Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ሙጀድላህ፤ (የመከራከር ምዕራፍ)

58:1
አላህ የዚያችን በባልዋ (ነገር) የምትከራከርህንና ወደአላህ የምታስሙተውን (ሴት) ቃል በእርግጥ ስማ አላህም። (በንግግር) መመላለሳችሁን ይስማል። አላህ ስሚ ተመልካች ነውና።

Certainly has Allah heard the speech of the one who argues with you, [O Muhammad], concerning her husband and directs her complaint to Allah . And Allah hears your dialogue; indeed, Allah is Hearing and Seeing.

58:2
እነዚያ ከናንተ ውስጥ ከሚስቶቻቸው እንደናቶቻቻን ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉ እነሱ እናቶቻቸው አይደሉም፤ እናቶቻቸው አሊያ የወለዱዋቸው ብቻ ናቸው። እነርሱም (በዚህ ቃል) ከንግግር የተጠላንና ውሸትን በእርግጥ ይናገራሉ፤ አላህም (ለሚጸጸት) ይቅርባይ መሃሪ ነው።

Those who pronounce thihar among you [to separate] from their wives - they are not [consequently] their mothers. Their mothers are none but those who gave birth to them. And indeed, they are saying an objectionable statement and a falsehood. But indeed, Allah is Pardoning and Forgiving

58:3
እነዚያም ከሚስቶቻቸው እንደ እናቶቻችን፣ ጀርባዎች ኽኑብን በማለት የሚምሉ፣ ከዚያም ወደ ተናገሩት የሚመለሱ ሳይነካኩ በፊት ጫንቃን ነጻ ማውጣት በነሱ ላይ አለባቸው። ይሃችሁ በርሱ ትገሠጹበታላችሁ፤ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።

And those who pronounce thihar from their wives and then [wish to] go back on what they said - then [there must be] the freeing of a slave before they touch one another. That is what you are admonished thereby; and Allah is Acquainted with what you do

58:4
ያላገኘም ሰው ከመነካካታቸው በፊት ሁለት የተከታተሉ ወሮችን መጾም አለበት ያልቻለም ሰው ስድሳ ድሆችን ማብላት (አለበት)፤ ይህ በአላህና በመልክተኛው እንድታምኑ ነው። ይህችም የአላህ ህግጋት ናት ለካሃዲዎችም አሳማሚ ቅጣት አልላቸው።

And he who does not find [a slave] - then a fast for two months consecutively before they touch one another; and he who is unable - then the feeding of sixty poor persons. That is for you to believe [completely] in Allah and His Messenger; and those are the limits [set by] Allah . And for the disbelievers is a painful punishment.

58:5
ግልጾች ማስረጃዎችን ያወረድን ስንኾን እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩ፣ እነዚያ ከነሱ በፊት የነበሩት እንደተዋረዱ ይዋረዳሉ፤ ለካሃዲዎችም አዋራጅ ቅጣት አልላቸው።

Indeed, those who oppose Allah and His Messenger are abased as those before them were abased. And We have certainly sent down verses of clear evidence. And for the disbelievers is a humiliating punishment.

58:6
አላህ ሁላቸውንም በሚቀሰቅሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል)፤ የሰሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፤ የረሱት ሲሆኑ አላህ ዐውቆታል አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነው።

On the Day when Allah will resurrect them all and inform them of what they did. Allah had enumerated it, while they forgot it; and Allah is, over all things, Witness.

58:7
አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውን፣ በምድርም ውስጥ ያለውን፣ ሁሉ የሚያውቅ መሆኑን አታይምን? ከሶስት ሰዎች መንሾካሾክ አይኖርም፣ እርሱ አራተኛቸው ቢሆን እንጂ፤ ከአምስትም (አይኖርም)፣ እርሱ ስድስተኛቸው ቢሆን እንጂ፤ ከዚያ ያነሰም የበዛም (አይኖርም)፣ እርሱ የትም ቢሆኑ አብሮዋቸው ቢሆን እንጂ፤ ከዚያም በትንሳኤ ቀን የሰሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል። አላህ ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነው።

Have you not considered that Allah knows what is in the heavens and what is on the earth? There is in no private conversation three but that He is the fourth of them, nor are there five but that He is the sixth of them - and no less than that and no more except that He is with them [in knowledge] wherever they are. Then He will inform them of what they did, on the Day of Resurrection. Indeed Allah is, of all things, Knowing

58:8
ወደነዚያ (በመጥፎ) ከመሾካሾክ ወደ ተከለከሉት፣ ከዚያም ከርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር ወደሚመለሱት በኃጢአትና ድንበርን በማለፍ መልክተኛውን በመቃወም ወደሚንሾካሸኩት አላየህምን? (ሰላም ሊሉ) በመጡህም ጊዜ አላህ በርሱ ባላናገረህ ቃል ያናግሩሃል። በነፍሶቻቸውም ውስጥ (ነቢይ ከሆንክ) በምንለው ነገር አላህ አይቀጣንም ኖሮዋልን? ይላሉ። ገሃነም የሚገቡዋት ሲሆኑ በቂያቸው ናት፤ ምን ትከፋም መመለሻ!

Have you not considered those who were forbidden from private conversation, then they return to that which they were forbidden and converse among themselves about sin and aggression and disobedience to the Messenger? And when they come to you, they greet you with that [word] by which Allah does not greet you and say among themselves, "Why does Allah not punish us for what we say?" Sufficient for them is Hell, which they will [enter to] burn, and wretched is the destination.

58:9
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተንሾካሾችሁ ጊዜ በሃጢአትና ወሰንን በማለፉ መልክተኛውንም በመቃወም አትንሾካሾኩ፤ ግን በበጎ ስራና አላህን በመፍራት ተወያዩ፤ ያንንም ወደርሱ የምሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ

O you who have believed, when you converse privately, do not converse about sin and aggression and disobedience to the Messenger but converse about righteousness and piety. And fear Allah , to whom you will be gathered.

58:10
(በመጥፎ) መንሾኮሾክ ከሰይጣንን ብቻ ነው። እነዚያ ያመኑት ያዝኑ ዘንድ፣ (ይቀሰቅሰዋል)፤ በአላህ ፈቃድ ካልሆ በቀር በምንም አይጎዳቸውም፤ በአላህ ላይም አማኞች ይጠጉ።

Private conversation is only from Satan that he may grieve those who have believed, but he will not harm them at all except by permission of Allah . And upon Allah let the believers rely.

58:11
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ለናንተ በመቀመጫዎች ስፍራ ተስፋፉ በተባላጩ ጊዜ፣ (ስፍራን) አስፉ፤ አላህ ያሰፋላችኋልና። ተነሱ በተባለም ጊዜ ተነሱ። አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል አላህም በምትሠሩት ሁሉ ወስጠ ዐዋቂ ነው።

O you who have believed, when you are told, "Space yourselves" in assemblies, then make space; Allah will make space for you. And when you are told, "Arise," then arise; Allah will raise those who have believed among you and those who were given knowledge, by degrees. And Allah is Acquainted with what you do.

58:12
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! መልክተኛውን በተወያያችሁ ጊዜ ከመወየያታችሁ በፊት ምጽዋትን አስቀድሙ፤ ይህ ለናንተ መልካም ነው፤ አጥሪም ነው ባታገኙም አላህ መሐሪ አዛኝ ነው።

O you who have believed, when you [wish to] privately consult the Messenger, present before your consultation a charity. That is better for you and purer. But if you find not [the means] - then indeed, Allah is Forgiving and Merciful.

58:13
ከውይይታችሁ በፊት ምጽዋቶችን ከማስቀደም (ድህነትን) ፈራችሁን? ባልሰራችሁም ጊዜ አላህ ከናንተ ጸጸትን የተቀበለ ሲሆን ሶላትን ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፤ አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፤ አላህም ውስጥ ዐዋቂ ነው።

Have you feared to present before your consultation charities? Then when you do not and Allah has forgiven you, then [at least] establish prayer and give zakah and obey Allah and His Messenger. And Allah is Acquainted with what you do.

58:14
ወደነዚያ አላህ በነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ሕዝቦች ወደ ተወዳጁት (መናፍቃን)፣ አላየኽምን? እነርሱ ከናንተ አይደሉም። ከነርሱም አይደሉም።እነሱም የሚያውቁ ሲኾኑ በውሸት ይምላሉ።

Have you not considered those who make allies of a people with whom Allah has become angry? They are neither of you nor of them, and they swear to untruth while they know [they are lying].

58:15
አላህ ለነርሱ ብርቱን ቅጣትን አዘጋጀ፤ እነሱ ይሰሩት የነበሩት ሥራ ምንኛ ከፋ!

Allah has prepared for them a severe punishment. Indeed, it was evil that they were doing.

58:16
መሐሎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ፤ ከአላህም መንገድ አገዱ፤ ስለዚህ ለነሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው።

They took their [false] oaths as a cover, so they averted [people] from the way of Allah , and for them is a humiliating punishment.

58:17
ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ (ቅጣት) ምንንም ከነሱ አያድኗቸውም። እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው። እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪ ናቸው።

Never will their wealth or their children avail them against Allah at all. Those are the companions of the Fire; they will abide therein eternally

58:18
አላህ የተሰበሰቡ ኾነው በሚያስነሳቸው ቀን ለናንተ እንደሚምሉላችሁም እነሱ (በሚጠቅም) ነገር ላይ መኾናቸውን የሚያስቡ ኾነው ለርሱ በሚምሉበት ቀን (አዋራጅ ቅጣት አላቸው)፤ ንቁ እነሱ ውሸታሞቹ እነርሱ ናቸው።

On the Day Allah will resurrect them all, and they will swear to Him as they swear to you and think that they are [standing] on something. Unquestionably, it is they who are the liars.

58:19
በነርሱ ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው፤ አላህንም ማስታወስን አስረሳቸው፤ እነዚያ የሠይጣን ጭፍሮች ናቸው፤ ንቁ፤ የሰይጣን ጭፍሮች ከሳሪዎቹ እነርሱ ናቸው።

Satan has overcome them and made them forget the remembrance of Allah . Those are the party of Satan. Unquestionably, the party of Satan - they will be the losers.

58:20
እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩት እነዚያ በጣም በወራዶቹ ውስጥ ናቸው።

Indeed, the ones who oppose Allah and His Messenger - those will be among the most humbled.

58:21
አላህ ፦ እኔ በእርግጥ አሸንፋለሁ፤ መልክተኞቼም (ያሸንፋሉ ሲል)፤ ጽፏል። አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና።

Allah has written, "I will surely overcome, I and My messengers." Indeed, Allah is Powerful and Exalted in Might.

58:22
በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች፣ አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው ወይም ልጆቻቸው፤ ወይም ወንድሞቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፤ እነዛ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፤ ከርሱም በኾነ መንፈስ ደግፏቸዋል፤ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል፤ አላህ ከነርሱ ወዷል። ከርሱም ወደዋል፤ እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፤ ንቁ የአላህ ሕዝቦች እነሱ ምኞታቸውን የሚያገኙ ናቸው።

You will not find a people who believe in Allah and the Last Day having affection for those who oppose Allah and His Messenger, even if they were their fathers or their sons or their brothers or their kindred. Those - He has decreed within their hearts faith and supported them with spirit from Him. And We will admit them to gardens beneath which rivers flow, wherein they abide eternally. Allah is pleased with them, and they are pleased with Him - those are the party of Allah . Unquestionably, the party of Allah - they are the successful.

Copyright 2013, AmharicQuran.com