Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ዋቂዓህ፤ (የመከራይቱ ቀን ምዕራፍ)

56:1
መከራዪቱ በወደቀች ጊዜ።

When the Occurrence occurs,

56:2
ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም።

There is, at its occurrence, no denial.

56:3
ዝቅ አድራጊና፣ ከፍ አድራጊ ናት።

It will bring down [some] and raise up [others].

56:4
ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ።

When the earth is shaken with convulsion

56:5
ተራሮችም መፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በሆኑ ጊዜ)።

And the mountains are broken down, crumbling

56:6
የተበተነ ብናኝ በሆኑም ጊዜ

And become dust dispersing.

56:7
ሦስት ዓይነቶችም በሆናችሁ ጊዜ፣ (ታዋርዳለች ታነሳለችም)።

And you become [of] three kinds:

56:8
የቀኝ ጓዶችም፣ ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው።

Then the companions of the right - what are the companions of the right?

56:9
የግራ ጓዶችም፣ ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው።

And the companions of the left - what are the companions of the left?

56:10
(ለበጎ ስራ) ቀዳሚዎቹም፣ (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው።

And the forerunners, the forerunners -

56:11
እነዚያ፣ ባለሟሎቹ ናቸው።

Those are the ones brought near [to Allah ]

56:12
በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲሆኑ።

In the Gardens of Pleasure,

56:13
ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው።

A [large] company of the former peoples

56:14
ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው።

And a few of the later peoples,

56:15
በተታቱ አልጋዎች ላይ ይሆናሉ።

On thrones woven [with ornament],

56:16
በርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲሆኑ።

Reclining on them, facing each other

56:17
በነሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ።

There will circulate among them young boys made eternal

56:18
ከጠጅ ምንጭም፣ በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በነሱ ላይ ይዞራሉ)።

With vessels, pitchers and a cup [of wine] from a flowing spring -

56:19
ከርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም።

No headache will they have therefrom, nor will they be intoxicated -

56:20
ከሚመርጡት ዓይነት በእሸቶች።

And fruit of what they select

56:21
ከሚሹትም በሆነ የበራሪ ሥጋ፣ (ይዞሩባቸዋል)።

And the meat of fowl, from whatever they desire.

56:22
አይናማዎች የሆኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው።

And [for them are] fair women with large, [beautiful] eyes

56:23
ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የሆኑ።

The likenesses of pearls well-protected,

56:24
በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይሆን ዘንድ፣ (ይህንን አደረግንላቸው)።

As reward for what they used to do.

56:25
በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም።

They will not hear therein ill speech or commission of sin -

56:26
ግን ሰላም መባባልን፣ (ይሰማሉ)።

Only a saying: "Peace, peace."

56:27
የቀኝ ጓዶችም፣ ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች!

The companions of the right - what are the companions of the right?

56:28
በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው።

[They will be] among lote trees with thorns removed

56:29
(ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም።

And [banana] trees layered [with fruit]

56:30
በተዘረጋ ጥላ ሥርም።

And shade extended

56:31
በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም።

And water poured out

56:32
ብዙ (ዓይነት) በሆኑ ፍራፍሬዎችም።

And fruit, abundant [and varied],

56:33
የማትቋረጥም፣ የማትከለከልም፣ የሆነች።

Neither limited [to season] nor forbidden,

56:34
ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም፣ (ሴቶችም፣ መካከል)።

And [upon] beds raised high

56:35
እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለነሱ) ፈጠርናቸው።

Indeed, We have produced the women of Paradise in a [new] creation

56:36
ደናግሎችም አደረግናቸው።

And made them virgins,

56:37
ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች፣ እኩያዎች (አደረግናቸው)።

Devoted [to their husbands] and of equal age,

56:38
ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)።

For the companions of the right [who are]

56:39
ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው።

A company of the former peoples

56:40
ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው።

And a company of the later peoples.

56:41
የግራ ጓዶችም፣ ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው።

And the companions of the left - what are the companions of the left?

56:42
በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው።

[They will be] in scorching fire and scalding water

56:43
ከጥቁር ጭስም በሆነ ጥላ ውስጥ።

And a shade of black smoke,

56:44
ቀዝቃዛም መልካምም ያልሆነ።

Neither cool nor beneficial

56:45
እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና።

Indeed they were, before that, indulging in affluence,

56:46
በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበርና።

And they used to persist in the great violation,

56:47
ይሉም ነበሩ ፦ በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በሆን ጊዜ፣ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን?

And they used to say, "When we die and become dust and bones, are we indeed to be resurrected?

56:48
የፊተኞቹ አባቶቻችንም?

And our forefathers [as well]?"

56:49
በላቸው ፦ ፊተኞቹም ኋለኞቹም።

Say, [O Muhammad], "Indeed, the former and the later peoples

56:50
በተወሰነ ቀን ቀጠሮ፣ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው።

Are to be gathered together for the appointment of a known Day."

56:51
ከዚያም፣ እናንተ ጠማሞች፣ አስተባባዮች ሆይ፤

Then indeed you, O those astray [who are] deniers,

56:52
ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ።

Will be eating from trees of zaqqum

56:53
ከርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ።

And filling with it your bellies

56:54
በርሱ ላይም ከፈላ ውኀ ጠጪዎች ናችሁ።

And drinking on top of it from scalding water

56:55
የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ቢጤ፣ ጠጪዎች ናችሁ።

And will drink as the drinking of thirsty camels.

56:56
ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው።

That is their accommodation on the Day of Recompense

56:57
እኛ ፈጠርናችሁ፤ አታምኑምን?

We have created you, so why do you not believe?

56:58
(በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁትን?

Have you seen that which you emit?

56:59
እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹ ነን።

Is it you who creates it, or are We the Creator?

56:60
እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን።እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም።

We have decreed death among you, and We are not to be outdone

56:61
ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)።

In that We will change your likenesses and produce you in that [form] which you do not know.

56:62
የፊተኛይቱንም አፈጣጠር (1) በእርግጥ አውቃችኋል፤ አትገነዘቡምን?

And you have already known the first creation, so will you not remember?

56:63
የምትዘሩትንም አያችሁን?

And have you seen that [seed] which you sow?

56:64
እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?

Is it you who makes it grow, or are We the grower

56:65
ብንሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በሆናችሁ ነበር።

If We willed, We could make it [dry] debris, and you would remain in wonder,

56:66
እኛ በዕዳ ተያዦች ነን።

[Saying], "Indeed, we are [now] in debt;

56:67
በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን፣ (ትሉ ነበር)።

Rather, we have been deprived."

56:68
ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አያችሁን?

And have you seen the water that you drink?

56:69
እናንተ ከደመና አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?

Is it you who brought it down from the clouds, or is it We who bring it down?

56:70
ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደርግነው ነበር። አታመሰግኑምን?

If We willed, We could make it bitter, so why are you not grateful?

56:71
ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?

And have you seen the fire that you ignite?

56:72
እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን?

Is it you who produced its tree, or are We the producer?

56:73
እኛ ለገሃነም ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት።

We have made it a reminder and provision for the travelers,

56:74
የታላቁን የጌታህን ስም አወድስ።

So exalt the name of your Lord, the Most Great

56:75
በክዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ።

Then I swear by the setting of the stars,

56:76
እርሱም ብታውቁ ታላቅ መሐላ ነው

And indeed, it is an oath - if you could know - [most] great

56:77
እሱ የከበረ ቁርአን ነው።

Indeed, it is a noble Qur'an

56:78
በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው።

In a Register well-protected;

56:79
የተጥራሩት እንጂ ሌላ አይነካውም።

None touch it except the purified.

56:80
ከአለማት ጌታ የተወረደ ነው።

[Itis] a revelation from the Lord of the worlds.

56:81
በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?

Then is it to this statement that you are indifferent

56:82
ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን?

And make [the thanks for] your provision that you deny [the Provider]?

56:83
(ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ።

Then why, when the soul at death reaches the throat

56:84
እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትሆኑ።

And you are at that time looking on -

56:85
እኛም ግን አታዩም እንጅ ከናንተ ይልቅ ወደርሱ የቀረብን ስንሆን።

And Our angels are nearer to him than you, but you do not see -

56:86
የማትዳኙም ከሆናችሁ።

Then why do you not, if you are not to be recompensed

56:87
እውነተኞች እንደሆናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም።

Bring it back, if you should be truthful?

56:88
(ሟቹ) ከባልሟሎቹ ቢሆንማ።

And if the deceased was of those brought near to Allah ,

56:89
(ለርሱ) ዕረፍት መልካም ሲሳይም የመጠቀሚያ ገነትም አለው።

Then [for him is] rest and bounty and a garden of pleasure.

56:90
ከቀኝ ጓዶችም ቢሆንማ።

And if he was of the companions of the right,

56:91
ከቀኝ ጓዶች ስለሆንክ ላንተ ሰላም አልልህ (ይባላል)።

Then [the angels will say], "Peace for you; [you are] from the companions of the right."

56:92
ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢሆንማ።

But if he was of the deniers [who were] astray,

56:93
ከፈላ ውሃ የሆነ መስተንግዶ አለው።

Then [for him is] accommodation of scalding water

56:94
በገሃነም መቃጠልም (አለው)።

And burning in Hellfire

56:95
ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው።

Indeed, this is the true certainty,

56:96
የታላቁን ጌታህን ስም አወድስ።

So exalt the name of your Lord, the Most Great.

Copyright 2013, AmharicQuran.com