Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል - ሶፍ (የሰልፍ ምዕራፍ)

61:1
በሰማያት ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሠ፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።

Whatever is in the heavens and whatever is on the earth exalts Allah , and He is the Exalted in Might, the Wise

61:2
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሠሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ?

O you who have believed, why do you say what you do not do?

61:3
የማትሠሩትን ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ።

Great is hatred in the sight of Allah that you say what you do not do.

61:4
አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ሆነው በመንገዱ (በሃይማኖቱ)የሚጋደሉትን ይወዳል።

Indeed, Allah loves those who fight in His cause in a row as though they are a [single] structure joined firmly

61:5
ሙሳም ለሕዝቦቹ ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ የአላህ መልክተኛ መሆኔን በእርግጥ የምታውቁ ስትሆኡ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ? ባለ ጊዜ (አስታውስ፤ ከውነት) በተዘነበሉም ጊዘ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበላቸው አላህም አመጠኞችን ሕዝቦች አያቀናም።

And [mention, O Muhammad], when Moses said to his people, "O my people, why do you harm me while you certainly know that I am the messenger of Allah to you?" And when they deviated, Allah caused their hearts to deviate. And Allah does not guide the defiantly disobedient people.

61:6
የመርየም ልጅ ዒሳም የ እስራኤል ልጆች ሆይ እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና ከኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በሆነው የማበስር ስሆን ወደናንተ (የተላክሁ) የአላህ መልክተኛ ነኝ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤በግልጽ ታምራቶች በመጣቸውም ጊዜ ይህ ግልፅ ድግምት ነው አሉ።

And [mention] when Jesus, the son of Mary, said, "O children of Israel, indeed I am the messenger of Allah to you confirming what came before me of the Torah and bringing good tidings of a messenger to come after me, whose name is Ahmad." But when he came to them with clear evidences, they said, "This is obvious magic."

61:7
እርሱ ወደ ኢስላም የሚጥጠራ ሲሆን በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰውም ይበልጥ በደለኛ ማነው? አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም።

And who is more unjust than one who invents about Allah untruth while he is being invited to Islam. And Allah does not guide the wrongdoing people

61:8
የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፤ አላህም ከሐዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው።

They want to extinguish the light of Allah with their mouths, but Allah will perfect His light, although the disbelievers dislike it.

61:9
እርሱ ያ አጋፋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በመምሪያ (መጽሐፍ) በውነተኛው ሃይማኖትም (በኢስላም) ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው።

It is He who sent His Messenger with guidance and the religion of truth to manifest it over all religion, although those who associate others with Allah dislike it.

61:10
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአሳማሚ ቅጣት የምታድናችሁ የሆነች ንግድ ላመላክታችሁን? (በላቸው)።

O you who have believed, shall I guide you to a transaction that will save you from a painful punishment?

61:11
(እርሷም) በአላህና በመልክተኛው ታምናላችሁ፣ በአላህ መንገድም በገንዘቦቻችሁ በነፍሶቻችሁም ትታገላላችሁ፤ ይሃችሁ የምታውቁ ብትሆኑ ለናንተ የተሻለ ነው።

[It is that] you believe in Allah and His Messenger and strive in the cause of Allah with your wealth and your lives. That is best for you, if you should know

61:12
ኃጢአቶቻችሁን ለናንተ ይምራል፤ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች ያገባችኋል፤በመኖሪያ ገነቶችም በሚያማምሩ ቤቶች ውስጥ (ያስቀምጣችኋል)፤ ይህ ታላቅ ዕድል ነው።

He will forgive for you your sins and admit you to gardens beneath which rivers flow and pleasant dwellings in gardens of perpetual residence. That is the great attainment.

61:13
ሌላይቱንም የምትወዷትን (ጸጋ ይሰጣችኋል) ከላህ የሆነ እርዳታና ቅርብ የሆነየአገር መክፈት ነው፤ ምእመናንንም አብስር።

And [you will obtain] another [favor] that you love - victory from Allah and an imminent conquest; and give good tidings to the believers.

61:14
እላንተ ያመናችሁ ሆይ የመርየም ልጅ ዒሳ ለሐዋርያቶቹ ወደ አላህ ረዳቴ ማነው? እንዳለ ሐዋርያቶቹም እኛ የአላህ ረዳቶች ነን እንዳሉት የአላህ ረዳቶች ሁኑ ከእስራኤል ልጆች አንደኛይቱ ጭፍራ አመነች፤ ሌላዋ ጭፍራም ካደች፤ እነዚያ ያመኑትንም በጠላታቸው ላይ አበረታናቸው፤ አሸናፊዎችም ሆኑ።

O you who have believed, be supporters of Allah , as when Jesus, the son of Mary, said to the disciples, "Who are my supporters for Allah ?" The disciples said, "We are supporters of Allah ." And a faction of the Children of Israel believed and a faction disbelieved. So We supported those who believed against their enemy, and they became dominant

Copyright 2013, AmharicQuran.com