Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ሐሽር፤ (ከአገር የማውጣት ምዕራፍ)

59:1
በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።

Whatever is in the heavens and whatever is on the earth exalts Allah , and He is the Exalted in Might, the Wise.

59:2
እርሱ ያ፣ ከመጽሐፉ ሰዎች እነዚያ የካዱትን ከቤቶቻቸው ለመጀመሪያው ማውጣት ያወጣቸው ነው፤ እነሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ(ኀይል) የሚከላከሉላቸው መሆናቸውን አሰቡ፤ አላህም ካላሰቡት ስፍራ መጣባቸው፤ በልቦቻቸውም ውስጥ መርበድበድን ጣለባቸው፤ ቤቶቻቸውን በእጆቻቸውና በምእምናኖቹ እጆች ያፈርሳሉ፤ አስተውሉም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ!

It is He who expelled the ones who disbelieved among the People of the Scripture from their homes at the first gathering. You did not think they would leave, and they thought that their fortresses would protect them from Allah ; but [the decree of] Allah came upon them from where they had not expected, and He cast terror into their hearts [so] they destroyed their houses by their [own] hands and the hands of the believers. So take warning, O people of vision.

59:3
በነሱም ላይ አላህ ከአገር መውጣትን ባልጻፈ ኖሮ በቅርቢቱ ዓለም በቀጣቸው ነበር፤ ለነርሱም በመጨረሻይቱ (ዓለም) የእሳት ቅጣት አላቸው።

And if not that Allah had decreed for them evacuation, He would have punished them in [this] world, and for them in the Hereafter is the punishment of the Fire.

59:4
ይህ እነርሱ አላህንና መልክተኛውን በመከራከራቸው ነው። አላህንም የሚከራከር ሰው (ይቀጣዋል)፤ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና።

That is because they opposed Allah and His Messenger. And whoever opposes Allah - then indeed, Allah is severe in penalty.

59:5
ከዘንባባ (ከተምር ዛፍ) ማንኛዋም የቆረጣችኋት ወይም በግንዶቿ ላይ የቆመች ሆና የተዋችኋት በአላህ ፈቃድ ነው፤ አመጠኞችንም ያዋርድ ዘንድ (በመቁረጥ ፈቀደ)።

Whatever you have cut down of [their] palm trees or left standing on their trunks - it was by permission of Allah and so He would disgrace the defiantly disobedient.

59:6
ከነርሱም (ገንዘብ) በመልክተኛው ላይ አላህ የመለሰው በርሱ ላይ ፈረሶችንና ግመሎችን አላስጋለባችሁበትም፤ (1) ግን አላህ መልክተኞቹን በሚሻው ሰው ላይ ይሾማል። አላህም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነው።

And what Allah restored [of property] to His Messenger from them - you did not spur for it [in an expedition] any horses or camels, but Allah gives His messengers power over whom He wills, and Allah is over all things competent.

59:7
አላህ ከከተሞቹ ሰዎች (ሀብት) በመልክተኛው ላይ የመለሰው (ሀብት) ከናንተ ውስጥ በሀብታሞቹ መካከል ተዘዋዋሪ እንዳይሆን ለአላህና ለመልክተኛው ለዝምድና ባለቤትም አባት ለሌላቸው ልጆችም ለድሆችም ለመንገደኛም (የሚሰጥ) ነው፤ መልክተኛው የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት። ከርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ። አላህንም ፍሩ፤ አላህ ቅታተ ብርቱ ነውና።

And what Allah restored to His Messenger from the people of the towns - it is for Allah and for the Messenger and for [his] near relatives and orphans and the [stranded] traveler - so that it will not be a perpetual distribution among the rich from among you. And whatever the Messenger has given you - take; and what he has forbidden you - refrain from. And fear Allah ; indeed, Allah is severe in penalty.

59:8
ለነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉ አላህንና መልክተኛውንም የሚረዱ ሆነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡት ስደተኞች ድሆች (ይሰጣል)፤ እነዚያ እነሱ እውነተኞቹ ናቸው።

For the poor emigrants who were expelled from their homes and their properties, seeking bounty from Allah and [His] approval and supporting Allah and His Messenger, [there is also a share]. Those are the truthful.

59:9
እነዚያም ከበፊታቸው አገሪቱን መኖሪያ ያደረጉት እምነትንም የለመዱት ወደነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ሰዎች ይወዳሉ፤ (ስደተኞቹ) ከተሰጡትም ነገር በልቦቻቸው ውስጥ ቅሬታን አያገኙም። በነሱ ችግር ቢኖርባቸውም በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ። የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው።

And [also for] those who were settled in al-Madinah and [adopted] the faith before them. They love those who emigrated to them and find not any want in their breasts of what the emigrants were given but give [them] preference over themselves, even though they are in privation. And whoever is protected from the stinginess of his soul - it is those who will be the successful.

59:10
እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት ጌታችን ሆይ ለኛም ለነዚያም በ እምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችን ምሕረት አድርግ። በልቦቻችንም ውስጥ ለነዚያ ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ። ጌታችን ሆይ! አንተ ርኅሩኅ አዛኝ ነህና ይላሉ።

And [there is a share for] those who came after them, saying, "Our Lord, forgive us and our brothers who preceded us in faith and put not in our hearts [any] resentment toward those who have believed. Our Lord, indeed You are Kind and Merciful."

59:11
ወደነዚያ ወደ ነፈቁት አላየህምን? ከመጽሐፉ ሰዎች ውስጥ ለነዚያ ለካዱት ወንድሞቻቸው (ከአገር) ብትባረሩ አብረናችሁ እንወጣለን፤ በናንተም (ጉዳይ)፣ አንድንም በፍጹም አንታዘዝም። ብትገደሉም፣ በ እርግጥ እንረዳችኋለን ይሏቸዋል፤ አላህም እነሱ ውሸታሞች መሆናቸውን ይመሰክራል።

Have you not considered those who practice hypocrisy, saying to their brothers who have disbelieved among the People of the Scripture, "If you are expelled, we will surely leave with you, and we will not obey, in regard to you, anyone - ever; and if you are fought, we will surely aid you." But Allah testifies that they are liars.

59:12
ቢወጥጡ አብረዋቸው አይወጡም፤ ቢገደሉም አይረዷቸውም፤ ቢረዷቸውም፣(ለሺሺት) ጀርባዎችን ያዞራሉ፤ ከዚያም እርዳታን አያገኙም።

If they are expelled, they will not leave with them, and if they are fought, they will not aid them. And [even] if they should aid them, they will surely turn their backs; then [thereafter] they will not be aided.

59:13
እናንተ በልቦቻቸው ውስጥ በማስፈራት ከአላህ ይልቅ የበረታችሁ ናችሁ፤ ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመሆናቸው ነው።

You [believers] are more fearful within their breasts than Allah . That is because they are a people who do not understand.

59:14
በተመሸጉ ከተሞች ውስጥ ወይም ከአጥሮች ጀርባ ሆነው እንጅ፤ የተሰበሰቡ ሆነው አይዋጉዋችሁም። ኀይላቸው በመካከላቸው ብርቱ ነው። ልቦቻቸው የተበታተኑ ሲሆኑ የተሰበሰቡ ናቸው ብለህ ትጠረጥራቸዋለህ። ይህ እነሱ አእምሮ የሌላቸው ህዝቦች በመሆናቸው ነው።

They will not fight you all except within fortified cities or from behind walls. Their violence among themselves is severe. You think they are together, but their hearts are diverse. That is because they are a people who do not reason.

59:15
(ብጤያቸው) እንደዚያ ከነሱ በፊት በቅርብ ጊዜ የነገራቸውን ቅጣት እንደቀመሱት ብጤ ነው፤ ለነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው።

[Theirs is] like the example of those shortly before them: they tasted the bad consequence of their affair, and they will have a painful punishment

59:16
እንደ ሰይጣን ብጤ ለሰውየው ካድ ባለው ጊዜና በካደም ጊዜ እኔ ከአንተ ንጹሕ ነኝ፣ እኔ አላህን የአለማትን ጌታ እፈራለሁ እንዳለው ነው።

[The hypocrites are] like the example of Satan when he says to man, "Disbelieve." But when he disbelieves, he says, "Indeed, I am disassociated from you. Indeed, I fear Allah , Lord of the worlds."

59:17
በመጨረሻውም እነርሱ በውስጡ ዘውታሪዎች ሲኮኑ በእሳት ውስጥ መሆን ነው። ይኽም የበዳዮች ዋጋ ነው።

So the outcome for both of them is that they will be in the Fire, abiding eternally therein. And that is the recompense of the wrong-doers.

59:18
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፤ አላህንም ፍሩ፤ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው።

O you who have believed, fear Allah . And let every soul look to what it has put forth for tomorrow - and fear Allah . Indeed, Allah is Acquainted with what you do

59:19
እንደነዚያም አልህን እንደረሱትና ነፍሶቻቸውን እንዳስረሳቸው (ሰዎች) አትኩኑ። እነዚያ እነሱ አመጠኞቹ ናቸው።

And be not like those who forgot Allah , so He made them forget themselves. Those are the defiantly disobedient.

59:20
የእሳት ጓዶችና የገነት ጓዶች አይስተካከሉም፤ የገነት ጓዶች እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው።

Not equal are the companions of the Fire and the companions of Paradise. The companions of Paradise - they are the attainers [of success].

59:21
ይህንን ቁርአን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ ከአላህ ፍራቻ (የተነሳ) ተዋራጅ ተሰንጣቂ ሆኖ ባየኸው ነበር፤ይህችን ምሳሌ ይገመግሙ ዘንድ ለሰዎች እንገልጻታለን።

If We had sent down this Qur'an upon a mountain, you would have seen it humbled and coming apart from fear of Allah . And these examples We present to the people that perhaps they will give thought.

59:22
እርሱ አላህ ነው፤ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ የሆነው፤ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ ነው።

He is Allah , other than whom there is no deity, Knower of the unseen and the witnessed. He is the Entirely Merciful, the Especially Merciful.

59:23
እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።

He is Allah , other than whom there is no deity, the Sovereign, the Pure, the Perfection, the Bestower of Faith, the Overseer, the Exalted in Might, the Compeller, the Superior. Exalted is Allah above whatever they associate with Him.

59:24
እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፤ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለርሱ ያሞግሳል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።

He is Allah , the Creator, the Inventor, the Fashioner; to Him belong the best names. Whatever is in the heavens and earth is exalting Him. And He is the Exalted in Might, the Wise.

Copyright 2013, AmharicQuran.com