Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል ጡር (የጡር ምዕራፍ)

52:1
በጡር (ጋራ) እምላለሁ።

By the mount

52:2
በተጻፈው መጽሐፍም።

And [by] a Book inscribed

52:3
በተዘረጋ ብራና ላይ፤ (በተጻፈው)።

In parchment spread open

52:4
በደመቀው ቤትም።

And [by] the frequented House

52:5
ከፍ በተደረገው ጣራም።

And [by] the heaven raised high

52:6
በተመላው ባሕርም እምላለሁ።

And [by] the sea filled [with fire],

52:7
የጌታህ ቅጣት በእርግጥ ወዳቂ ነው፤ (የማይቀር ነው)።

Indeed, the punishment of your Lord will occur.

52:8
ለርሱ ምንም ገፍታሪ የለውም።

Of it there is no preventer

52:9
ሰማይ ብርቱ መዞርን በምትዞርበት ቀን (ይሆናል)።

On the Day the heaven will sway with circular motion

52:10
ተራራዎችም መኼድን በሚኼዱበት (ቀን)።

And the mountains will pass on, departing -

52:11
ለአስተባባዮች ያን ጊዜ ወዮላቸው።

Then woe, that Day, to the deniers,

52:12
ለነዚያ እነርሱ በውሸት ውስጥ የሚጫወቱ ለሆኑት።

Who are in [empty] discourse amusing themselves

52:13
ወደ ገሀነም እሳት በኀይል መግገፍተርን በሚግገፈተሩበት ቀን፤

The Day they are thrust toward the fire of Hell with a [violent] thrust, [its angels will say],

52:14
ይህች ያቺ በርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁ እሳት ናት።

"This is the Fire which you used to deny.

52:15
ይህ (ፊት ትሉ እንደነበራችሁት) ድግምት ነውን? ወይስ እናንተ አታዩምን?

Then is this magic, or do you not see?

52:16
ግቧት፤ ታገሡም፤ ወይም አትታገሡ በናንተ ላይ እኩል ነው፤ የምትመነዱት፣ ትሠሩት የነበራችሁትን (ፍዳ) ብቻ ነው (ይባላሉ)።

[Enter to] burn therein; then be patient or impatient - it is all the same for you. You are only being recompensed [for] what you used to do."

52:17
አላህን ፈሪዎች በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው።

Indeed, the righteous will be in gardens and pleasure,

52:18
ጌታቸው በሰጣቸው ፀጋ ተደሳቾች ሆነው፣ (በገነት ውስጥ ናቸው)። የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው።

Enjoying what their Lord has given them, and their Lord protected them from the punishment of Hellfire.

52:19
ትሠሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ሆናችሁ ብሉ፤ ጠጡም፤ (ይባላሉ)።

[They will be told], "Eat and drink in satisfaction for what you used to do."

52:20
በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ሆነው (በገነት ይኖራሉ)። ዓይናማዎች በሆኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን።

They will be reclining on thrones lined up, and We will marry them to fair women with large, [beautiful] eyes.

52:21
እነዚያም ያመኑትና ዝርያቸውም በ እምነት የተከተልቻቸው፣ ዝርያቸውን በነሱ እናስጠጋለን፤ ከሥራቸውም ምንም አናጎድልባቸውም፤ ሰው ሁሉ በሰራው ሥራ ተያዢ ነው።

And those who believed and whose descendants followed them in faith - We will join with them their descendants, and We will not deprive them of anything of their deeds. Every person, for what he earned, is retained.

52:22
ከሚሹትም ሁሉ እሸትንና ስጋን እንጨምርላቸዋለን።

And We will provide them with fruit and meat from whatever they desire.

52:23
በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ፤ በውስጧ ውድቅ ንግንግርና መውወንጀልም የለም።

They will exchange with one another a cup [of wine] wherein [results] no ill speech or commission of sin.

52:24
ለነርሱም የሆኑ ወጣቶች፣ ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በነርሱ ላይ (ለማሳለፍ) ይዘዋወራሉ።

There will circulate among them [servant] boys [especially] for them, as if they were pearls well-protected.

52:25
የሚጠያየቁ ሆነውም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይዞራል።

And they will approach one another, inquiring of each other.

52:26
እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ (ከቅጣት) ፈሪዎች ነበርን ይላሉ።

They will say, "Indeed, we were previously among our people fearful [of displeasing Allah ].

52:27
አላህም በኛ ላይ ለገሰ፤ የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን።

So Allah conferred favor upon us and protected us from the punishment of the Scorching Fire.

52:28
እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበርን፤ እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውና (ይላሉ)።

Indeed, we used to supplicate Him before. Indeed, it is He who is the Beneficent, the Merciful."

52:29
(ሰዎችን) አስታውስም፤ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም ዕብድም አይደለህም።

So remind [O Muhammad], for you are not, by the favor of your Lord, a soothsayer or a madman.

52:30
ይልቁንም የሞትን አደጋ በርሱ የምንጠባበቅበት የሆነ ባለ ቅኔ ነው ይላሉን?

Or do they say [of you], "A poet for whom we await a misfortune of time?"

52:31
ተጠባበቁ፤ እኔም ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ በላቸው።

Say, "Wait, for indeed I am, with you, among the waiters."

52:32
አእምሮዎቻቸው በዚህ ያዟቸዋልን? አይደለም በውነቱ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናቸው።

Or do their minds command them to [say] this, or are they a transgressing people?

52:33
ወይም ቀጠፈው ይላሉን? አይደለም፤ በውነቱ አያምኑም።

Or do they say, "He has made it up"? Rather, they do not believe.

52:34
እውነተኞችም ቢሆኑ መሰሉ የሆነ ንግግር ያምጡ።

Then let them produce a statement like it, if they should be truthful.

52:35
ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን?

Or were they created by nothing, or were they the creators [of themselves]?

52:36
ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም።

Or did they create the heavens and the earth? Rather, they are not certain.

52:37
ወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነሱ ዘንድ ናቸውን? ወይስ እነሱ አሸናፊዎች ናቸውን?

Or have they the depositories [containing the provision] of your Lord? Or are they the controllers [of them]?

52:38
ወይስ ለነሱ በርሱ ላይ (ከሰማይ) የሚያዳምጡበት መሰላል አላቸውን? አድማጫቸውም (ሰማሁ ቢል) ግልጽን አስረጅ ያምጣ።

Or have they a stairway [into the heaven] upon which they listen? Then let their listener produce a clear authority.

52:39
ወይስ ለርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን? ለናንተም ወንዶች አሏችሁን?

Or has He daughters while you have sons?

52:40
ወይስ ዋጋን ትጠይቃላችሁን? ስለዚህ እነሱ ከዕዳው የተከበዱ ናቸውን?

Or do you, [O Muhammad], ask of them a payment, so they are by debt burdened down?

52:41
ወይስ ሩቅ ሚስጢር እነሱ ዘንድ ነውን? ስለዚህ እነሱ ይጽፋሉን?

Or have they [knowledge of] the unseen, so they write [it] down?

52:42
ወይስ ተንኮልን (ባንተ) ይሻሉን? እነዚያ የካዱት እነሱ በተንኮል ተሸናፊዎች ናቸው።

Or do they intend a plan? But those who disbelieve - they are the object of a plan.

52:43
ወይስ ለነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ አላቸውን? አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።

Or have they a deity other than Allah ? Exalted is Allah above whatever they associate with Him.

52:44
ከሰማይም ቁራጭን (በነሱ ላይ) ወዳቂ ሆኖ ቢያዩ ኖሮ ይህ የተደራረበ ደመና ነው ይሉ ነበር።

And if they were to see a fragment from the sky falling, they would say, "[It is merely] clouds heaped up."

52:45
ያንንም በርሱ የሚግገደሉበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው።

So leave them until they meet their Day in which they will be struck insensible -

52:46
ተንኮላቸው ከነርሱ ምንንም የማይጠቅማቸውንና እነሱም የማይረዱበትን ቀን (እስከሚገናኙ ተዋቸው)።

The Day their plan will not avail them at all, nor will they be helped.

52:47
ለነዚያ ለበደሉትም ከዚህ ሌላ ቅርብ ቅጣት አላቸው፤ (1) ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም።

And indeed, for those who have wronged is a punishment before that, but most of them do not know.

52:48
ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፤ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፤ ጌታህንም በምትንነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው።

And be patient, [O Muhammad], for the decision of your Lord, for indeed, you are in Our eyes. And exalt [ Allah ] with praise of your Lord when you arise.

52:49
ከሌሊቱም አወድሰው፤ በከዋክብት መደበቂያ ጊዜም አወድሰው (እንጋት ላይ አወድሰው)።

And in a part of the night exalt Him and after [the setting of] the stars.

Copyright 2013, AmharicQuran.com