፤ የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል አላህ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው።

He knows what is within the heavens and earth and knows what you conceal and what you declare. And Allah is Knowing of that within the breasts.

64:5
የነዚያ ከአሁን በፊት የካዱትና የክህደታችሁን ቅጣት ቅመሱ የተባሉት ሕዝቦች ወሬ አልመጣላችሁምን? ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አልላቸው።

Has there not come to you the news of those who disbelieved before? So they tasted the bad consequence of their affair, and they will have a painful punishment.

64:6
ይህ(ቅጣት)እርሱ መልክተኞቻቸው በአስረጂዎች ይመጡባችው ስለነበሩ ሰዎችም ይመሩልናልን? ስላሉና ስለካዱ ( ከእምነት) ስለዞሩም ነው አላህም (ከነሱ እምነት) ተብቃቃ፤ አላህም ተብቃቂ ምስጉን ነው።

That is because their messengers used to come to them with clear evidences, but they said, "Shall human beings guide us?" and disbelieved and turned away. And Allah dispensed [with them]; and Allah is Free of need and Praiseworthy

64:7
እነዝያ የካዱት በፍፁም የማይቀሰቀሱ መሆናቸውን አስቡ፤ አይደለም በጌታዬ እምላለሁ፤ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፤ ከዝያም በሰራችሁት ሁሉ ትነገራላችሁ ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው፤ በላቸው።

Those who disbelieve have claimed that they will never be resurrected. Say, "Yes, by my Lord, you will surely be resurrected; then you will surely be informed of what you did. And that, for Allah , is easy."

64:8
በአላህና በመልክተኛውም በዚያም ባወረድነው ብርሃን እመኑ፤ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው (በላቸው)።

So believe in Allah and His Messenger and the Qur'an which We have sent down. And Allah is Acquainted with what you do.

64:9
ለመሰብሰቢያ ቀን የሚሰበስባችሁን ቀን (አስታውሱ)፤ይህ የመጎዳዳኢቶቹን ይሰረይለታል፤ (ይፍቅለታል) ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች፣ በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያገባዋል፤ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው።

The Day He will assemble you for the Day of Assembly - that is the Day of Deprivation. And whoever believes in Allah and does righteousness - He will remove from him his misdeeds and admit him to gardens beneath which rivers flow, wherein they will abide forever. That is the great attainment.

64:10
እነዚያም የካዱና በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ እነዚያ በውስጡ ዘውታሪዎች ሲሆኑ የ እሳት ጓዶች ናቸው፤ መመለሻቸውም ከፋ!

But the ones who disbelieved and denied Our verses - those are the companions of the Fire, abiding eternally therein; and wretched is the destination.

64:11
ከመከራም (ማንንም) አይነካም በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ፤ በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን (ለት ዕግሥት) ይመራዋል፤ አላህም ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነው።

No disaster strikes except by permission of Allah . And whoever believes in Allah - He will guide his heart. And Allah is Knowing of all things.

64:12
አላህን ተገዙ፤ መልክተኛውንም ታዘዙ፤ ብትዞሩም (መልክተኛውን አይጎዱም)፤ በመልክተኛውም ላይ ማድረስ ያለበት ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው።

And obey Allah and obey the Messenger; but if you turn away - then upon Our Messenger is only [the duty of] clear notification.

64:13
አላህ ከርሱ በቀር አምላክ የለም፤ በአላህም ላይ አማኞቹ ይመኩ።

Allah - there is no deity except Him. And upon Allah let the believers rely

64:14
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተካከል) ለናንተ ጠላቶች የኾኑ አልሉ፤ ስለዚህ ተጠንቀቋቸው፤ ይቅርታ ብታደርጉ ብታልፏቸውም ብትምሯቸውም አላህ በጣም መሐሪ አዛኝ ነው።

O you who have believed, indeed, among your wives and your children are enemies to you, so beware of them. But if you pardon and overlook and forgive - then indeed, Allah is Forgiving and Merciful.

64:15
ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው፤ አላህም እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለ።

Your wealth and your children are but a trial, and Allah has with Him a great reward.

64:16
አላህን የቻላችሁትን ያክል ፍሩት፤ ትእዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ነፍሶቻችሁ መልካምን (ይሰጣችኋልና)፤ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠብቅ ሰው እነዚያ እነሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙት ናቸው።

So fear Allah as much as you are able and listen and obey and spend [in the way of Allah ]; it is better for your selves. And whoever is protected from the stinginess of his soul - it is those who will be the successful.

64:17
ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ (ምንዳውን) ለናንተ ይደራርበዋል፤ ለናንተም ይምራል፤ አላህ አመስጋኝ ታጋሽ ነው።

If you loan Allah a goodly loan, He will multiply it for you and forgive you. And Allah is Most Appreciative and Forbearing.

64:18
ሩቁን ሚስጢር ግልጹንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው ጥበበኛው ነው።

Knower of the unseen and the witnessed, the Exalted in Might, the Wise

Copyright 2013, AmharicQuran.com